ET Securities
661 subscribers
584 photos
7 videos
28 files
297 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
ንብ ባንክ በዘንድሮ ዓመት ሊከፋፈል የሚገባው የትርፍ ክፍያ ገንዘብ እንደማይኖር አሳወቀ!!

ንብ ባንክ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት ከግብር በፊት 1.2 ቢሊዮን ብር ማትረፉን እና ከግብር በኋላ ደግሞ 957.97 ሚሊዮን ብር እንዳተረፈ አሳውቋል።

ነገር ግን ለባለአክሲዮኖች ሊከፈል የሚገባው የትርፍ ድርሻ ቀደም ባሉ ዓመታት ለተሠሩ ስህተቶች የሒሳብ ማስተካከያ ሥራዎች እንዲውል ተወስኗል፡፡
 
ንብ ባንክ የT24 ሲስተም ለውጥ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ የፋይናንስ ችግር በተለይም የጥሬ ገንዘብ እጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ይምጣ እንጂ መነሻው ካለፉት አምስት ዓመታት ጀምሮ መሆኑ ተገልጿል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የባንኩ አጠቃላይ ዕዳ 56.7 ቢሊዮን ብር መሆኑ ታውቋል፡፡    

በሒሳብ ዓመቱ የባንኩ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን 45.1 ቢሊዮን ብር ነው። ይህም ካለፈው ዓመት አንፃር የ14.3 ቢሊዮን ብር ወይም የ24.1 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡

የባንኩ አጠቃላይ ካፒታል 10.4 ቢሊዮን ብር ሲሆን ካለፈው ዓመት የ1.5 ቢሊዮን ብር ወይም የ16.8 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡

የተከፈለ ካፒታሉም በ26.3 በመቶ አድጎ 7.6 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡

የንብ ባንክ አጠቃላይ ሀብት 67.0 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን ባንኩ የሰጠው ብድር ክምችት መጠንም ከአጠቃላይ ሀብቱ 72.3 በመቶ ነው፡፡

ባንኩ በ2016 የሰጠው አጠቃላይ ብድርና የቅድሚያ ክፍያዎች 49.2 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡ ካለፈው ዓመት የ4.6 ቢሊዮን ብር ቅናሽ አሳይቷል፡፡

የባንኩ ዓመታዊ ገቢ 10.8 ቢሊዮን ብር ሲሆን ካለፈው ዓመት የ1.9 ቢሊዮን ብር ዕድገት ማሳየቱን ተገልጿል።

የባንኩ አጠቃላይ ወጪው ደግሞ በ38 በመቶ ጨምሮ 9.6 ቢሊዮን ብር ሆኖ ተመዝግቧል

YouTube
TikTok
ቢትኮይን ለመጀመሪያ ጊዜ 100 ሺህ ዶላር መመንዘር ጀመረ‼️

በዚህም የአንድ ቢትኮይን ዋጋ በ100 ሺህ ዶላር በመመንዘር ላይ ሲሆን ይህም በዲጂታል መገበያያ ገንዘቡ ታሪክ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

የቢትኮይን ዋጋ እንዲህ ሊጨምር የቻለው ተመራጩ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የክሪፕቶ ከረንሲን የሚደግፉ ፖሊሲዎችን እንደሚቀበሉ በማሳወቃቸው መሆኑ ተገልጿል።

ትራምፕ የቀድሞን የአሜሪካ የሴኪውሪቲስ እና ኤክስቼንጅ ኮሚሽነር ፖል አትኪንስ የሃገሪቱ የስቶክ ገበያ የሆነውን ዎል ስትሪት እንዲመሩ ማጨታቸው ከተሰማ ከሰዓታት በኋላ የቢትኮይን ዋጋ እንዲጨምር ምክንያት መሆኑም ተነግሯል፡፡

ሚስተር አትኪንስ አሁን ካሉት የሴኪውሪቲስ እና ኤክስቼንጅ ኮሚሽን ኃላፊ ጋሪ ጌንስለር የበለጠ የክሪፕቶ ከረንሲ ደጋፊ ስለመሆናቸውም ነው የተገለፀው።

