ET Securities
647 subscribers
570 photos
7 videos
26 files
286 links
At Et securities our aim is in creating condusive space concerning capital markets and financial markets so as to enable learning and awareness creation to the society.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
" ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች (ነጋዴዎችና ወኪሎች አነስተኛ ንግድ) ቢዝነስ እንዲጀምሩ ወይም እዲያስፋፉ በዋስትና እና ያለዋስትና እስከ 1.2 ሚሊየን ብር የሚደርስ ብድር ማግኘት ያስችላቸዋል " - ኢትዮ ቴሌኮም

ኢትዮ ቴሌኮም በሲንቄ ባንክ የ15 ቢሊየን ብር የፋይናንስ ድጋፍ አቅራቢነት አዳዲስ የፋይናንስ ፕሮዳክቶችን የማስተዋወቅ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት አከናውኗል።

ይፋ የተደረጉት ፕሮዳክቶች በቴሌ ብር ሱፐር አፕ ' Financial service with Siinqee ' ስር የሚገኙ አራት ፕሮዳክቶች ናቸው።

አገልግሎቶቹ ፦
- ወቢ የብድር አገልግሎት ፣
- የትናንሽ እና የመካከለኛ ብድር አገልግሎት(SME) ፣
- የማይክሮ ሴቪንግ
- የዲቫይስ ፋይናኒስንግ አገልግሎቶች ናቸው።

የብድር አገልግሎቶቹ የሚቀርቡት ደንበኞች በቴሌ ብር ላይ ባደረጓቸው የገንዘብ እንቅስቃሴዎች ታይተው በሚቀመጥላቸው የብድር ጣሪያ መሰረት እንደየአቅማቸው ይሆናል ተብሏል።

ሲንቄ ባንክ ካቀረበው 15 ቢሊየን ብር ውስጥ 10 ቢሊየን ብር የሚሆነው ትናንሽ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማስፋፋት የብድር አገልግሎት የሚውል ገንዘብ ነው።

ብድሩ ሙሉ በሙሉ በዲጂታል መንገድ በቴሌ ብር ሱፕር አፕ አማካኝነት የሚከናወን ሲሆን በማስያዣ እና ያለ ማስያዣ ይከናወናል ተብሏል።

ከሲንቄ ባንክ ጋር በተደረገ ስምምነት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች (ነጋዴዎችና ወኪሎች አነስተኛ ንግድ) ቢዝነስ እንዲጀምሩ ወይም እዲያስፋፉ በዋስትና እና ያለዋስትና እስከ 1.2 ሚሊየን ብር ብድር ማግኘት እንደሚያስችል ተገልጿል። በዚህ አገልግሎትም በዓመት እስከ 10 ቢሊዮን ብር እንደሚቀርብ ተመላክቷል።

በዓመት 960 ሺህ ዲቫይሶችን (የሞባይል ቀፎዎችን) ሲያቀርብ መቆየቱን የገለጸው ኢትዮ ቴሌኮም በአሁኑ የሲንቄ ባንክ ስምምነት መሰረት በዓመት እስከ 2 ሚሊየን ዲቫይሶችን እንደሚያቀርብ ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA