የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ስለሚፈቅደው የፖሊሲ ውሳኔ የዘርፉ ባለሙያዎች ምን አሉ?
#ሪፖርተር በዳዊት ታዬ
September 7, 2022
"የአገር ውስጥ ባንኮች ጠንካራ ካፒታል ከፈጠሩና ራሳቸውን ከጊዜው ጋር ሊያራምድ ወደሚችል ውሳኔ ከደረሱ ምንም ተፅዕኖ እንደማይገጥማቸው፣ ሰፊ ገበያ ያለበት አገር በመሆኑ እንደማይቸገሩ ገልጸዋል።........"
+++++++++++++++++++
ኢትዮጵያ ከ20 ዓመታት በላይ በተለያየ መንገድ አስተያየት ሲሰጥበት የቆየውና ከዛሬ ነገ ዕውን ይሆናል እየተባለ ሲጠበቅ የነበረው የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ እንዲገቡ የሚፈቅደው የፖሊሲ ውሳኔ በመንግሥት ተወስኗል፡፡ ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም. በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ያረፈበት የውጭ የፋይናንስ ተቋማት እንዲገቡ መፈቀድ ታሪካዊ የሚባል እንደሆነም እየገለጸ ነው፡፡
ይህ ውሳኔ የውጭ ባንኮች ከግማሽ ምዕተ ዓመት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ዳግም እንዲገቡና የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት እንደሚሆን መንግስት በይፋ የገለጸበት የፖሊሲ ሰነድ ነው፡፡
የውጭ የፋይናንስ ተቋማት ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ የፖሊሲ ውሳኔ መተላለፉ ታሪካዊ የሚባል መሆኑን ከገለጹት የኢኮኖሚ ባለሙያዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ አሰግድ ገብረመድን የፖሊሲ ውሳኔው ከታሪካዊነቱ ባሻገር ወቅቱን የጠበቀ ስለመሆኑም ያመለክታሉ፡፡
የውጭ የፋይናንስ ተቋማት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡበት መንገድ ምንም ይሁን ምን በኢትዮጵያ በፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ አዲስና ጠቃሚ የሚባል አሠራር የሚፈጥር መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው የሚገልጹት አቶ አሰግድ በፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ በርካታ ሥር ነቀል ለውጦች የሚፈጥር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
አቶ አሰግድ የሚኒስሮች ምክር ቤት የፋይናንስ ዘርፉ ክፍት እንዲሆን መወሰኑ ለአገሪቱ ቀጣይ ዕድገት አስፈላጊ ነው ብለዋል። ውሳኔው ወቅቱን የጠበቀ ስለመሆኑና የኢንዱስትሪውን አሠራር አደረጃጀትና አጠቃላይ ይዘት የሚለውጥ እንደሚሆን የገለጹት የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር ምክትል ፕሬዚዳንትና የዳሸን ፕሬዚዳንት አቶ አስፋው ዓለሙ በበኩላቸው የኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት ራሳቸውን እንደ አዲስ የሚያደራጁበትና ውድድሩን ለመወጣት ምን ማድረግ እንዳለባቸው የሚተልሙበት ወሳኝ ሰዓት ላይ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡
በእርግጥም ይህ ውሳኔ ዝርዝር መረጃዎችን ያላመላከተ ቢሆንም ታሪካዊ ሊባል እንደሚችል የጠቀሱት አቶ አስፋው ለአገራዊ ኢኮኖሚው ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል፡፡ ዋናው ጉዳይ ግን እነዚህ የውጭ ባንኮች እንዴት ይገባሉ የሚለው ነገር በቶሎ መገለጽና መታወቅ ያለበት መሆኑን ነው፡፡ ይህ የመንግሥት ውሳኔ ዝርዝር መሰጃው ባይገለጽም እስከዛሬ ድረስ በቃል ሲነገር የነበረውን የፋይናንስ ዘርፉን ለውጭ ባንኮች ክፍት የማድረግ ፍላጎት መንግስት ለመጀመሪያ ጊዜ በፖሊሲ ደረጃ በይፋ ያሳወቀበትና ሁሉም ተዋንያኖች እንዲያውቁት መልዕክት የተላለፈበት ነው ብለዋል፡፡ ይህ የፖሊሲ ውሳኔ
የውጪ ባንኮች መግባት እርግጥ መሆኑንና እያንዳንዱ የአገር ውስጥ ባንክ የራሱን ዝግጅት ከወዲሁ በትኩረት እንዲሠራ ያደርጋል ብለዋል፡፡
