ET Securities
675 subscribers
593 photos
7 videos
30 files
300 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
የውጪ ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ በመግባታቸው የሀገር ውስጥ ባንኮች ደንበኞቻቸውን ያጣሉ?


ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የውጪ ባንኮች ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ መታሰቡን ተከትሎ ብዙ ሰዎች የሀገር ውስጥ ባንኮች ህልውና አሉታዊ ተጽኖ እንደሚደርስበት ያስባሉ! የሀገር ውስጥ ባንኮች ደንበኞቻቸውን ሊያጡ ስለሚችሉ ይጎዳሉ የሚል መከራከሪያ ያነሳሉ!


በመጪው ጊዚያት ውስን የሀገር ውስጥ ባንኮች ሊጎዱ ይችላሉ! ነገር ግን የሚጎዱት የውጪ ባንኮች ስለሚገቡ ወይም መሰረታዊ ደንበኞቻቸውን ስለሚያጡ ነው ብዬ አላስብም!


ለዚህ ውይይት እንዲረዳን የፋይናንስ ገበያውን ባህል እንመልከት! የቆጣቢው ህዝብ ብዛት፤ ሰዎች የሚቆጥቡበት/የባንክ ደብተር የሚከፍቱበት ምክንያት እና አማካይ ሰዎች በየባንክ አካውንታቸው እየቆጠቡ ያሉት የቁጠባ መጠን፤ ወዘተ፡፡


በተመሳሳይ የውጪ ባንኮች መሰረታዊ ትኩረት ቁጠባን በማሰባሰብ ለብድር ማቅረብ ሳይሆን ከተከማቸ ካፒታል ብድር በማቅረብ ከከፍተኛ የብድር ወለድ ትርፍ መሰብሰብ ነው፡፡ ስለዚህ የሀገር ውስጥ ባንኮች ሰፊ የቁጠባ ስርዓት ላይ መሳተፋቸውን ከቀጠሉ ለብድር ሊያቀርቡት የሚችሉት ካፒታል ተቀማጭ ገንዘብ ሳያጡ በገበያው ሊቆዩ ይችላሉ፡፡


#ለምሳሌ፡- የውጪ ባንኮች በሀገር ውስጥ የማህበራዊ ተሳትፏቸው ደካማ ነው! እንዲሁም ዋና መስሪያ ቤት ላይገነቡም ይችላሉ! ምን ማለት ነው በተዘዋዋሪ በተደረገላቸው ጥበቃ ወይም ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን ለመወጣት በከፍተኛ ሁኔታ ወጪ በማውጣት የሚሳተፉ የሀገር ውስጥ ባንኮች በተወሰነ መልኩ ከተሳትፏቸው ሊቀንሱ ይችላሉ! ነገር ግን ከጠቅላላ ኢኮኖሚው ፋይዳ አንጻር የሚቻቻል ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡


ልብ በሉ አሁንም የውጪ ባንክ ሳይገባም የባንክ ሴክተሩን ፉክክር መቋቋም ያቃታቸው የሀገር ወስጥ ባንኮች አሉ! በተመሳሳይ ከ5 ዓመት በኋላ (ለአዳዲስ ባንኮች እስከ 7 ዓመት) መሟላት የሚገባው የ5 ቢሊየን ብር ተቀማጭ ካፒታል ለሟሟላት ብዙ የሚቀራቸው ባንኮች ብዙ ናቸው፡፡


በርካታ ሃብቶቻቸውን ዋስትና በማስያዝ በቢሊየን እና በመቶ ሚሊየን ብድር ውስጥ ያሉ ደንበኞች እስከ 30 ዓመት የሚቆይ የእዳ ዋስትና ውስጥ በመሆናቸው በቀላሉ ከነባር የሀገር ውስጥ ባንኮች በመላቀቅ ከውጪ ባንኮች ዋስትና አስይዘው ብድር ለመውሰድ የሚያስችል አቅም ሊኖራቸው ስለማይችል የሀገር ውስጥ ባንኮች ከፍተኛ ተበዳሪ ደንበኞቻቸው እንደያዙ በገበያው ትርፋማነታቸውን ይዘው የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡


የውጪ ባንኮች መግባት ከፍተኛ መጠን ያለው ብድር ለማቅረብ ድፍረት ወይም አሰራር ሊኖራቸው ስለማይችል ወደ ተለያዩ ታዳጊ ሀገራት ገበያ ሲገቡ ዝቅተኛ ብድሮች ላይ የመሳተፍ ልምድ ስላላቸው የሀገር ውስጥ ባንኮች ከፍተኛ የብድር ጥያቄዎችን በማስተናገድ በገበያው ሊፎካከሩ መቻላቸው አይቀርም፡፡


ባንኮች ያለባቸው አደጋ የውጪ ባንኮች ከመግባታቸው በፊትም ለረጅም ዓመታት ለባለሃብቶች/ድርጅቶች ያቀረቡትን ብድር ወለድ እንጂ ዋናውን በመሰብሰብ የተመዘገበ ትርፋቸው ዝቅተኛ በመሆኑ የመጪው ጊዜ ስጋታቸው ከውጪ ባንኮች ጋር ከመፎካከር በላይ እስካሁን ሲያቀርቡ የኖሩትን ዋናውን/Principal ብድር ማስመለስ ላይ ነው (ሁሉም ብድር በበቂ ዋስትና የቀረበ ነው ብሎ ማሰብ ጤነኛ አይደለም)፡፡


