የአፍሪካ አመራር አካዳሚና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
የአፍሪካ አመራር አካዳሚን በመወከል ስምምነቱን የተፈራረሙት የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ ሕይወት አለማሁ ሲሆኑ በስነስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት አካዳሚው እንደ አዲስ ከተደራጀ አንድ ዓመት ማስቆጠሩን አስታውሰው ተልዕኮውን ለማሳካት ከሀገር ውስጥና ከውጭ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሆነና የኢትዮጵያ አየር መንገድም ስኬታማ ተቋም በመሆኑ አብረው በመስራታቸው ደስተኛ እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡
ሁለቱ ተቋማት በጋራ ሊሰሩ የተስማሙባቸው ጉዳዮች በስልጠና፤ በምርምር፤ በማማከርና በዕውቀት ሽግግር እንደሆነ የገለፁት ምክትል ርዕሰ አካዳሚዋ አብረው በመስራታቸው ተቋሙ ሊያሳካ የሚያስበውን የፓን አፍሪካኒዝም አስተሳሰብን ተግባራዊ ለማድረግ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለውም አመላክተዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድን በመወከል ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ ማኒጂንግ ዳይሬክተር አቶ መሳይ ሽፈራው በበኩላቸው አየር መንገዱ በሀገር ውስጥና በውጭ ካሉ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራና ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውሰው ሁለቱ ተቋማት በትብብር ለመስራት መስማማታቸው በሀገር ደረጃ የተያዘውን ራዕይ ለማሳካት እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡

ከጤና ሚኒስቴር፣ ከክልል ጤና ቢሮና ኤጀንሲዎች የተወጣጡ ባለሙያዎች የአካዳሚውን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ፡፡
በ4ኛ ዙር በጤናው ዘርፍ የአመራር ስልጠና በመውሰድ ላይ የሚገኙት ከጤና ሚኒስቴር፣ ከክልል ጤና ቢሮና ኤጀንሲዎች የተወጣጡ ባለሙያዎች የአካዳሚውን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡
በስልጠና ወቅት ያገኙትን ዕውቀት ለማሳደግና በተግባር ስራዎች ለማስደገፍ ወደ አካዳሚው መምጣታቸውን የገለፁት ባለሙያዎቹ በጉብኝታቸው ወቅት ባዩት ነገር ደስተኛ መሆናቸውን በማስታወስ በቀጣይ በአካዳሚው ስልጠና የመውሰድ ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

ሀና አጥናፉ በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የርዕሰ አካዳሚ ፅ/ቤት ኃላፊ ሆነው ተቋሙን ተቀላቅለዋል፡፡
ከማኔጅመንቱና ከማኔጅመንት ምክር ቤቱ ጋርም ትውውቅ አድርገዋል፡፡ ኃላፊዋ በቀደመ የስራ ህይወታቸው በበርካታ መስሪያ ቤቶች በአመራርነት እንዳገለገሉም ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ በዲያስፖራ ትረስት ፈንድና በሰላም ሚኒስትር ውስጥ በከፍተኛ አመራርና ኃላፊነት ሰርተዋል፡፡ በያዝነው ሳምንት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን ለማገልገል መጥተዋል፡፡ የአካዳሚው ማኔጅመነትና ዳይሬክተሮችም ለሀና አጥናፉ መልካም የስራ ዘመንን ተመኝተዋል፡፡ እንኳን ደህና መጡ!!

የሲቪል ማህበረሰብ አካላት በሀገረ-መንግስት ግንባታ ውስጥ ያላቸውን ሚና ለማሳደግ እየተሰራ እንደሆነ ተገለፀ፡፡
ይህ የተገለፀው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት (ECSOC) ጋር በመሆን በዘርፉ ያለውን የአመራር ክፍተትና ተግዳሮቶች መለየት የሚያስችል የምክክር ጉበኤ ሲያካሔድ ነው፡፡
በጉባኤው መክፈቻ ላይ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕስ አካዳሚ ዶ/ር ምህረት ደበበ እንደገለፁት የሲቪል ማህበራት ለሀገር መንግስት ግንባታ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ አስታውሰው በሙሉ አቅምና በተደራጀ መልኩ ወደ ተግባር እንዲገቡ በዘርፉ ያለውን የአመራር ክፍተት በመለየት ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ንጉሡ ለገሰ በበኩላቸው ምክር ቤቱ የዘርፉን የመሪነት አቅም ለመገንባት በሚያደርገው ጥረት ውስጥ ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር መስራቱ ተገቢና ትክክለኛ ምርጫ እንደሆነ ተናግረው በቀጣይ በሚደረጉ ስትራቴጂያዊ ግንኙነቶች ያለውን የአመራር ክፍተት በመለየት በጋራ እንደሚሰሩ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡
በምክክር ጉባኤው ላይ ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት (ECSOC) የተውጣጡ ከ300 በላይ ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን መድረኩ የሲቪል ማህበረሰብ አካላት በሰላምና በዴሞክራሲ ግንባታ ዙሪያ የሚያበረክቱትን አስተዋፅኦ የሚያሳድግ እንደሆነ ተገልጸል፡፡
ይህን ውይይት መነሻ በማድረግ በዘርፉ የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየትና የመፍትሔ ሀሳቦችን በማመንጨት የሲቪል ማህበረሰብ አካላት ለሀገረ መንግስት ግንባታ የሚኖራቸውን ሚና የማስገንዘብና ወደ ተግባር የሚገቡበትን አቅጣጫ እንደሚያመላክት በመድረኩ ተገልጧል፡፡

በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ተደረገ
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራሮችና ሰራተኞች በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
ውይይቱን የመሩት የአካዳሚው ስራ አመራር ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሠ (ዶ/ር) የአካዳሚው አመራርና ሰራተኛ በተሰማራበት የስራ መስክ ስራውን በኃላፊነት እንዲሰራ፣ የሚሰራጩ ሃሰተኛ መረጃዎችን እንዲከላከልና አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ አሳስበዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የአካዳሚው አመራርና ሰራተኞች በበኩላቸው በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት መደረጉ ተገቢና ወቅታዊ መሆኑን በማንሳት በተሰማሩበት ሙያ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንደሚወጡና እየተወጡ እንዳሉም አንስተዋል፡፡ በየአካባቢያቸውም የፀጥታ ሃይሉን በማገዝ አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥማቸው ለሚመለከተው አካል እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል፡፡