ዶናልድ ትራምፕ ምንም እንኳን ከዚህ በፊት ክሪፕቶከረንሲን የተቹ ቢሆንም አሁን ግን አሜሪካን የምድራችን የክሪፕቶከረንሲ መዲና አደርጋታለሁ ሲሉ ቃል መግባታቸውን ተከትሎ የቢትኮይን ዋጋ እየናረ መምጣቱ ተጠቁሟል።

በተለይም ባለፈው ወር ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ካሸነፉ በኋላ የቢትኮይን ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ ሲያሳይ መቆየቱ ነው የተገለፀው።

አንዳንድ ትልልቅ ኩባንያዎችና ተቋማት ቢትኮይንን እንደ ገንዘብ መቀበል መጀመራቸውም ለተፈላጊነቱ ማደግ ሌላ ምክንያት ነው ተብሏል።

የዲጂታል መገበያያ ገንዘቡ 100 ሺህ ዶላር መግባቱን ተከትሎ በዓለም ዙሪያ ያሉ የቢትኮይን ተጠቃሚዎች እና ደንበኞች ደስታቸውን እየገለፁ መሆኑን የዘገበው ቢቢሲ ነው።

Source: BBC
የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ለውጭ ውድድር ሊከፈት መሆኑ ተሰማ

ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የባንክ ዘርፉን ለውጭ ውድድር ለመክፈት በዝግጅት ላይ ትገኛለች። ይህን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት አዲስ ህግ በፓርላማ እየተገመገመ እና በሚቀጥለው ወር ይፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

ይህ ውሳኔ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ገጽታ ላይ ከፍተኛ ለውጥን የሚያመለክት ሲሆን ይህም ውድድርን ለማሳደግ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እና የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ያለመ ነዉ ተብሏል ።

ርምጃው በኢትዮጵያ መንግስት እና በብሄራዊ ባንክ የተጀመሩት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች አካል ሲሆን እነዚህ ማሻሻያዎች የተነደፉት የፋይናንስ ሴክተሩን ለማዘመን እና ለሀገር ውስጥ እና ለአለም አቀፍ ንግዶች የበለጠ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ጭምር ነዉ።

የውጭ ባንኮችን ወደ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ምኅዳር ማስገባቱ ፉክክር እንደሚያመጣ የሚጠበቅ ሲሆን ይህም ለተጠቃሚዎች የተሻሻሉ አገልግሎቶችን እና ምርቶችን ሊያመጣ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።

ህጉ የውጭ አካላት በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ እንዳይሳተፉ በታሪክ የሚገድቡ እንቅፋቶችን ለመበተን ያለመ ነው። የውጭ ባንኮች ከአገር ውስጥ ተቋማት ጋር አብረው እንዲሠሩ በመፍቀድ፣ መንግሥት የፋይናንስ አካታችነትንና ፈጠራን ሊያጎለብት የሚችል ዓለም አቀፍ እውቀትና ካፒታል ለመጠቀም ያለመ መሆኑ ታዉቋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ በቅርቡ በተካሄደዉ እና የአውሮፓ ምክር ቤት በኢትዮጵያ ባዘጋጀው ዝግጅት እንደተናገሩት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ ማሻሻያው ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል ።

ከዚህ በተጨማሪ የግሉ ሴክተር በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ያለው ፍላጎትና ተሳትፎ በተለይም የውጪ ንግዶች ለእድገት ፍፁም ወሳኝ ናቸዉ ሲሉም አክለዋል ።
እስላሚክ ካፒታል ገበያ!!

