African Leadership Excellence Academy
2.15K subscribers
2.38K photos
90 videos
6 files
105 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
በሃሳብ እና በፈጠራ ወይም ግኝቶች መካከል ንጽጽራዊ መረጃ አቅርበው ሃሳብ በሁሉም ነገር ላይ ፍጹም የበላይነት እንዳለው አሳይተዋል። “አሁን ላይ መሪ የሚባለው በጉልበት ሳይሆን በሃሳብ ልቆ የተገኘ ነው!” ብለዋል በገለጻቸው።

“እድገት ማስመዝገብ ከፈለግን የት ነበርን፣ አሁን የት ነን፣ ወዴት መሄድስ እንፈልጋለን? የሚሉትን ጉዳዮች ጠንቅቀን ልናውቅ እና ልንመልስ ይገባል።” ብለዋል።

“እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ ስለ ጉዞአችን እና ስለሚገጥሙን ፈተናዎች ጥልቅ መረዳት እንዲኖረን እናም ሁሉን አቀፍ እድገት ማስመዝገብ እንድንችል ይረዳናል።” ሲሉም ተናግረዋል።

አመራር እና ሰራተኛው የአካዳሚውን የለውጥ ጉዞ በብቃት እንዲመራ ክህሎቶችን የማስታጠቅ አላማን የሰነቀው ስልጠና አሁንም መካሄዱን ቀጥሏል።
የመንግስት ግዥ እና ንብረት ባለስልጣን በአፍሌክስ የአመራር ልማት ስልጠና መውሰድ ጀመረ

ሱሉልታ መጋቢት 11/2017 (አፍሌክስ) - የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን አመራሮች ሱሉልታ በሚገኘው የአፍሌክስ የአመራር ልማት ማዕከል የአመራር አቅም ግንባታ ስልጠና መውሰድ ጀምረዋል።

መርሃ ግብሩ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን የቡድን መሪዎች፣ ስራ አስፈፃሚዎችና የጽሕፈት ቤት ኃላፊዎችን ጨምሮ 30 ተሳታፊዎችን ይዟል።

ጅማሮውን ዛሬ ያደረገውና ለተከታታይ 4 ቀናት የሚቆየው ስልጠናው እንደ ትራንስፎርሜሽን እና አገልጋይ አመራር፣ የለውጥ አስተዳደርና የሰራተኞች ልማትን የመሳሰሉ ለተቋም አመራር ወሳኝ የሆኑ ርዕሶችን አካቷል።

የስልጠናው ርዕሶች የተመረጡት ተሳታፊዎች በተቋማቸው ውስጥ ውጤታማ አመራር እንዲኖራቸው አስፈላጊ የሆኑት ክህሎቶችን ለማስታጠቅ ታስቦ እንደሆነ ተገልጿል።

ስልጠናው መሪዎቹ በስራ ላይ የሚገጥሙ ውስብስብ ፈተናዎችን በመፈተሽ እና አወንታዊ የስራ አካባቢን በመፍጠር ውጤታማ የለውጥ አመራርን መተግበር እንዲችሉ ማገዝን አላማው አድርጓል።

የአመራር መርሆዎችን ግንዛቤ ለማሳደግ የሚያስችሉ ገለጻዎች እና ውይይቶች የስልጠናው አካላት ናቸው።