African Leadership Excellence Academy
2.13K subscribers
2.38K photos
89 videos
6 files
104 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የአፍሌክስ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ እና በኢትዮጵያ የማልታ አምባሳደር በትብብር ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዱ።

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2017 (አፍሌክስ) -
የአፍሌክስ ፕሬዝደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ በኢትዮጵያ የማልታ ሪፐብሊክ አምባሳደር ሮናልድ ሚካሌፍ ጋር ቀደም ሲል በተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት (MoU) አፈፃፀም ላይ ተወያይተዋል።

በአፍሌክስ ዋና መስሪያ ቤት የተካሄደው ስብሰባ በማልታ እና በኢትዮጵያ መካከል በአመራር ልማት እና ተያያዥ ዘርፎች ዙሪያ ትብብርን ማሳደግ ላይ ያተኮረ ነው።

አቶ ዛዲግ በውይይቱ ላይ "በተለዩ የትብብር መስኮች ላይ ስራዎችን በፍጥነት ተግባራዊ ለማድረግ ቅድሚያ ልንሰጥ ይገባል" ብለው። የመግባቢያ ሰነዱን ስኬታማነት ለማረጋገጥ የሚወሰዱ እርምጃዎችን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

አምባሳደር ሚካሌፍ በንግግራቸው ኢትዮጵያ እንደ ሃገር አፍሌክስ እንደ ተቋም እያካሄዱ ላለው ለውጥ አድናቆታቸውን ገልፀው፣ "ኢትዮጵያ በጥቂት አመታትውስጥ በተሃድሶው ብዙ ለውጥ አድርጋለች። ይህም በእጅጉ የሚደነቅ ነው" ብለዋል። በተጨማሪም፣ የአረንጓዴ ልማት አጀንዳ፣ ሰውሰራሽ አስተውሎትና የስነምግባር አመራርን ጨምሮ በርካታ የትብብር መስኮችን ጠቁመው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የአመራር ክህሎትን በማዳበር ለነዚህ ውጥኖች መሳካት ቁልፍ ተቋም መሆኑን ጠቅሰዋል።

በውይይቱ የመግባቢያ ስምምነቱ የትብብር መስኮች ብሎ የዘረዘራቸው የሥልጠና መርሃ ግብሮችን በጋራ ማዘጋጀትን ጨምሮ ሌሎች የአመራር ልማትን ለማሳደግ ያለሙ ውጥኖች ተነስተው፣ እንዴት ይተግበሩ በሚለው ላይ ከስምምነት ተደርሷል።

ውይይቱ ሲጠናቀቅ፣ አምባሳደሩ እና የአፍሌክስ ፕሬዝዳንት የመግባቢያ ሰነዱን ስኬታማ ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራር እና ሰራተኞች የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር እቅድ ሃገራዊ እና ተቋማዊ አፈፃፀም ላይ ውይይት አደረገ::
የእቅድ አፈጻጸም ከተቀመጠው ግብ አንጻር 87.67 % ያሳካ እንደሆነም ተገልጿል።

ሱሉልታ 8/8 2017 ዓ.ም /አፍሌክስ/ የአካዳሚው የአመራር ልማት ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ መሰረት ደስታ በፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የቀረበውን የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ሃገራዊ እቅድ አፈፃፀም ሱሉልታ በሚገኘው የአካዳሚው የአመራር ልማት ላይ ገለፃ ሰተዋል፡፡

ኃላፊዋ ኢትዮጵያ አንደ ሀገር በበጀት አመቱ 8.4 እድገት ለማስመዝገብ እቅድ የያዘች አንደሆነ እና አለም አቀፍ የኢኮኖሚ አዝማሚያና ለኢትዮጵያ ያለው እንድምታ ምን ይመስላል፣ ሀገራችን ላይ እየተከናወኑ ያሉ ዋና ዋና መሰረተ ልማት እና ፕሮጀክት አፈፃፀም ላይ የተሰሩ ስራዎች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 98.66% የተናቀቀ መሆኑ፣ የ ኮሪደር ልማቱ በአዲስ አበባ እና በዋና ዋና የክልል ከተሞች በአፋጣኝ ሁኔታ እየተገነባ መሆኑ ከተሞቻችንን ከማስዋብ በላይ የቱሪዝም ተደራሽነት እና ትራንስፖርትና ፍሰትን ከማሳለጥ አኳያ ብዙ ስራ እንደተሰራ ተናግረዋል።

