African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና የቻይና ብሔራዊ አስተዳደር አካዳሚ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከቻይና ብሔራዊ አስተዳደር አካዳሚ ጋር በጋራ ለመስራት የስምምነት ሠነድ ተፈራርሟል።
የተደረገው ስምምነት በሁለቱ አካዳሚዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል ተብሏል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ብቁ አመራሮችን ለማፍራት እየሠራ በሚገኘው ስራ የተደረገው ስምምነት ከቻይና በርካታ ተሞክሮዎችን መውሠድ እንደሚያስችለው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሠ አካዳሚ ዛዲግ አብረሀ ገልፀዋል።
የቻይና ብሔራዊ አስተዳደር አካዳሚ በአመራር ልህቀት ዘርፍ ያለውን ልምድና ተሞክሮ ለኢትዮጵያ ለማካፈል ዝግጁ መሆኑን የማዕከሉ ሀላፊ ገልፀዋል።
የልህቀት ማዕከሉ በሁሉም ዘርፎች ብቁ የሆኑ አመራሮችን ለማፍራት እየሠራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ማዕከሉ የተለያዩ ሀገራት አጋሮችን ለማፍራትና ልምዶችን ለመቅሠም እየሠራ ነው።
በቻይናው ብሔራዊ የአስተዳደር አካዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጎንግ ዌቢን የተመራው ልዑክ በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የነበረውን ቆይታ አጠናቆ ወደ ቻይና ተመልሷል። ልዑኩ በነበረው የሶስት ቀናት ቆይታ ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ እና ከተቋሙ አመራሮች እንዲሁም ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ጋር ውይይት አድርጓል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትንም አግኝቷል። በአዲስ አበባ ያሉ የቱሪስት መዳረሻዎችንም ጎብኝተዋል። ሁለቱ አቻ ተቋማት በጋራ በሚሰሩባቸው መስኮች ላይም ውይይት ተደርጓል። የጋራ መግባቢያ ስምምነትም ተፈራርመዋል። ስምምነቱም በሁለቱ የአመራር አካዳሚዎች መካከል የነበረውን ግንኙነት የሚያሳድግና በሀገራችን ያለውን የአመራር ስልጠና፤ ምርምርና የፖሊሲ ማማከር ተግባር በተሻለ መንገድ ለመፈፀም ዕድል የሚሰጥ እንደሆነ ተገልጿል።