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የእስላሚክ ካፒታል ገበያን ኢትዮጵያ ውስጥ ለማስተዋወቅ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ማድረጉ ዋዜማ ሚዲያ ጠቁሟል።

ይህ ፕሮጀክት የአምስት ወራት ቆይታ ያለው መሆኑ እና ለእስላሚክ ካፒታል ገበያ የሕግ ማዕቀፍ ለማበጀት ጠቃሚ እንደሆነ ተገልጿል።

ባለሥልጣኑ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የልማት ፕሮግራምና ሌሎች አሕጉራዊ ተቋማት ጋር በመተባበር ነው የሚሰራው ተብሏል።

የዓለማቀፉ እስላሚክ ፋይናንስ የምክር አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ እስላሚክ የካፒታል ገበያ ለማቋቋም ብሄራዊ ባንክንና የኢትዮጵያ ሙዓለ ንዋይ ገበያን ጨምሮ በርካታ ባለድርሻዎች የተሳተፉባቸውን ግምገማዎችና አውደ ጥናቶችን ማካሄዱን ተገልጿል።

በፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ላይ ይሄው አማካሪ ኩባንያ የእስላሚክ ካፒታል ገበያ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ ያቀርባል ተብሏል።
Oromia Insurance Company achieves remarkable growth in 2023/24 solidifying its market position in Ethiopia’s insurance industry

Oromia Insurance (OIC) has announced impressive financial results for the fiscal year ending June 30, 2024, reinforcing its position as one of Ethiopia’s premier private insurers. Despite the challenges posed by a volatile economic landscape, OIC has made substantial strides in expanding its services, delivering exceptional results, and achieving key milestones throughout the fiscal year ending June 30, 2024, across multiple key indicators.

Website (https://www.condoaddis.com/category/etstocks )
| Facebook (https://www.fb.me/etstocks)
| X (https://www.X.com/@etstocks1)
| TikTok (https://www.tiktok.com/@etstocks
| Linkedin (https://www.linkedin.com/company/etstocks)
|Youtube (https://www.YouTube.com/@etstocks)
ግዙፉ የአሜሪካው የቢትኮይን ኩባንያ "ቢ አይ ቲ" ኢትዮጵያ ውስጥ ከቢትኮይን መረጃ ማቀነባበሪያ ማዕከል ከፍተኛ የአክሲዮን ድርሻ በመግዛት ኢንቨስትመንቱን ሊያስፋፋ እንደኾነ አስታውቋል። ኩባንያው እስከ ሚያዝያ ድረስ በክሪፕቶ መረጃ ማቀነባበሪያ ማዕከላት ተጨማሪ ድርሻዎችን በመግዛት 51 ሜጋዋት ኃይል የሚጠቀም ማዕከል ባለቤት እንደሚኾንም ገልጧል። ኩባንያው፣ ይህንኑ ሂደት ሲያጠናቅቅ በጠቅላላው 45 ሚሊዮን 278 ሺሕ የአክሲዮን ድርሻዎችን ለመሸጥ እንዳሰበ አመልክቷል።
ምንም እንኳን በየሰኮንዱ ዋጋው ቢቀያየርም አንድ Bitcoin በቅርቡ 100,000 ዶላር መሸጡ ይታወሳል።
አማራ ባንክ ከታክስ በፊት ከ550 ሚሊየን ብር በላይ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።

በ2013 ከ180 ሺህ በላይ ባለ አክሲዮኖች የተመሰረተው አማራ ባንክ ባለፉት አመታት ኪሳራዎች ገጥመውት እንደነበር ይታወሳል።

እየተጠናቀቀ ባለው የፈረንጆቹ 2024 ሰኔ ወር ድረስ ከገባበት ኪሳራ በመውጣት ከ550 ሚሊየን ብር በላይ ጠቅላላ ትርፍ ማስመዝገቡን የባንኩ 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተነግሯል።

ባንኩ ከ801 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞችን አግኝቻለሁ ያለ ሲሆን በዚህም አጠቃላይ የደንበኞቹን ቁጥር ከአንድ ሚሊየን ስምንት መቶ ሺህ በላይ ለማድረስ መቻሉ ነው የገለፀው።

የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ ጋሻው ደበበ ባለፈው አመት በባንክ ኢንደስትሪው አወንታዊና አሉታዊ ሁኔታዎችን የፈጠሩ አለም አቀፋዊና አገራዊ ክስተቶች ማጋጠማቸውን አስታውሰው የተፈጠሩት ጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል በኢኮኖሚው ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩን ጠቁመዋል።

በሀገሪቱም በአንዳንድ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች ተደማምረው አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደራቸውን ተናግረዋል።