ወ/ሮ መሰረት ዘላቂ ልማት ማህበራዊ አካታችነት ላይ ልማቱ ለማህበረሰቡ አንድምታ ያለው ጥቅም፣ በበጀት ዓመቱ የኢነርጂ ተጠቃሚነት በሰፊው ጭማሪ ማሳየቱ፣ የትምህርት ዘርፉን ተደራሽነት ማስፋት፣ የእናቶች እና ህፃናትን ሞት በመቀነስ ላይ ብዙ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል፡፡ ሃገራችንን ከተረጅነት ለመላቀቅና ሰብአዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች መሰራታቸውንም አብራርተዋል።
ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ አውድን በመገንዘብ እየተገኙ ያሉ ስኬቶችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም አስታውቀዋል፡፡

በአፍሌክስ የስትራቴጂ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አቶ ሲሳይ ዘሪሁን የአካዳሚውን የ 2017 ዓ. ም የ9 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል ።
መሰረታዊ አገልግሎትን ማቀላጠፍ እና ፋሲሊቲ ማዘመንና አገልግሎት አሰጣጥንና ቅልጥፍና በማሳደግ ረገድ በተሰራው የአገልግሎት እርካታ ዳሰሳ ጥናት የአገልግሎቶች እርካታ የ9ወሩ አማካይ ከ96% በላይ ለማድረስ መቻሉን ገልጸዋል።

የመሰረተ ልማት ፕሮጀክት ላይ ሱሉልታ የሚገኘውን የአስተዳደር ህንጻ የማገባደድ ስራ እየተከናወነ እንደሆነና የአካዳሚው ዋና የስራ ቦታ ወደ ሱሉልታ የሚዞር መሆኑን ተናግረዋል።

በአካዳሚው የሚሰጡ ስልጠናዎች የሥነ ምግባር ግንባታ እና የሞራል ግንባታን ያካተቱ እንዲሆኑ የመከታተል ስራም ተሰርቷል ብለዋል።
በሚዲያና ኮሚኒኬሽን የአካዳሚውን ገጽታ ለማሻሻልና ለመገንባት የተለያዩ የተግባቦት መሳሪያዎችን እና ስልቶችን በመጠቀም የተቋሙን ስራዎች ለማስተዋወቅ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውንም አብራርተዋል።

በቀረበው ገለጻ ላይ የአካዳሚው ሰራተኞች ሃሳባቸውን አንስተው የተወያዩ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎችም ምላሽ ተሰጥቷቸዋል።
በአጠቃላይ እቅዱ አፈጻጸም ከተቀመጠው ግብ አንጻር 87.67 % ያሳካ እንደሆነ ተገልጿል።
አፍሌክስ ከሲዲ ሞሀመድ ቤን አብደላህ ዩኒቨርሲቲ ጋር አጋርነት መሰረተ

አዲስ አበባ/ ሚያዚያ 8/2017 (አፍሌክስ) -
አካዳሚው መገኛውን በፌዝ፣ ሞሮኮ ካደረገው የሲዲ ሞሀመድ ቤን አብደላህ ዩኒቨርሲቲ ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራርሟል።

ትብብሩ በአመራር ልማት እና ተያያዥ ዘርፎች ላይ ያተኮረ ነው።

አፍሌክስን በመወከል የአካዳሚው ፕሬዝደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ፣ የሞሮኮውን ዩኒቨርሲቲ ወክለው ደግሞ የዩኒቨርሲቲው የሳይንሳዊ ጥናትና ትብብር ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ኤል መስታፋ ኤል ሃድራሚ የመግባቢያ ሰነዱን ፈርመዋል። የፊርማ ስነ ስርዓቱ በአፍሌክስ ዋና መስሪያ ቤት በቨርቹዋል መንገድ ተከናውኗል።

አቶ ዛዲግ አብርሃ በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር "ኢትዮጵያ እና ሞሮኮ ብዙ የሚያመሳስላቸው ሁለት በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ናቸው። ከሞሮኮ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት ስናስብ ቆይተናል እናም የዛሬው ፊርማ ይህን ሃሳብ ወደተግባር የምንቀይርበት ትልቅ ምዕራፍ ነው" ብለዋል። የሚቀጥለው እርምጃ በትብብር መስኮች ላይ የስራ ሂደቱን የሚመራ ኮሚቴ ማቋቋም መሆኑን በመግለጽ ስምምነቱን ለመፈጸም አፍሌክስ ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

