ET Securities
651 subscribers
573 photos
7 videos
26 files
288 links
At Et securities our aim is in creating condusive space concerning capital markets and financial markets so as to enable learning and awareness creation to the society.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የብድር ወለድ እና የአገልግሎት ዋጋ ማሻሻያ ሊያደረግ ነው‼️

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ በሚያደርግበት ወቅት ለደንበኞቹ ቀደም ብሎ እንደሚያሳውቅ ገልጿል፡፡

ይህን ተከትሎም ባንኩ በሚሰጣቸው የብድር፣ የቅርንጫፍ እና የዲጂታል እንዲሁም በዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎቶች ላይ በቅርቡ የብድር ወለድ እና የአገልግሎት ዋጋ ማሻሻያ ሊያደርግ መሆኑን አስታውቋል።

ባንኩ በቅርቡ ለሰራተኞቹ የደመወዝ ጭማሪ ማድረጉ ይታወሳል።

https://www.condoaddis.com/category/etstocks
የአዋሽ ባንክ ትርፍ!!

አዋሽ ባንክ 10 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ከግብር በፊት ማትረፉ በ29ኛው የባለአሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተገልጿል፡፡

በ2016 ዓ.ም 45 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰቡን ያስታወቀው ባንኩ የተቀማጭ ገንዘቡ ከባላፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ20 በመቶ እድገት ማሳየቱንና በፈረንጆቹ ጁን 30፣ 2024 የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ 232 ነጥብ 4 ቢሊዮን መድረሱም ተገልጿል፡፡

ባንኩ ዘንድሮ ያገኘው ትርፍ ደግሞ በሰኔ 30፣ 2024 ያገኘው ትርፍ የ11 በመቶ እድገትን ያሳየ ነው ተብሏል፡፡

በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት የባንኩ የብድር መጠን ካለፈው ዓመት በ21 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ወይም በ13 ነጥብ 3 በመቶ እድገት ያሳየ ሲሆን የባንኩ አጠቃላይ የብድር መጠንም 183  ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተገልጿል፡፡

በሌላም በኩል ከውጭ ይገባሉ በተባሉትና በሀገር ውስጥ በቅርቡ በተመሰረቱት ባንኮች የተነሳ ከፍተኛ ውድድር ይኖራል ይሄንንም በቁርጠኝነት ለመወጣት ባንኩ ዝግጁ ነው ተብሏል፡፡

የውጭ ምንዛሬ ግኝትን በተመለከተ ባንኩ በሂሳብ ዓመቱ 1 ነጥብ 52 ቢሊዮን ዶላር መሰብሰቡንም የባንኩ ዳይሬክተሮች የቦርድ ሊቀመንበር ጉሬ ኩምሳ አክለው ገልጸዋል።
Wegagen Bank has made monumental strides in its operations to provide value to its shareholders, including optimising fund management for ensured liquidity and focusing on loan collections. Analysts see these moves as crucial, particularly in light of regulatory credit caps imposed by the National Bank of Ethiopia (NBE). The Bank has also seen a surge in income by 40pc to 9.8 billion Br, indicating its strategy's effectiveness.

Read More

Source: addisfortune
@Etstocks
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ትርፍ!!

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2017 የመጀመሪያ ሩብ አመት 1.2 ቢሊዮን ትርፍ ማግኘቱን ገለፀ።

ይህም ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ258 በመቶ ብልጫ አለው ተብሏል።

የሩብ አመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ ያካሄደው ባንኩ በግብርና፣ ማዕድንና ኢነርጂ ዘርፍ የብድር አሰጣጡን በማሳደግ የብድር አሰባሰብ ሂደቱ ተሻሽሏል ብሏል።

የባንኩ የቦንድ ሽያጭ 19 በመቶ ማደጉ የባንኩ ቁልፍ ስኬት ማሳያ መሆኑም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር እመቤት ባንኩ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ጋር ራሱን በማጣጣም እና በተሻሻሉ የምርምር ችሎታዎች በመጠቀም ትርፋማነቱን እንዳሳደገ ተናግረዋል።

