ET Securities
714 subscribers
650 photos
9 videos
34 files
353 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

www.Etsecurities.com

YouTube.com/@etstocks

Fb.me/etstocks
Download Telegram
November 11, 2024
ለመንግስት የልማት ድርጅቶች በሰጠውና ባልተመለሰለት ወደ 900 ቢሊዮን ብር የተጠጋ ብድር ምክንያት ሊፈርስ ነበር የተባለውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ለማትረፍ መንግስት እዳውን የሚመጥን የግምጃ ቤት ሰነድ ለሽያጭ ሊያቀርብ መሆኑ ታውቋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር የግምጃ ቤት ሰነዱን ለሚገዙት ተቋማት ገንዘቡን ከነወለዱ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡

ይህም ወጭውን ስለሚያንረው የበጀት ጉድለቱን እየለጠጠው እንደሚቀጥል የምጣኔ ሐብት ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

@Etstocks
November 14, 2024
የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያ ባለስልጣን በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን የሰነደ ሙዓለ ንዋይን ለህዝብ የማቅረብ እና የግብይት መመሪያ (IPOs)
ማፅደቁ ታውቋል። ይህም የተስተካከለ የሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያን ለመመስረት ትልቅ ርምጃ ነው።

ማንበብ ይቀጥሉ
Https://www.condoaddis.com/category/etstocks
November 14, 2024
November 14, 2024
November 14, 2024
November 14, 2024
November 15, 2024
November 15, 2024
November 17, 2024
የታክስ ቅሬታ ማመልከቻ ይዘት

በታክስ ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያለው ታክስ ከፋይ ቅሬታውን ሲያቀርብ የሚከተሉትን ያሟላ መሆን አለበት:-

1. ታክስ ከፋዩ የሚያቀርበው የቅሬታ ማስታወቂያ የቅሬታውን ፍሬ ነገር ምክንያቶች መያዝ አለበት፤

2. በዚህ ተራ ቁጥር | የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ቅሬታ አቅራቢው:-

👉 የቅሬታ አቅራቢውን ስም፣ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር እና አድርሻ፣

👉 ቅሬታ የቀረበበትን የታክስ ውሳኔ ይዘት፣

👉 ውሳኔው የተሰጠበትን ቀን፣

👉 ውሳኔ የሰጠውን ቅ/ጽ/ቤት እና

👉 ሌሎች ለውሳኔ የሚረዱ ፍሬ ነገሮችና ማስረጃዎችን መግለጽ አለበት፡፡

3. ቅሬታ አቅራቢው የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የምስክር ወረቀት፣ እንዲሁም ጉዳዩ በታክስ ወኪሉ የሚቀርብ ከሆነ ለወኪሉ ቅሬታ አቅራቢው ውክልና የሰጠበት ማስረጃ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ ከሆነ የምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ አለበት፤

4. የቀረበውን ቅሬታ የሚያስረዳ አግባብ ያላቸው ሌሎች ኮፒ የሰነድ ማስረጃዎች ከዋናው ጋር እንዲገናዘቡ ከቅሬታ ማመልከቻው ጋር በአባሪነት ማቅረብ ይኖርበታል::

5. የታክስ ውሳኔ ቅሬታ አቅራቢው የሚያቀርበው ቅሬታ ባልተስማማበት የታክስ ስሌት ማስታወቂያ ላይ እንጅ በተስማማበት የታክስ ስሌት ላይ ስላልሆነ በታመነበት ላይ መከፈል ካለበት ሊከፈል ይገባል፡፡
***


ምንጭ፥ የገቢዎች ሚኒስቴር ገፅ🙏🏾
November 18, 2024
November 19, 2024
November 19, 2024
November 20, 2024
November 20, 2024
ብሔራዊ ባንክ " የባንክ ኢንዱስትሪውን" ነፃ ከማድረጉ በፊት አሰራሩን ወደ ላቀ ደረጃ ያሻግራሉ የተባሉ አደረጃጀቶች ሊያደረግ ነዉ
የፋይናንስ ዘርፉ ለውጭ ተዋንያን ቢከፈትም ቁጥጥር ማድረጌን እቀጥላለው ሲል ማእከላዊ ባንኩ ገልጿል።
የፋይናንስ ስርዓቱ ወደ ሊበራላይዜሽን እየተሸጋገረ ባለበት ወቅት መረጋጋትን ለማረጋገጥ በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ አዲሱን ማቋቋሚያ አዋጅ ይቀበላል ተብሎ የሚጠበቀው ብሔራዊ ባንክ አዳዲስ ክፍሎችን በማቋቋም ተቋማዊ ማሻሻያ እንደሚያደርግ አስታዉቋል።
የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ
በቅርቡ በፓርላማ ቀርበው የባንክ ኢንዱስትሪውን ነፃ ለማድረግና የብሔራዊ ባንክን አሠራር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በጉጉት የሚጠበቁትን ሁለት አዋጆችን ማንሳታቸው ታዉቋል።
ተቆጣጣሪ አካሉ ኢኮኖሚውን በዘመናዊ አሰራር ለመንዳት አካሄዱን በአዲስ መልክ እንደሚያደራጅና ይህም በብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ በተደረጉ ለውጦች የተመቻቸ መሆኑን ገልጸዋል።
በሚቀጥሉት ሳምንታት ይፀድቃል ተብሎ በሚጠበቀው ረቂቅ አዋጅ መሰረት ማዕከላዊ ባንክ አዲስ ኮሚቴ ያቋቁማል። የህዝብ አስተያየትን ባካተተው የሁለት ቀናት ስብሰባ ላይ አቶ ማሞ አዲሱ አዋጅ ሰባት አባላት ያሉት የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ እንዴት እንደሚፈጥር አብራርተዋል። ይህ ኮሚቴ ለቦርዱ ይሁንታ የገንዘብ ፖሊሲን የማውጣት እና የመምከር ሃላፊነት አለበት።
በገዥው የውሳኔ ሃሳብ፣ የብሔራዊ ባንክ ቦርድ በገዥው እና በምክትል ገዥው የሚመራውን የገንዘብ ኮሚቴ እንዲቀላቀሉ በብሔራዊ ባንክ የተመረጡ ሁለት የውጭ ባለሙያዎችን ይሰይማል።
ኮሚቴው ቢያንስ በየሁለት ወሩ የሚሰበሰበው የብሄራዊ ባንክ ምጣኔን መወሰንን ጨምሮ የገንዘብ ፖሊሲዎችን ለሀገሪቷ እንደሚያቀርብ አቶ ማሞ አስረድተዋል። በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ምጣኔን 15 በመቶ አስቀምጧል።
ሌላው በአዲሱ አዋጅ የተቋቋመው አዲስ ክፍል የፋይናንስ መረጋጋት ኮሚቴ ነው። ይህ ኮሚቴ ለቦርዱ የውሳኔ አሰጣጥ ማክሮ እና ማይክሮ ፕራክቲካል ፖሊሲዎችን ያቀርባል እና በየወሩ በሚያደርጋቸው ስብሰባዎች የፋይናንስ ስርዓቱን በየጊዜው ይገመግማል፣ ይተነትናል እና የስርዓት ስጋቶችን ይለያል።
ቦርዱ የመጨረሻ አማራጭ አበዳሪን እና ሌሎች የችግር ጊዜ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎችን በተመለከተ ከኮሚቴው በሚሰጠው ጥቆማ መሰረት ለብሔራዊ ባንክ የሚቀርቡ ፖሊሲዎችን በተመለከተ ውሳኔ ተብሏል።
November 20, 2024
November 21, 2024