"አፍሌክስ የሃሳብ ማመንጫ፣ ማከማቻ እና ማሰራጫ ማዕከል ሆኖ የማገልገል ራዕይ አለው!” ዛዲግ አብርሃ የአፍሌክስ ፕሬዝደንት
አቶ ዛዲግ አብርሃ የአፍሌክስን የሃሳብ ማዕከል የመሆን ራዕይ እና ለዚህም ከአመራሩ እና ከሰራተኛው የሚጠበቀውን ሃላፊነት የተመለከተ ገለጻ አደረጉ።
ሱሉልታ መጋቢት 12/2017 (አፍሌክስ) - ፕሬዝደንቱ አካዳሚው የሃሳብ ማመንጫ፣ ማከማቻ እና ማሰራጫ ማዕከል የመሆን ራዕዩን ከግብ ለማድረስ የጀመረውን የለውጥ ጉዞ በብቃት ለመምራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።
ገለጻው የተደረገው አራተኛ ቀኑን በያዘው ስልጠና ላይ ሲሆን በቀደሙት የስልጠናው ቀናት የሃሳብን ሃያልነት አጽንዖት ሰጥተው ሲናገሩ የቆዩት አቶ ዛዲግ፣ ዛሬ የአፍሌክስን የሃሳብ ማዕከልነት የንንግራቸው ትኩረት አድርገዋል።
ስለ-አይዲዬሽን ስፔስ (Ideation Space) /የሃሳብ ማመንጫ፣ ማከማቻ እና ማሰራጫ ስርዐት በሰፊው ያብራሩት ፕሬዝደንቱ፣ ይህ ስርዐት በግለሰብ፣ በቡድን፣ በተቋም እና በሃገር ደረጃ የሚለካባቸውን መስፈርቶች ገልጸው በስርዐቱ ላይ አዎንታዊ እና አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ሁነቶችን በዝርዝር አስረድተዋል።
በሃገራችን ብሎም በአፍሪካ ይህ ስርዐት በእጅጉ እንደሚያስፈልግ አሳስበው ስለአፍሌክስ ሲናገሩ “አፍሌክስ የሃሳብ ማመንጫ፣ ማከማቻ እና ማሰራጫ ማዕከል ሆኖ የማገልገል ራዕይ አለው! ይህንን ራዕዩን ከግብ ለማድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሃላፊነታቸውን በብቃት ሊወጡ ይገባል።” ብለዋል።

March 21
March 21
March 21
በሃሳብ እና በፈጠራ ወይም ግኝቶች መካከል ንጽጽራዊ መረጃ አቅርበው ሃሳብ በሁሉም ነገር ላይ ፍጹም የበላይነት እንዳለው አሳይተዋል። “አሁን ላይ መሪ የሚባለው በጉልበት ሳይሆን በሃሳብ ልቆ የተገኘ ነው!” ብለዋል በገለጻቸው።
“እድገት ማስመዝገብ ከፈለግን የት ነበርን፣ አሁን የት ነን፣ ወዴት መሄድስ እንፈልጋለን? የሚሉትን ጉዳዮች ጠንቅቀን ልናውቅ እና ልንመልስ ይገባል።” ብለዋል።
“እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ ስለ ጉዞአችን እና ስለሚገጥሙን ፈተናዎች ጥልቅ መረዳት እንዲኖረን እናም ሁሉን አቀፍ እድገት ማስመዝገብ እንድንችል ይረዳናል።” ሲሉም ተናግረዋል።
አመራር እና ሰራተኛው የአካዳሚውን የለውጥ ጉዞ በብቃት እንዲመራ ክህሎቶችን የማስታጠቅ አላማን የሰነቀው ስልጠና አሁንም መካሄዱን ቀጥሏል።

የመንግስት ግዥ እና ንብረት ባለስልጣን በአፍሌክስ የአመራር ልማት ስልጠና መውሰድ ጀመረ
ሱሉልታ መጋቢት 11/2017 (አፍሌክስ) - የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን አመራሮች ሱሉልታ በሚገኘው የአፍሌክስ የአመራር ልማት ማዕከል የአመራር አቅም ግንባታ ስልጠና መውሰድ ጀምረዋል።
መርሃ ግብሩ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን የቡድን መሪዎች፣ ስራ አስፈፃሚዎችና የጽሕፈት ቤት ኃላፊዎችን ጨምሮ 30 ተሳታፊዎችን ይዟል።
ጅማሮውን ዛሬ ያደረገውና ለተከታታይ 4 ቀናት የሚቆየው ስልጠናው እንደ ትራንስፎርሜሽን እና አገልጋይ አመራር፣ የለውጥ አስተዳደርና የሰራተኞች ልማትን የመሳሰሉ ለተቋም አመራር ወሳኝ የሆኑ ርዕሶችን አካቷል።
የስልጠናው ርዕሶች የተመረጡት ተሳታፊዎች በተቋማቸው ውስጥ ውጤታማ አመራር እንዲኖራቸው አስፈላጊ የሆኑት ክህሎቶችን ለማስታጠቅ ታስቦ እንደሆነ ተገልጿል።
ስልጠናው መሪዎቹ በስራ ላይ የሚገጥሙ ውስብስብ ፈተናዎችን በመፈተሽ እና አወንታዊ የስራ አካባቢን በመፍጠር ውጤታማ የለውጥ አመራርን መተግበር እንዲችሉ ማገዝን አላማው አድርጓል።
የአመራር መርሆዎችን ግንዛቤ ለማሳደግ የሚያስችሉ ገለጻዎች እና ውይይቶች የስልጠናው አካላት ናቸው።