African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
በአዲሱ መንግሥት የተካተቱ ሚኒስትሮች እና ሚኒስትር ዴኤታዎች በዚህ ሳምንት በሚኖራቸው የሥራ ማስጀመሪያ በሚሳተፉበት ወቅት፣ በአገልጋይ መሪነት ልብ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ። የዚህች ታላቅ ሀገር ዜጎች ከዚህ ያነሰ አገልግሎት አይገባቸውም።
በየአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የተናገሩት

ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር
በየአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ስልጠና እየወሰዱ ካሉ ሚኒስትሮችና ሚኒስትር ዲኤታዎች መካከል ስለ አካዳሚው አገልግሎት አስተያየት ከሰጡን መካከል የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትሩ አብርሐም በላይ (ዶ/ር) አንዱ ናቸው ፡፡
ይህን ብለውናል፡- በሌሎች አገራት ያለውን የአመራር አቅም መገንቢያ የሚስተካከል ተቋም በዚህ ግቢ ውስጥ አይቻለሁ፡፡ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ ቢሰራ ጥሩ ነው የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡ በተረፈ ጥራት ያለው አካዳሚ መኖሩን አይቻለሁ፡፡
አብርሐም በላይ (ዶ/ር)
የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር
በየአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ስልጠና እየወሰዱ ካሉ በአዲሱ መንግሥት የተካተቱ ሚኒስትሮች፤ ሚኒስትር ዴኤታዎች እና የመንግስት ተሹዋሚዎች ውስጥ ስለ አካዳሚው አገልግሎት አስተያየት ከሰጡን መካከል የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍስሃ ይታገሱ ይገኙበታል፡፡
ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህን ብለውናል፡- የአካዳሚው አገልግሎት አሰጣጥ በጣም ጥሩ ነው፡፡ የህንፃው ጥራት፤ የመኝታ ክፍሎቹ፤ መወያያ ክፍሎቹና አዳራሹ በጣም ጥሩዎች ናቸው፡፡ አካዳሚው ዓለም አቀፍ ደረጃን ባሟላ መልኩ የተገነባ ነው፡፡ በሀገራችን ታሪክም የመጀመሪያው የማሰልጠኛ ማዕከል ሳይሆን አይቀርም፡፡ ሀገራችን ውስጥ ባልተለመደ መልኩ ስልጠናውን እዚሁ ወስዶ እዚሁ የመኝታ አገልግሎት አግኝቶ አቅምን መገንባት ጥሩ ነው፡፡ በተሟላ የስልጠና አገልግሎት ውስጥ ጥሩ የሚባል የቡድን መንፈስ ይፈጠራል፡፡ መቀራረብ እንዲኖር ያስችላል፡፡
አቶ ፍስሃ ይታገሱ
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ
በየአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ስልጠና እየወሰዱ ካሉ በአዲሱ መንግሥት የተካተቱ ሚኒስትሮች፤ ሚኒስትር ዴኤታዎች እና የመንግስት ተሹዋሚዎች ውስጥ ስለ አካዳሚው አገልግሎት አስተያየት ከሰጡን መካከል በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ኢንጂነር ይገኙበታል፡፡
ዶክተሩ ይህን ብለውናል፡- በአካዳሚው እያገኘነው ያለው አገልግሎት እጅግ በጣም ዘመናዊና ባደጉ አገራት ውስጥ ያሉትን አይነት ነው፡፡ የአየር ሁኔታውም ለስልጠና ምቹ የሆነ ነው፡፡ በተለይም የስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ተግባራት ቢከናወኑ የተሟላ ይሆናል፡፡ የግቢውን ይዘትም በተወሰነ መልኩ በማሻሻል እጅግ ውብ ማድረግ ይቻላል፡፡ ከግቢው ውጭ ባሉ ቦታዎች ላይም ትኩረት ተደርጎ በደንብ የማስዋብ ስራ ቢሰራ አገልግሎቱን ውብ ያደርገዋል፡፡
ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ኢንጂነር
በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ
በየአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ስልጠና እየወሰዱ ካሉ በአዲሱ መንግሥት የተካተቱ ሚኒስትሮች፤ ሚኒስትር ዴኤታዎች እና የመንግስት ተሹዋሚዎች ውስጥ ስለ አካዳሚው አገልግሎት አስተያየት ከሰጡን መካከል ሰላማዊት ካሳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ይገኙበታል፡፡
ሚኒስትር ዲኤታዋ ይህን ብለውናል፡- በዚህ አካዳሚ አገልግሎት ሳገኝ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ በዚህ ተቋም ውስጥ ገብቼ በመሰልጠኔም እድለኛ እንደሆንኩ ነው የሚሰማኝ፡፡ የተቋሙ አገልግሎት ለማስተዋል ለማሰላሰል ሰፊ ዕድል ይሰጣል፡፡ ስልጠናውን ወደ ተግባር ለመመንዘርም የሚያስችል አገልግሎት ነው ያለው፡፡ የግቢው ስፋትም እየተንቀሳቀሱ ሀሳብን ለማንሸራሸር ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ ካፍቴሪያው፤ አዳራሹ፤ የመወያያ ክፍሎቹ እና ጂሙን የማየት አጋጣሚ አግኝቻለሁ እጅግ ምቹዎች ናቸው፡፡ አፍሪካዊ መሪዎችን ለማፍራት የሚያስችል ደረጃ ላይ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡
ሰላማዊት ካሳ
የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ
አዲስ ምዕራፍ፤ በአገልጋይ መሪነት
ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት በሚፈጠሩ ችግሮች ሳይሸነፍ የነገ ብሩህ ተስፋዋን ዕውን የሚያደረግ አመራር ነው

ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት በየጊዜው በሚፈጠሩ ችግሮች ሳይሸነፍ የነገ ብሩህ ተስፋዋን ዕውን የሚያደረግ አመራረ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ያሉት በአፍሪካ ልህቀት ማዕከል ሲሰጥ የነበረውን የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ማጠናቀቂያ መድረክ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

በኢትዮጵያ አሁናዊ ሁኔታ ችግሮች ቢበዙም የነገዋ ኢትዮጵያ ግን በብሩህ ተስፋ የተሞላች ናት ብለዋል።

በመሆኑም አመራሩ በየጊዜው በሚያጋጥሙ ችግሮች ሳይሸነፍ የተሻለ ነገን ዕውን ለማድረግ ሊተጋ ይገባል ነው ያሉት።

ኃላፊነት የተሰጣቸው አመራሮችም ስራዎቻቸውን ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ እንዲከውኑ አሳስበዋል።

ላለፉት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው የአዳዲስ ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና በሁሉም ክልሎች ተሿሚ አመራሮች ዘንድ እንደሚቀጥል ተገልጿል::
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አህጉራዊ የአመራር ክህሎት ክፍተቶችን ለመሙላት የራሱን ድርሻ ለማበርከት እንደሚሰራ የአካዳሚው ርዕሰ- አካዳሚ ዶክተር ምህረት ደበበ ገለጹ።
ዶክተር ምህረት እንደተናገሩት÷ አካዳሚው በአገሪቷና በአህጉሪቱ የአመራር ክፍተቶችን ለመሙላት የሚሰራ ተቋም ነው።
በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ መሰል የአመራር ክፍተቶች መኖራቸውን ጠቁመው አካዳሚው እነዚህን ችግሮች ለማቃለል የራሱን ድርሻ እንደሚወጣ ነው የተናገሩት።
የአካዳሚው ርዕሰ- አካዳሚ ሆነው ተቋሙን ከተቀላቀሉ ጀምሮ ተልዕኮውን በብቃት እንዲወጣ የሚቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ እየሰሩ መሆኑንም ገልጸዋል።
አካዳሚው ብቁ አመራር ለመፍጠር የሚያስችል ሁሉን አቀፍ የአመራር የሥልጠና ማዕከል መሆኑን ገልጸው የተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ጭምር የሚጠቅም መሆኑን አስረድተዋል።
በዚህ እሳቤ መሰረት አዲስ የተሾሙ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የሕዝብ አገልጋይ መሪ መሆን የሚያስችላቸው የአመራር ክህሎት ሥልጠና ተሰጥቷቸዋል ብለዋል።
ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎቹ በአካዳሚው በነበራቸው ቆይታ ከአካላዊ እንቅስቃሴ ጀምሮ ሥነ-ልቦናቸውን የሚያነቃቁ ለሥራ ዝግጁ የሚያደርጋቸው ሥልጠና መውሰዳቸውንም ጠቁመዋል።