የውጭ ባንኮች መግባት ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ትልቅ ኢኮኖሚ ይዛ እንድትወጣና ተፅዕኖ ፈጣሪነቷን ለማጉላት መንገድ የሚቀድ ነው ያሉት አቶ አሰግድ ፣ የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡበት መልክ የተገለጸ ባይሆንም የእነዚህ ተቋማት መግባት በእጅጉ ጠቃሚ እንደሆነ የምናሉ፡፡
የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ችግር ለመፍታት፣ በአነስተኛ ወለድ ብድር ለማግኘትና ከ50 እና 60 ዓመታት በላይ በተለምዶ ሲሠራበት የነበረው የባንክና የኢንሹራንስ አገልግሎት ዓለም አቀፍ ስታንዳርድን ይዞ እንዲሠራ ጭምር ይህ ውሳኔ ትልቅ ዕገዛ እንደሚያደርግም ገልጸዋል፡፡
ይህ ብቻ ሳይሆን የአገሪቱ የፋይናንስ ተቋማት በኢትዮጵያ ብቻ የታጠረውን አገልግሎታቸውን ድንበር ተሻግረው እንዲሠሩ ጭምር የሚያግዝ እንደሆነ አቶ አስፋውና አቶ አሰግድ የገለጹ ሲሆን ወደ ተግባር ለመግባት ግን አሁንም ተጨማሪ ሥራዎች የሚጠበቁ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡እነዚህ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡት መልክ ምን ይሁን ምን በሊያመጣ የሚችለው ተፅዕኖ እንደሌለ አቶ አሰግድ ይገልጻሉ። አቶ አስፋው ግን የውጭ ባንኮች አገባብ ደረጃ በደረጃ ቢሆን ይመረጣል የሚል ምልከታ አላቸው፡፡
ሙሉ በሙሉ ቢገቡም ብዙዎች እንደሚሉት ከአገር ውስጥ ባንኮች ጋር በመጣመር እንዲገቡ ቢፈቅድም ጠቀሜታው ለአገር ነው የሚል አስተያየታቸውን ያጎሉት አቶ አሰግድ የአገር ውስጥ ባንኮች ተወዳዳሪ ለመሆን ግን ከወዲሁ ሊዘጋጁባቸው ይገባል ሲሉ መክረዋል። ለአብነት ካነሱዋቸው መካከል በየትኛውም መንገድ የውጭ ባንኮች ቢገቡ ይዘውት የሚመጡት ካፒታል ከፍተኛ መጠን ያለው ስለሚሆን ይህንን የሚመጥን ካፒታል የአገር ውስጥ ባንኮች ማደራጀት ይኖርባቸዋል፡፡ ስለዚህ አሁን ያሉት ባንኮች በያዙት ካፒታል ተወዳዳሪ ሊሆኑ ስለማይችሉ ትልልቅ የሚባሉት ባንኮች ሁለት ሦስት ሆነው፣ እንዲሁም አነስተኛ ካፒታል ያላቸው ደግሞ አምስት ስድስት ሆነው መዋሃድ ሊጠይቃቸው እንደሚችል ያምናሉ፡፡ ይህንን ማድረግ ግድ የሚል መሆኑንም የሚገልጹት አቶ አሰግድ የአገር ውስጥ ባንኮች ወህደት በመፍጠር ጠንካራ የኢትዮጵያ ባንክ በመመሥረት ከውጪዎቹ ጋር መወዳደር ወይም ተጣምረው በመሥራት ከኢትዮጵያ ውጪ በመውጣት ተወዳዳሪ ባንክ መፍጠር የሚያስችላቸው ዕድል ለመፍጠር ጭምር የሚረዳቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አቶ አስፋው ግን የውጭ ባንኮች በአንድ ጊዜ ሙሉ በሙሉ እንዲገቡ የሚፈቀድ ከሆነ ተፅዕኖ ሊያመጣ እንደሚችል በመጥቀስ ፣ የውጭ ባንኮች ከአገር ውስጥ ባንኮች ጋር ተጣምረው እንዲሠሩ በማድረግ ውሳኔውን ማስጀመር ተገቢ እንደሆነ ያመለክታሉ፡፡
ነገር ግን ከመደበኛው ባንክ አገልግሎት ሌላ በአንድ ዘርፍ ላይ ያተኮሩ (ስፔሻላይዝድ በሆኑ) ለምሳሌ እንደ እርሻ፣ ኢንቨስትመንትና በመሳሰሉ ዘርፎች ባንኮችን እንዲያቋቁሙ ቢፈቀድ የበለጠ ጠቀሜታ እንዳለውም አቶ አስፋው ይናገራሉ፡፡
በሰሞናዊው የመንግሥት ውሳኔ በቀጥታ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፋይናንስ ተቋማት የውሳኔው ዝርዝር መረጃ ያልደረሳቸው ሲሆን ውሳኔው ግን በተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የለተያዩ አስተያየቶች እየተሰጡበት ይገኛል፡፡
መንግሥት ገንዘብ ስለቸገረው የወሰነው ውሳኔ ነው የሚሉ ያሉትን ጨምሮ ፣ ውሳኔው ተገቢ ቢሆንም ፈጠነ የሚሉ ትችቶችም እየቀረቡበት ነው፡፡ አቶ አሰግድ እንዲህ ያለውን አስተያየት አይቀበሉም፡፡ እንደውም የዘገየ ውሳኔ ነው ብለው ያምናሉ፡፡ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ አሁን ያለውን ችግር ለመፍታት ከተፈለገ ከዚህ ዕርምጃ ሌላ ሊወሰድ የሚችል የተሻለ ውሳኔ ያለመኖሩን ያሰምሩበታል፡፡ ስለአገር መበልፀግና ዕድገት ከታሰበ ከዚህ ውሳኔ በተፃራሪ መቆም ተገቢ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡
