የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ በአፍሪካ ህብረት የትምህርት፤ የሳይንስ፤ የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ሞሀመድ ቤልሆሲኔ Professor Mohammed Belhocine, Commissioner for Education, Science, Technology and Innovation (ESTI) ጋር ተወያዩ።
አቶ ዛዲግ በአካዳሚው የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች ዙሪያ ለኮሚሽነሩ ገለጻ አድርገውላቸዋል።
ገለጻውን ያዳመጡት ኮሚሽነሩ በሰጡት አስተያየት ከአፍሌክስ ጋር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር ከአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ በሁዋላ ቀጠሮ እንዲያዝላቸውና በዝርዝር ለመነጋገር ዝግጁ እንደሆኑ ተናግረዋል።

የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ በምስራቅ አፍሪካ አርብቶ አደሮች ኤክስፖ East Africa Pastoralist Expo ላይ በመገኘት የአካዳሚውን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች ለኤክሰፖው ተሳታፊዎች ገለጻ አድርገዋል።
በተለይም አካዳሚው በልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሙ ውስጥ የአርብቶ አደር ፕሮግራም ማካተቱን እና የዘርፉን አመራርና ባለሙያ አቅም ለመገንባት እየተሰራ እንደሆነ አቶ ዛዲግ አብራርተዋል።
ከአርብቶ አደር ጋር በተያያዘ ያለውን የጥናት እና ምርምር ስራዎች ለማስፋት እና የዘርፉ አመራር በሀሳብ ማመንጫ ማዕከላት ውስጥ ሆነው ጥናትና ምርምር ለማድረግ እንዲችሉም በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ውስጥ Center for Pastoralist Economic Transformation (CPET) እንዲገነባ ሀሳብ አቶ ዛዲግ ሀሳብ አቅርበዋል።
በዘርፉ የተሻለ የስራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎችም ሀገር አቀፍ ሽልማት እና ዕውቅና የሚሰጥበት የአፍሌክስ አዋርድ ፕሮግራም እንደሚኖርም አቶ ዛዲግ ገልጸዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ባቀረቧቸው ሶስቱም ፕሮጀክቶች ላይ የጋራ መግባባት የተፈጠረ ሲሆን በቀጣይ ሳምንታት ለሀሳብ ማመንጫ ማዕከሉ ስራ እንደሚጀመር ታውቋል።