Condoaddis.com
ዓባይ ባንክ ከወለድ ነፃ አገልግሎት ከ 3 ቢሊዮን ብር በላይ ማግኘት መቻሉን አስታውቋል

በ2016 ሂሳብ ዓመት 8 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘት መቻሉን የገለፀው ዓባይ ባንክ ከወለድ ነፃ አገልግሎት ዘርፍ 3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር እንዳገኘም አመልክቷል።

ዓመታዊ ሪፖርቱን ከሰሞኑ ያቀረበዉ ባንኩ ተቀማጭ ገንዘቡን 52 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ማድረሱንም አስታዉቋል።

ዓባይ ባንክ አጠቃላይ የሃብት መጠኑ 66 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር እንደደረሰ እና የደንበኞቹን ቁጥርም 3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ማድረስ እንደቻለም ገልጿል።

ዓባይ ባንክ በሀገር አቀፍ ደረጃ 548 ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን፤ ከዘጠኝ ሺህ በላይ ቋሚና ጊዜያዊ ሰራተኞችን በስሩ ይዞ እንደሚገኝ ለካፒታል በላከው ሪፖርት መረዳት ተችሏል።

የባንኩ 15ኛው የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደተገለጸው በሂሳብ አመቱ ከግብር በፊት 1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን እና የዲጂታል ግብይቶች ደግሞ ከጠቅላላው ግብይቶች 54% እንደሚሸፍኑ አስታውቋል።

Source: capitalethiopia
@ETstocks
በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ስነ-ምህዳርን ለማሳደግ ወሳኝ እርምጃ መሆኑ የተነገረለት መመሪያ ተግባራዊ መደረጉን ባለስልጣኑ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ሲጠበቅ የነበረዉን መመሪያ መፅደቁን ያስታወቀ ሲሆን ይህም የባለስልጣኑን የተወሰኑትን ስልጣን እና ኃላፊነት በዉክልና ለመስጠት እንደሚያስችለዉ ተገልጿል ።

"ራሳቸውን በራሳቸው የሚቆጣጠሩ ድርጅቶች እዉቅና አሰጣጥ እና ቁጥጥር" የተሰኘዉ መመሪያ ቁጥር 1031/2017 ከባለስጣኑ  ኃላፊነቶቹ ውስጥ እንዳስፈላጊነቱ የተወሰኑትን ስልጣን እና ሀላፊነትን በውክልና እውቅና ለሚሰጠው ራሱን በራሱ ለሚቆጣጠር ድርጅት የሚያስተላልፍበትን ስርዐት እንደሆነም ተነግሯል ።

በካፒታል ገበያ አዋጅ 1248/2021 መሠረት ይህን ራሳቸውን በራሳቸው የሚቆጣጠሩ ድርጅቶች እውቅና አሰጣጥ መመሪያ በፍትህ ሚኒስቴር መፅደቁን እና 1031/2017 ሆኖ መመዝገቡን ባለስልጣኑ አስታዉቋል ።

ይህ ምእራፍ በኢትዮጵያ በሚገባ የተስተካከለ የካፒታል ገበያ ስነ-ምህዳርን ለማሳደግ ወሳኝ እርምጃ መሆኑ የተሰማ ሲሆን ይህ አዲሱ መመሪያ ፍትሃዊ ውድድርን በማጎልበት እና የባለስልጣኑን የቁጥጥር ሀላፊነት ጫና በመቀነስ ረገድ ጠቃሚ ሚና እንደሚጫወቱ ለመረዳት ተችሏል።

Source: capitalethiopia
@Etstocks
IMF ለኢትዮጵያ የ251 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሊያፀድቅ ነው!!

