African Leadership Excellence Academy
2.35K subscribers
2.56K photos
96 videos
6 files
120 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
በኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የዋር ኮሌጅ ከፍተኛ አመራሮች እና ተማሪዎች የአፍሌክስን ፋሲሊቲ ጎበኙ።
ለከፍተኛ አመራሮቹና ተማሪዎቹ አቀባበል ያደረጉት የአፍሌክስ የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) ሲሆኑ አካዳሚው የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች ውስጥ እንደሆነ ጠቅሰው ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን ልዩ የአርሚ የአመራር ልማት ፕሮግራም ለመቅረጽ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
ለልኡካን ቡድኑ የአካዳሚውን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች ገለጻ ያደረጉት አቶ መስፍን በሀይሉ ሲሆኑ አፍሌክስ በአመራር ስርአት ውስጥ ያሉ ስብራቶችን ለመጠገን እንዲችል አስራ ሶስት ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ወደ ስራ እንደገባ ጠቅሰው አራት የጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ተቀርጸዋል ብለዋል።
ጉብኝት ካደረጉ እና ገለጻውን ከተከታተሉ የዋር ኮሌጅ ከፍተኛ አመራሮች እና ተማሪዎች ውስጥ አራት ብርጋዴር ጄኔራሎች፤ ሁለት የውጭ ሀገር ጄኔራሎች፤ የረጅም እና የአጭር ኮርስ ተማሪዎች ተሳትፈዋል።
ከአፍሌክስ ጋር ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ዋና ዳይሬክተሩ በአመራር ልማት ፕሮግራም: በአፍሌክስ አዋርድ: በውጭ ሀገር የሚካሄዱ አጫጭር ስልጠናዎችን በመቀነስ እና በማስቀረት አብሮ መስራት እንደሚቻል ጠቁመው: በስራቸው ካሉ ኢንተርፕራይዞች ጋር በመወያየት የሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ለመገንባት የሚቻልበት ሁኔታ እንዳለ ተናግረዋል::
አቶ ዛዲግ አብርሃ የአፍሌክስን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች ለኢፌዴሪ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ገለጻ አደረጉ።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከኢፌዴሪ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ እንደገለጹት አካዳሚው ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካውያን የአመራር ልማት ፕሮግራም የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ እንደሆነ እና ይህንን ዓላማውን ለማሳካትም አራት የጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ቀርጾ በሶሰት ዓመት ውስጥ ለመፈጸም እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
አፍሌክስ ከኢፌዴሪ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታ አስተዳደር ጋር በመሆን በዘርፉ ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራም በመቅረጽ ወደ ስራ ለመግባት ዝግጁ መሆኑን የገለጹት አቶ ዛዲግ፤ ተቋሙ ያለውን ሰፊ የባለሙያ አቅም እና ልምድ በመጠቀም ከአፍሌክስ ጋር እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል። የሀሳብ ማመንጫ ማዕከል በመገንባትም በዘርፉ ያለውን የጥናትና ምርምር ስራዎች በማጎልበት ሳይንሳዊ እና ችግር ፈቺ የምርምር ውጤቶችን ማፍለቅ እንደሚገባ ርዕሰ አካዳሚው ተናግረዋል።