በዚህ ውሳኔ ዙሪያ የተለያዩ አመለካከት እንዳለ የጠቆሙት አቶ አስፋው ደግሞ ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቅሱት አዲስ የሆነ አሠራር የሚፈጠር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሚፈጠር ብዥታ በመኖሩ ነው ይላሉ፡፡ ሁሌም ወደ አዲስ አሠራር በሚገባበት ጊዜ እንዲህ ያለ ግርታ ይፈጠራል፡፡
www.facebook.com/Etstocks

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
የተወሰነ ድርሻቸውን ለሕዝብ የሚሸጡ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተለዩ!
*
#ሪፖርተር
»ባህር ትራንስፖርትና የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በድርሻ ሽያጩ ተካተዋል።
በሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ላይ የተወሰ ድርሻቸውን ለሕዝብ የሚሸጡ ስድስት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች መለየታቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ (Ethiopian Investment Holdings – EIH) ኃላፊዎች ገለጹ፡፡
በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያን መጀመር አስመልክቶ የተወሰኑ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች (State Owned Enterprises) ውስን ድርሻዎቻቸውን በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ላይ እንደሚሸጡ ሲገለጽ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
ከቅርብ ጊዜያት በፊት ይፋ እንደሆነውም መንግሥት የኢትዮ ቴሌኮምን አሥር በመቶ ድርሻ ለሕዝብ እንደሚሸጥ ገልጾ ነበር፡፡ ምን ያህል መጠናቸው እንደሆነ ውሳኔ ላይ ባይደረስም ሌሎች አምስት የልማት ድርጅቶች ድርሻዎቻቸው በገበያው ላይ እንዲሸጡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ መወሰኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ አብዱረህማን ዒድ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ድርሻቸው ለሽያጭ የሚቀርበው የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት (አባትሎአድ)፣ የኢትዮጵያ መድኅን ድርጅት፣ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት፣ የትምህርት ማምረቻና ማሠራጫ ድርጅትና የኢትዮጵያ የቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ሲሆኑ፣ አምስቱ ተጨማሪ የልማት ድርጅቶች፣ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን ስድስት ድርጅቶች ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ላይ ድርሻቸውን ይሸጣሉ፡፡
ከትምህርት ማምረቻና ማሠራጫ ድርጅትና ከኢትዮጵያ የቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ውጭ ያሉት አራቱ የልማት ድርጅቶች፣ በበላይ ከሚቆጣጠራቸው ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ጋር አምስት በመሆን የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያን (ESX) 25 በመቶ ድርሻ በመግዛት ገበያውን በዚህ ዓመት መስከረም ወር ላይ ማቋቋማቸው የሚታወስ ነው፡፡
እንደ አቶ አብዱረህማን ገለጻ፣ እነዚህን አራቱ ድርጅቶች የገበያውን አክሲዮን ገዝተው እንዲያቋቁሙ የተመረጡበት ምክንያትም በገበያው ላይ በኋላ ድርሻቸውን እንዲሸጡ በመወሰኑ ነው፡፡ በኋላ ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአራቱ የልማት ድርጅቶችና ከሆልዲንጉ ጋር በመግባት ስድስተኛ ተቋም ሆኖ የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይን 25 በመቶ ድርሻ በጋራ መግዛቱ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድርሻቸውን እንደ ኢትዮ ቴሌኮምና ሌሎቹ የልማት ድርጅቶች ለሕዝብ እንዲሸጥ አለመወሰኑን አቶ አብዱረህማን ተናግረዋል፡፡