በባንኮች የቁጠባ ታሪክ ውስጥ ብዙ የባንክ ደብተር የሚከፍቱ ሰዎች እና በምክንያት ሳይሆን በሰዎች ጉትጎታ ብዙ አካውንት የሚከፍቱ ሰዎች በአካውንቶቻቸው የሚያንቀሳቅሱት ገንዘብ ከፍተኛ ባለመሆኑ አዳዲስ የውጪ ባንኮች በገቡበት ቅስፈት ብዙ ሰዎች ተጨማሪ አካውንት ከውጪ ባንኮች ቢያወጡ ከፍተኛ ቁጠባ ወደ ውጪ ባንኮች የሚዛወር እና ከፍተኛ ቁጠባ ከሃገር ውስጥ ባንኮች የሚወጣ ሊሆን ይችላል ብዬ አላስብም፡፡


#ለምሳሌ፡- የሰዎች ልምድ በመሆኑ የመጀመሪያ ወራቶች ላይ የውጪ ባንክ አካውንት የሚኖራቸው ሰዎች ቁጥር እንደወረት መጨመሩ አይቀርም! በተመሳሳይ የሳፋሪኮም 07 መነሻ ሲም ካርድ የሚያወጣ ሰው ቁጥር ቀላል ሊሆን አይችልም፡፡


መደበኛ የሀገር ውስጥ ባንኮች ገጠሩን ሲነኩ ስላልኖሩ እና የገጠሩ ክፍለ ኢኮኖሚ የፋይናንስ አቅርቦት እየተሸፈነ ያለው በመደበኛ የዋስትና ማስያዣ ባለመሆኑ አደጋ በመጋራት የብድር እና ቁጠባ ተቋማት ህልውና የውጪ ባንኮች በመግባታቸው ይበልጥ የሚፈተን ሊሆን ይችላል፡፡


ነገር ግን የገጠሩ ማህበረሰብ ንቃተ ህሊና እና ለአዳዲስ አሰራሮች የሚኖራቸው ተሳትፎ ፈጣን ባለመሆኑ ከተለመደው የብድር እና ቁጠባ የደንበኝነት መዝገቦቻቸው ወደ አዳዲሶቹ የውጪ ባንኮች ደንበኛ ለመሆን ፈጣን ምላሽ ይሰጣሉ ለማለት እንደሚያስቸግር ይሰማኛል፡፡


#ለምሳሌ፡- አዳዲስ የግብርና አሰራር (ምርጥ ዘር፤ መስኖ/ውሃ ማቆር፤ ኩታ ገጠም፤ የመኖ ዝርያ፤ ወዘተ) ለማስተዋወቅ በጣም ከፍተኛ ተግዳሮት የሚኖረው ከተለመደው የወጡ ልምዶችን ቶሎ ያለመቀበል ባህሪ በብዛት ስላል ነው)፡፡


የውጪ ባንኮች ባይመጡም ወደፊት ሁሉም የሀገር ውስጥ ባንኮች የተለመደውን ትርፋቸውን ይዘው ሊቀጥሉ አይችሉም! ውስን ባንኮች አሁንም በተሻሉ ባንኮች እየተዋጡ ነው፡፡ የስራ ማስኬጃ ወጪያቸውን እስከሸፈኑ ድረስ እንዳልወደቁ የሚያስቡ እንዲሁም ለባለአክሲዮን የትርፍ ክፍፍል መስጠት ተቸግረው/ዝቅተኛ መጠን የትርፍ ክፍፍል በተደጋጋሚ እያቀረቡ ያሉ ባንኮችን ታዘቡ፡፡


#ለምሳሌ፡- አንድ ባንክ በበቂ ሁኔታ ከፍተኛ ደሞዝ ለሃላፊዎቹ፤ ለሰራተኞቹ እና አበል ለቦርዶቹ እስከከፈለ እና የስራ ማስኬጃ ወጪውን እስከሸፈነ ድረስ አክሲዬን የገዙ ደንበኞች ምንም ትርፍ አላገኙም በሚል የሚጨነቅበት ደረጃ ምን ያህል ነው? በተመሳሳይ የባንከ ባለአክሲዮኖች  ባንካችን የትርፍ ክፍፍል እየሰጠን አይደለም ስለዚህ ይቅርብን ቢሉ! ለሶስተኛ ወገን ከስረው ካላስተላለፉ በቀር አሰራሩ ቀላል ነው?


የውጪ ባንኮች ቢገቡም ባይገቡም ወደ ፊት የካፒታል ገበያው ሲከፈት አሁን ካለው በተሻለ የነባር/ውጤታማ ባንኮች አክሲሆን ለገበያ በሰፊው ሊዘዋወር ስለሚችል ባለአክሲዮኖቻቸውን እያጡ የሚመጡ ባንኮች እንዲሁም አዳዲስ ባንኮች ለመክፈት ለገበያ ለሚቀርብ አክሲዬን ለመግዛት ፍላጎቶቻቸው የሚቀንስ ትርፍ ላይ ትኩረት የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ስለሚመጣ አሁን ላይ ደካማ ባንኮች እስከ ጥምረት የደረሰ ስትራቴጂ ማሰብ መጀመር አለባቸው (ጠቅላላ ጉባዬ ላይ ባለአክሲዬኖች ይህንን የመፍትሄ ሃሳብ ቢያነሱ ስህተት ነው?)፡፡


