African Leadership Excellence Academy
2.13K subscribers
2.38K photos
89 videos
6 files
104 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የአፍሌክስ ፕሬዚደንት ዛዲግ አብርሃ በሚል ርዕስ #የማወቅ_የመፈጸምና_በማያቋርጥ_ሁኔታ_ውጤታማ_የመሆን_ምስጢርና_የጉጉት_ኃይልና_አስተዋጽኦ ለአመራሮች የሰጡትን የአመራር ልማት ስልጠና ከአካዳሚው ዩቱዩብ ቻናል እና የፌስቡክ ገጽ ይከታተሉ። በዩቱዩብ ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ
https://www.youtube.com/watch?v=TkDJRy1GNTI

👉 የአንድን ሰው፤ የአንድን ተቋም እና የአንድ ሀገር መነሻዎች የሚወስኑት አራት ነገሮች ምንድን ናቸው?

👉 የት መሔድ ነው የምንፈልገው? የት ነበርን? ዛሬስ የት ላይ ነን? ነገ የት መሔድ ነው የምንፈልገው ? እነዚህን ጥያቄዎች የመለሱ ግለሰቦች፤ ተቋማት እና ሀገራት ምን ያገኛሉ?

👉 ሰዎች የረጅም ጊዜ አሻጋሪ የስትራቴጂ ስራዎችን ትተው በዛሬ ስራ ላይ ለምን ይጠመዳሉ?

👉 አንድን ሀሳብ ማሰብ ብቻ የት ያደርሳል? መፈጸምስ?

👉 የተሟላ ስትራተጂ ምልከታ ያለው ግለሰብ፤ ተቋም እና መሪ ሀሳቡን ወደ ተጨባጭ ስትራቴጂ ለመቀየር ምን ያስፈልገዋል?

👉 የወደፊቱን የሚያስቡ ግለሰቦች፤ ቡድኖች፤ ካምፓኒዎች፤ መሪዎች እና ሀገራት መለያቸው ምንድን ነው?

👉 የጉጉታችን መነሻ ምንድን ነው? ጉጉት የምንለውስ የትኛውን ነው? ትክክለኛ ጉጉታችንን በምን እንለየዋለን?
የልህቀት አካዳሚና የጋራ ምክር ቤቱ በአቅም ግንባታና ምርምሮች በጋራ ለመሥራት የደረሱበትን ስምምነት ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 17/2017(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በአቅም ግንባታ፣ ጥናትና ምርምሮች ላይ በጋራ ለመሥራት የደረሱበትን ስምምነት ተግባራዊ ማድረግ ጀምረዋል።

ተቋማቱ ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም በተለያዩ መስኮች በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

የመግባቢያ ሰነዱን ወደ መሬት ለማውረድ ከሁለቱ ተቋማት የተውጣጣ የቴክኒክ ቡድን በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራት ላይ የጋራ ዕቅድ አዘጋጅቷል።

በዛሬው ዕለትም በተዘጋጀው ዕቅድ ዙሪያ የአካዳሚው እና የጋራ ምክር ቤቱ አመራር አባላት የተወያዩ ሲሆን፤ በአቅም ግንባታ፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች በጋራ የመስራት እንቅስቃሴ ጀምረዋል።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት መሰረት ደስታ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በስምምነቱ መሰረት አካዳሚው ለፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባlaት የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን ይሰጣል።

በዚህም ያሉ ክፍተቶችን በጥናት በመለየት እንደሚሰራ ጠቁመው፤ የፖሊሲ ማማከር ሥራዎችንም አካዳሚው እንደሚያከናውን አብራርተዋል።

በዚህ ዓመት ለ120 የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላት የአቅም ግንባታ ሥልጠና እንደሚሰጥ ገልጸው፤ ሥልጠናው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስረድተዋል።

በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ሁኔታዎችን በላቀ ደረጃ የሚረዳና በቂ ግንዛቤ የጨበጠ አመራር ወሳኝ ነው ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቷ፤ በተቋማቱ መካከል የተደረገው ትብብር ይሄን ግብ ለማሳካት ያለመ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ በበኩላቸው፤ ያለን አንድ ሀገር ነው፤ ኢትዮጵያን በጋራ ለመገንባት መረባረብ አለብን ነው ያሉት።

በስምምነቱ መሰረት ኢትዮጵያን በጋራ መገንባት የሚያስችሉ ሀሳቦች የሚንሸራሸርባቸው የውይይት መድረኮች እንደሚካሄዱም ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ሰፍኖ የቆየውን የፖለቲካ ስብራት ለመጠገን መሰል ትብብሮች ቁልፍ ሚና እንዳላቸውም ነው ያስረዱት።

ምክር ቤቱ ከአካዳሚው ጋር በፈጠረው ግንኙነት ሀገራዊ አስተዋጽኦን የሚያሳድግበት ልምድ የቀሰመ ሲሆን፤ ግንኙነቱ በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ አቶ መለሰ ዓለሙ በበኩላቸው፤ ተቋማቱ በጋራ ለመስራት መወሰናቸው ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አዎንታዊ ሚና ይጫወታል።

