African Leadership Excellence Academy
2.35K subscribers
2.56K photos
96 videos
6 files
120 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
The African Leadership Excellence Academy President met with the National Democratic Institute Resident Country Director to discuss the Leadership Program and potential partnership.
Mr. Zadig Abreha, President of The African Leadership Excellence Academy, met with Franklin Oduro, Resident Country Director of the National Democratic Institute in Ethiopia, to explore potential collaborations.
The meeting discussed the Academy's leadership development program, aimed at developing Ethiopian and African leaders' skills, promoting democratic governance, and economic development through joint research, experience-sharing, and staff exchange initiatives.
Zadig Abreha expressed enthusiasm for potential collaboration with the National Democratic Institute, stating their shared goals of promoting democratic values and strengthening local leadership align perfectly.
Franklin Oduro, NDI Resident Country Director, emphasized the significance of fostering robust connections between civil society organizations and government institutions to promote democratic progress in Africa.
During the meeting, AFLEX and NDI discussed several areas of potential collaboration, including Joint Research Initiatives: The Academy and NDI may conduct joint research projects on topics such as leadership development, democratic governance, and economic development.
Organizations can exchange best practices and experiences in leadership development, capacity-building, and institutional strengthening.
The Academy and NDI are planning to exchange staff members to exchange knowledge and insights about each other's programs and methodologies.
The organizations may enter into a partnership agreement to collaborate on promoting democratic values and enhancing Ethiopian and African leadership.
The meeting concluded with both parties agreeing to continue exploring collaboration and partnership, with Mr. Zadig Abreha expressing the hope of positively impacting African leaders' skills.
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት ተስማሙ::

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ዛዲግ አብርሃ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ተፈራርመዋል።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ዛዲግ አብርሃ በፊርማው ስምምነት ወቅት እንደገለፁት ፈጠራ ለሀገር እድገት እጅጉን ጠቃሚ በመሆኑ ለዚህ ብቁ የሆነ አመራር ለመፍጠር ከተቋሙ ጋር በአመራር ልማት ፕሮግራም: በአፍሌክስ አመራር ሽልማት እና በሀሳብ ማመንጫ የመሰረተ ልማት ግንባታ ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በበኩላቸው በሀገሪቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ባህል ተስፋፍቶ እንዲተገበር ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን አብራርተው በዚህም መልካም ውጤት እየተገኘ መሆኑን ገልፀዋል።

ሀገራት በአንድ ዘርፍ ብቻ ኢኮኖሚያቸውን ለማሳደግ የሚያደርጉት ጥረት ብዙም ውጤት ሲያመጣ አይስተዋልም በመሆኑም እኛም ግብርና ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚያችንን አድማሱን ለማስፋት የሚያስችል የአመራር ልማት ስለሚያስፈልግ ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር በመሆን የዘርፉን አመራር አቅም ለመገንባት እየሰራን ነው ብለዋል።

በዚህ ውስጥ የቴክኖሎጂው ዘርፍ የራሱን አበርክቶ እንዲወጣ ለማስቻልም ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

የስምምነቱን አስፈላጊነት ሲገልፁም በግል ከመስራት ይልቅ መተባበርና በጋራ መስራት ውጤታማ እንደሚያደርግ በመታመኑ በሶስቱ ጉዳዮች ላይ ከአፍሌክስ ጋር ለመስራት ተስማምተናል ብለዋል።
👍1
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ነው።
ሀያ ሶስት ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ስልጠና ለስምንት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በተለያዩ የስልጠና ርዕሶች ላይ ሰፊ ስልጠና እየወሰዱ እንደሆኑ በገንዘብ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ማሻሻያና ፕራይቬታይዜሽን ጽ/ቤት ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት እና የስልጠናው አስተባባሪ አቶ ልሳነወርቅ ይርሳው ገልጸዋል።
አስተባባሪው እንደሚገልጹት በተቋማቸው ያለውን የሰው ሀይል አቅም በማስተባበርና በቡድን በመስራት ውጤታማ አፈጻጸም ማምጣት የሚቻልበትን መንገድ የሚያመላክት ስልጠና እያገኙ እንደሆነ ጠቅሰው፤ ለዚህም በአካዳሚው ውስጥ ያሉ አሰልጣኞችም ሙሉ አቅማቸውን በመጠቀም እውቀት እና ክህሎት እያስጨበጧቸው እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ከስልጠናው ርዕሶች መካከልም Future thinking,Discovery and Readiness of future Proof Thinking, Tools and Methods in future Thinking, Developing Future Thinking Competencies and Mindset, Strategies for embedding Future Thinkingin to daily Ministry of Finance Organizational Processes and Strategic Roles, Problem Analysis and Solution design ተጠቃሾች ናቸው።
ስልጠናው በተግባር የተደገፈ በመሆኑ በስራ ውስጥ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት እንደሚያግዝ የገለጹት አቶ ልሳነወርቅ፤ የአካዳሚው የአገልግሎት አሰጣጥም ሰልጣኞች ሀሳባቸው ሳይከፋፈል ሙሉ ለሙሉ ስልጠናው ላይ ብቻ በማተኮር እንዲከታተሉ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል።
ስልጠናው በተለያዩ ዙሮች እንደሚቀጥልም ተገልጿል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ቅድመ ዝግጅት ስራዎች በምስል ይህን ይመስላሉ።
👍4
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና የኢንዱስትሪሚኒስቴር በጋራ ለመስራት ተስማሙ::

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ዛሬ ሀምሌ 12 ቀን 2016 ዓ.ም ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ዛዲግ አብርሃ እና የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ተፈራርመዋል።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ዛዲግ አብርሃ በፊርማው ስምምነት ወቅት እንደገለፁት ከረጅም ጊዜያት ውይይት በሁዋላ ለፊርማ የበቃው ይህ ስምምነት የኢንዱስትሪውን ዘርፍ በብቃት የሚመሩ እና የኢትዮጵያን ብልፅግና የሚያረጋግጡ አመራሮችን በአመራር ልማት ፕሮግራም ለማብቃት ስምምነቱ ወሳኝ ሚና ይኖረዋል ብለዋል::

የዛሬው ስምምነት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚና የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በኢንዱስትሪ አመራር ልማት ፕሮግራም: በኢንዱስትሪ አመራር ሽልማት እና በኢንዱስትሪ የትራንስፎርሜሽን የሀሳብ ማመንጫ የመሰረተ ልማት ግንባታ ላይ እና ጥናት እና ምርምር በጋራ ለመስራት እንደሚያስችላቸው አቶ ዛዲግ አብርሃ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በበኩላቸው አሁን ያለንበት የአለም የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ሁኔታ ተለዋዋጭ በመሆኑ ይህንን ነባራዊ ሁኔታ የሚረዳና አርቆ የሚያስብ እንዲሁም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚደገፍ የኢንዱስትሪ ዘርፍ አመራር ለማፍራት እና ለማብቃት ስምምነቱ አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀዋል።
👍2