African Leadership Excellence Academy
2.33K subscribers
2.52K photos
96 videos
6 files
119 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
"የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ በቅብብሎሽ የሚያሳኩ ተተኪ አመራሮችን መፍጠር ይገባል"-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 26/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ በቅብብሎሽ የሚያሳኩ ተተኪ አመራሮችን መፍጠር ይገባል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ነጸብራቅ የመሪነት ኮንፍረንስ"ን በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አስጀምረዋል።
👍8
በመክፈቻ ንግግራቸውም ኢትዮጵያ ታላላቅ ድሎችን ያስመዘገቡ፣ የስልጣኔ ከፍታን የተቀዳጁ መሪዎች ሀገር ብትሆንም ያንን ማስቀጠል ባለመቻሉ ወደኋላ መቅረቷን ገልጸዋል።
በረዥሙ የሀገራችን ታሪክ ታላላቅ መሪዎች እንደነበሩ በማውሳት በአንድ ወቅት በርተው የጠፉና ሊደገሙ የማይችሉ አመራሮች ሆነዋል ሲሉም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ገናናነት የሚጠቀስባቸው ስኬቶች ከዘመን ዘመን መሸጋገርና መሳካት ያልቻሉት የአመራር ግንባታን እንደሀገር ባለማስቀጠላችን ነው ብለዋል።

አሁን ላይ ኢትዮጵያ የምትጠቀስባቸውን ጉድለቶች በመሙላት ወደ ከፍታ የማሻገር ጉዞ መጀመሩን ገልጸው የተተኪ አመራር ልማትም የዚሁ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል።

ተተኪ ወጣት አመራሮችና ነባሩ አመራር የሚመክሩባቸውና ልምድ የሚለዋወጡባቸው መድረኮች ሲፈጠሩ በአመራር ትውልዶች መካከል መናበብ በመፍጠር ሀገራዊ ትልሞችን ለማሳካት ያስችላል ብለዋል።
በመሆኑም ኢትዮጵያ አመራሮች የምትፈጥርበት እንዲሁም በአመራሮች መካከል የትውልዳዊ ቅብብሎሸ ሥርዓት የምትገነባበት አሠራርና ተቋም እንደሚያስፈልጋት ተናግረዋል።

ይህ የተተኪም ሆነ የነባሩ አመራር ቁልፍ ተልዕኮ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
የሀገር ቀጣይነት ያለው ዕድገትም ሆነ ውድቀት የሐሳብ ጥራት፣ የአመራር ብቃት እና ቁርጠኝነት ላይ የተመሠረተ መሆኑን ጠቅሰው ችግሮችን ወደ ዕድል በመቀየር የሀገርን ዕድገት የሚያሳካ መሪ መሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ነፀብራቅ የመሪነት ኮንፍረንስ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የተሣለጠ የትውልዶች አመራር ቅብብሎሽ የሚቀጥልበትን መንገድ የሚያሳይ ሊሆን ይገባል ብለዋል።
የተጀመሩ ሀገራዊ ኢኒሼቲቮችን በውጤታማነት በማስቀጠል የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ ለማሳካት በትጋትና በብቃት የሚሠራ ተከታታይ አመራር በየዘመኑ ሲኖር መሆኑንም አፅኖት ሰጥተዋል።
👍8
"የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ በቅብብሎሽ የሚያሳኩ ተተኪ አመራሮችን መፍጠር ይገባል"-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
👍8
"ተተኪ ወጣት አመራሮችና ነባሩ አመራር የሚመክሩባቸውና ልምድ የሚለዋወጡባቸው መድረኮች ሲፈጠሩ በአመራር ትውልዶች መካከል መናበብ በመፍጠር ሀገራዊ ትልሞችን ለማሳካት ያስችላል"ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
👍8
H.E. Dr. Ergoge Tesfaye (PhD), Minister of Women and Social Affairs, delivered a powerful message at the Netsebrak Leadership Conference, highlighting the vital leadership role young people play today. She emphasized that youth are not only the leaders of tomorrow, but also key change-makers in the present. By empowering them now, we’re building a more inclusive and prosperous future.