በተቃራኒው የውጪ ባንኮች መግባትን እንደ እድል በመቁጠር በቴክኖሎጂ፤ በዘርፉ በሰለጠነ የሰው ሃይል፤ በቀልጣፋ አሰራር፤ በደህንነት አመራር፤ በጥምረት ብድር የማቅረብ አሰራር፤ ወዘተ ላይ ማሻሻያዎችን በማድረግ በጋራ ለማደግ ቀዳዳዎችን መፍጠር የሚችሉ የሀገር ውስጥ ባንኮች ለውጡን በብዙ ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡

Wase.belay12@gmail.com
(0913243956)
አይ ካፒታል አፍሪካ ኢንስቲትዩት ከናይሮቢ ሴክዩሪቲስ ኤክስቼንጅ ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራረመ

👉ከፋይናንስ ተቋማት ለተውጣጡ ባለሙያዎች በካፒታል ገበያ ዙሪያ የኹለት ቀን ስልጠና ተሰጥቷል

ዕረቡ መስከረም 25 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) አይ-ካፒታል አፍሪካ ኢንስቲትዩት በካፒታል ገበያው የ68 ዓመታት ልምድ ካለው የኬንያው ናይሮቢ ሴክዩሪቲስ ኤክስቼንጅ(NSE) ጋር ትናንት መስከረም 24/2015 በሳፋየር አዲስ ሆቴል የትብብር ስምምነት ተፈራርሟል።

በስምምነቱ መሰረትም ኹለቱ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ውስጥ በካፒታል ገበያ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ድርጅቶችና ቡድኖች የማማከርና የስልጠና አገልግሎቶችን፣ በገበያው አመሰራረት ዙሪያ ለኢትዮጵያ መንግስት ተሞክሮን መሰረት ያደረገ ድጋፍ እንዲሁም የድርጅቶችን ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን በጋራ የሚሰጡ ይሆናል።

የአይ ካፒታል አፍሪካ ኢንስቲትዩት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ገመቹ ዋቅቶላ(ዶ/ር) እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ውጤታማ ይሆን ዘንድ የሰው ኃይልና የተቋማት ግንባታ አስፈላጊ ሲሆን፣ ለዚህም ሲባል ልምድ ካላቸው አገራትና ድርጅቶች ልምዳቸውን መካፈል አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

የናይሮቢ ሴክዩሪቲስ ኤክስቸንጅ ሥራ አስኪያጅ ዴቪድ ዋኔይና ደግሞ፤ ምንም እንኳን በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ምስረታ የዘገየ ቢሆንም፣ የድርጅታቸውን ልምድና የአገሪቱን የህዝብ ቁጥር በመጠቅም ስኬታማ የካፒታል ገበያ መመስረት እንደሚቻል ገልፀዋል።

በስምምነቱ መሰረትም የመጀመሪያ የሆነው፣ ከፋይናንስ ተቋማት ለተውጣጡ ባለሙያዎች በካፒታል ገበያ ባለድርሻዎችና ከገበያው ጋር ተያይዘው ስለሚመጡ የሥራ እድሎች የኹለት ቀናት ስልጠና  በሳፋየር አዲስ ሆቴል የተሰጠ ሲሆን፣ መሰል ስልጠናዎች ቀጣይነት እንደሚኖራቸው ተገልጿል።

አይ ካፒታል አፍሪካ ኢንስቲትዩት ከተመሰረተ ሰባት ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን፤ የምስራቅ አፍሪካ ዓመታዊ የፋይናንስ ጉባኤን ለተከታታይ አምስት ዓመታት በማዘጋጀት ይታወቃል።

በእሱባለው ጋሻው
የአዲስ ማለዳ
Standard Bank weighs up options to join Ethiopia’s finance industry



By Ethiopian reporter

South African, Kenyan bank to get the first licenses

Standard Bank Group Limited, the largest lender in Africa in terms of assets, is considering joining the banking sector in Ethiopia. The bank is waiting until the National Bank of Ethiopia (NBE) starts the process of granting international banks licenses in Ethiopia, which is anticipated to happen in less than a year.

Yinka Sanni, the bank’s CEO of Africa Regions, was in Ethiopia between November 30 and December 2, 2022, leading a series of meetings with various partners, clients, and stakeholders, including the Ethiopian government as well as the bank’s clients operating in Ethiopia.
Yinka Sanni, the bank’s CEO of Africa Regions, was in Ethiopia between November 30 and December 2, 2022, leading a series of meetings with various partners, clients, and stakeholders, including the Ethiopian government as well as the bank’s clients operating in Ethiopia.

The Council of Ministers approved a policy and strategy for allowing foreign investment in Ethiopian banking, putting an end to a half-century of protectionism. The subsequent amendment of the Banking Business Proclamation by the NBE also stipulated four modalities for the foreign banks’ entry: subsidiary, branch, commercial representative office, and acquiring up to 30 percent of the existing local banks.

“Standard Bank is in the process of considering all options. We are respectful of the process outlined by the banking authorities and the government in Ethiopia, and we look forward to the time when regulatory approval allows us to establish a bank,” said officials of Standard Bank in an email response to The Reporter. “We have not decided on the modality or exact business model that we will use to enter the Ethiopian market.”

