African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
ክቡር አቶ አወሉ አብዲ የአካዳሚያችን ፕሬዚደንት ሆነው በቆዩባቸው ጊዜያቶች ላደረጉልን ሁሉ እናመሰግናለን፡፡ ቀጣይ የስራ ዘመንዎም የስኬት እንዲሆን እንመኛለን፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራሮችና ሰራተኞች “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ሃገራዊ ዘመቻ መርሃ ግብርን አከናወኑ፡፡
አሸባሪው የህወሀት ቡድን በሀገራችን ላይ እያደረሰ ያለውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት ለአሜሪካ መንግስትና ለመላው አለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማድረስ ያለመውን ዘመቻ የአካዳሚው አመራርና ሰራተኞች የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት ” መርሀ ግብርን አከናውነዋል፡፡
የአሜሪካ መንግስት በሃገራችን ላይ እያደረገ ያለውን ጫና በመቃወም እውነታውን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅ የአካዳሚው አመራሮችና ሰራተኞች በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ሃገራዊ ዘመቻ መርሃ ግብርን ሲያከናውኑ እንደተገለፀው 128 የሚሆኑ የአካዳሚው አመራሮችና ሰራተኞች “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ- መንግስት” ዘመቻን ተቀላቅለው ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ የአሜሪካ መንግሰት በአሸባሪው ህወሃት ቡድን የተጋረጠብንን አደጋ ለመመከት የሚደረገውን ትግል ለማደናቀፍና በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ ለመግባት የሚያደርገውን ሙከራ እንዲያቆም ተጠይቋል። የተፈረመው ፖስታም ለአሜሪካ መንግሰት ተልኳል፡፡
ክቡር አቶ ስዩም መኮንን የአካዳሚያችን የስልጠና ዘርፍ ምክትል ፕሬዚደንት ሆነው በቆዩባቸው ጊዜያቶች ላደረጉልን ሁሉ እናመሰግናለን፡፡ ቀጣይ የስራ ዘመንዎም የስኬት እንዲሆን እንመኛለን፡፡
ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የኢፊዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሰየሙ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን በሚመለከት ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ሃሳቦች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የሚከተለውን ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከዚህ ቀደም እንደነበረው አይነት ሳይሆን ተቋሙን የሚመጥኑ ብቃት ያላቸውንና ከፓርቲያችን ወጣ ብለን የተሻለ ብቃት ያላቸውን ሰዎች አምጥተን እያደራጀነው ነው፡፡
ዶ/ር ምህረት ደበበ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል
በየአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የሚሰጡ ስልጠናዎች ውጤታማ እንዲሆኑና የታሰበውን ግብ እንዲያሳኩ የሚያስችል ውይይት እየተካሄደ ነዉ::