ፕሮፌሰር ኤል ሃድራሚ በበኩላቸው ስለ ትብብሩ ሲናገሩ "ይህ ስምምነት በሁለቱ ተቋማት አልፎም በኢትዮጵያና በሞሮኮ መካከል አካዳሚክ ትብብርን የሚያሳድግ እና ውጤታማ የአመራር ልማትን የሚያስፋፋ ነው“ ብለዋል።

የመግባቢያ ሰነዱ የሁለቱን ተቋማት ግንኙነት ለማጠናከር እና የአመራር ክህሎትን ለማሻሻል የሚረዱ የእውቀትና የልምድ ልውውጥን እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ተግባራትን ለመከወን መሰረት የሚጥል መሆኑ ተገልጿል።
እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ!!

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እና ለአፍሌክስ ቤተሰቦች በሙሉ በአሉ የሰላም እና የደስታ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ::

መልካም በአል!

ዛዲግ አብርሃ
የአፍሌክስ ፕሬዝዳንት
የአፍሌክስ ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚሰጡትን የአመራር ልማት ስልጠና እንደቀጠሉ ነው::

በቀጣይ የሚሰጡ ስልጠናዎችን አሳውቁን ባላችሁት መሰረት በቀጣይ ሳምንታት ወደ እናንተ በአካዳሚው የዩቱዩብ ቻናል እና የፌስቡክ ገፃችን የምናደርሳቸውን የአመራር ልማት የስልጠና ቪዲዮዎች ስንጠቁማችሁ በክብር ነው::

1. The power and the art of execution and the fate of our generation from individual to national

2.The science and the art of finishing from individual to national endeavours

3. The key to the secret of leaders and leadership development from individual to national endeavours

4.Communication and its manifold benefits and practices, Communication as a tool of conflict resolution and peacebuilding

5. The power of ideas and our destiny from individual to national

በቅርቡ ይጠብቁን!! በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን ላይ ያገኙናል!!
የአፍሌክስ ፕሬዚደንት ዛዲግ አብርሃ በሚል ርዕስ #የማወቅ_የመፈጸምና_በማያቋርጥ_ሁኔታ_ውጤታማ_የመሆን_ምስጢርና_የጉጉት_ኃይልና_አስተዋጽኦ ለአመራሮች የሰጡትን የአመራር ልማት ስልጠና ከአካዳሚው ዩቱዩብ ቻናል እና የፌስቡክ ገጽ ይከታተሉ። በዩቱዩብ ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ
https://www.youtube.com/watch?v=TkDJRy1GNTI

👉 የአንድን ሰው፤ የአንድን ተቋም እና የአንድ ሀገር መነሻዎች የሚወስኑት አራት ነገሮች ምንድን ናቸው?

👉 የት መሔድ ነው የምንፈልገው? የት ነበርን? ዛሬስ የት ላይ ነን? ነገ የት መሔድ ነው የምንፈልገው ? እነዚህን ጥያቄዎች የመለሱ ግለሰቦች፤ ተቋማት እና ሀገራት ምን ያገኛሉ?

👉 ሰዎች የረጅም ጊዜ አሻጋሪ የስትራቴጂ ስራዎችን ትተው በዛሬ ስራ ላይ ለምን ይጠመዳሉ?

👉 አንድን ሀሳብ ማሰብ ብቻ የት ያደርሳል? መፈጸምስ?

👉 የተሟላ ስትራተጂ ምልከታ ያለው ግለሰብ፤ ተቋም እና መሪ ሀሳቡን ወደ ተጨባጭ ስትራቴጂ ለመቀየር ምን ያስፈልገዋል?

👉 የወደፊቱን የሚያስቡ ግለሰቦች፤ ቡድኖች፤ ካምፓኒዎች፤ መሪዎች እና ሀገራት መለያቸው ምንድን ነው?

👉 የጉጉታችን መነሻ ምንድን ነው? ጉጉት የምንለውስ የትኛውን ነው? ትክክለኛ ጉጉታችንን በምን እንለየዋለን?