Headquartered in Johannesburg, South Africa, with 159 years of history, Standard Bank has a footprint in 20 countries across the continent. The bank already has an extensive commitment in East Africa, with operations in Tanzania, Uganda, Kenya, and South Sudan, and a representative office in Ethiopia.

“We have many success stories from other countries. We believe that we are uniquely positioned to support the government’s plans to attract more investments into the country through our client base on the continent and facilitate the financing on their behalf,” Taitu Wondwossen, Head Standard Bank Representative Office in Ethiopia, said.

Establishing a presence in Ethiopia is also in recognition of the increasing interest by investors and clients, in the country’s economic growth and significant investment opportunities, according to Taitu. “We note that over the last decade, Ethiopia has emerged as one of Africa’s most profound growth stories. This growth has been driven by structured government development plans, positioning Ethiopia as a regional industrial hub and global aviation center.”

The Standard Bank intends to bring its clients from around the world to its Ethiopian operation. “Standard Bank is committed to Ethiopia, which remains a vital market for our clients seeking investment opportunities with the potential of driving development in the region, through our client base on the continent and facilitating the financing on their behalf,” Sanni said.

Other African banks, including Kenya’s KCB, have also disclosed their appetite to join the Ethiopian market over the past couple of months. Officials of Standard Bank believe that South African and Kenyan banks are the top candidates to get the first licenses once the NBE starts implementing the open-up legislation.

However, experts question what unique services African banks can bring to the table, given that most stick to similar traditional banking services.

“Standard Bank will be well-positioned to take advantage of the cross-sectorial investment opportunities both in Ethiopia and the region. Our experience in East African markets will benefit all our clients by providing them with insights into how to best capitalize on their investments in the region,” Kate Johns, reputation and communication manager at Standard Bank, said.
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የገንዘብ ሚኒስትር አማካሪ የሆኑትን ዶ/ር ብሩክ ታዬን የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾሙ።

ዶ/ር ዐቢይ ለሥራ አመራር ቦርዱ የብሄራዊ ባንክ ገዢ ይናገር ደሴን ሰብሳቢ አድርገው እንደሾሙ የገለጸው ዘገባው፣ ሒክመት አብደላ፣ ብሩክ ታዬ፣ ወንድማገኝ ነገራ፣ እዮብ ተስፋዬ ኃ/ሚካዔል እና አባተ አበበ የቦርድ አባል ሆነው እንደተሾሙ አመልክቷል። ብሩክ ታዬ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሆነው እንደተሾሙ ተገልጧል። አንደኛው የቦርድ አባል አባተ አበበ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመረጡ ናቸው።
(ካፒታልና ሪፖርተር ጋዜጣ)
የውጭ ኢንቨስትመንት ባንኮች በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ እንዲሠማሩ የሚፈቅድ መመርያ እየተዘጋጀ ነው

ኤልያስ ተገኝ
January 29, 2023በቅርቡ ወደ ሥራ ይገባል ተብሎ የሚጠበቀው የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን፣ የውጭ ኢንቨስትመንት ባንኮች በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ እንዲሠማሩ የሚፈቅድ መመርያን ጨምሮ ሌሎች መመርያዎችን እያዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ፡፡

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የአክሲዮን ገበያ ለማስጀመር የሚያስችሉ በርካታ መመርያዎችን እያዘጋጀ እንደሚገኝ ያስታወቀው የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን፣ በዝግጅት ላይ ካሉት መመርያዎች መካከል የኢንቨስትመንት ባንኮች ኢትዮጵያ ውስጥ ገብተው እንዲሠሩ የሚፈቅድ መመርያ፣ እንዲሁም ደላሎች (Brokers)፣ ነጋዴዎች፣ ደረጃ ሰጪ ኤጀንሲዎችና የኢንቨስትመንት አማካሪዎች የሥራ ፈቃድ መስጠትን የሚመለከቱት ተጠቃሾች መሆናቸውን አስታውቋል፡፡

የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር በመሆን በቅርቡ የተሾሙት ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)፣ በፌዴራል መሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን አዘጋጅነት በኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም በተዘጋጀው “Invest Origins 2023” የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ በኢትዮጵያ ዕውን ሊሆን ዝግጅት እየተረደገበት በሚገኘው የካፒታል ገበያ ምንነት ዙሪያ፣ ለዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮችና የዘርፉ ተዋንያን ሰፊ ገለጻ አቅርበዋል፡፡

የካፒታል ገበያ ለዜጎች በባንኮች ተቀማጭ ሆኖ በተለያዩ ምክንያቶች ዋጋው እየቀነሰ የሚመጣን ሀብት ውጤታማ ወደ ሆኑ ዘርፎች ገብቶ ለባለቤቱ ጥቅም የማስገኘት አማራጭን እንደሚሰጥ የገለጹት ብሩክ (ዶ/ር)፣ ለመንግሥትና ለተቋማት ደግሞ ሀብት እንዲገላበጥና እንዲንቀሳቀስ በዚህም የተሻለ ውጤት እንዲገኝ የሚያስችል እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ በደላሎች፣ በነጋዴዎችና በኢንቨስትመንት አማካሪዎች የሚደረጉ የሥራ እንቅስቃሴዎች ያልተያያዙና በተበታተነ መንገድ የሚከወኑ መሆናቸውን የገለጹት ብሩክ (ዶ/ር)፣ በዚህም ሕጋዊ ዕውቅና የሌላቸው ደላሎችና የሕግ ሰውነት የሌላቸው ነጋዴዎች ከፍተኛ የባንክ አክሲዮኖችን ቴሌግራምና ዋትስአፕን በመሳሰሉ የማኅበራዊ ትስስር አማራጮች እንደሚያገበያዩ (እንደሚያሻሽጡ) ተናግረው፣ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ይህንን መስመር ለማስያዝ ተገቢውን የሥራ ፈቃድ የሚሰጥበት አሠራር እንደሚፈጠር አስታውቀዋል፡፡

