ET Securities
649 subscribers
572 photos
7 videos
26 files
287 links
At Et securities our aim is in creating condusive space concerning capital markets and financial markets so as to enable learning and awareness creation to the society.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
አቢሲኒያ ባንክ በተጠናቀቀው በጀት አመት 4.23 ቢሊዮን የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ገለፀ!!

የአቢሲኒያ ባንክ አጠቃላይ የተቀማጭ የገንዘብ መጠኑ ከ158.54 ቢሊዮን ብር ወደ 192.51 ቢሊዮን መድረሱንም አስታውቋል፡፡

ይህም ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የ21.43 በመቶ ወይም የ33 ቢሊዮን ብር እድገት ያሳየ ነው፡፡

ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት አመት 4.23 ቢሊዮን የተጣራ ትርፍ ሲያገኝ ጠቅላላ ገቢው ደግሞ 27.75 ቢሊዮን መድረሱ ተገልጿል፡፡

የባንኩን ብድር እና ቅድመ ክፍያዎች መጠን ከወለድ ነፃ የተሰጡን ብድሮችን አካቶ 167.74 ቢሊዮን መድረሱ ተነግሯል፡፡

በ2016 በጀት አመት የተገኘው የውጭ ምንዛሬ መጠን 424 ሚሊዮን ዶላር መሆኑ ተገልጿል፡፡

@Etstocks
"የግል ባንኮች ከ518 ሚሊዮን ዶላር እዳ ነፃ ሆነዋል!!''
ብሔራዊ ባንክ

የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያው የውጭ ምንዛሬ ግኝትን እያሳደገ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ተናግረዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ዘመናዊ የገንዘብ ፖሊሲ ለመተግበር፣ ጤናማ የፋይናንስ ሥርዓት ለመፍጠር፣ እና የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያ እንዲመራ ለማስቻል ነው የተተገበረው ብለዋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዥው የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ግኝት ከኤክስፖርት በወር በአማካኝ 500 ሚሊዮን ዶላር መድረሱን ገልጸዋል። 

በዚህም የብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ከሪፎርሙ በፊት ከነበረበት 1.4 ቢሊየን ዶላር ወደ 3.4 ቢሊዮን ዶላር አድጓል።

ባንኮች የሚገዙትና የሚያቀርቡት የውጭ ምንዛሬ በየቀኑ እየጨመረ መሆኑንም ተናግረዋል።

የግል ባንኮች የውጭ ምንዛሬ ሀብት ተሻሽሎ ከነበረባቸው 518 ሚሊዮን ዶላር እዳ ነፃ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው ላኪዎች ያመነጩትን የውጭ ምንዛሬ 50 በመቶ ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውን 50 በመቶ ላልተወሰነ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለ አካውንታቸው ማስቀመጥ እንዲችሉ መፈቀዱንም አስታውቀዋል፡፡

Condoaddis.com/category/etstocks
The launch of Ethiopia’s first interbank market trading platform on ESX marks a historic milestone

The launch of Ethiopia’s first interbank market trading platform on the Ethiopian Securities Exchange (ESX) marks a historic achievement as it becomes one of the few African exchanges to introduce interbank trading, setting a new standard for short term money markets on the continent. With dual regulatory oversight from the National Bank of Ethiopia (NBE) and the Ethiopian Capital Market Authority (ECMA), the ESX is proud to host a modern and flexible trading platform that promotes efficient price discovery, better transparency, and enhances liquidity in the Ethiopian banking sector. This enables a more stable, resilient, and adaptable financial sector, one that’s better equipped to support the nation’s long-term growth ambitions.

Read More
https://tinyurl.com/yz9e849z

Source: capitalethiopia
@Etstocks
🌟🇪🇹 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ 7ቱ ምርጥ የግል ባንኮች ጋር ሲነጻጸር

የኢትዮጵያ ባንኮች የፋይናንስ አፈጻጸም እና ቁልፍ መለኪያዎች ፈጣን እይታ።

ሁሉም መረጃዎች የየራሳቸው ባንክ የእ.ኤ.አ 2022-23 አመታዊ ሪፖርቶች የተገኙ ናቸው።

💡 አሁን ኢንቨስት ማድረግ ጀምሩ!
የግል ባንኮች ፈጣን እድገት እና ትርፋማነት እያሳዩ ነው, ይህም ለባለሀብቶች አስደሳች እድሎችን ያቀርባል።

ምንጭ_ Ethio Aksion
@etstocks
የታክስ ቅሬታ ማመልከቻ ይዘት

በታክስ ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያለው ታክስ ከፋይ ቅሬታውን ሲያቀርብ የሚከተሉትን ያሟላ መሆን አለበት:-