#NLC2024 | Lead with Purpose, Serve with Integrity.
#NLC2024 #LeadershipForChange #YouthEmpowerment #InspiredLeadership #EthiopiaRising #BuildingTomorrow #EmpoweredYouth #FutureLeaders #ConnectingMinds #CollaborationForChange #Networking #BeTheChange #InspiringGenerations #LeadersOfTomorrow #EthiopianLeadership #EthiopiaRising #BoldLeaders #VoicesForChange
👍9
በነጸብራቅ የመሪነት ኮንፈረንስ የመክፈቻ ስነ ስርዐት ላይ የአፍሌክስ ፕሬዝደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ
የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የእለቱ የክብር እንግዳ
ክቡራን ሚኒስትሮች
ክቡራን ሚኒስትር ዴኤታዎች
ክቡራን ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች
ክቡራን የሀይማኖት አባቶች
ክቡራን የሀገር መከላከያ ሰራዊት አመራሮች
ክቡራትና ክቡራን

በቅድሚያ ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትራችን እንኳን ወደ አፍሌክስ ግቢ በደህና መጡ እያልኩኝ ጊዜዎ በእጅጉ የተጣበበ ቢሆንም ተቋሙ ያቀረበልዎትን የክብር እንግድነት ጥሪን ከተቀበሏቸው ሌሎች መሰል ጥሪዎች በላይ የቅድሚያ ቅድሚያ በመስጠት በመካከላችን በመገኘትዎ የተሰማኝን ልባዊ ደስታ እና ምስጋና በዚህ ኮንፈረንስ ታዳሚዎች፣ በተቋሙና በራሴ ስም እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ፡፡ በተመሳሳይም ያቀረብንላችሁን የእንወያይ ጥሪን ተቀብላችሁ በመካከላችን ለተገኛችሁ የዚህ ኮንረንስ ተሳታፊዎች ሁሉ በተቋሙና በራሴ ስም ልባዊ ምስጋናዬን እያቀረብኩኝ በድጋሜ ወደ አፍሌክስ እንኳን በደህና መጣችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡
👍10
ክቡር የእለቱ የክብር እንግዳ
ክቡራትና ክቡራን

ይሄ መድረክ በወትሮ ከሚሰናዱ መድረኮች በእጅጉ ይለያል፡፡ ኮንፈረንሱ ከሁሉም የአገሪቱ ክልሎች የተውጣጡ ተሳታፊዎችን የያዘ በመሆኑ የተሳታፊዎችን ስብጥር ከተለያዩ መስፈርቶች አንጻር ስንመዝነው በከፍተኛ ደረጃ አካታችና በአመዛኙ ወካይ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በእድሜ ስንመለከት ትንሹ የኮንፈረንሱ ተሳታፊ እድሜ 20 ዓመት ሲሆን ትልቁ ደግሞ 59 ዓመት ነው፡፡
አብዛኞቹ ተሳታፊዎች ከ20-29 ኣመት እድሜ ያላቸው ሲሆን ይህም በኮንፈረንሱ ጠንካራ የወጣቶችተሳትፎ መኖሩን ያንጸባርቃል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ጉልህ የሆነው የተሳታፊ ቁጥር ደግሞ ከ30-39 ኣመት የእድሜ ክልል ውስጥ ይወድቃል፡፡ ከ40-45 እድሜ ክልል ውስጥ የሚወድቁት ተሳታፊዎች በቁጥር አናሳ ቢሆኑም ግን ተጽእኖዋቸው ከፍተኛ እንደሚሆን ይገመታል፡፡ በተመሳሳም የኮንፈረንሱን ተሳታፊዎች ስብጥርን በቅጡ በማየት ብቻ አፍን ሞልቶ መናገር አንደሚቻለው በዚህ ኮንፈረንስ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች በአግባቡ ተወክለዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ኮንፈረንሱ በእርግጠኝነት የስርዓተጾታ ሚዛን መስፈርትን በወጉ አሳክቷል ለማለት ያስችላል፡፡ የዚህ ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች

• የሀይማኖት መሪዎች፣
• የሴት አመራሮች፣
• የሚዲያ መሪዎች፣
• የመንግስት አመራሮች፣
• የሀይማኖት መሪዎች፣
• የወጣት አመራሮች ፣
• የንግዱ ዘርፍ መሪዎች፣ እና
• ባለሀብቶች ናቸው፡፡

