#ሰበር
ኢትዮጵያ ሲጠበቅ የነበረዉን የብርን የምንዛሪ መጠን በገበያ እንዲወሰን የማድረግ ዉሳኔ ተግባራዊ ልታደርግ ነዉ
ኢትዮጵያ ከአይኤምኤፍ ጋር ስታደርገው የነበረዉን ድርድር ማጠናቀቋን እና ብድር ማግኘት የምትችልበት ሁኔታ መፈጠሩ ተገልጿል።
ከድርድሩ ዉሳኔዎች መካከል ሲጠበቅ የነበረዉ የብርን የምንዛሪ መጠን በገበያ እንዲወሰን ማድረግ የሚለዉ የስምምነቱ አካል መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ አስታዉቋል ።
የዉጪ ምንዛሪ ግብይቱ በገበያዉ አማካኝነት እንዲበየን ያደርጋል የተባለው "በገበያ ላይ የተመሰረተ የገንዘብ ፖሊሲ" በአቅርቦትና በፍላጎት መካከል ያለዉን የዉጪ ምንዛሪ መዛባት እንደሚያስተካክል ታምኖበታል።
ኢትዮጵያ ወደ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራ መግባቷን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በሰጡት መግለጫ ከአለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ጋር በተደረገው ስምምነት መሰረት ከፋይናንስ ተቋማት በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ብዙ ቢሊዮን ዶላር ታገኛለች ብለዋል።
ውሳኔው ተግባራዊ ሲሆን ብር፤ ዶላር እና ፓውንድን ከመሳሰሉ ዋና ዋና የመገበያያ ገንዘቦች አኳያ ያለው የምንዛሬ ተመን ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያመጣ ታምኖበታል፤የዚህን ሪፎርም በተመለከተ ብሔራዊ ባንክ እና የገንዘብ ሚኒስትር ዝርዝር በየጊዜው የሚገለጡ መሆኑ ተነግሯል።
https://youtu.be/--HOHHMRPFI?si=9ZC4s5A2QjLW6bqF
Condoaddis.com/category/etstocks