‹‹የንግድ ባንክ አሁን አይሆንም፡፡ ምናልባት ወደፊት ከሆነ እንጂ አሁን አልተወሰነም፤›› ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ‹‹ኢትዮ ቴሌኮም በጣም ግዙፍ ድርጅት ነው፣ የእሱን ድርሻ በተወሰነ መጠን ከሸጥን የንግድ ባንክ አለመሸጥ ምንም አይደል፤›› ሲሉ አክለዋል፡፡
የኢትዮጵያ መድኅን ድርጅትም ግዙፍ መሆኑንና ከ50 በመቶ በላይ የመድኅን ገበያውን የሚቆጣጠር መሆኑን፣ ኢባትሎአድም በጣም ትልቅ ድርጅት እንደሆነ፣ እንዲሁም ብርሃንና ሰላም በአገሪቱ ትልቁ የኅትመት ድርጅት እንደሆነ ያስታወሱት አቶ አብዱረህማን፣ የእነዚህ ድርጅቶች በገበያው ላይ መቅረብ ትልቅ ነገር እንደሆነ ለሪፖርተር አብራርተዋል፡፡
ድርጅቶቹ ምን ያህል የድርሻ መጠናቸውን ለሕዝብ እንደሚያቀርቡ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ሥራ አስፈጻሚው፣ ‹‹የኢትዮ ቴሌኮም አሥር በመቶ እንደሆነ ይታወቃል፣ ነገር ግን ሌሎቹ ምን ያህል መጠናቸውን እንደሆነ የሚሸጡት ገና አልወሰንም፤›› ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ በውጭ አጋሮቹ ድጋፍ በቅርብ የድርጅቱን ዝግጁነት እያስጠና ሲሆን፣ በገበያው ላይ ለመሸጥ በጣም ጥብቅ የሆኑ መሟላት ያለባቸውን መሥፈርቶች ማሟላት ያለባቸው እንዳሉ ተገልጿል፡፡
የልማት ድርጅቶቹ በገበያው ለመቅረብ ምን መቀየር እንዳለባቸው ሐሳቡ ያላቸው መሆኑን፣ በዚህ ሳምንትም ጨምሮ በየጊዜው ጥልቅ ውይይት እንደሚያደርጉ አቶ አብዱረህማን ተናግረዋል፡፡
ሆልዲንጉ በካፒታል ገበያ ላይ ትኩረ አድርጎ የሚሠራ ልዩ ቡድን የሚያቋቁም ሲሆን፣ ቡድኑ የልማት ድርጅቶቹን ለገበያ ለማቅረብ እንዲዘጋጁ የሚያግዛቸው ይሆናል፡፡
#ESX #Stockmarket #ኢትዮጵያ #አክሲዮን

የንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኑ።
#ሪፖርተር
በቅርቡ ዋና ሥራ አስፈጻሚውን ያሰናበተው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩትን እመቤት መለሰ ዘለቀ (ዶ/ር)ን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ ሰየመ፡፡
ከንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመላክተው እመቤት (ዶ/ር) የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲያገለግሉ ለብሔራዊ ባንክ የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ ሹመቱ ፀድቆላቸዋል፡፡
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በሥራ አስፈጻሚነት የሚመራ የባንክ ባለሙያ ሲያፈላልግ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፣ ካወዳደራቸው ሦስት የባንክ ባለሙያዎች መካከል እመቤት (ዶ/ር)ን ሊመርጥ ችሏል፡፡
አዲሷ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እመቤት (ዶ/ር) በባንክ ኢንዱስትሪ ውሰጥ ከ22 ዓመታት በላይ ልምድ ያላቸው ሲሆን የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እስከ ተሰየሙበት ድረስ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እስትራቴጂክ ፕላኒንግ እና ትራንስፎርሜሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ሲያገለግሉ እንደ ነበር ታውቋል፡፡
www.condoaddis.com/etstocks

ንብ ባንክ አቶ ሔኖክ ከበደን ዋና ሥራ አስፈጻሚነት መረጠ።
****
#ሪፖርተር
የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ የቀድሞውን የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሔኖክ ከበደን፣ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ እንደገና መምረጡ ታወቀ፡፡
