ET Securities
709 subscribers
640 photos
7 videos
33 files
335 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

www.Etsecurities.com

YouTube.com/@etstocks

Fb.me/etstocks
Download Telegram
January 7
January 8
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
January 9
January 10
January 10
January 10
January 10
የኢትዮጵያ ሰነድ ሙዓለ ገበያ (Ethiopia Security Exchange -ESX ) ግብይት በይፋ ተጀመረ- ደወሉ ተደወለ!!

በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ 50 ያህል ኩባንያዎች በአዲሱ የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ላይ የአክሲዮን ድርሻዎችን ለግብይት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።

https://t.me/Etstocks
January 10
እንኳን ደስ አለን!

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ዛሬ በይፋ ሥራ ጀምሯል!

በገበያው የተመዘገበ ኩባንያ (Listed company) ለመሆን ፍላጎት ካለዎት፣ ስለቀረቡት የኢንቨስትመንት ዕድሎች የበለጠ ማወቅ ከፈለጉ ድረ-ገፃችንን www.esxethiopia.com ይጎብኙ።

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር::
January 10
Share and Share Trading in AA 1960s.pdf
39.9 MB
January 10
January 10
January 10
የኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን የሽያጭ ጊዜ ተራዘመ!!

ኢትዮ ቴሌኮም ለህዝብ አክሲዮን እየሸጠ ያለበት ግዥ ቀነ-ገደብ በአምስት ሳምንታት ተራዝሟል።

የሼር ሽያጩ የካቲት 07 ቀን 2017 የሚዘጋ ሲሆን ከጥቅምት 2017 ጀምሮ 100 ሚሊየን አክሲዮኖችን እያንዳንዳቸው በ300 ብር እየተሸጠ ይገኛል።

ኢትዮ ቴሌኮም እያከናወነ ያለው የድርሻ ሽያጭ ጥር 2/2017 ስራ በጀመረው የኢትዮጵያ የሰነደ መዋዕለነዋዮች ገበያ አሰራር መሰረት እንደሚደለደል ይጠበቃል።
January 11
የናይጀሪያው ፈርስት ባንክ በኢትዮጵያ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው አስታውቋል።

ኢትዮጵያ በሯን ለውጭ ባንኮች ክፍት ማድረጓን ተከትሎ የተለያዩ የውጭ ባንኮች እንደሚገቡ በመግለጽ ላይ ናቸው። አሁን ደግሞ የናይጀሪያው ፈርስት ባንክ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአንጎላ እና ኮትዲቯር የመስራት ፍላጎት እንዳለው የባንኩ ምክትል ሀላፊ ለአፍሪካን ሪፖርት ተናግረዋል። የኬንያው ኬቢሲ፣ የደቡብ አፍሪካው ስታንዳርድ ባንክ እና ሌሎችም በኢትዮጵያ ፍላጎት ካሳዩ ባንኮች መካከል ዋነኞቹ ናቸው።
January 13
January 14
Dashen Bank Super App Dashen Bank has launched a banking super app, providing an all-in-one banking solution that is a first for Ethiopia’s banking sector. Developed in partnership with . . .

Read more condoaddis.com/250114-1
January 15
የኢትዮጵያ ሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ሥራ አስፈጻሚ ጥላሁን ካሳሁን፣ ገበያው በርካታ ኩባንያዎችን ለመሳብ የሚያገበያያቸውን ምርቶችና አገልግሎቶች ዓይነት ለማብዛት ማቀዱን እንደነገሩት ጠቅሶ የአሜሪካው ሴማፎር ድረገጽ ዘግቧል።

ኩባንያው፣ ወደፊት ለመጀመር ካሰባቸው አማራጮች መካከል እስላሚክ ቦንድ አንዱ እንደኾነ ዋና ሥራ አስፈጻሚው መግለጣቸውንም ዘገባው አመልክቷል።

ትላልቅ የአክሲዮን ማኅበራትንና በግል ይዞታ ሥር የሚገኙን ጨምሮ የግል ኩባንያዎች ገበያውን ይቀላቀላሉ ብለው እንደሚጠብቁ የጠቆሙት ጥላሁን፣ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ በትንሹ 90 ኩባንያዎች በገበያው አማካኝነት የአክሲዮን ገበያውን እንዲቀላቀሉ ዓላማ ተይዞ እየተሠራ እንደሚገኝም ተናግረዋል ተብሏል።

በአገሪቱ ከሚገኙ 30 ንግድ ባንኮች መካከል እስካኹን በገበያው የአክሲዮን ድርሻዎቹን ለማገበያየት የተመዘገበው ወጋገን ባንክ ብቻ ነው።

(ዋዜማ
)
January 21
ለውጭ ገበያ ከቀረበ ቡና 908 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የቡናና ሻይ ባለስልጣን ገለጸ ፡፡

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሻፊ ኡመር ባለፈው ስድስት ወር ከ204 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለውጭ ገበያ በማቅረብ 908 ሚሊዮን ዶላር  ገቢ መገኘቱን አስታውቀዋል ።

አፈጻጸሙም ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት የ8 ሺህ 251 ነጥብ 17 ቶን ወይም 73 በመቶ ብልጫ እንዳለው ነው የተናገሩት ፡፡
ባለስልጣኑ በ2017 በጀት አመት 400 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ በመላክ 2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ማቀዱ ይታወሳል ፡፡

ስማርት መረጃ
January 21