‹‹ተገቢውን ፈቃድ ለመስጠት ዝግጁ ነን፤›› ያሉት ብሩክ (ዶ/ር) የንግድ ድርጅቶች፣ ደላሎች፣ ነጋዴዎች፣ እንዲሁም የኢንቨስትመንት ባንኮች እንዲቋቋሙ የሚረዱ ድጋፎችን መስጠትን ጨምሮ ክትትል ይደረጋል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አዋጅ ሐምሌ 16 ቀን 2013 ዓ.ም. የወጣ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ የአዋጁ መውጣት ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያት ተደርገው ከተጠቀሱት ውስጥ ካፒታል በመሰብሰብ የገንዘብ ሥርዓቱን በአዲስ ፈጠራዎች በመደገፍና የኢንቨስትመንት ሥጋቶችን የመጋራት አሠራርን በማስፋፋት፣ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ልማት ለመደገፍ የሚል ይገኝበታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በቅርቡ ወደ ሥራ ይገባል ተብሎ ለሚጠበቀው የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የሚያገለግሉ ስድስት የቦርድ አባላትን መሾማቸውና የቀድሞ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነው መሰየማቸው ይታወሳል፡፡

በካፒታል ገበያ ላይ ትኩረት አድርገው በተዘጋጁ የውይይት መድረኮች ላይ እንደሚገለጸው፣ የካፒታል ገበያ በቀጥታ ሳይሆን የተለያዩ ጥናቶችና የሕግ ማዕቀፎች ታይተው የሚገባበት ነው፡፡

አንድ ባለሀብት በካፒታል ገበያ አንድን ድርጅት ወይም የድርጅት ድርሻን ከመግዛቱ በፊት የፋይናንስ አቅም የሚያሳይ መረጃ ስለሚያስፈልገው፣ መረጃውን የሚመረምሩለት የተጠናከሩ የሒሳብ አዋቂ ድርጅቶች ያስፈልጉታል፡፡

የካፒታል ገበያ በሰነድ ግብይት ላይ የተመረኮዘ እንደ መሆኑ መጠን፣ ያለ ሕግ ባለሙያዎችና ድርጅቶች ዕገዛ የቱንም ያህል ዕርምጃ መሄድ እንደማይቻል ይገለጻል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ባለሀብቶች የተሳሳተ መረጃ ይዘው ወደ ካፒታል ገበያ እንዳይገቡ የጥናትና ማማከር ድርጅቶች ከፍተኛውን ሚና እንደሚጫወቱ፣ የካፒታል ገበያ መቋቋም ተቋማትን የማስፋፋትም ሆነ የማነቃቃት ዕድሉ ሰፊ እንደሆነ ይነገራል፡፡

በኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም በተዘጋጀው “Invest Origins 2023” የኢንቨስትመንት ፎረም የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ከባቢ ሁኔታዎችን በተመለከተ፣ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ባለሙያዎችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ውይይት አድርገዋል፡፡
On Thursday February 2nd, Skylight will be hosting a panel discussion regarding Consultative Workshop On Capital Market

Panelists
➡️ Michael Habte, Ethiopian Capital Market Authority
➡️ Ambaye Merga, Ethiopian Capital Market Authority
➡️ Asfaw Alemu, Dashen Bank
➡️ Solomon Zedie, Ethiopian Capital Market Authority
➡️ Hanna Tadla, Ethiopian Capital Market Authority
➡️ Sirak Solomon, Ethiopian Capital Market Authority

Moderator
➡️ Yohannes T. Arega, Ethiopian Capital Market Authority

➡️ Mesenbet Shenkut
President, AACCSA
➡️ Shibeshi Bettemariam
Secretary General, AACCSA

Hosting Company: Addis Ababa Chamber of Commerce and Sectoral Associations(AACCSA)
የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ፍቃድ መስጠት ሊጀምር ነዉ::

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በምስረታ ላይ የሚገኘዉ የካፒታል ገበያ የሚገቡ ኩባንያዎችን ፈቃድ መስጠት ሊጀምር ነዉ፡፡

የአዲስ አበባ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት በዛሬዉ ዕለት በካፒታል ገበያ ዙሪያ በስካይላይት ባካሄደዉ የምክክር መድረክ ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ታዬ ባለስልጣኑ ፈቃድ እና የክትትል ስራ ለማከናወን የሚያስችሉትን በርካታ መመሪያዎች እና ደምቦች አዘጋጅቶ ለቦርድ እንዳቀረበ ተናግረዋል፡፡