ተቋማቱ በጋራ ለመተግበር የያዟቸው ግቦች እንዲሳኩ ሁሉን አቀፍ ርብርብ ማድረግ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል።
የመንግስት ግዥ እና ንብረት ባለስልጣን ሴት አመራሮች በአፍሌክስ የአመራር ልማት ስልጠና ወሰዱ

ሱሉልታ ሚያዚያ 17/2017 (አፍሌክስ) - የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን ሴት አመራሮች ሱሉልታ በሚገኘው የአፍሌክስ የአመራር ልማት ማዕከል የአመራር አቅም ግንባታ ስልጠና መውሰድ ጀምረዋል።

መርሃ ግብሩ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ሴት የቡድን መሪዎችን እና ስራ አስፈፃሚዎች ጨምሮ 44 ተሳታፊዎችን ይዟል።

ስልጠናው የአመራር ልማት እና የልቦና ውቅር ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ ለተቋም አመራር ወሳኝ የሆኑ ርዕሶችንም አካቷል።

ስልጠናው መሪዎቹ በስራ ላይ የሚገጥሙ ውስብስብ ፈተናዎችን በመፈተሽ እና አወንታዊ የስራ አካባቢን በመፍጠር ውጤታማ የለውጥ አመራርን መተግበር እንዲችሉ ማገዝን አላማው አድርጓል።

የአመራር መርሆዎችን ግንዛቤ ለማሳደግ የሚያስችሉ ገለጻዎች እና ውይይቶች የስልጠናው አካላት ናቸው።
በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች የከተማዋን ተወዳዳሪነት በእጅጉ የሚያጎሉ ናቸው

በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ እየተከናወኑ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎች የከተማዋን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በእጅጉ የሚያሳድጉ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

የፕሮጀክቶች በፍጥነትና በጥራት መጠናቀቅ የመፈጸም አቅምን ከፍ ያደረገ ስለመሆኑም ተጠቁሟል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ተጠሪ ተቋማት እና የብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የካሳንቺስ የኮሪደር ልማት ስራዎችን፣ የመልሶ ማልማት፣ የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል፣ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልና ጨምሮ ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

በዚሁ ወቅት በሰጡት አስተያየትም የልማት ስራዎቹ የከተማዋን ዕድገት የሚያፋጥኑና የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የተሳተፉት አለሙ ገላን ለልማት ተነሺዎች ሁሉንም ዓይነት የመሠረተ ልማት ያሟላ የመኖሪያ ቤት ጨምሮ ለኑሮ ምቹ የሆነ ከባቢ መሰጠቱ ልማቱ ህዝቡን ተጠቃሚ እያደረገ ለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

አቶ ብሩክ አመንቴ በበኩላቸው፥ አዲስ አበባ ለሌሎች ከተሞች ሞዴል መሆን ወደ ምትችልበት ደረጃ እየተሸጋገረች መሆኗን አንስተዋል፡፡

አዲስ አበባ በከፍተኛ የለውጥ ሂደት ላይ እንደምትገኝ የተጠናቀቁና በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ የልማት ስራዎች ማሳያ እንደሆኑም የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡
የአካዳሚው ስራ አስፈፃሚዎች እንደገለጹት በአዲስ አበባ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡና የስራ ባህልን የቀየሩ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

በዚህም በኮሪደር ልማት፣በመልሶ ማልማት፣በወንዝ ዳርቻ፣ የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል፣ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እንዲሁም ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የብቃትና የሰው ሃብት ስራ አስፈፃሚ ገዛኸኝ መጎ በበኩላቸው፥ የልማት ስራዎቹ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ መጠናቀቃቸው የፕሮጀክት የመፈጸም አቅም እያደገ ለመምጣቱ ሁነኛ ማሳያ ናቸው ብለዋል፡፡

በከተማዋ የኮሪደር ልማትና ሌሎች ፕሮጀክቶች የአዲስ አበባን ገፅታ እየቀየሩ መሆኑን እንደተመለከቱም ጠቅሰዋል።

አስተያየት ሰጪዎቹ አክለውም፥ በአዲስ አበባ በከተማ ግብርና ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡

የልማት ስራዎቹ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረጉ መሆኑን በማንሳት በፕሮጀክቶቹ ውስጥ በርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ገልጸዋል።

ህብረተሰቡም ለልማት ስራዎቹ ስኬታማነት እያደረገ የሚገኘውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

መረጃዎቹን ከኢዜአ አግኝተናል::
#Miss_it_not!

Dear staff and interested individuals, you are cordially invited to participate in Training and discussion on "Contemporary National and International Issues and Ethiopia's Response."

#Presenter:- Mr Zadig Abraha

Date: 20-24/08/2017 E.C
Time:- 2:30 Local time
place:- Multipurpose Hall
AFLEX Collaborates with LLEAP to Deliver Transformative Leadership Program in Ethiopia

Addis Ababa, Ethiopia – April 25, 2025 – AFLEX has joined forces with the Leveraging Leadership in Ethiopia Accelerator Program (LLEAP) to provide an immersive leadership training program for leaders at the Academy.