የኢፌዴሪ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታ አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ አቶ ኃብታሙ ኃይለሚካኤል በበኩላቸው አፍሌክስ ይዞ የተነሳውን አህጉር አቀፍ የሪፎርም፤ የማስፋት እና የሽግግር ዕቅድ አድንቀው ለተግባራዊነቱ ተቋማቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
አቶ ዛዲግ አብርሃ ከኖርዌይ አምባሳደር ስቲአን ክሪስተንሰን Stian Christensen, Ambassador and Permanent Representative to AU, IGAD and UNECA ጋር ተወያዩ።
ለአምባሳደሩ ስለ አፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ሪፎርም፤ ማስፋትና ሽግግር በርዕሰ አካዳሚው ሰፊ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
አቶ ዛዲግ እንዳብራሩት አካዳሚው አስራ ሶስት ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ወደ ስራ እየገባ እንደሆነ እና በሀገራችን የነበረውን የስልጠና ስርአት ወደ አመራር ልማት ፕሮግራም ለማሳደግ ሰፊ ዕቅድ መታቀዱን ጠቅሰው፤ ለዚህም የሚሆን አራት ጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
አካዳሚው በሚቀርጻቸው የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ላይ ከኖርዌይ መንግስት እና በኖርዌይ ካሉ የስልጠና እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር መስራት እንደሚፈልጉ የጠቆሙት አቶ ዛዲግ፤ ለዚህም አምባሳደሩ በጎ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉም ግብዣ አቅርበዋል።
በኖርዌይ ከሚገኙ ትልልቅ ተቋማት ጋርም ስትራቴጂያዊ አጋርነት በመመስረት አፍሌክስ ያቀደውን ተግባራዊ ለማድረግ ይፈልጋል ያሉት አቶ ዛዲግ፤ በተለይም ከከፍተኛ የስልጠና ተቋማት ጋር በመሆን የአሰልጣኞች እና የተመራማሪዎች ልውውጥ ማድረግ የአፍሌክስን ልህቀት ማረጋገጥ ተገቢ እንደሆነ ተናግረዋል።
በአፍሌክስ ውስጥ ከሚገነቡ የሀሳብ ማመንጫ ማዕከላት ውስጥም ኤምባሲው የመሰረተ ልማት ግንባታ እንዲያደርግ እና የተሻለ ሀሳብ እንዲፈልቅ በትውልድ ግንባታ ላይ እንዲሳተፍ አቶ ዛዲግ ጥሪ አቅርበዋል።
የኖርዌይ አምባሳደር ስቲአን ክሪስተንሰን Stian Christensen, Ambassador and Permanent Representative to AU, IGAD and UNECA በበኩላቸው አፍሌክስ ያቀረበውን ገለጻ አድንቀው በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር ኤምባሲያቸው ፈቃደኛ መሆኑን ጠቅሰው በሚቀርቡ ዝርዝር ጥናቶች ላይ ተመስርተው በስፋት ለመነጋገር ቀጠሮ በመያዝ ውየዕይቱ ተጠናቋል።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከአፍሪካ አቅም ግንባታ ፋውንዴሽን ከፍተኛ አመራሮች Mbacke Niang MBE, Director Program and Impact at The African Capacity Building Foundation (ACBF) እና Barassou Diawara,Senior knowledge management expert at The African Capacity Building Foundation ጋር ተወያዩ።
አቶ ዛዲግ አብርሃ በአፍሌክስ ሪፎርም(Reform)፤ ማስፋት (Scaling Up) እና ሽግግር (Transformation) ዙሪያ ለከፍተና የስራ ሀላፊዎቹ ገለጻ አድርገዋል።
አፍሌክስ የጀመረውን የአመራር ልማት ፕሮግራም ለማሳካት በአፍሪካ ውስጥ ከሚገኙ ፋውንዴሽኖች ጋር ጋር በመሆን እንደ ስሙ አፍሪካዊ ተቋም ለመሆን እየሰራ እንደሆነ ርዕሰ አካዳሚው ተናግረዋል።
አካዳሚው ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካውያን የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ እንደሆነ እና ይህንን ዓላማውን ለማሳካትም አራት የጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ቀርጾ በሶሰት ዓመት ውስጥ ለመፈጸም በመስራት ላይ እንደሆነም አቶ ዛዲግ ገልጸዋል።
