የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራርና ሠራተኞች የተለያዩ ተቋማትን ጎበኙ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራርና ሠራተኞች የኢፌዲሪ አየር ኃይልን፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አሰተዳደር፣ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትንና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ በተቋማቱ ያለው ጠንካራ የሥራ ባህል የታየበትና አገሪቱ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ እያለፈች ቢሆንም እየተተገበሩ ያሉ አገራዊ ሪፎርሞች ውጤታማ መሆናቸውን የተገነዘቡበት ነው።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ምክትል ርእሰ አካዳሚ ወይዘሮ ሕይወት አለማየሁ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት፤ በተቋማቱ የታየው ጠንካራ የሥራ ባህልና ስኬት ለአካዳሚው ሠራተኞች ትልቅ መነሳሳት የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመው፤ ጠንክሮ በመሥራት ችግር ፈቺ የሆኑ ተግባራትን ለአገር ማበርከት እንደሚቻል ልምድ ያገኘንበት ነው ብለዋል።
አካዳሚው በአፍሪካ ደረጃ የአመራር ልህቀት ማዕከል የመሆን ራዕይ አንግቦ እየተንቀሳቀሰ ነው ያሉት ምክትል ርእሰ አካዳሚዋ፤ አካዳሚው ከእነዚህ ተቋማት ጋር በትብብር በመሥራት የታለመውን አገራዊ የመልማት እቅድ እውን ለማድረግ የበኩሉን ሚና ለመወጣት ዝግጁ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
ጉብኝቱ ትልቅ መነሳሳትና ሞራል እንደፈጠረላቸው የጠቆሙት የአካዳሚው ሠራተኞች፤ በተቋማቱ ውስጥ በተመለከቱት ሥራ አገራዊ ኩራት እንደተሰማቸውም ጠቁመዋል።
የአካዳሚው አመራርና ሠራተኞች ጉብኝት ከትናንት ጀምሮ ዛሬም በመከናወን ላይ ያለ ሲሆን፣ ከተቋማቱ ጉብኝት በተጨማሪ በምሥራቅ ሸዋ ዞን በክላስተር የለማ የስንዴ ማሳንም ጎብኝተዋል።
በፋንታነሽ ክንዴ

እናመሰግናለን!!
አቶ አሸብር አህመድ በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ውስጥ በልዩ ስልጠና ዳይሬክተርነት ሰርተዋል፡፡ በጡረታ እስከተሰናበቱበት ድረስም በቅንነትና በታማኝነት አገልግለዋል፡፡ አካዳሚውም የምስጋና በዓል አዘጋጅቶ በክብር ሸኝቷቸዋል፡፡ አቶ አሸብር በተቋሙ ውስጥ በሰጡት አመራር እናመሰግናለን፡፡

የደቡብ ሱዳን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ልዑክ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን ጎበኘ፡፡
ልዑኩ ሱሉልታ በሚገኘው የተቋሙ የስልጠና ማዕከል ሲደርስ የአካዳሚው የፕሮግራም ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ ሕይወት አለማየሁ እና የስራ አመራር ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) አቀባበል ያደረጉለት ሲሆን ስለ አካዳሚው ተግባርና ኃላፊነት ሰፊ ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡
አካዳሚው እንደ አዲስ ከተቋቋመ ጀምሮ የአፍሪካን አመራር አቅም በሁለንተናዊ መልኩ ለመገንባት እየሰራ እንደሆነ የገለፁት ወ/ሮ ሕይወት የደቡብ ሱዳን የመረጃና ደህንነት ተቋምም አመራሮቹን የማሰልጠን ፍላጎት ካለው በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ም/ርዕሰ አካዳሚዋ አያይዘውም የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከፓን አፍሪካ ጋር የተያያዙ አዳዲስ የስልጠና ፕሮግራሞችን በመቅረፅ ወደ ስራ እየገባና የአፍሪካውያንን የስልጠና ፍላጎት በተደራጀ የስልጠና ማዕከል ውስጥ ለማሟላት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የደቡብ ሱዳን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና አስተዳደር አብርሀም ኬት ቢቾክ በበኩላቸው ለተደረገላቸው አቀባበልና ለተደረገላቸው ገለፃ አመስግነው በአካዳሚው ውስጥ ለመሰልጠን ፍላጎት እንዳላቸውና በአጭር ጊዜ ውስጥ የስልጠና ፍላጎታቸውን እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል፡፡ የአካዳሚውን የስልጠና ማዕከል በመጎብኘታቸውም ደስተኛ እንደሆኑና በማዕከሉ ባዩት መሰረተ ልማት መደነቃቸውን ተናግረዋል፡፡