አማራ ባንክ በ3ኛው የባለ አክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ 43 አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመጨመር የቅርንጫፎቹን ብዛት 310 ማድረሱ የተገለፀ ሲሆን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎትን የሚሰጡ ቅርንጫፎቹም ብዛት 15 ደርሰዋል።
ስኬት ባንክ ክፍተኛ የፋይናንሻል ዕድገት በማሳየት 1.54 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ አስመዝግቧል። ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ50 በመቶ ብልጫ አለው። ይህ አፈጻጸም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከሚጠይቀው ዝቅተኛ የካፒታል መስፈርት ብልጫ ያለው የተከፈለ ካፒታል የ25 በመቶ እድገት አሳይቷል፣ አሁን 5.46 ቢሊዮን ብር ደርሷል።

ቁልፍ ውጤቶች
📈 በአጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ 36 በመቶ እድገት፣ 4.9 ቢሊዮን ብር ደርሷል
📈 የብድር ፖርትፎሊዮን አሁን በ9 ቢሊዮን ብር ሰፍቷል
📈 8% የተሰበሰበ ዕዳ ጨምሯል፣ በአጠቃላይ 4.2 ቢሊዮን ብር
📈 አጠቃላይ ገቢው 41% ከፍ ያለ ሲሆን 2.37 ቢሊዮን ብር ሲሆን 75% በወለድ ገቢ

በጠቅላላ ወጪው የ28 በመቶ እድገት ቢኖረውም፣ 828.5 ሚሊዮን ብር ቢደርስም፣ ስኬት ባንክ ጤናማ የትርፍ አስመዝግቧል።
የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ጥር ወር 2017 ዓ.ም ስራ እንደሚጀምር ተገለፀ!!

የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጥላሁን ኢስማኤል (ዶ/ር) ባለፈው አንድ ዓመት ኩባንያውን እውን ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ገልፀዋል።

ገበያው የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ሽያጭ፣ ግዥ እና ልውውጥ በቋሚነት የሚደረግበት ሲሆን ለመንግሥትና የግሉ ዘርፍ የገንዘብ ምንጭ በመሆን ለምጣኔ ኃብት እድገት ጠቃሚ መሆኑን ገልፀዋል።

መንግስት እና የግሉ ዘርፍ ለሚያከናውኗቸው ኢንቨስትመንቶች ካፒታል ለማሰባሰብ አቅም እንደሚጨምር ይጠበቃል።

በሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ አክስዮን የሚሸጡ ኩባንያዎች በየጊዜው የሂሳብ ሁኔታቸው እየተገመገመ ይፋ የሚሆንበት አሰራር መዘርጋቱ ተጠቁሟል።

ይህ ጅምር የኢትዮጵያን አዲስ የካፒታል ገበያ ለማራመድ የተቀናጀ ሲሆን ከኢንተር ባንክ ስራዎች ባሻገር ለንግዶች እና ባለሀብቶች አዳዲስ እድሎችን የሚከፍት ቀልጣፋ የገበያ ቦታ ነው።
Vacancy Announcement for Fresh Graduates
-------------------------------------
Abay Bank S.C. invites interested and qualified applicants for Customer Service Officer (CSO)-II position.

For detail information, please visit our website with the link attached below.
https://www.abaybanksc.com/vacancy-announcement-8/

Follow our social media pages for new vacancy announcements.
ፌስቡክ (http://www.facebook.com/abaybanksharecompany)
ቴሌግራም (https://t.me/abaybanksharecompany)
ትዊተር (https://twitter.com/AbayBank)
ሊንክድኢን (https://www.linkedin.com/company/abaybank)
ዩትዩብ (https://www.youtube.com/@abaybank4665)
ቲክቶክ (https://www.tiktok.com/@abaybank)

Good Luck!p
አንበሳ ኢንሹራንስ በኢንዱስትሪዉ ከፍተኛዉን የአርቦን ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አስታውቋል

