ET Securities
708 subscribers
647 photos
8 videos
34 files
342 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

www.Etsecurities.com

YouTube.com/@etstocks

Fb.me/etstocks
Download Telegram
December 31, 2024
January 2
January 2
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ትርፍ 40 በመቶ ቀነሰ!!

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ በተጠናቀቀው የ2016 ሒሳብ ዓመት 1.6 ቢሊዮን ብር ትርፍ  ማግኘቱን አስታውቋል፡፡

ከቀዳሚ ዓመት ጋር ሲነፃፀር በአንድ ቢሊዮን ብር ዝቅ ያለ መሆኑ አመታዊ ሪፖርቱ ያሳያል።

ባንኩ ለትርፉ መቀነስ ዓለም አቀፋዊና አገራዊ የኢኮኖሚ መቀዛቀዝን እና የአገር ውስጥ የፀጥታ ችግር እንደ ምክንያት ተጠቅሷል፡፡

በሒሳብ ዓመቱ 903 ሚሊዮን አዲስ ተቀማጭ ገንዘብ በማሰባሰብ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን 117.1 ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡ 

አጠቃላይ የባንኩ የብድር ክምችት መጠን 117.15 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡

ባንኩ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት የ19.03 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱ የተገለጸ ሲሆን ይህም ከቀዳሚው ዓመት አንፃር ሲታይ 7.5 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡

ከዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ባንኩ በሒሳብ ዓመቱ 258.3 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ያገኘ ሲሆን ይህም አፈጻጸሙ ከቀዳሚው ዓመት ቅናሽ ያለው መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት መጨረሻ ላይም የተከፈለ ካፒታሉን 11.16 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን የባንኩ አጠቃላይ ሀብት መጠን 139.7 ቢሊዮን ብር ሆኗል፡፡ 
January 2
January 2
በኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮች ከቀናት በኋላ በነባሩም ሆነ አዳዲስ ውለታ የሚገቡትን ተበዳሪዎች የብድር ወለድ ምጣኔን ከ3 እስከ 5 በመቶ ከፍ ሊያደርጉ በዝግጅት ላይ መሆናቸው ተሰማ‼️

ይህም #የብድር_የወለድ ምጣኔው እስከ 20 እና 22 በመቶ ይደርሳል እንደማለት ነው፡፡

ከዓመታት በፊት የነበረውን የገንዘብ የመግዛት አቅም እና የኢኮኖሚውን ሁኔታ እንዲሁም የገቢ መጠናቸውን ታሳቢ በማድረግ ከባንክ በመበደር ከውጭ እቃ የሚያስመጡ ነጋዴዎች ሆኑ ቤት የገዙ ተበዳሪዎች በተበደሩት ወለድ ላይ ከ3 እስከ 5 በመቶ ጭማሪ ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡

አንድ ተበዳሪ ከዓመታት በፊት ከባንክ በ17 በመቶ ወለድ ተበድሮ ከነበረ በአሁኑ ወቅት ባንኮች ወለዱን 5 በመቶ በመጨመር 22 በመቶ ሊያደርሱት በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ታማኝ ምንጮች ነግረውናል፡፡

በአሁኑ ወቅት ገበያው እራሱን እያረጋጋ ነበር ይሁንና ጥቂት ቁጥር ባላቸው #ባንኮች ምክንያት ተመልሶ ዋጋ ሊንር ነው የሚሉት ምንጫችን በተለይም ከውጭ እቃ ለማስገባት ከባንኮች ብድር አስቀድመው ውል ገብተው የተበደሩትም ሆኑ አዳዲስ ተበዳሪዎች ከፍተኛ በሆነው የብድር የወለድ ጭማሪ ምክንያት የሚስገቡት እቃ እጅግ ይንራል ይህም መልሶ ሸማቹ ላይ የሚወደቅ ይሆናል ብለዋል፡፡

አንድ ተበዳሪ ከባንክ ጋር የብድር ኮንትራት ሲገባ ባንኩ ወለድ እንዲጨምር ይሁንታውን ይሰጣል፡፡

ባንኮች ብድር ስለሚሰጡ እና በኮንትራቱ መሰረት የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሁኔታ በመመልከት የወለድ ምጣኔውን እንዲጨምሩ ስምምነት ተደረገ ማለት ግን እንደፈለጉት ህግንም እንዲተላለፉም ሆነ ሀገርን ወደ አደገኛ የኢኮኖሚ ችግር የማስገባት መብት አላቸው ማለት አይደለም ተብሏል፡፡

