የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ካደረጉ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ጋር ውይይት አድርጓል።
በውይይት መድረኩ ላይ ገለፃ ያደረጉት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ (አፍሌክስ)ፕሬዝዳንት ዛዲግ አብርሃ፤ አካዳሚው በኢትዮጵያ ብቻ ሳይወሰን በአፍሪካ አህጉር ብቁ መሪዎችን ለማፍራት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በአፍሪካ ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ ለማረጋገጥና ብቁ አመራር ለማፍራት በሚደረገው ጥረት የኢትዮጵያ ሚና ከጥንት እስካሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ አፍሌክስም ይህንኑ ለማገዝ እየሰራ ነው ብለዋል::
ኢትዮጵያ የቀድሞውን የኬንያ መሪ ጆሞ ኬንያታ እና የነፃነት ታጋዩን ኔልሰን ማንዴላ ማሰልጠኗን አስታውሰው፤ አፍሌክስ ይህንኑ በማስቀጠል በዘመናዊ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ በርካታ አፍሪካውያን እየሰለጠኑ መሆኑን ተናግረዋል።
አካዳሚው የአፍሪካን ችግር የሚፈታ ብቁ አመራር ለማፍራት በሚያስችል መልኩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት በዘመናዊ መልኩ የተደራጀ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
አሁን ላይ ሥልጠና ለመውሰድ ከተለያዪ የአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን ገልጸው፤ ይህንን ፍላጎት ተግባራዊ መልስ ለመስጠትም በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
አካዳሚው በአህጉሪቱ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት የሚያስችሉ ሥራዎችን በስፋት እያከናወነ መሆኑን ተናግረው፤ ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ ከ120 በላይ የአፍሪካ አገራት አመራሮች ሥልጠና መውሰዳቸውን ጠቅሰዋል።

👍2
የመድረኩ ተሳታፊዎችም በተሟላና ዘመናዊ በሆነ መልኩ የተገነባው አካዳሚው ዓላማውም የሚደነቅ በመሆኑ የሁላችንም ድጋፍና እገዛ ያስፈልገዋል ብለዋል።
በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ እያደረገች ላለው የላቀ አስተዋጽዖ ምስጋናቸውን በማቅረብ ሌሎች አገራትም ይህንን መልካም አርዓያ ሊከተሉ ይገባል ብለዋል።

አፍሌክስ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ያደረገው ውይይት በፎቶ:-