ከላይ ያቀረብኩት አሀዝ የሚሳየው ኮንፈረንሱ ምን ያክል አካታች እንደሆነና ይሄ ኮንፈረንስ ከዚህ ነጥብ አንጻር ሲለካም ከሌሎች መሰል ኮንፈረንሶች በእጅጉ ቀዳሚ እንደሆነ ነው፡፡ እኔ እስከማውቀው ድረስ የአስፈጻሚው አካላት፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት መኮንኖች፣ የፌደራል ፖሊስ አመራር አባላት፣ የክልል መንግስታት ተወካዮች ፣ የሲቪል ማህበረሰቡ አመራር አባላት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት አመራሮች፣ የትምህርት ተቋማት አመራሮች፣ የግሉ ዘርፍ አመራሮች እንዲሁም ከሁሉም በላይ ደግሞ የተተኪ አመራሮች በስፋት የሚታደሙበት፣ በአንድ ጀማ ታድመው ሀሳብ የሚለዋወጡበት እና በአንድ የመናገሻ አዳራሽ ውስጥ ተገኝተው ማእድ የሚቋደሱበት ከዚህኛው በቀር ሌላ ሸንጎ የለም፡፡

ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
ክቡራትና ክቡራን

ዛሬ ላይ አፍሌክስ ወዳጅ አልባ ተቋም አይደለም፡፡ አለም የማያውቀው ባልንጀራ የጎደለው የጋን መብራትም አይደለም፡፡ በሀገር ውስጥ ከአስፈጻሚው ፣ ከጠቅላይ ፍ/ቤት፣ ከሁለቱ ምክር ቤቶች ፣ ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ፣ ከሲቪክ ማህበራት ፣ ከግል ተቋማት ፣ ከትምህርት ተቋማት ፣ ከመከላከያ ሚኒስቴር ፣ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከደህንነት ተቋማት ጋር አብረን መስራት ጀምረናል፡፡ ወደ ምስራቁ የአለማችን ክፋይ ብትሄዱ ከሲንጋፖሩ ሊ ኩዋን ዪው ስኩል ኦፍ ፐብሊክ ፖሊሲ እስከ ቻይኒስ አካደሚ ኦፍ ገቨርናንስ እና አካደሚ ኦፍ ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ኦፊሻልስ ከተሰኙት ታላላቅ ተቋማት ጋር የወዳጅነት ፊርማ አኑረን ለተግባራዊነቱ እየተረባረብን ነው፡፡ ከዚሁ አካባቢ አሁንም ሳትወጡ ከበርካታ የራሺያ አቻ ተቋማትም ጋር በተመሳሳይ አብሮ የመስራት ስምምነትን በማድረግ ላ እንገኛለን፡፡ በምናብ በምታደርጉት ጉዞ ድካም እንዳይገባችሁ በማሰብ ከዚሁ የኤዥያ አለም ሳንወጣ ፍቃዳችሁ ይሁንና ወደ መካከለኛው ምስራቅ የዣችሁ ልሂድ፡፡ በዚሁ ቀጠናም ውስጥ አንቱታን ካተረፉ ከተባበሩት አረብ ኤመሬትስ እና ከሳውዲ አረቢያ አቻ ተቋማት ጋር ጽኑ የወዳጅነት እርሾ እና አብሮ የመስራት ልምምድ የመሰረት ድንጋይን ቀስ በቀስ በማኖር ላይ እንገኛለን፡፡

