African Leadership Excellence Academy
2.17K subscribers
2.39K photos
90 videos
6 files
107 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
Happening Now: 🎉

In a stirring keynote address, H.E Ergogie Tesfayie (PhD), Minister of Women and Social Affairs, celebrated the graduates’ unwavering determination.

She highlighted that empowering women not only transforms families but also reshapes society.

Urging unity for national progress, she emphasized the government's strong commitment to enhancing women's participation, recognizing it as essential for unlocking Ethiopia's vast potential.

Together, we rise! 💪🌍
Celebrating Now! 🎉

The atmosphere is electric as we honor the graduates of the Women’s Leadership Development program!

These empowered women are currently stepping into their future, ready to lead and drive change.

#AFLEX #WomensLeadershipDevelopment #Graduation2025 #WLDP
Happening Now: 🎉
Event Highlight

Ms. Mastewal, one of our inspiring graduates, unveiled an innovative tourism project created by her all-female team👩‍🎓.

Their journey through the leadership development program blends practical skills with real-world experience.

This project not only showcases their talent but also sets the stage for a brighter future!

👩‍🎓Empowered to lead🎉!

#AFLEX #WomensLeadershipDevelopment #Graduation2025 #WLDP
የአፍሌክስ ፕሬዝደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ በሴቶች የአመራር ልማት ፕሮግራም ምርቃት ላይ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰዱ ነጥቦች 👇

👉ባለፉት አሰር ሺህ አመታት ሴቶች ወገባቸው ጎብጦ እና ትከሻቸው ተጣሞ እኛ ወንዶች እመሳልሉ ላይ ሽቅብ እንድንወጣ ፈቅደውልናል!

👉ዛሬ ላይ እየተጠየቅን ያለነው ታሪክ እራሱን እንዲደግም ማለትም እኛም በፈንታችን ከመሰላሉ  በመውረድ እነሱ ደግሞ በተራቸው በትከሻችን እና በወገባችን ላይ ተረማምደው የመሳልሉ ጉብታ ላይ እንዲወጡ አይደለም!

👉የተጠየቅነው እኛ እዛው ባለንበት ቦታ ላይ እያለን እንደው ወደ ላይ ለመውጣት እየተፍጨረጨሩ ያሉትን ሴቶች እጃችን በመሰጠት እና ወደ ላይ በመሳብ ትንሽየ አጋዠ ሚና በመጫወት ፍትሀዊ እና ሚዛናዊ የሆነ ማህበረሰብን እውን እናድርግ ብቻ ነው!

👉እንደአፍሌክስ እምነት ከሆነ የእያንዳንዷ ሴት ልጅ መዳረሻ ስፍራና ማረፊያ ቦታ በእሷ ፍላጎት ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚከወን ጉዳይ እስኪሆን ድረስ ሴቶችን የማብቃትና ወደ ፊት የማምጣት ትግሉ ሳያለሰልስ ሊከናውን ይገባል!

👉በመሆኑም አፍሌክስ ይሄው ልምምድ በህረተሰቡ ወግና ባህል ውስጥ የሰረፀና የፀና የአዘቦት አሰራር እስዲሆን በሚሰራው ስራ ውስጥ የበኩሉን አዎንታዊ ሚና ለመጫወት እንደሚታጋ ሊያረጋግጥላችሁ ይወዳል!
አፍሌክስ እና የሸገር ሲቲ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ - የካቲት 13/2017 ዓ.ም (አፍሌክስ)- አፍሌክስ እና የሸገር ከተማ አስተዳደር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የአፍሌክስ ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ እና በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምክትል ፕሬዝደንት ማዕረግ የሸገር ሲቲ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ፈርመዋል።

ትብብሩ የሱሉልታ ዳቮስ ፕሮጀክትን እውን ለማድረግ እና የሸገር ከተማ አመራሮችን በአመራር ልማት ለማብቃት ያለመ ነው።

በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የአፍሌክስ ፕሬዝደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ የከተማ ልማትን አስፈላጊነት አስመልክተው "መጪው ጊዜ የከተሞች ነው፣ በ2040ዎቹ ደግሞ ከአለም ህዝብ ሶስት አራተኛው የከተማ ነዋሪ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል" ብለዋል። አክለውም "ከተሞች የእድገትና የብልፅግና ምንጭ በመሆናቸው በከተሞች ላይ ኢንቨስት ማድረግ አለብን" ሲሉ አሳስበዋል።

አቶ ዛዲግ "ሱሉልታ በተፈጥሮ የታደለችው ነፋሻማ አየርና ለአዲስ አበባ ያላት ቅርበት ለአለም አቀፍ እና አህጉራዊ ዝግጅቶች ተስማሚ ያደርጋታል" ሲሉ ተናግረው፣ "አፍሌክስ በሸገር ሲቲ እድገት ውስጥ ትልቅ ሚና መጫወት ይፈልጋል" ሲሉ የአፍሌክስን ሃሳብ አስረድተዋል።

በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምክትል ፕሬዝደንት ማዕረግ የሸገር ሲቲ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ሸገር አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ከተማ ለመሆን ያላትን ፍላጎት አፅንኦት ሰጥተው ለዚህ አላማ የአመራር ክህሎትን አስፈላጊነት ሲናገሩ፡ “ከተማዋን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ከተማ ለማድረግ አቅደናል፤ ይህንንም ለማሳካት የአመራር ክህሎት አስፈላጊ ነው፣ ለዚህም አፍሪካዊ የአመራር ልማት ማዕከል ከሆነው ከአፍሌክስ ጋር እንሰራለን” ብለዋል።
ከንቲባው አያይዘውም ያለንን ሀብት ለህብረተሰቡ ጥቅም ከማዋል ጋር በተያያዘ ያለውን ተግዳሮቶች ጠቅሰው " የዛሬው ስምምነት ያለንን ሃብት አስተባብረን ከተማችንን እውቀት መር፣ አፍሌክስን ደግሞ የላቀ ተቋም ለማድረግ መንገድ ይከፍታል" ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ አጋርነት በሸገር ሲቲ አስተዳደር ውስጥ የአመራር የልማት እንቅስቃሴዎችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንዲሁም ሱሉልታን ወደአለም አቀፍ የሃሳብ ማመንጫ ማዕከል ለማሸጋገር ወሳኝ እርምጃ ነው።
AFLEX Partners with Pan African Youth Union and Ethiopian Youth Council to Empower African Youth Leadership

Addis Ababa, February 20, 2025 (AFLEX) – AFLEX has officially entered into partnerships with the Pan African Youth Union (PAYU) and the Ethiopian Youth Council, signing Memorandums of Understanding (MoUs) today at the SkyLight Hotel in Addis Ababa. These collaborations aim to enhance leadership development among African youth and address the challenges that hinder their full potential.

During the signing ceremony, AFLEX President Zadig Abreha highlighted Africa's demographic advantage, stating, "Africa is a young continent in terms of demography. Amid a global demographic crisis, Africa stands as a beacon of hope with its vibrant youth." He further emphasized the critical choices facing the continent's youth: "The youth of Africa face a choice—seize the opportunity or miss it. We are here together, to empower African youth and transform the continent into a hub of innovation."