ካፒታል ገበያ የሚገቡ ኩባንያዎች፣ አገናኝ አካላት፣ ኢንቨስትመንት ባንኮች እና የሂሳብ ባለሙያዎች ፈቃድ ለመስጠት የሚያስችሉ መመሪያዎች እና ደምቦች ለቦርድ የተላከ ሲሆን በቀጣይ ለህዝብ ዉይይት እንደሚቀርብም ዶ/ር ብሩክ ገልጸዋል፡፡

‹‹ይህን ሂደት በአጭር ጊዜ ዉስጥ አጠናቀን ፈቃድ መስጠት እንጀምራለን፡፡ የመንግስት ትልቅ ድጋፍ አለን፡፡ከመንግስት የተሰጠን መመሪያ በአጭር ጊዜ የካፒታል ገበያዉን ስራ እንድናስገባ ነዉ፡፡›› ብለዋል፡፡

በዉይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ንግድ ምክርቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ የካፒታል ገበያ መመስረት ለንግዱ ማህበረሰብ ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል፡፡ ካፒታል በማመንጨት ፣ የገንዘብ ፍሰት በመፍጠር እና የዉጪ ኢንቨስትመንት በመሳብ ለኢኮኖሚ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረዉ ወ/ሮ መሰንበት ተናግረዋል፡፡

በአክሲዮን ገበያ ዉስጥ አክሲዮን ሻጭ ኩባንያዎች ፣ አገናኝ አካላት/ደላሎች/ ፣ ኢንቨስትመንት ባንኮች እና የተመሰከረላቸዉ የሂሳብ ባለሙያዎች ዋነኛ ተዋንያን እንደሆኑ በዉይይቱ የተገለጸ ሲሆን ዉጤታማ የአክሲዮን ገበያ ለመመስረት ጠንካራ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን፣ ግልጽ የሆኑ ህጎች እና ደምቦች በማዘጋጀት አስቻይ እና ምቹ ሁኔታ ማመቻቸት ወሳኝ መሆኑ በባለሙያዎች ተጠቅሷል፡፡

አክሲዮን ገበያ በኢትዮጵያ ከ 50 ዓመት በፊት ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም በወታደራዊ መንግስት በእንጭጩ እንዲቀጭ ተደርጓል፡፡ በግሉ ዘርፍ በ1990 ዓም ለመመስረት የተጀመረዉ ጥረት በኢህአዴግ መንግስት እንዲቋረጥ መደረጉ የሚታወስ ነዉ።

Source: @ETIradioshow
The Capital Market Authority is about to start issuing licenses. The Ethiopian Capital Market Authority is about to start issuing licenses to companies entering the capital market. The Addis Ababa Chamber of Commerce and Sector Associations, who gave an explanation at the consultation forum held by Skylight on the capital market today, said that the director general of the Ethiopian Capital Market Authority, Dr. Brock Taye, said that the authority has prepared and presented to the board a number of guidelines and rules that allow the authority to carry out licensing and monitoring work. Dr. Brock stated that guidelines and rules for licensing companies entering the capital market, affiliates, investment banks and accountants have been sent to the board and will be submitted for public discussion. "We will complete this process in a short time and start issuing permits. We have great support from the government. The instructions given to us by the government are to get the capital market working in a short period of time," he said. The president of the Addis Ababa Chamber of Commerce, Mrs. Mesenbat Shenkute, who gave the opening speech of the discussion, stated that the establishment of the capital market will create a great opportunity for the business community. Mrs. Mesenbat said that it will contribute greatly to economic growth by generating capital, creating cash flow and attracting foreign investment. In the discussion, it was stated that stock selling companies, liaison bodies/brokers, investment banks and certified accountants are the main actors in the stock market, and it was mentioned by the experts that it is important to create a strong regulatory authority, clear rules and regulations to establish an effective stock market. The stock market was started in Ethiopia 50 years ago, but it was suppressed by the military government. It is to be remembered that the effort to establish a private sector in 1990 was stopped by the EPRDF government.

Source: @ETIradioshow
በካፒታል ገበያ የሚሳተፉ የኢንቨስትመንት ባንኮች 100 ሚሊዮን ብር የካፒታል ፈንድ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባሥልጣን ባወጣው ረቂቅ መመሪያ በካፒታል ገበያ ውስጥ ተዋንያን እንደሚሆኑ የሚጠበቁ የኢንቨስትመንት ባንኮች እስከ 100 ሚሊዮን ብር የደረሰ የተጣራ የካፒታል ፈንድ ምጣኔ ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው አስቀመጠ፡፡

የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ለመጀመርያ ጊዜ ሦስት የሚደርሱ ረቂቅ መመሪያዎችን ለሕዝብ አስተያየት ክፍት ያደረገ ሲሆን፣ ባለሙያዎች ምክረ ሐሳቦችን እንዲሰጡባቸው ይፋ የሆኑት ረቂቅ መመሪያዎች የሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ እና የግብይት መድረኮች የፍቃድ አሰጣጥና አሠራር መመሪያ (Licensing and Operating Securities Exchanges and Trading Platforms)፣ ራስን በራስ የሚቆጣጠሩ ድርጅቶች ዕውቅና አሰጣጥ መመሪያ (Recognition of self-regulatory Organizations) እንዲሁም የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪ ፍቃድ አሰጣጥና ክትትል መመሪያ (Capital Market Service Providers Licensing and Supervision) ናቸው፡፡