1. ታክስ ከፋዩ የሚያቀርበው የቅሬታ ማስታወቂያ የቅሬታውን ፍሬ ነገር ምክንያቶች መያዝ አለበት፤

2. በዚህ ተራ ቁጥር | የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ቅሬታ አቅራቢው:-

👉 የቅሬታ አቅራቢውን ስም፣ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር እና አድርሻ፣

👉 ቅሬታ የቀረበበትን የታክስ ውሳኔ ይዘት፣

👉 ውሳኔው የተሰጠበትን ቀን፣

👉 ውሳኔ የሰጠውን ቅ/ጽ/ቤት እና

👉 ሌሎች ለውሳኔ የሚረዱ ፍሬ ነገሮችና ማስረጃዎችን መግለጽ አለበት፡፡

3. ቅሬታ አቅራቢው የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የምስክር ወረቀት፣ እንዲሁም ጉዳዩ በታክስ ወኪሉ የሚቀርብ ከሆነ ለወኪሉ ቅሬታ አቅራቢው ውክልና የሰጠበት ማስረጃ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ ከሆነ የምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ አለበት፤

4. የቀረበውን ቅሬታ የሚያስረዳ አግባብ ያላቸው ሌሎች ኮፒ የሰነድ ማስረጃዎች ከዋናው ጋር እንዲገናዘቡ ከቅሬታ ማመልከቻው ጋር በአባሪነት ማቅረብ ይኖርበታል::

5. የታክስ ውሳኔ ቅሬታ አቅራቢው የሚያቀርበው ቅሬታ ባልተስማማበት የታክስ ስሌት ማስታወቂያ ላይ እንጅ በተስማማበት የታክስ ስሌት ላይ ስላልሆነ በታመነበት ላይ መከፈል ካለበት ሊከፈል ይገባል፡፡
***


ምንጭ፥ የገቢዎች ሚኒስቴር ገፅ🙏🏾
#Addis International Bank SC#

▪️Job Position 1 - HR ClerkJob Position 2 - Store Clerk
▪️Job Position 3 - Storekeeper
▪️Job Position 4 - Legal Aide
▪️Job Position 5 - Junior Construction and Design Officer
▪️Job Position 6 - Procurement Officer
▪️Job Position 7 - Programmer/System Analyst
▪️Job Position 8 - Hardware Engineer
▪️Job Position 9 - Digital Banking Technology Support Officer
▪️Job Position 10 - Attorney
▪️Job Position 11 - Senior MIS Officer
▪️Job Position 12 - Construction and Design Officer
▪️Job Position 13 - Senior Construction and Design Officer
▪️Job Position 14 - Branch Manager I
▪️Job Position 15 - Manager, Construction and Design Division
▪️Find More Details here
          💧💧💧💧💧

https://kebenajobs.com/job/addis-international-bank-sc-nov-18-24/

Deadline: November 22/ 2024
Ethiopia Looks to U.S. Regulators for Insights Ahead of Stock Exchange Launch

As the Ethiopian Capital Markets Authority (ECMA) polishes the regulatory landscape in anticipation of the country’s maiden stock exchange, it has tapped support from regulators overseeing the biggest financial market in the world.