አሁን ያለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከ1 በመቶ እስከ 2 በመቶ የብድር የወለድ ምጣኔን ሊያስጨምር የሚችል መሆኑን ማየት ይቻላል ይሁንና ከ3 - 5 በመቶ ግን በፍጹም የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ሊሸከመው የሚችል ዓይነት አይደለም ሲሉ ምንጫችን ነግረውናል፡፡
#ሸገርኤፍም
January 2
ለውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች ፈቃድ መስጠትን ማቆም!!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ  በህጋዊ መንገዶች የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎችን ለሚከፍቱ ተቋማት ፈቃድ መስጠት ለጊዜውም ማቆሙን አስታውቋል፡፡

በፈረንጆቹ ኦክቶበር 2024 ብሔራዊ ባንክ ለአምስት የሀገር ውስጥ የግል ውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች ፈቃድ መስጠቱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

በፖሊሲ አውጪ ባንኩ በኩል ይህ ውሳኔ የተላለፈው ደግሞ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የትይዩ ውጭ ምንዛሬ ገበያውም ወይም በተለምዶ ጥቁር ገበያው ጋር ያለውን የምንዛሬ ዋጋ ልዩነት በማጥበብ ቀስ በቀስም ትይዩ ገበያውን ለማዳከም በማሰብ ነው፡፡

በዚህም መሰረት ዱግዳ ፊደሊቲ ኢንቨስትመንት ፒኤልሲ፣ ኢትዮ ኢንዲፔንደንት፣ ግሎባል ኢንዲፔንደንት፣ ሮበስት ኢንዲፔንደንትና ዮጋ የውጭ ምንዛሬ መገበያያ ቢሮዎች ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ እንደተሰጣቸው ይታወሳል፡፡.

አሁን ላይ ታዲያ ሌሎች አዳዲስ ተቋማትን ወደዚሁ ገበያ ከማስገባት አስቀድሞ እነዚህ የውጭ ምንዛሬ መመንዘሪያ ቢሮዎች አፈጻጸማቸው ምን ይመስላል? የሚለውን ለመገምገም ሲባል አዲስ ፈቃድ መስጠት መቆሙን ነው ብሔራዊ ባንክ ይፋ ያደረገው፡፡

እነዚህ ተቋማት ከዚህ ቀደም የባንክ ሥራዎችን ሰርተው የማያውቁ በመሆናቸውና ወደገበያው ሲገቡ ለመጀመሪያ ጊዜ በመሆኑ ምክንያት ለገበያው አዲስ አሰራርን ይዘው መምጣታቸውንና ይህም ሁኔታ ባለፉት ጥቂት ወራት ያስመዘገበው ውጤት መገምገም እንዳለበትም ነው በምክንያትነት የቀረበው፡፡

የፋይናንስ ዘርፉን የሚቆጣጠረው ብሔራዊ ባንክ ቢሮውን ለመክፈት እያንዳንዱ ተቋም 15 ሚሊዮን ብር ካፒታልና ለአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ የሚሆን 30 ሚሊዮን ብር በዝግ አካውንት እንዲያስገቡ በመስፈርትነት ማስቀመጡም የሚታወቅ ነው፡፡

@Etstocks
January 5
ቤንዚን  በሊትር 101.47 ብር ሲገባ ናፍጣ በሊትር 98.98 ብር ሆኗል።

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ።

በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደርጓል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ይፋ እንዳደረገው ከዛሬ ታኅሣሥ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆነው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ተወስኗል።

በዚሁ መሰረት ፦

አንድ ሊትር ቤንዚን 101.47 ብር፣

አንድ ሊትር ናፍጣ 98.98 ብር፣

አንድ ሊትር ኬሮሲን 98.98 ብር፣

የአውሮፕላን ነዳጅ 109.56 ብር፣

አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 105.97 ብር

አንድ ሊትር ቀላል ጥቁር ናፍጣ 108.30 ብር ሆኖ እንዲሸጥ ተወስኗል።
January 7
January 7
January 8
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
January 9
January 10
January 10
January 10
January 10
የኢትዮጵያ ሰነድ ሙዓለ ገበያ (Ethiopia Security Exchange -ESX ) ግብይት በይፋ ተጀመረ- ደወሉ ተደወለ!!

በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ 50 ያህል ኩባንያዎች በአዲሱ የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ላይ የአክሲዮን ድርሻዎችን ለግብይት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።

https://t.me/Etstocks
January 10
እንኳን ደስ አለን!

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ዛሬ በይፋ ሥራ ጀምሯል!

በገበያው የተመዘገበ ኩባንያ (Listed company) ለመሆን ፍላጎት ካለዎት፣ ስለቀረቡት የኢንቨስትመንት ዕድሎች የበለጠ ማወቅ ከፈለጉ ድረ-ገፃችንን www.esxethiopia.com ይጎብኙ።

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር::
January 10
Share and Share Trading in AA 1960s.pdf
39.9 MB
January 10