በሰነድ መዋዕለ ንዋይ ገበያና የግብይት መድረኮች የፍቃድ አሰጣጥና አሠራር ረቂቅ መመሪያው እንደሰፈረው፣ ፍቃድ ፈላጊዎች የሚያቀርቧቸው መረጃዎችና ሰነዶችን መሠረት በማድረግ የቀረበው የፍቃድ ጥያቄ የሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ገበያ (Securities Exchange)፣ የተዛማጅ ውሎች ገበያ (Derivatives Exchange) ያልተማከሉ የጠረጴዛ ዙሪያ ግብይት መድረኮች (over-the Counter Facility) እንደሆነ ይለያል፡፡

ለግብይት የቀረቡት ሰነደ መዋለ ንዋዮችና ለመገበያየት የቀረቡ ባለሀብቶች ይለያሉ፣ የሰነደ መዋለ ንዋይ ፍቃድ፣ የተዛማጅ ውሎች ገበያ ፍቃድ በመመሪያው ክፍል ሁለት ላይ በተቀመጠው መሠረት፣ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን አመልካቾች በቂ ዓቅም ያለውና ያለምንም የአገልግሎቶች መቆራረጥና እንከን መሥራት ይችላሉ የሚለውን ባመነ ጊዜ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪ ፍቃድ አሰጣጥና ክትትል ረቂቅ መመሪያው ላይ እንደተቀመጠው፣ ባለሥልጣኑ የካፒታል ገበያ ተዋንያን ዝቅተኛ የካፒታል ዓቅም መጠንን እንደሚወስን ተገልጾ፣ ይህም የተከፈለ ካፒታል ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኝ የንግድ ባንክ በጥሬ ገንዘብ ተቀማጭ የሚከፈል እንደሆነ ያሳያል፡፡

በረቂቅ መመሪያው እንደተደነገገው እያንዳንዱ የካፒታል ገበያ አገልግሎት አቅራቢ አስፈላጊውን የተጣራ ባለአክሲዮኖች ገንዘብ ወይም የሚጠበቅበት የተጣራ ባለአክሲዮኖች ፈንድ  መሥፈርት ተቀምጧል፡፡

በረቂቅ መመሪያው ሰንጠረዥ አንድ ላይ እንደተቀመጠው እንደ ባንክ የሚወሰዱ የኢንቨስትምንት ባንኮች (Investment Bank-within a Banking Group) እስከ 100 ሚሊዮን ብር የተጣራ የባለአክሲዮኖች ፈንድ ማሟላት የሚጠበቅባቸው ሲሆን፣ እንደ ባንክ የማይወሰዱ የኢንቨስትመንት ባንኮች (Investment Bank- Not Part of a Banking Group)  ደግሞ የአገልግሎት ፍቃድ ለማግኘት 25 ሚሊዮን ብር የተጣራ የባለአክሲዮኖች ፈንድ ማቅረብ (ማሟላት) እንደሚገባቸው ተጠቅሷል፡፡

በሌላ በኩል የጋራ ኢንቨስትመንት ፈንድ አገልግሎት ሰጪዎች (Collective Investment Scheme Operator) 25 ሚሊዮን ብር የተጣራ የባለአክሲዮኖች ፈንድ ማሟላት የሚጠበቅባቸው ሲሆን፣ የብድር የመመለስ ብቃት ምዘና አገልግሎት አቅራቢዎች (Credit Rating Agency) 15 ሚሊዮን ብር፣ የሰነደ መዋለ ንዋይ ደላሎች (Securities Broker) ስድስት ሚሊዮን ብር፣ የሰነደ መዋለ ንዋይ ገበያ አከናዋዮች (Securities Dealer) አራት ሚሊዮን ብር የተጣራ ፈንድ ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል፡፡

ከሶስቱ መመሪያዎች የሰነደ መዋለ ንዋይ ገበያና የግብይት መድረኮች የፍቃድ አሰጣጥና አሠራር መመሪያ ላይ እንደተመለከተው ሕጋዊና ዕውቅና ባላገኘ የግብይት እንቅስቃሴ ውስጥ በሚገኙ አካላት የአስተዳደራዊ ዕርምጃን ጨምሮ የተለያዩ ቅጣቶች የሚተላለፍ ይሆናል።(ሪፖርተር)
በካፒታል ገበያ የሚሳተፉ የኢንቨስትመንት ባንኮች 100 ሚሊዮን ብር የካፒታል ፈንድ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባሥልጣን ባወጣው ረቂቅ መመሪያ በካፒታል ገበያ ውስጥ ተዋንያን እንደሚሆኑ የሚጠበቁ የኢንቨስትመንት ባንኮች እስከ 100 ሚሊዮን ብር የደረሰ የተጣራ የካፒታል ፈንድ ምጣኔ ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው አስቀመጠ፡፡

የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ለመጀመርያ ጊዜ ሦስት የሚደርሱ ረቂቅ መመሪያዎችን ለሕዝብ አስተያየት ክፍት ያደረገ ሲሆን፣ ባለሙያዎች ምክረ ሐሳቦችን እንዲሰጡባቸው ይፋ የሆኑት ረቂቅ መመሪያዎች የሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ እና የግብይት መድረኮች የፍቃድ አሰጣጥና አሠራር መመሪያ (Licensing and Operating Securities Exchanges and Trading Platforms)፣ ራስን በራስ የሚቆጣጠሩ ድርጅቶች ዕውቅና አሰጣጥ መመሪያ (Recognition of self-regulatory Organizations) እንዲሁም የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪ ፍቃድ አሰጣጥና ክትትል መመሪያ (Capital Market Service Providers Licensing and Supervision) ናቸው፡፡

