“We have no intention of threatening the sovereignty of any nation but we would like a rules based access to the Red Sea. Our request is to initiate discussions towards sustainable solutions.”
#PMAbiyResponds
#PMOEthiopia
#PMAbiyResponds
#PMOEthiopia
"ነጠላ ትርክት፣ የተዛባ ትርክት፣ አፍራሽ ትርክት ሀገር አይገነባም"፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)
******************************
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ነው።
የምክር ቤቱ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ሊሰጡባቸው ይገባል ያሏቸውን ጥያቄዎች አቅርበዋል፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
በዚህም የፓለቲካ እና ጸጥታ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ "ችግሮቻችንን በጋራ እና በእኩል መልክ ከተረዳን ጉዟችን ወደ መፍትሄ ይሄዳል" ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ችግር አባባሽ ነገር የሆነው ትርክት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ነጠላ ትርክት፣ የተዛባ ትርክት፣ አፍራሽ ትርክት ሀገር አይገነባም ብለዋል።
አክለውም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚስተዋለው የችግር ትንታኔ ስሜት ይጫነዋል ያሉ ሲሆን፤ ስሜት የሚጫነው የችግር ትንታኔ ደግሞ አያግባባም ነው ያሉት።
ሁሉም የራሱን ሰፈር እና እምነት ቢያወድስ፤ ከሌሎች ጋር በሰላም ለመኖር የሌላውን እሳቤ መቀበል እንደሚያስፈልግም ነው የተናገሩት።
ኢትዮጵያ ውስጥ ልዩ ልዩ እምነቶች እና ቋንቋዎች አሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እነዚህን ማክበር ያስፈልጋልም ብለዋል።

የፕሪቶሪያው ስምምነት እናቶች ተጨማሪ ልጆች እንዳይሞትባቸው አድርጓል – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2016 የፕሪቶሪያው ስምምነት ቢያንስ ቢያንስ ለኢትዮጵያ እናቶች ተጨማሪ ልጆች እንዳይሞትባቸው ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የፕሪቶሪያውን ስምምነት በተመለከተ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በማብራሪያቸውም÷ ከስምምነቱ በኋላ ተጨማሪ ሰዎች እንዳይሞቱ ማድረግ መቻሉን በአጽንኦት ገልጸው ከዚህ አንጻር በፕሪቶሪያ የተደረገውን ስምምነት በቀላሉ ማየት እንደማይገባ አስረድተዋል፡፡
ከስምምነቱ በኋላ በትግራይ ክልል ተቋርጠው የነበሩ የኤሌክትሪክ፣ የስልክ፣ የትራንስፖርት፣ ባንክና መሰል አገልግሎቶች በስፋት እንዲጀመሩ መደረጉንም አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም÷ በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም መደረጉንና ለክልሉ በጀት መፈቀዱን ገልጸዋል፡፡
ቀሪ ሥራዎችንም የፌዴራል መንግስት ከአማራ እና ትግራይ ክልሎች ጋር በመተባበር በቀጣይ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 4/2016 ፦ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ የቢዝነስ ሕግን መሠረት ያደረገ የጋራ እድገትና ተጠቃሚነትን የተከተለ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ነው።
ኢትዮጵያ የባህር በርና አማራጭ ወደብ የማግኘት ጥያቄ ማንሳቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል።
በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ሀገራትና መላው ዓለም የኢትዮጵያን እውነተኛ ችግሮችና ፍላጎት መረዳት አለበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ ከ30 ዓመታት በፊት የሁለት ወደብ ባለቤት እንደነበረች አስታውሰዋል።
በወቅቱ የነበራት የሕዝብ ቁጥርና ኢኮኖሚያዊ እድገት አነስተኛ እንደነበር በማስረዳት፤ ዛሬ ላይ የሕዝብ ቁጥሯና ኢኮኖሚዋ በብዙ እጥፍ ቢያድግም አማራጭ ወደብ የላትም ብለዋል።
የአካባቢው ጂኦ-ፖለቲካ ተለዋዋጭነትና ብልሽት ለኢትዮጵያ ስጋት በመሆኑ አማራጭ ወደብ ያስፈልጋታል ነው ያሉት።
የጂቡቲ መንግሥትና ሕዝብ ኢትዮጵያ ላለፉት ዓመታት ወደባቸውን እንድንጠቀም በማድረግ ላሳዩት አጋርነት አመስግነው፤ የባህር በርና የወደብ ተጠቃሚነትን በሚመለከት ያቀረብነውን ጥያቄ ጎረቤት ሀገራት በቀዳሚነት መረዳት አለባቸው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚና የሕዝብ ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ በመምጣቱ ያንን የሚሸከም አማራጭ ወደብ ማግኘት አስፈላጊ እንደሆነም አብራርተዋል።
በዓለም ላይ ቀይ ባህርን የማይፈልግ አገር እንደሌለ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ ስለ ቀይ ባህር ተጠቃሚነት ስታነሳ ትክክል የማይሆንበት ምክንያት የለም ነው ያሉት። የቀይ ባህርን ጉዳይ የኤርትራን ሉዓላዊነት ከመዳፈር ጋር አያይዘው የሚያነሱ አካላት ትክክል አለመሆናቸውን ገልጸዋል።

