በክቡር ጠቅላይ ሚ/ር የተሠጡ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተደረገ
ሱሉሉታ፡ ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም /አአልአ/ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በ2015 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዋና ዋና አፈፃፀም እና በስድስት ወራት የግምገማ መድረክ በክቡር ጠቅላይ ሚ/ር ዐብይ አህመድ የተሠጡ አቅጣጫዎች ላይ በአካዳሚው ሱሉልታ አዳራሽ ውይይት አደረገ፡፡
ውይይቱ በማክሮ ኢኮኖሚ፣ ክፍላተ ኢኮኖሚ፣ መሰረተ ልማት፣ የሰው ሀብት ልማትና ማህበራዊ ጉዳይ እንዲሁም አስተዳደር፣ ፍትህና ውጭ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው፡፡
በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ /ዶ/ር/ በ2015 በጀት የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የመንግስት ገቢና ወጪ፣ የጋራ ገቢ፣ የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የወጪ ንግድ፣ ተኪ ምርቶች፣ የዲጂታል ፋይናስ፣ የአገልግሎት ወጪ ንግድ፣ ሬሚታንስ፣ ፋይናስ ዘርፍና የዋጋ ግሽበት ላይ ሰፋ ያለ ገለፃ አድርገዋል፡፡
ዶ/ር ወንድዬ የስድስት ወራት አፈፃፀም ግምገማ ላይ ለገንዘብ ሚኒስቴር፣ ለገቢዎች ሚኒስቴር፣ ለፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣ ለንግድ ዘርፍ፣ የተሰጡ አቅጣጫዎች ላይም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተካፈሉ የመስሪያ ቤቱ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በቀረበው ገለፃ ላይ ጥያቄና አስተያየት ያቀረቡ ሲሆን በአወያዩ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