በሰነድ መዋዕለ ንዋይ ገበያና የግብይት መድረኮች የፍቃድ አሰጣጥና አሠራር ረቂቅ መመሪያው እንደሰፈረው፣ ፍቃድ ፈላጊዎች የሚያቀርቧቸው መረጃዎችና ሰነዶችን መሠረት በማድረግ የቀረበው የፍቃድ ጥያቄ የሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ገበያ (Securities Exchange)፣ የተዛማጅ ውሎች ገበያ (Derivatives Exchange) ያልተማከሉ የጠረጴዛ ዙሪያ ግብይት መድረኮች (over-the Counter Facility) እንደሆነ ይለያል፡፡

ለግብይት የቀረቡት ሰነደ መዋለ ንዋዮችና ለመገበያየት የቀረቡ ባለሀብቶች ይለያሉ፣ የሰነደ መዋለ ንዋይ ፍቃድ፣ የተዛማጅ ውሎች ገበያ ፍቃድ በመመሪያው ክፍል ሁለት ላይ በተቀመጠው መሠረት፣ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን አመልካቾች በቂ ዓቅም ያለውና ያለምንም የአገልግሎቶች መቆራረጥና እንከን መሥራት ይችላሉ የሚለውን ባመነ ጊዜ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪ ፍቃድ አሰጣጥና ክትትል ረቂቅ መመሪያው ላይ እንደተቀመጠው፣ ባለሥልጣኑ የካፒታል ገበያ ተዋንያን ዝቅተኛ የካፒታል ዓቅም መጠንን እንደሚወስን ተገልጾ፣ ይህም የተከፈለ ካፒታል ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኝ የንግድ ባንክ በጥሬ ገንዘብ ተቀማጭ የሚከፈል እንደሆነ ያሳያል፡፡

በረቂቅ መመሪያው እንደተደነገገው እያንዳንዱ የካፒታል ገበያ አገልግሎት አቅራቢ አስፈላጊውን የተጣራ ባለአክሲዮኖች ገንዘብ ወይም የሚጠበቅበት የተጣራ ባለአክሲዮኖች ፈንድ  መሥፈርት ተቀምጧል፡፡

በረቂቅ መመሪያው ሰንጠረዥ አንድ ላይ እንደተቀመጠው እንደ ባንክ የሚወሰዱ የኢንቨስትምንት ባንኮች (Investment Bank-within a Banking Group) እስከ 100 ሚሊዮን ብር የተጣራ የባለአክሲዮኖች ፈንድ ማሟላት የሚጠበቅባቸው ሲሆን፣ እንደ ባንክ የማይወሰዱ የኢንቨስትመንት ባንኮች (Investment Bank- Not Part of a Banking Group)  ደግሞ የአገልግሎት ፍቃድ ለማግኘት 25 ሚሊዮን ብር የተጣራ የባለአክሲዮኖች ፈንድ ማቅረብ (ማሟላት) እንደሚገባቸው ተጠቅሷል፡፡

በሌላ በኩል የጋራ ኢንቨስትመንት ፈንድ አገልግሎት ሰጪዎች (Collective Investment Scheme Operator) 25 ሚሊዮን ብር የተጣራ የባለአክሲዮኖች ፈንድ ማሟላት የሚጠበቅባቸው ሲሆን፣ የብድር የመመለስ ብቃት ምዘና አገልግሎት አቅራቢዎች (Credit Rating Agency) 15 ሚሊዮን ብር፣ የሰነደ መዋለ ንዋይ ደላሎች (Securities Broker) ስድስት ሚሊዮን ብር፣ የሰነደ መዋለ ንዋይ ገበያ አከናዋዮች (Securities Dealer) አራት ሚሊዮን ብር የተጣራ ፈንድ ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል፡፡

ከሶስቱ መመሪያዎች የሰነደ መዋለ ንዋይ ገበያና የግብይት መድረኮች የፍቃድ አሰጣጥና አሠራር መመሪያ ላይ እንደተመለከተው ሕጋዊና ዕውቅና ባላገኘ የግብይት እንቅስቃሴ ውስጥ በሚገኙ አካላት የአስተዳደራዊ ዕርምጃን ጨምሮ የተለያዩ ቅጣቶች የሚተላለፍ ይሆናል።(ሪፖርተር)
Ethiopian Capital Market Authority

1st Round of Registration has started at the School of Commerce and will be open until May 19th.

Limited space available so please Register today!!!!! If space fills up, you will automatically be considered for the 2nd and 3rd rounds.
-----------------------------------------------------------------------------------------
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን
1ኛ ዙር ምዝገባ በንግድ ትምህርት ቤት የተጀመረ ሲሆን እስከ ግንቦት 19 ክፍት ይሆናል።
የተገደበ ቦታ አለ ስለዚህ እባክዎ ዛሬ ይመዝገቡ!!!!!
ቦታው ከሞላ በራስ ሰር ለ2ኛ እና ለ3ኛ ዙር ግምት ውስጥ ይገባል። https://www.condoaddis.com/230517