ከዚያም ወደ ምእራቡ ብታቀኑ የኔዘርላንዱ ክሊንዳል (Clingdal) ኢንስቲቲዩት እስከ የአሜሪካኖቹ ሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ እና ሲራከስ ዩኒቨርሲቲ ድረስ የተዘረጋ የአጋርነት መረብን ዘርግተናል። መቼም እሰካሁን ድረስ ለምንድን ነው የዚህ ሁሉ አገር እና አህጉር ስም ሲጠቀስ የአንድም አፍሪካዊ ተቋም ስም በአጋርነት ዝርዝሩ ውስጥ ያልተጠቀሰው ስትሉ ጥያቄ ማንሳታችሁ እና በሁኔታው አፍሪካ ቀረች እንዴ ስትሉ ሀሳብ ገብቷችሁ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ። እንደው ሀሳብ ገብቷችሁ ከሆነ ደግሞ በሀሳቡ ጠልቃችሁ ከመጓዛችሁ በፊት የሚገላግላችሁን አንዳች ቁም ነገር ላካፍላችሁ። የማጋራችሁ ሀሳብም ግድ የለም ሀሳብ አይግባችሁ እስካሁን አጋርነትን ከፈጠርንባቸው የተቋማት ዝርዝር ውስጥ የአህጉሪቷ ስም ያልተጠቀሰው መቼም አፍሪካ የኛ ነችና በአጠራር ቅደም ተከተሉ ወደ ሀላ እንድተጠቀሰ ፈልጌ እንጂ ከእሷም ተቋማት ጋር ስላልተወዳጀን አይደለም የሚለውን እውነት ነው። እንዲያውም ከአህጉራዊ ተቋማት ጋር እና ከተናጠል የየአገራቱ ብሄራዊ ተቋማትም ጋር አድማሰ ብዙ በሆነ ሁኔታ እየተወዳጀን ነው። እናማ ከአፍሪካዊ ተቋማትም ጋር በጥብቁ መቆራኘት ጀምረናል ስል ከተጋባባችሁ ሀሳብ የሚገላግል ማረጋገጫ ልሰጣችሁ እፈልጋለሁ። ከአፍሪካ ህብረት ጀምራችሁ ዘ አፍሪካን ካፓሲቲ ቢዩልዲንግ ፋውንዴሽን፣ ዩ ኤን አፍሪካ፣ ኢጋድ ብላችሁ ሳትጨርሱ ከጋና፣ሞሮኮ፣ቱኒዥያ ፣ኬንያ እና ሴኔጋል አቻ ተቋማትም ጋር እንዲሁ ለጋራ ህልም እውንነት አብረን ደፋ ቀናና ተፍ ተፍ በማለት ላይ እንገኛለን። ከዚያም ከባለብዙ ድርሻ ተቋማትም ጋር ከተባበሩት መንግስታት እስከ የደቡብ ደቡብ ትብብር ድረስ የተንሰራፋ የትብብር አድማስን በመገንባት ላይ እንገኛለን።በመሆኑም ዛሬ ላይ እናንተ ፊት ደረታችንን ነፍተን ቆመን ከአራቱም የአለም ክፋይ አቻ ተቋማት ጋር አድማሰ ብዙና አካታች የሆነ ጠንካራ የወዳጅነት መንበርን እያስቀመጥን ነው ብለን ለመናገር በቅተናል። እንግዲህ አንድ ነገር ብንሆን እንኳን ኢትዮጰያውያን የልብ ሀኪሞች ይደርሱልናል በሚል ፅኑ እምነት የማራቶን እሩጫን በመቶ ሜትር የረጅም ጊዜ ባለ ክብረ ወሰን በሆነው በዩሴን ቮልት ፍጥነት እየሮጥን ነው። በእርግጥ እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባው ሀቅና ሊጤን የሚገባው እውነታ እኛ የአፍሌክሰ ሰራተኞቸ በሰራነው ጥቂት ስራ ረክተን ፣ተኩራርተን እና በአጉል የመታበይ ስሜት ተወረን እግራችንን አጣጥፈን የምንቀመጥ ሞኞሞኞችና ተስፋው ጥቂቶች አለመሆንናችንን ነው።

ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
ክቡራትና ክቡራን

የራያው አያቴ ልጄ ውጣና ተወዳጅ እንጂ ሲል አበክሮ ይመክረኝ ነበረ። በዚህ ዘመን እንደ ቡዙዎቹ የተቀየሩ ነገራት ሀሉ የባለፀጋነት ትርጉሙም ሆነ መስፈሪያ እና መለኪያው ደርሶ የተቀየረ ይመስላል። እንደው በአጭሩ በቃ ምን አለፋችሁ ሁሉም ነገር ከኔትወርክ የተቆራኘ ከመሆኑም ባሻገር ይሄው ሀሳብም የብዙ ነገሮች አልፋና ኦሜጋ የሆነበት ወቅት ላይ እንገኛለን። ለዚህ ኮንፈረንስ ታዳሚዎች ልለግሰው የምልፈልገው አንድ ምክር ቢኖር እድሉ ሲገኝ መጠቀም ይገባልና እባካችሁን ይሄን አጋጣሚ ኒትወርካችሁን ለማስፋት ተጠቀሙበት የሚለውን ወንድማዊ ምክር ነው። ሀሳብ ሞልቶ ተርፏችሁ ችግራችሁ የካፒታል ይጥረት ከሆነ ባንኩም ሆነ ባለሀብቱም እዚሁ አሉላችሁ። አለያም ለብዙ ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥር ወርቅ ሀሳብ ይዛችሁ ውጥናችሁ በሆነ ሰንካላ ምክንያት ያልሰመረ ወይም ተሰነካክሎ ከሆነ ክብርት የክህሎትና የስራ እድል ፈጠራ ሚኒስትሯ እዚሁ አሉላችሁ። ሌላ አገር ቢሆን ኖሮ እንደዚህ አይነቱ መድረክ ላይ ለመታደም ስንት ክፍያንና ደጅ መጥናትን በጠየቀ ነበረ።

ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
ክቡራትና ክቡራን
👍8