የኢትዮጵያ አየር መንገድን የሰባ አምስት ዓመታት ስኬታማ ጉዞ የሚያሳይ የመጀመሪያ ደረጃ የጥናት ምርምር ሪፖርት ቀረበ። ጥናቱን ያካሔደው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ሲሆን የአየር መንገዱ ስራ አመራር አባላት ተገኝተው ሪፖርቱን ገምግመዋል።
የጥናቱ ዋና ዓላማም የአየር መንገዱን የስኬት ምስጢር በሳይንሳዊ ጥናት እና ምርምር ማረጋገጥና ለሌሎች ተቋማት እንደ ግብዓት የሚሆን የጥናት ሪፖርት ማቅረብ እንደሆነ በመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ላይ ተመላክቷል።
የመጀመሪያ ደረጃ የጥናት ሪፖርት ሲገመገም በመድረኩ የተገኙት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ እንደተናገሩት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስኬት ታሪክ ለሀገራችን ስኬታማ ጉዞ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ቀላል እንዳልሆነ ጠቅሰው፤ አካዳሚው እንደ ኬዝ ጥናት ወስዶ ማጥናቱ ለአመራር ልማት ፕሮግራሞቹ ግብዓት ከመሆኑም በላይ ለሌሎች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት የስኬት መንገድ ማሳያ ሊሆን እንደሚችል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
አቶ ዛዲግ አያይዘውም የተገኘው የጥናት ውጤት እንዴት እንደሚሰፋ እና በስራ ላይ እንደሚውል ሀሳብ የሰጡ ሲሆን፤ ከመድረኩ የተገኘውን ግብዓት በማካተት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ባለድርሻ አካላት ሊጠቀሙበት የሚችል ውጤታማና ተግባራዊ የጥናት ውጤት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በበኩላቸው የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ የጥናት ሪፖርት የተቀመጠለትን ግብ ማሳካቱን እና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መሰራቱን አረጋግጠው፤ ጥናቱ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ለባለድርሻ አካላት የሚኖረውን ጥቅም ከግምት በማስገባት የተሰጡትን ሀሳቦች እና አስተያየቶች አካቶ ስራ ላይ ቢውል ለተቋም ግንባታ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።
በመድረኩ የተሳተፉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀድሞ ዋና ስራ አስፈጻሚዎች፤ የቀድሞ የቦርድ አመራሮች፤ የማኔጅመንት አባላት እና የአፍሌክስ አመራሮች በመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ላይ አስተያየት እና ሀሳብ የሰጡ ሲሆን የተሰጡትን ግብዓቶች በማካተት የመጨረሻ የጥናት ሪፖርት እንደሚቀርብም ለማወቅ ተችሏል።

የሁለት ውኃዎች ዐቢይ ስትራቴጂ መፅሐፍ የምርቃት ሥነ-ሥርዓት በአብርሆት ቤተ መፅሐፍት እየተደረገ ይገኛል
**********
የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ከዋልታ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ኮርፖሬት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት "የሁለት ውኃዎች ዐቢይ ስትራቴጂ" የተሰኘ መፅሐፍ የምረቃ የምርቃት ሥነ-ሥርዓት እየተደረገ ይገኛል።
መፅሐፉ ለኢትዮጵያ ህልውና ከፍተኛ ሚና ባላቸው የዓባይ ወንዝ እና ቀይ ባሕር ላይ የሚያጠነጥን ሲሆን፤ በስድስት ምዕራፎችም የተከፋፈለ ነው።
መፅሐፉ የዓባይ ተፋሰስ እና የባሕር በር ጉዳይ ዐቢይ ስትራቴጂ አዲስ ዕይታ፣ በዓባይ ተፋሰስ የውኃ ተጠቃሚነት ጉልህ ሚና መጫወት፣ የሕግና የፖሊሲ ጉዳዮች እንዲሁም ስለ ባሕር በር የዓለም አቀፍ ሕግ፣ የሀገራት ተሞክሮ እና የባሕር በር ታሪካችን በስፋት ተዳሰውበታል።
የሁለት ውኃዎች ዐቢይ ስትራቴጂ መፅሐፍ በሁለቱ የውኃ አካላት ላይ ጥቅሞቻችን፣ ልንከተላቸው የሚገቡ መርሆችና ስትራቴጂዎችም ተካተውበታል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ በመፅሃፉ ላይ ዳሰሳ አቅርበዋል::
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይየመንግስት ኃላፊዎችና አመራሮች፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ ጋዜጠኞች እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተዋል።

የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከUNDP Regional Service Center for Africa ዳይሬክተር እና ከሳሙኤል ግባይዴ ዶኤ (Samuel Gbaydee Doe, UNDP, Resident Representative) ጋር ተወያዩ::
ርዕሰ አካዳሚው ለማትያስ ዘ. ናብ (ዶ/ር) Matthias Z. Naab (PhD) እና ለሳሙኤል ግባይዴ ዶኤ (Samuel Gbaydee Doe, UNDP, Resident Representative) አፍሌክስ በሶስት ዓመት ውስጥ ስለሚተገብራቸው የአመራር ልማት ፕሮጀክቶች ገለፃ አድርገውላቸዋል::
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በጠቅላላ (General) አራት እና በልዩ (Specialized )ሰላሳ ስምንት የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ቀርፆ ወደ ስራ እንደገባ የጠቀሱት አቶ ዛዲግ ለሁሉም ፕሮግራሞች ማስፈፀሚያ የሚሆን ከ2,500 በላይ ገፆች ያሉት ዝርዝር ስትራቴጂ እንደተዘጋጀ ለሀላፊዎቹ አብራርተዋል::
አቶ ዛዲግ አያይዘውም አፍሌክስ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገራት ባለ ድርሻ አካላት ጋር እየሰራ እንደሆነ እና ከ ዩ ኤን ዲ ፒ ጋርም በትብብር በመስራት ያቀደውን ማሳካት እንደሚፈልግ ጠቅሰዋል።

ማትያስ ዘ. ናብ (ዶ/ር) Matthias Z. Naab (PhD) በበኩላቸው አፍሌክስ የአመራር ለውጥ ባደረገ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያቀደው የሪፎርም፤ የማስፋት እና የሽግግር ስትራቴጂ የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው፤ የአፍሌክስ የአመራር ልማት ማዕቀፍ እንዲሳካ ዩ ኤን ዲ ፒ ከአፍሌክስ ጋር ለመስራት ፍላጎት እንዳለው አሳውቀዋል።
ከአፍሌክስ ጋር በትብብር ለመስራትም ጉዳዩን የሚከታተል የዩ ኤን ዲ ፒ ከፍተኛ ባለሙያ እንደተመደበም ማትያስ ዘ. ናብ (ዶ/ር) Matthias Z. Naab (PhD ገልጸዋል::
ከሳሙኤል ግባይዴ ዶኤ (Samuel Gbaydee Doe, UNDP, Resident Representative) በበኩላቸው ከአቶ ዛዲግ ጋር ከዚህ ቀደም የተጀመረውን ግንኙነት ወደ ተግባር ለማሸጋገር የዛሬው ውይይት ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸው፤ የሁለቱን ተቋማት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ መርሀ ግብር እንደሆነ ተናግረዋል።
የUNDP Regional Service Center for Africa ዳይሬክተር እና ከሳሙኤል ግባይዴ ዶኤ (Samuel Gbaydee Doe, UNDP, Resident Representative) የአፍሌክስን ፋሲለቲ ጎብኝተዋል።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና Public Leadership for Gender Equality (PL4GE) የተሰኘ ዓለምአቀፍ ድርጅት በጋራ ሊሰሩ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ።
ውይይቱ የተደረገው በzoom meeting ሲሆን ሁለቱም ተቋማት በስርዓተ ጾታ እና በሴቶች አመራር ልማት ፕሮግራሞች ያከናወኗቸውን ተግባራት እና ወደ ፊት ሊፈጽሟቸው ያቀዷቸው ስራዎች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከPublic Leadership for Gender Equality (PL4GE) ጋር መስራት የሚቻልባቸውን የአመራር ልማት ፕሮግራሞች የገለጹ ሲሆን፤ በተለይም በሴቶች አመራር ልማት ፕሮግራም፤ በህዝብ አመራር ልማት ፕሮግራም እና በተተኪ አመራር ልማት ፕሮግራም ላይ በጋራ መስራት የሚቻልባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ ተናግረዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ የሴቶች አመራር ልማት ፕሮጀክት ቀርጾ እየሰራ እንደሆነ የገለጹት የፕሮጀክቱ ማኔጀር አቶ መስፍን በሀይሉ በበኩላቸው ከፌዴራል መንግስት እና ከከተማ አስተዳደሩ የተውጣጡ ከ50 በላይ ሴቶችን አቅም በአመራር ልማት ፕሮግራም ለመገንባት እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
በPublic Leadership for Gender Equality (PL4GE) የGlobal Center for Gender Equality የFeminist Leadership Director አሌክስ ሙኒቭ Alex Munive በበኩላቸው የተቋማቸውን አጠቃላይ ተልዕኮ እና ከአፍሌክስ ጋር ለመስራት በሚቻልባቸው የትብብር መስኮች ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ አቅርበዋል።
ሁለቱ ተቋማት በቀጣይ በትብብር መስራት እንዲችሉ በተመረጡ የሰነድ ዝግጅቶች ላይ ባለሙያዎችን መድበው ውይይቱ ተጠናቋል።