African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የደቡብ ሱዳን የደህንነትና የሲቪል ሹማምንት ከፍተኛ ልዑክ ከአካዳሚው ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጉት እንዳለው ገለፀ
የደቡብ ሱዳን የደህንነትና የሲቪል ልዑክ አባላት እና የኢትዮጵያ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን የደቡብ ሱዳን ልዑክ አባላት የአካዳሚውን መሰረተ ልማት ከጎበኙ በኃላ እንደተናገሩት ከአካዳሚው ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡
የአካዳሚው የስራ አመራር ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሠ (ዶ/ር) የልዑካን ቡድኑ አባላት ወደ አካዳሚው በመምጣታቸው ደስተኛ እንደሆኑና ተቋሙ አፍሪካዊ ተልዕኮን ያነገበ በመሆኑ ከአፍሪካ አገራት ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይ በኢትዮጵያዊና በአፍሪካዊ መስተንግዶ የሚቀበሏቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት በበኩላቸው አካዳሚው እያከናወናቸው ያሉ ስራዎችን በማድነቅ በቀጣይ በተለይም በስልጠና ስራዎች አብሮ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጉት እንዳላቸውና በቅርቡ የቴክኒክ ልዑክ በመላክ በቀጣይ ሊሰሩ ስለሚገቡ ስራዎች ዝርዝር ውይይት እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡
የኡጋንዳ የልዑካን ቡድን በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጉብኝት አደረገ፡፡
በኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ኦኬሎ ኦሪየም የተመራው ልዑክ ነሐሴ 15 ቀን 2014 ዓ.ም በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በመገኘት የስልጠና ማዕከሉን ጎብኝቷል፡፡
የኡጋንዳ የምድር ኃይል ዋና አዛዥና የፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የልዩ ዘመቻ ከፍተኛ አማካሪ ሌተናል ጀነራል ሙሆዚ ኪኑሩጋባን ጨምሮ ሌሎች የደኅንነትና ወታደራዊ ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተው የልዑካን ቡድን ሱሉልታ በሚገኘው የአካዳሚው የስልጠና ማዕከል ሲደርስ አቀባበል ያደረጉለት የአካዳሚው ስራ አመራር ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) እና የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ናቸው፡፡
ምክትል ርዕሰ አካዳሚው ለልዑካን ቡድኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ ስለ አካዳሚው ተልዕኮና ተግባራት ሰፊ ገለፃ አድርገዋል፡፡ ተቋሙ የአፍሪካውያንን የመሪዎች ሚና ለማሳደግና ለማበልፀግ እንደሚሰራና ይህንን ግቡን ለማሳካት ሰፊ የሪፎርም ስራ ላይ እንደሚገኝም ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ መሪ የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ኦኬሎ ኦሪየም በበኩላቸው አካዳሚው የአፍሪካውያንን የአመራር ክፍተት ለመሙላትና የመሪዎችን አቅም በስልጠና ለመገንባት የሚያደርገውን ጥረት አድንቀው የኡጋንዳ መሪዎችን በተቁሙ ውስጥ ለማሰልጠን ፍላጎት እንዳለቸው ተናግረዋል፡፡
ሌሎች የልዑካን ቡድኑ አባላትም በአካዳሚው ውስጥ ባዩት የስልጠና ፋሲሊቲ እና በተደረገላቸው አቀባበል ደስተኛ መሆናቸውን በመግለፅ በቀጣይ ከአካዳሚው ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
አካዳሚው ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
የስልጠናውን ሂዴት በተመለከተ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የአካዳሚው ርዕሰ አካዳሚ ዶ/ር ምህረት ደበበ ሃገር የምትለወጠው በስራ እንደሆነ እና ስራ ደግሞ የሚመራው በክህሎት መሆኑን በማንሳት በቆይታቸው ስኬታማ ጊዜን እንደሚያሳልፉ እምነታቸውን ገልፀዋል፡፡
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በበኩላቸው አካዳሚው የስልጠና ፍላጎት ጥያቄያቸውን ተቀብሎ ስልጠናውን ስላመቻቸ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው በተሟላ የስልጠና ማዕከል ስልጠና መውሰዳቸው ለቀጣይ ተልዕኳቸው እንደሚያግዛቸው ገልፀዋል፡፡
የአፍሪካ አመራር አካዳሚና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
የአፍሪካ አመራር አካዳሚን በመወከል ስምምነቱን የተፈራረሙት የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ ሕይወት አለማሁ ሲሆኑ በስነስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት አካዳሚው እንደ አዲስ ከተደራጀ አንድ ዓመት ማስቆጠሩን አስታውሰው ተልዕኮውን ለማሳካት ከሀገር ውስጥና ከውጭ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሆነና የኢትዮጵያ አየር መንገድም ስኬታማ ተቋም በመሆኑ አብረው በመስራታቸው ደስተኛ እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡
ሁለቱ ተቋማት በጋራ ሊሰሩ የተስማሙባቸው ጉዳዮች በስልጠና፤ በምርምር፤ በማማከርና በዕውቀት ሽግግር እንደሆነ የገለፁት ምክትል ርዕሰ አካዳሚዋ አብረው በመስራታቸው ተቋሙ ሊያሳካ የሚያስበውን የፓን አፍሪካኒዝም አስተሳሰብን ተግባራዊ ለማድረግ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለውም አመላክተዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድን በመወከል ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ ማኒጂንግ ዳይሬክተር አቶ መሳይ ሽፈራው በበኩላቸው አየር መንገዱ በሀገር ውስጥና በውጭ ካሉ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራና ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውሰው ሁለቱ ተቋማት በትብብር ለመስራት መስማማታቸው በሀገር ደረጃ የተያዘውን ራዕይ ለማሳካት እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