African Leadership Excellence Academy
2.29K subscribers
2.47K photos
96 videos
6 files
114 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸውን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ገለፁ።

ፕሬዝዳንቱ "በእውቀትና በክህሎት የተገነባ አመራር ለላቀ ውጤት " በሚል መሪ ቃል ለክልሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት ላይ ናቸው።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ እንዳሉት ድህነት የሀገርን እና የዜጎችን ክብር ዝቅ የሚያደርግ መሆኑን መረዳት እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

የአመራሮች የመሪነት ጥበብና የዜጎች የስራ ትጋት እምቅ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ሀብት ጋር ተደምሮ ከተሰራ ድህነትን መሻገር ይቻላል ብለዋል ።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የድህነት መጥፎ የታሪክ ገፅን መቀየር የሚያስችሉና በምሳሌነት የሚጠቀሱ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አሳውቀዋል ።

እናም በመከናወን ላይ ያሉ ሁሉን አቀፍ ስራዎች ቀጣይነት ባለው መልኩ ሁለንተናዊ ልዕልና እውን እንዲሆን የአመራሮችን ቁርጠኝነት ያስፈልጋል ብለዋል ።