African Leadership Excellence Academy
2.35K subscribers
2.56K photos
96 videos
6 files
120 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከUNDP Regional Service Center for Africa ዳይሬክተር እና ከሳሙኤል ግባይዴ ዶኤ (Samuel Gbaydee Doe, UNDP, Resident Representative) ጋር ተወያዩ::
ርዕሰ አካዳሚው ለማትያስ ዘ. ናብ (ዶ/ር) Matthias Z. Naab (PhD) እና ለሳሙኤል ግባይዴ ዶኤ (Samuel Gbaydee Doe, UNDP, Resident Representative) አፍሌክስ በሶስት ዓመት ውስጥ ስለሚተገብራቸው የአመራር ልማት ፕሮጀክቶች ገለፃ አድርገውላቸዋል::
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በጠቅላላ (General) አራት እና በልዩ (Specialized )ሰላሳ ስምንት የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ቀርፆ ወደ ስራ እንደገባ የጠቀሱት አቶ ዛዲግ ለሁሉም ፕሮግራሞች ማስፈፀሚያ የሚሆን ከ2,500 በላይ ገፆች ያሉት ዝርዝር ስትራቴጂ እንደተዘጋጀ ለሀላፊዎቹ አብራርተዋል::
አቶ ዛዲግ አያይዘውም አፍሌክስ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገራት ባለ ድርሻ አካላት ጋር እየሰራ እንደሆነ እና ከ ዩ ኤን ዲ ፒ ጋርም በትብብር በመስራት ያቀደውን ማሳካት እንደሚፈልግ ጠቅሰዋል።
ማትያስ ዘ. ናብ (ዶ/ር) Matthias Z. Naab (PhD) በበኩላቸው አፍሌክስ የአመራር ለውጥ ባደረገ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያቀደው የሪፎርም፤ የማስፋት እና የሽግግር ስትራቴጂ የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው፤ የአፍሌክስ የአመራር ልማት ማዕቀፍ እንዲሳካ ዩ ኤን ዲ ፒ ከአፍሌክስ ጋር ለመስራት ፍላጎት እንዳለው አሳውቀዋል።
ከአፍሌክስ ጋር በትብብር ለመስራትም ጉዳዩን የሚከታተል የዩ ኤን ዲ ፒ ከፍተኛ ባለሙያ እንደተመደበም ማትያስ ዘ. ናብ (ዶ/ር) Matthias Z. Naab (PhD ገልጸዋል::
ከሳሙኤል ግባይዴ ዶኤ (Samuel Gbaydee Doe, UNDP, Resident Representative) በበኩላቸው ከአቶ ዛዲግ ጋር ከዚህ ቀደም የተጀመረውን ግንኙነት ወደ ተግባር ለማሸጋገር የዛሬው ውይይት ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸው፤ የሁለቱን ተቋማት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ መርሀ ግብር እንደሆነ ተናግረዋል።
የUNDP Regional Service Center for Africa ዳይሬክተር እና ከሳሙኤል ግባይዴ ዶኤ (Samuel Gbaydee Doe, UNDP, Resident Representative) የአፍሌክስን ፋሲለቲ ጎብኝተዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና Public Leadership for Gender Equality (PL4GE) የተሰኘ ዓለምአቀፍ ድርጅት በጋራ ሊሰሩ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ።
ውይይቱ የተደረገው በzoom meeting ሲሆን ሁለቱም ተቋማት በስርዓተ ጾታ እና በሴቶች አመራር ልማት ፕሮግራሞች ያከናወኗቸውን ተግባራት እና ወደ ፊት ሊፈጽሟቸው ያቀዷቸው ስራዎች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከPublic Leadership for Gender Equality (PL4GE) ጋር መስራት የሚቻልባቸውን የአመራር ልማት ፕሮግራሞች የገለጹ ሲሆን፤ በተለይም በሴቶች አመራር ልማት ፕሮግራም፤ በህዝብ አመራር ልማት ፕሮግራም እና በተተኪ አመራር ልማት ፕሮግራም ላይ በጋራ መስራት የሚቻልባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ ተናግረዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ የሴቶች አመራር ልማት ፕሮጀክት ቀርጾ እየሰራ እንደሆነ የገለጹት የፕሮጀክቱ ማኔጀር አቶ መስፍን በሀይሉ በበኩላቸው ከፌዴራል መንግስት እና ከከተማ አስተዳደሩ የተውጣጡ ከ50 በላይ ሴቶችን አቅም በአመራር ልማት ፕሮግራም ለመገንባት እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
በPublic Leadership for Gender Equality (PL4GE) የGlobal Center for Gender Equality የFeminist Leadership Director አሌክስ ሙኒቭ Alex Munive በበኩላቸው የተቋማቸውን አጠቃላይ ተልዕኮ እና ከአፍሌክስ ጋር ለመስራት በሚቻልባቸው የትብብር መስኮች ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ አቅርበዋል።
ሁለቱ ተቋማት በቀጣይ በትብብር መስራት እንዲችሉ በተመረጡ የሰነድ ዝግጅቶች ላይ ባለሙያዎችን መድበው ውይይቱ ተጠናቋል።
አቶ ዛዲግ አብርሃ_trial_0.mpg
51.2 MB
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ የሁለት ውሀዎች ዐቢይ ስትራቴጂ መፅሐፍ ላይ ዳሰሳ አቅርበዋል። ስለ መጽሀፉ ከሰጡት አስተያየት ውስጥ የሚከተሉት ሀሳቦች ይገኙባቸዋል።
መፅሀፉ በውስጡ የያዛቸው ጉዳዮች
• በሁለቱ የአባይ ተፋሰስ እና በቀይ ባህር ላይ ያላትን አቋም የሚያንፀባርቅ የፖሊሲ ሰነድ ሆኖ ተዘጋጅቷል
• መፅሀፉ የአባይ ተፋሰስ እና ቀይ ባህር ቁልፍ የብሔራዊ ደህንነትን ይዳስሳል
• ሀገራችን ቀዳዳዎቿን እየደፈነች ስብራቶቿን እየጠገነች የምትሔድበት ነው
• የባህር ህግ አጠቃላይ ስምምነቶች መርሆዎችና ድንጋጌዎች
• የኢትዮጵያን የባህር በር የማግኘት ጥያቄዎች ከህግ መርሆዎች አንፃር ይመለከታል
• የባህር በር አልባ ሀገራት ተሞክሮን በዝርዝር ይዳስሳል
• በአክሱምና ዛግዌ ዘመናተ መንግስት የነበረውን መልክ ያሳያል
• በዘመናዊ ኢትዮጵያ 1855-1991 የባህር በር ለማስመለስ የነበረውን ትግል ያስመለክታል
• ከ1983-2014 ዓ.ም የነበረውን የኢትዮጵያ የባህር በር ማጣት ምክንያቶች ያያል
መፅሀፉ
• የዓባይ ተፋሰስ እና የባሀር በር ጉዳይ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው
• ዐቢይ ስትራቴጂ እና አዲስ ዕይታ ያመጣ ነው
• ሁለቱ ውሀዎች ለሀገሪቱ ስልጣኔ ያላቸው አስተዋፅኦ በመረዳት ሁሉም እውቀቱን እንዲያካፍል የሚጋብዝ ነው፡፡
• ስድስት ምዕራፎች፣ሀያ ሁለት ንዑስ ርዕሶችን ይዟል
• ቀጣይ የእድገት ተስፋ ላይ ያላትን የውሃ ሃብት መጠቀም ላይ ያተኩራል
• የኢትዮጵያን የዓባይ ተፋሰስ ውሀ ተጠቃሚነት የህግ እና የፖሊሲ ጉዳዮች ይዘረዝራል
• ዓለም አቀፍ የስምምነት ህግ ከድንበር ተሻጋሪ ወንዞች አንፃር ያስቃኛል
• የግብፅን የውሀ ግንኙነት ቅኝትና የመከበብ የውጭ ፖሊስ ቃኝቷል
• ቁልፍ ብሔራዊ ፍላጎቶችን ያመላክታል
• የአባይ ተፋሰስ እና ቀይ ባህርን በተመለከተ መከተል ያሉብንን መርሆዎች ይጠቁማል
• የዓባይ ተፋሰስ ተጠቃሚነት ዝርዝር ስትራቴጂን አስቀምጧል
• የባህር በር ለማግኘት የሚረዱ ስትራተጂዎች በግልፅ ሰፈረዋል
እንኳን ለ128ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ!!