Read More

Source: shegamedia
@Etstocks
የአፍሪካ ሀገራት ከዓለም ባንክ ያግኙት ብድር

🇪🇹 ኢትዮጵያን እንመልከት

https://youtube.com/shorts/LnKQ1-n4Nsc?si=HkNzRxmi9FaffvCf
ብሔራዊ ባንክ " የባንክ ኢንዱስትሪውን" ነፃ ከማድረጉ በፊት አሰራሩን ወደ ላቀ ደረጃ ያሻግራሉ የተባሉ አደረጃጀቶች ሊያደረግ ነዉ
የፋይናንስ ዘርፉ ለውጭ ተዋንያን ቢከፈትም ቁጥጥር ማድረጌን እቀጥላለው ሲል ማእከላዊ ባንኩ ገልጿል።
የፋይናንስ ስርዓቱ ወደ ሊበራላይዜሽን እየተሸጋገረ ባለበት ወቅት መረጋጋትን ለማረጋገጥ በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ አዲሱን ማቋቋሚያ አዋጅ ይቀበላል ተብሎ የሚጠበቀው ብሔራዊ ባንክ አዳዲስ ክፍሎችን በማቋቋም ተቋማዊ ማሻሻያ እንደሚያደርግ አስታዉቋል።
የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ
በቅርቡ በፓርላማ ቀርበው የባንክ ኢንዱስትሪውን ነፃ ለማድረግና የብሔራዊ ባንክን አሠራር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በጉጉት የሚጠበቁትን ሁለት አዋጆችን ማንሳታቸው ታዉቋል።
ተቆጣጣሪ አካሉ ኢኮኖሚውን በዘመናዊ አሰራር ለመንዳት አካሄዱን በአዲስ መልክ እንደሚያደራጅና ይህም በብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ በተደረጉ ለውጦች የተመቻቸ መሆኑን ገልጸዋል።
በሚቀጥሉት ሳምንታት ይፀድቃል ተብሎ በሚጠበቀው ረቂቅ አዋጅ መሰረት ማዕከላዊ ባንክ አዲስ ኮሚቴ ያቋቁማል። የህዝብ አስተያየትን ባካተተው የሁለት ቀናት ስብሰባ ላይ አቶ ማሞ አዲሱ አዋጅ ሰባት አባላት ያሉት የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ እንዴት እንደሚፈጥር አብራርተዋል። ይህ ኮሚቴ ለቦርዱ ይሁንታ የገንዘብ ፖሊሲን የማውጣት እና የመምከር ሃላፊነት አለበት።
በገዥው የውሳኔ ሃሳብ፣ የብሔራዊ ባንክ ቦርድ በገዥው እና በምክትል ገዥው የሚመራውን የገንዘብ ኮሚቴ እንዲቀላቀሉ በብሔራዊ ባንክ የተመረጡ ሁለት የውጭ ባለሙያዎችን ይሰይማል።
ኮሚቴው ቢያንስ በየሁለት ወሩ የሚሰበሰበው የብሄራዊ ባንክ ምጣኔን መወሰንን ጨምሮ የገንዘብ ፖሊሲዎችን ለሀገሪቷ እንደሚያቀርብ አቶ ማሞ አስረድተዋል። በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ምጣኔን 15 በመቶ አስቀምጧል።
ሌላው በአዲሱ አዋጅ የተቋቋመው አዲስ ክፍል የፋይናንስ መረጋጋት ኮሚቴ ነው። ይህ ኮሚቴ ለቦርዱ የውሳኔ አሰጣጥ ማክሮ እና ማይክሮ ፕራክቲካል ፖሊሲዎችን ያቀርባል እና በየወሩ በሚያደርጋቸው ስብሰባዎች የፋይናንስ ስርዓቱን በየጊዜው ይገመግማል፣ ይተነትናል እና የስርዓት ስጋቶችን ይለያል።
ቦርዱ የመጨረሻ አማራጭ አበዳሪን እና ሌሎች የችግር ጊዜ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎችን በተመለከተ ከኮሚቴው በሚሰጠው ጥቆማ መሰረት ለብሔራዊ ባንክ የሚቀርቡ ፖሊሲዎችን በተመለከተ ውሳኔ ተብሏል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢንቨስትመንት ባንክ ሊያቋቁም መሆኑ ታውቋል።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.condoaddis.com/20241121-1
የሚንስትሮች ምክር ቤት ተጨማሪ 581.9 ቢልዮን ብር በጀት በማፅደቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስተላልፏል::

ዛሬ በተደርገው የሚንስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ከዚህ በፊት ከፀደቀው 1 ትሪልዮን ብር በተጨማሪ 581.9 ቢሊዮን ብር አፅድቋል።

የተጨማሪ በጀት እና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያው የተሻሻለውን የ2017-2021 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊስካል ማዕቀፍ ማስፈጸም በሚያስችል መልኩ የመንግስት የፋይናንስ አቅምና ተጠባቂ ገቢዎችን ታሳቢ በማድረግ፣ የተጨማሪ በጀት ታሳቢዎችንና የወጭ ታሳቢዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት ተዘጋጅቷል ብሏል ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ በመግለጫው፡፡

ምክር ቤቱ በሌላ በኩል የሂሣብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ የተወያየ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ ብቁ እና ብዛት ያላቸውን ባለሙያዎች በማፍራት በመንግስት እና በግል ተቋማት የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀት እና አቀራረብ ሥርዓት በመዘርጋት ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ የሚኖረው ነው ተብሏል፡፡

ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብዓቶችን በማከል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

Website
LinkedIn | YouTube | X | Facebook | TikTok
Tilahun Kassahun, CEO of the Ethiopian Securities Exchange, underlined the essence of inclusivity in the market, envisioning listings from startups, SMEs, family-owned businesses, state-owned companies and financial institutions. He warned that without diversity, the Exchange could face stagnation and called for domestic banks to take on roles as investment banks and corporate issuers.

Read More

Source: addisfortune
@Etstocks