የአፍሪካ አቅም ግንባታ ፋውንዴሽን The African Capacity Building Foundation (ACBF) ከፍተኛ ሀላፊዎች በበኩላቸው የአፍሌክስን ፕሮጀክቶች እና የአመራር ልማት ፕሮግራሞች በማወቃቸው ተደስተው ከአካዳሚው ጋር ሊሰሩ የሚችሉባቸውን መስኮች በመለየት ስትራቴጂያዊ አጋር ለመሆን እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
በቅርቡ ከአፍሪካ ህብረት ጎን ለጎን በሚደረግ ጉባኤ ላይም የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ተገኝተው ንግግር በማድረግ የአፍሌክስን ተልዕኮ እና ራዕይ ለሌሎች አፍሪካውያን እንዲያጋሩ ጋብዘዋቸዋል።
# አሁን
*********************
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራሮች እና ሰራተኞች በወቅታዊ ጉዳይ ላይ እየተወያዩ ነው።
ውይይቱ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን በሁለት አበይት ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩር የአፍሌክስ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ምክትል ርዕሰ አካዳሚው ውይይቱ የተዘጋጀበትን ዋና ዓላማ ሲያብራሩም የአካዳሚው አመራር እና ባለሙያ ስለ አጠቃላይ ሀገራዊ እና ክልላዊ ከባቢያዊ፤ ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበራዊ እና የሰላም ሁኔታ ላይ በበቂ ሁኔታ ከመንግስት ጋር በመወያየት ለመፍትሔው የጋራ ርብርብ ማድረግ አስፈላ በመሆኑ ነው ብለዋል ።
ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) በውይይቱ ላይ እንዳብራሩት ሀገራችን እጅግ ከባድ ፈተናዎችን እየተጋፈጠች አንድነቷን አስጠብቃ የቀጠለች ፤ ተግዳሮቶችን ተቋቁማ በለውጥ ጎዳና ወደ ብልጽግና ለመሸጋገር ጥረት በማድረግ ላይ እንደሆነች፤ ሀገራዊ ኢኮኖሚውን ከፍጹም ቀውስ እና ከፍተኛ የእዳ ጫና ለመታደግ የሚያስችል ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ተግባራዊ መደረጉን እና የተጀመረው የለውጥ ጉዞ የኢትዮጵያውያንን ማህበራዊ መስተጋብር እና ትስስር በአዲስ ሀገራዊ ገዥ ትርክት ለመገንባት ፈር የቀደደ የለውጥ ጉዞ ላይ እንገኛለን ብለዋል።
ሀብት የመፍጠር ጉዞአችን ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች በሚል በዛሬው ዕለት ውይይቱ የተጀመረ ሲሆን በነገው ዕለትም በስልጡን ሲቪል ሰርቪስ ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግ ም/ርዕሰ አካዳሚው ጠቁመዋል።
የፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በትብብር ትላልቅ ድሎችን አስመዝግበዋል:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
****************

በፕሪቶሪያ ከተደረሰው የሰላም ስምምነት በኋላ፤ የፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በትብብር ትላልቅ ድሎችን ማስመዝገብ ችለዋል ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።

በስብሰባው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፤ በፕሪቶሪያ ከተደረሰው የሰላም ስምምነት በኋላ የተገኙት ድሎች የፌድራል መንግስቱ ለብቻው ያመጣቸው እንዳልሆኑ ገልጸው፤ ከትግራይ ክልል ጊዜያው አስተዳደር ጋር ተዳምረው የተገኙ አሙርቂ ውጤቶች ስለመሆናቸው ነው የተናገሩት።

የተገኘው ሰላም ካመጣቸው ድሎች ውስጥ የአየር ትራንስፓርት ወደ ትግራይ ክልል መጀመሩ አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለብዙዎች እፎይታ የሰጠ መሆኑንም አንስተዋል።

በክልሉ የስልክ እና የኤሌክትሪክ አገልግሎት መጀመሩን ገልጸው፤ በፌዴራል መንግስት እና በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ትብብር የትግራይ ህዝብ አገልግሎቶቹን እንዲያገኝ መደረጉን አብራርተዋል።