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት አዳነች አቤቤ እና ከከተማዋ የካቢኔ አባላት ጋር ተወያዩ::
ርዕሰ አካዳሚው ለክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ለካቢኔ አባላቱ አፍሌክስ በሶስት ዓመት ውስጥ ስለሚተገብራቸው የአመራር ልማት ፕሮጀክቶች ገለፃ አድርገውላቸዋል::
አቶ ዛዲግ በውይይቱ ላይ አፍሌክስ በአካዳሚው ዘርፍ እና በነባራዊው ዓለም መካከል ያለውን ክፍትት ለመሙላት እየሰራ እንደሆነ ጠቅሰው፤ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ውስጥ ተራርቀው እና ተነጣጥለው ያሉ ተቋማትን እና መሪዎችን እንደ ድልድይ ሆኖ ለማገናኘት ፕሮግራም መቅረጹንም ተናግረዋል።
ርዕሰ አካዳሚው አያይዘውም የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በጠቅላላ (General) አራት እና በልዩ (Specialized )ሰላሳ ስምንት የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ቀርፆ ወደ ስራ እንደገባ የጠቀሱት አቶ ዛዲግ ለሁሉም ፕሮግራሞች ማስፈፀሚያ የሚሆን ከ2,500 በላይ ገፆች ያሉት ዝርዝር ስትራቴጂ እንደተዘጋጀም አብራርተዋል::
አዲስ አበባ ከተማ ላይ እምቅ የሰው ሀብት እና የአመራር አቅም መኖሩን የጠቀሱት ርዕሰ አካዳሚው፤ ይህን አቅም በጋራ ለመጠቀም የሚያስችል ፕሮግራም እንደተዘጋጀ እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋርም በትብብር በመስራት ሀብትን በተገቢው መንገድ ስራ ላይ ለማዋል አፍሌክስ ቅድመ ዝግጅቱን እንደጨረሰ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት አዳነች አቤቤ በበኩላቸው አፍሌክስ በሶስት ዓመታት ውስጥ ሊሰራ ያቀደው እና ርዕሰ አካዳሚው ያቀረቡበት መንገድ ሳቢ እና ማራኪ መሆኑን ጠቅሰው፤ አፍሌክስ የሰነቀው ራዕይ ከተቋሙ ባሻገር ለአዲስ አበባ ከተማም ትልቅ አቅም የሚፈጥር እንደሆነ እና በሀገር ደረጃም እንዲህ አይነት ሁሉን ዓቀፍ የአመራር አቅም መገንቢያ ማዕከል መኖሩ የሚፈጥረው አዎንታዊ ተጽዕኖ በቀላሉ የሚታይ አይደለም ብለዋል።
ክብርት ከንቲባዋ አያይዘውም ርዕሰ አካዳሚው ያቀረቡትን የአብረን እንስራ ጥያቄ መቀበላቸውን ገልጸው፤ አዲስ አበባ ከተማ እንደ አፍሪካ መዲና መቀመጫነቷ የራሷን አሻራ በአካዳሚው ውስጥ ማሳረፍ ትፈልጋለች ብለዋል። ለዚህም የሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ለመገንባት የሚያስፈልጉ ዝርዝር መረጃዎች እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ሌሎች የካቢኔ አባላትም አስተያየት የሰጡ ሲሆን፤ አፍሌክስ ከተሰጠው ተልዕኮ አንጻር የቀረጸው የሶስት ዓመት ስትራቴጂ እና ሁሉን ዓቀፍ የሆኑ የአመራር ልማት ፕሮግራም ማዕቀፎቹ ወዳሰበው መዳረሻ ሊያደርሱት የሚችሉ እንደሆኑ ተናግረዋል።
The African Leadership Academy and the United Nations in Ethiopia signed an agreement to work together.
Addis Ababa: February 27/2016 (EZA) African Leadership Excellence Academy and the United Nations Coordinating Office signed an agreement to work together.
The agreement has been signed by the Chief of the African leadership Excellence academy Zadig Abraha and the chief convener of the United Nations in Ethiopia and humanitarian aid coordinator Dr. Ramiz Alakbarov.
The purpose of the agreement is to increase leadership capacity and collective thinking to achieve sustainable development goals in Ethiopia and Africa.