በኢንዱስትሪ ደረጃ በበጀት ዓመቱ በጠቅላላ መድን ዘርፉ ብር 28.3 ቢሊዮን አረቦን የተሰበሰበ ሲሆን፤ የአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ ደግሞ ብር 1.178 ቢሊዮን የእረቦን ገቢ በማስመዝገብ የገበያ ድርሻውን 4.38 በመቶ ማድረስ መቻሉን ገልጿል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከጠቅላላ መድን ዘርፍ ብር 1.15 ቢሊዮን እና ከህይወትና ጤና መድን ዘርፍ 23.1 ሚሊዩን በድምሩ ብር 1.173 ቢሊዮን የአረቦን ገቢ በማስመዝገብና ግብርና ህጋዊ መጠባበቂያ ተቀንሶ የተገኘው የተጣራ ትርፍ 185.3 ሚሊዮን ብር መሆኑን በሪፖርቱ ጠቁሟል።

ይህ የተባለው ኩባንያው ባካሄደው 17ኛ የባለ-አክሲዮኖች መደበኛ ጉባኤ ላይ ነዉ ። በዚህም በተጠናቀቀዉ ሂሳብ ዓመት አንበሳ ኢንሹራንስ አጠቃላይ ሃብት ብር 2.78 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን፤ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃጸር የብር 705.9 ሚሊዮን ወይም 33.9 በመቶ እድገት ማስመዝገብ ችሏል ብሏል።
የኢትዮጵያ ሠነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያሞሮኮ አክሲዮን ገበያ ጋር የትብብር ስምምነት ፈጸመ!!

የኢትዮጵያ ሠነደ ሙዓለ-ንዋዮች ገበያ ከሞሮኮ ካዛብላንካ አክሲዮን ገበያ ጋር ስትራቴጂካዊ የትብብር ስምምነት መፈራረሙ ተገለፀ።

አላማውም በዋናነት በእውቀት ማጋራት እና ተግባራዊ ድጋፍ መስጠት ላይ የሚያተኩር መሆኑ ተገልጿል።

ደኅንነቱን የጠበቀ እና ቀልጣፋ የንግድ ሥርዓት እንዲፈጥር የቴክኖሎጂ ማዕቀፍን፣ የአሠራር አቅም እና የአደጋ አሥተዳደር አቅምን የሚያጎለብቱ ሥራዎች ለመስራት ያስችላል ተብሏል።

በተጨማሪም ኢንቨስትመንትን እና ዘላቂ እድገትን ለማበረታታት እንደሚያግዝ ተገልጿል፡።
ከታክስ በፊት 930 ሚሊየን ብር ትርፍ አተረፍኩ! – ቡና ባንክ
ከተመሰረተ 15 አመት የሞላው ባንኩ ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ትርፉ በ4መቶ29 ሚሊየን ብር ቅናሽ ማሳየቱንም አስታውቋል።

በበጀት አመቱ እንደ አገር የተከሰተው ከፍተኛ የዋጋ ንረት ፣ የውጭ ምንዛሬ ዕጥረት ፣ ተደራራቢ የሆኑ የተቆጣጣሪ አካላት መመሪያዎች መውጣት እንዲሁም ተግባራዊ መሆን ለባንኩ ዘርፍ አስቸጋሪ ሁኔታ እንደነበር ተገልጿል።

የባንኩ የቦርድ ሊቀመንበር አምባሳደር አለማየሁ ሰዋገኝ፤ እነዚህ ችግሮች የባንኮችን የማበደር ብቻ ሳይሆን ተቀማጭ የማሰባሰብ እንቅስቃሴ ላይም ተፅዕኖ ማሳደራቸውን ተናግረዋል።

ነገርግን ባንኩ ላስመዘገበው የሀብት ዕድገት የተሰጡ የብድር አቅርቦቶች ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዙም ገልጸዋል።

በዚህም የባንኩ አጠቃላይ የሀብት መጠን ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ8.14 ቢሊየን ብር ዕድገት በማሳየት 54.53 ቢሊየን ብር መድረሱን አስታውቀዋል።

በበጀት አመቱ የተመዘገበው የባንኩ የተከፈለ ካፒታል ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ549.2 ሚሊየን ብር ጭማሪ በማሳየት ወደ ብር 4.83 ቢሊየን ማደግ ችሏል ነው የተባለው።