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በመተግበሯ እያስመዘገበች ያለችውን እድገት በማድነቅ የ251 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሊፈቅድ መሆኑን ፎርቹን ዘግቧል።

IMF ለኢትዮጵያ በአራት አመታት ውስጥ በተራዘመ ብድር ለመስጠት ከፈቀደው የ3.4 ቢሊየን ዶላር ውስጥ ሁለተኛውን የ251 ሚሊየን ዶላር ብድር ለመልቀቅ መስማማቱ ተሰምቷል።

በኢትዮጵያ የ IMF ልዑክ መሪ አልቫሮ ፒሪስ “የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም በጥሩ ሁኔታ መሄዱን ቀጥሏል” ብለዋል።

ወደ ወለድ መር የገንዘብ ፖሊሲ በሚደረግ ሽግግር ወቅት የዋጋ ግሽበትን ዝቅተኛ ለማድረግ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲዎች መተግበርን መክረዋል።

በባንክ እና በጥቁር ገበያው መካከል ያለውን የምንዛሪ ተመን ልዩነት ከ10 በመቶ በታች መውረዱ እና የውጭ ምንዛሬ እጥረት መቀነሱ እንደ ስኬት ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እስካሁን ሙሉ በሙሉ ሥራ ላይ ባያውለውም የፋይናንስ ሥርዓት ውህደትንና የሒሳብ አያያዝን ለማሻሻል የአገር ውስጥ ባንኮች የገንዘብ ግብይትን ማስጀመሩ ይታወሳል።

የIMF ስራ አስፈፃሚ ቦርድ ሁለተኛውን ግምገማ ሲያጠናቅቅ ብድር በሚቀጥሉት ሳምንታት እንደሚለቀቅ ተጠቅሷል።
https://www.condoaddis.com/20241128-1
🚨 Special Edition Webinar Alert! 🚨

Dive into the future of broker technology with Brokerage 104 – Special Edition, happening virtually on November 29, 2024, from 9:00 AM to 11:00 AM. 💻

Highlights:
✔️ Exclusive demo of the Broker Back Office System
✔️ Lessons and best practices to empower brokers
✔️ Engaging Q&A session

📢 This is an invitation-only webinar!

Participants will be selected from those who register. Don’t miss your chance to secure a spot—register NOW using the link below!

Register Here- https://forms.office.com/Pages/DesignPageV2.aspx?subpage=design&FormId=knfrikdTVkKLp6Azyr6Mhp2MAH1y0ypJmxTeOr5sbptUQTJCQVRZSlFEWExRUjBVTzhPWUdENTQ1OC4u&Token=4b44e494e3c8473296b15230995ca1d9

Hurry, limited slots available! 🕒
ሕብረት ባንክ 3.08 ቢሊየን ብር ትርፍ አገኘ!!

ሕብረት ባንክ 27ኛ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት አጠቃላይ ተቀማጭ የገንዘብ መጠኑ 74.65 ቢሊየን ብር መድረሱን ገልጿል።

ካለፈው አመት ከነበረው መጠን ጋር ሲነፃፀር የ10.11 ቢሊየን ብር ጭማሪ አሳይቷል ብሏል።

ባንኩ ከግብር በፊት 3.08 ቢሊየን ብር ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን ካለፈው አመት የ22.5 ሚሊየን ብር ጭማሪ መኖሩን አስታውቋል።

ከወለድ ነፃ ፋይናንስን ጨምሮ የባንኩ አጠቃላይ የብድር መጠን 68.89 ቢሊየን ብር ደርሷል።

ብሔራዊ ባንክ ለንግድ ባንኮች የሚሰጠው የአስቸኳይ ጊዜ ብድር የወለድ ምጣኔ ከፍ ማለት እና የልማት ባንክ ቦንድ ግዢ ግዴታ መሆን ካጋጠማቸው ችግሮች መሀል መሆናቸው ተጠቅሷል።

Website| https://www.condoaddis.com/category/etstocks
Facebook| https://www.fb.me/etstocks
LinkedIn| https://www.linkedin.com/company/etstocks
|X| https://www.x.com/@etstocks1
TikTok| https://www.tiktok.com/@etstocks
YouTube| https://www.youtube.com/@etstocks