አቶ ሔኖክ የንብ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲያገለግሉ ከቦርዱ የቀረበላቸውን ጥያቄ በመቀበላቸው፣ የንብ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሹመቱ እንዲፀድቅለት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማመልከቱ ታውቋል፡፡
ንብ ባንክ ከስድስት ወራት በፊት አቶ ሔኖክን ለዋና ሥራ አስፈጻሚነት ዕጩ አድርጎ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም፣ በወቅቱ ብሔራዊ ባንክ ሹመቱን እንዳላፀደቀው ይታወሳል፡፡
ብሔራዊ ባንክ ሹመታቸውን ያላፀደቀው ከአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚነታቸው እንዲነሱ የተደረጉበት ምክንያት ሊጣራ ይገባል ተብሎ እንደነበር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ሆኖም አቶ ሔኖክ ከአማራ ባንክ የለቀቁበት ምክንያት አግባብ እንዳልነበር ከሥራ ሲሰናበቱ በአማራ ባንክ ቦርድ የተጻፈባቸው ደብዳቤ እሳቸውን የማይገልጽ መሆኑን በማመልከት ለብሔራዊ ባንክ ባቀረቡ አቤቱታ መሠረት፣ በአማራ ባንክ የተጻፈባቸውን ደብዳቤ መሠረት ያደረገው ዕግድ በብሔራዊ ባንክ ተነስቶላቸዋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ንብ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ መርጧቸዋል፡፡
ብሔራዊ ባንክም ከዚህ ቀደም ጥሎባቸው የነበረውን ዕገዳ በማንሳቱ እንደገና በዋና ሥራ አስፈጻሚነት እንዲያገለግሉ የቀረበውን ጥያቄ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የቀድሞዋ የንብ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እመቤት መለሰ (ዶ/ር) ከኃላፊነታቸው ከለቀቁ በኋላ፣ ባንኩ አቶ በላይ ጎርፉን በተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚነት መመደቡ ይታወሳል፡፡
የንብ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁት አቶ ሔኖክ በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከ20 ዓመታት በላይ ልምድ ያላቸው ናቸው፡፡ በትምህርት ዝግጅታቸውም ከእንግሊዝ ግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ በበዓለም አቀፍ ቢዝነስ የኤምቢኤ ዲግሪ ያላቸው ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም በማኔጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪ አላቸው፡፡
በሥራው ዓለምም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተለያዩ ኃላፊነቶች ከስድስት ዓመታት በላይ የሠሩ ሲሆን፣ የባንኩ የብራንች ኦፊሰር ሆነው አገልግለዋል፡፡ በተለይም ለሰባት ዓመታት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲስትሪክት ማኔጀር በመሆንም ሠርተዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከለቀቁ በኋላ ዳሸን ባንክን በመቀላቀል ከስድስት ዓመታት በላይ የባንኩ ቺፍ ባንኪንግ ኦፊሰር (ምክትል ፕሬዚዳንት) በመሆን ሠርተዋል፡፡ ከዳሸን ባንክ የለቀቁት የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲያገለግሉ የቀረበላቸውን ጥያቄ ተቀብለው ነበር፡፡
የአማራ ባንክ የመጀመሪያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆንም ለሁለት ዓመታት ካገለገሉ በኋላ፣ ከአማራ ባንክ ቦርድ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ኃላፊነታቸውን መልቀቃቸው አይዘነጋም፡፡ የንብ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እስከታጩበት ጊዜ ድረስም በአንድ የፋይናንስ ተቋም ውስጥ በከፍተኛ አማካሪነት እያገለገሉ ነበር፡፡