ቀይ ባህር የኢትዮጵያ ብቸኛ መተንፈሻዋ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2016 ቀይ ባህር የኢትዮጵያ ብቸኛ መተንፈሻዋ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደብን በሚመለከት በሰጡት ማብራሪያ እንዳሉት ፥ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ሀገራት እንዲሁም መላው የአፍሪካ ሀገራት፣ የምዕራብና የምስራቁ ዓለም ሀገራት እንዲገነዘቡ የምንፈልገው ይህ የኢትዮጵያ እውነተኛ ፍላጎትና ችግር ነው፡፡
የዛሬ 30 ዓመት ገደማ ኢትዮጵያ የሁለት ወደብ ባለቤት እንደነበረች አስታውሰው ፥ የሕዝብ ብዛቷም 46/47 ሚሊየን ገደማ ሕዝብ እንደነበራትና ከ12 እስከ 13 ቢሊየን ዶላር ገደማ ጠቅላላ የሀገር ውስ ገቢ እንደነበራት ጠቁመዋል፡፡
ከ30 ዓመት በኋላ ግን ከሁለት ወደብ ባለቤትነት ወደቦችን በንግድ ሕግ ወደምትጠቀምበት ደረጃ ዝቅ ማለቱን ጠቅሰዋል፡፡

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 4/2016 ፦ ሌብነት ተቋም የሚያፈርስና የሀገር እድገትን የሚገታ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ሌብነትን በተመለከተ ላቀረቡላቸው ጥያቄ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
እንደ ኢትዮጵያ ባለ ድሃ ሀገር ሌብነት ሲንሰራፋ በተለይ ህዝብ እናገለግላለን ያሉ ሰዎች ሲሰርቁ እድገትን ማረጋገጥ ፈታኝ መሆኑን ገልጸዋል።
"ሌብነት ተቋም የሚያፈርስ ምስጥ ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሌብነት አሳቢያን እንዳያስቡ የሚያደርግ ካንሰር ነው ብለዋል።
በልበ ሙሉነት መናገር፣ መስራት፣ ከህዝብ ጋር መገናኘት የማያስችል ሽባ የሚያደርግ እንደሆነ በማንሳት ሌብነትን መታገል ቀላል እንዳልሆነም አንስተዋል።
መንግስት ከፍተኛ የቁጥጥር ስራዎችን እያካሄደ መሆኑንም ገልጸዋል።
ፕሮጀክቶች በቀጥታ ቁጥጥር ስለሚደረግባቸው ሌብነትን መቀነስ መቻሉን ገልጸው፤ ጥቃቅን የሙስና ችግሮችን ለማረም የባህል ትግል፣ ህግና ስርዓትን ማሳደግ፣ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርምን መተግበርና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል መቀየር እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።
በርካቶች በህግ ተጠያቂ እየተደረጉና ከስፍራቸው እየተነሱ ቢሆንም አሁንም ሌብነት ፈተናው አላለቀም ብለዋል።
እስካሁንም ገቢዎችን ጨምሮ ከ190 በላይ የመንግሥት አገልግሎቶች ወደ ዲጂታል መቀየራቸውን ጠቅሰው ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ያነሱት።
በተገልጋይና አገልጋይ መካከል ቀጥተኛ የሰው ንክኪ እንዳይኖር በማድረግ ሌብነትን ለመቀነስ እንሰራለን ሲሉም አረጋግጠዋል።

# አሁን በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ውስጥ
የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት አመራርና ባለሙያዎች ስልጠና እየወሰዱ ነው::
ስለ አካዳሚው አገልግሎትና ተልዕኮ የአካዳሚው ጽ/ ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሀና አጥናፉ ገለፃ አድርገዋል::