የአርብቶ አደር ኢኮኖሚ ሽግግር ማዕከል (Center for Pastoralist Economic Transformation) (CPET) በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ውስጥ ሊቋቋም ነው::
የአርብቶአደሩን ጥያቄዎች በዘላቂነት ለመመለስና በአጠቃላይ በዘርፉ ልማት ላይ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚያስችል የአርብቶአደር ኢኮኖሚ ሽግግር ማዕከል በአፍሪካ አመራር ልኅቀት አካዳሚ ሊቋቋም ነው፡፡
የአርብቶአደሩን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ራሱን የቻለ ፖሊሲና ተቋም በማስፈለጉ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የተቋቋመና የኢትዮጵያ አርብቶአደር ፖሊሲና ማስፈፀሚያ ስትራቴጂ ጸድቆ ተግባር ላይ መዋሉ በተገለፀበት በዛሬው የምስራቅ አፍሪካ አርብቶአደሮች ኤክስፖ የፓናል ውይይት፣ መሠረታዊ የሚባሉ ችግሮች የተፈቱ ቢሆንም የአርብቶአደር አመራር ልማት፣ የድርቅ ተደጋጋሚ ክስተት፣ አካባቢያዊ ግጭቶች፣ ባህላዊና ዘመናዊውን የአስተዳደር ዘይቤዎች ቀላቅሎ መጠቀም፣ ክፍተቶች መኖራቸው ተመላክቷል፡፡
አቶ ዛዲግ አብርሃ የአፍሪካ አመራር ልኅቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ እንደተናገሩት የአርብቶአደሩንና ሌሎች ተዋናዮችን በአጠቃላይ ወደ አንድ ማዕቀፍ የሚያሰባስብ፣ ለጥናትና ምርምር፣ ለዘርፉ ልማት አመራር በማፍራትም ጭምር ድርሻውን ሊወጣ የሚችል ማዕከል ይሆናል፡፡
በሌላ በኩል ፓናል ውይይቱ ላይ የተገኙት የአፋር ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ ኤለማ አቡበከር የአፍሪካ አመራር ልኅቀት አካዳሚ ሊያቋቁም ስላሰበው የአርብቶአደር ኢኮኖሚ ሽግግር ማዕከል አመስግነው በዘርፉ ያለውን የአመራር ክፍተት ለመሙላት የሚደረግ ጥረት አካል ስለሆነ ዘላቂነት ያለው ልማት ለማረጋገጥ የጎላ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የ19ኛው የአርብቶአደር ቀንን በማስመልከትና ቀጠናዊ ትስስርን ለማሳደግ ታስቦ ‘‘አርብቶ አደርነት: የምስራቅ አፍሪካ ኅብረ-ቀለም’’ በሚል መሪ ቃል በሚሊኒየም አዳራሽ የምስራቅ አፍሪካ የአርብቶአደሮች ኤክስፖ በይፋ የተከፈተው ባለፈው አርብ ጥር 17/2016 ዓ.ም ነው፡፡
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከቢል ኤንድ ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን Bill & Melinda Gates Foundation ካንትሪ ዳይሬክተር ሀዲስ ታደሰ ጋር ተወያዩ።
አቶ ዛዲግ አብርሃ በአፍሌክስ ሪፎርም(Reform)፤ ማስፋት (Scaling Up) እና ሽግግር (Transformation) ዙሪያ ለካንትሪ ዳይሬክተሩ ገለጻ አድርገዋል።
ርዕሰ አካዳሚው እንደገለጹት አፍሌክስ የጀመረውን የአመራር ልማት ፕሮግራም ለማሳካት መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እና ፋውንዴሽኖች ጋር በመሆን ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል።
አካዳሚው ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካውያን የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ እንደሆነ እና ይህንን ዓላማውን ለማሳካትም አራት የጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ቀርጾ በሶሰት ዓመት ውስጥ ለመፈጸም እየሰራ እንደሆነም አቶ ዛዲግ ገልጸዋል።
አፍሌክስን የዓለም አቀፍ የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግም ሱሉሉታን እንደ ዳቮስ የሚል ፕሮጀክት ተቀርጾ እየተሰራ እንደሆነ እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ይህንኑ ዓላማ ለማሳካት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የፋውንዴሽኑ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችን በአፍሌክስ ውስጥ እንዲደረጉ አቶ ዛዲግ ለካንትሪ ዳይሬክተሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ካንትሪ ዳይሬክተሩ ሀዲስ ታደሰ ስለ አፍሌክስ በተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው ከአፍሌክስ ጋር አብረው ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ሰጥተዋል።
ቢል ኤንድ ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን Bill & Melinda Gates Foundation የሚሰራባቸውን ዘርፎች ያብራሩት ካንትሪ ዳይሬክተሩ ከአፍሌክስ ጋር ሊሰሩ የሚችሉባቸውን ዘርፎች በመለየት አብረው ለመስራት ዝግጁ እንደሆኑ ጠቅሰው በተለይም በሴቶች ጤና፤ በግብርና በምግብ ዋስትና እና ዲጂታል ፋይናንስ ዙሪያ የአመራሩን አቅም መገንባት

በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ በረጅም እና በመካከለኛ ጊዜ ውስጥ የሚሰሩ ስራዎችን በመለየት ወደ ስራ መግባት እንደሚቻል ተናግረዋል።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ለትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ሚኒስትር ክቡር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ስለ አካዳሚው የሶስት ዓመት ስትራቴጂ እና ፕሮግራም ገለጻ አድርገዋል።
አቶ ዛዲግ እንደጠቀሱት አፍሌክስ የአህጉሪቱን እና የሀገራችንን አመራሮች ለማብቃት ስልጠና ብቻውን በቂ እንዳልሆነ በማመኑ አራት ጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ነድፎ ወደ ስራ እየገባ እንደሆነ ተናግረዋል። በእነዚህ የአመራር ልማት ፕሮግራም ማዕቀፎች ውስጥም ከፍተኛ አመራሮች አቅማቸውን እንደሚገነቡ እና ሀሳብ እያፈለቁ የምርምር ስራዎችን እንደሚያበረክቱ ገልጸዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ (ዶ/ር) አፍሌክስ ይዞ የተነሳው የአመራር ልማት ፕሮግራም ማዕቀፍ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች የሚኖረውን ጥቅም አስታውሰው፤ በተለይም ከመንግስት ልማት አቅጣጫ እና የብልጽግና መስመር ጋር በተናበበ መልኩ የተቀረጹት የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ለሀገር እድገት ግብዓት እንደሚሆን ተናግረዋል። ተቋማቸውም ለዚህ ፕሮግራም መሳካት ማድረግ የሚችለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ክቡር ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ለሀሳብ ማመንጫ ማዕከል የሚሆን የመሰረተ ልማት ግንባታም በአፍሌክስ ውስጥ ለመስራት ውይይት እንደሚያስፈልግ የጠቀሱት ክቡር ሚኒስትሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውሳኔ ላይ እንደሚደርሱም አሳውቀዋል።