ባንኩ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የተቀመጠውን ዝቅተኛ የካፒታል መጠን እንዲሁም የተከፈለ ካፒታል መጠን ከተቀመጠው ጊዜ ቀደም ብሎ ለማሟላት ዕቅድ አውጥቶ እየሰራ መሆኑም ተገልጿል።

ከዕቅዱ አንፃር ዝቅ ያለ ቢሆንም 4መቶ90 ሚሊየን 1መቶ16 ሺህ ብር ለባንኩ ባለአክሲዮኖች በትርፍ ክፍያ እንዲከፋፈል ውሳኔ መደረሱንም ገልፀዋል።

ባንኩ በያዝነው በጀት አመት ሩብ አመት መጀመሪያ ላይ ከዕቅዱ በላይ 1.2 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱንም ሰምተናል።

ቡና ባንክ የባለአክሲዮኖች 15ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።
ገቢዎች ቢሮ ድርጅቶች ሊኖራቸው የሚገባውን የሰራተኞችን ቁጥር እና ሊከፈል የሚገባውን ዝቅተኛ ደመወዝ ወለል ወሰነ!

በዚህ ውሳኔ በሆቴሎች እና ሌሎች የንግድ ዘርፎች ላይ አሰሪዎች ለሰራተኞቻቸው የደሞዝ ጭማሪ እንዲያደርጉ የሚያስገድድ ተመን ይሆናል።

ከአስተናጋጅ፣ ጥበቃና የፅዳት ሙያ ውጭ ላሉ ሰራተኞች ትንሹ የሚከፍሉት ደመወዝ 5,000 ብር ሆኖ ተተምኗል።

በዚህም የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በግብር  ሂደት  ውስጥ የሚፈጠሩ ማጭበርበሮችን ለመቀነስ ዓላማው ያደረገ ለሆቴሎች፣ ለስጋ ቤቶች፣ ለመጠጥ ቤቶች እና ለተለያዩ የተመረጡ የንግድ ዘርፎች ለሰራተኞቻቸው አነስተኛ የደመወዝ ወለል እና የሰራተኞችን ብዛት የሚተምን ተመን ይፋ አድርጓል።

Source: theethiopianeconomistview
@Etstocks
የውጭ ሀገራት ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ የሚፈቅደው የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ መርምሮ እንደሚያፀድቅ ተገለፀ፡፡

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ11ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ከተወያየ በኃላ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡

በነገው መደበኛ ስብሰባ የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ለምክር ቤቱ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡

ረቂቅ አዋጁ ሰኔ 18 ቀን ፣ 2ዐ16 ዓ/ም ለፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተመራ ሲሆን ምክር ቤቱ፤ ቋሚ ኮሚቴው የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል፡፡

ረቂቅ አዋጁ ሲጸድቅ የውጭ ባንኮች በሃገር ውስጥ ተቀጥላ ወይም ሰብሲዲያሪ ጽህፈት ቤታቸውን እንዲከፍቱ ከመፍቀዱ በተጨማሪም የሀገር ውስጥ ባንኮችን ድርሻ መግዛት እንዲችሉ የሚፈቅድም ነው፡፡

ከዚህም ባሻገር የውጭ ባንኮች ቅርንጫፎቻቸውን እንዲከፍቱ፣ ኢትዮጵያውያንና የውጭ ሀገራት ዜጎችም በባንኮቻቸው የሥራ እድልን ማግኘትና የቦርድ ሊቀመንበር አባላት እንዲሆኑ መንገዱን የሚያቀናላቸው ነው ይኸው ረቂቅ አዋጅ፡፡

መንግስትም የአዋጁን መጽደቅ ተከትሎ ለአምስት የውጭ ባንኮች ፈቃድ ለመስጠት ያስችለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ገበያ ለመሥራት ፍላጎት ካሳዩ የውጭ ባንኮች ውስጥ የኬንያው ኬሲቢ እንዲሁም ስታንዳርድ ባንኮች ይጠቀሳሉ፡፡