ET Securities
651 subscribers
572 photos
7 videos
26 files
287 links
At Et securities our aim is in creating condusive space concerning capital markets and financial markets so as to enable learning and awareness creation to the society.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
⭕️ LIVE

ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ባለቤትነት የተያዘው ኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻውን ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች በራሱን የቴሌብር መተግበሪያ በመጠቀም ለመሸጥ የሚያስችለውን ፈቃድ ማግኘቱን ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በይፋ ያበስራል።

ይህንን ዝግጅት Voice Chat በቀጥታ ይከታተሉ
https://t.me/tikvahethmagazine?livestream

@etstocks
#ኢትዮቴሌኮም : ዛሬ የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ ይፋ ሆኗል።

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በተካሄደ ሥነ-ስርዓት የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ ይፋ ተደርጓል።

የአክሲዮን ሽያጭ ጊዜው ከዛሬ ጥቅምት 6 ጀምሮ እስከ ታኅሣስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል፡፡

ዝርዝር መረጃ ፦

- በ2016 በወጣው የሂሳብ ሪፖርት የድርጅቱ ካፒታል ➡️ 100 ቢሊዮን ብር ነው።

- በዓለም አቀፍ የ3ተኛ ወገን የገበያ ተመን መሰረት ድርጅቱ የሚያወጣው ዋጋ ➡️ 300 ቢሊዮን ብር ነው።

- በመጀመሪያው ዙር መደበኛ የአክሲዮን ሽያጭ የቀረበው ➡️ 100 ሚሊዮን ብር ነው።

- የአንድ ሼር ዋጋ ➡️ 300 ብር ነው።

- 100 ሚሊዮን ሼር በ300 ብር ሲሸጥ ኢትዮ ቴሌኮም ከሼር ሽያጭ ➡️ 30 ቢሊዮን ብር ያገኛል።

- ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን  ➡️ 33 ሼር ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 9,900 ብር ይሆናል።

- ከፍተኛው መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 3,333 ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ ➡️999,900 ብር ይሆናል።

- መግዛት የሚቻለው ከዛሬ ጥቅምት 6 እስከ ታህሳስ 25 ድረስ ይሆናል።

- የሼር አባላቱ የሚታወቁት ➡️ ጥር 23/2017

- ሽያጩ በቴሌብር ብቻ የሚደረግ ይሆናል።

- ክፍያውን በ48 ሰዓት ውስጥ መክፈል ይቻላል።

- አንድ አክሲዮን ግዢ ሲፈጸም ከአክስዮኑ ዋጋ በተጨማሪ 1.5% የአገልግሎት ክፍያ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፍል ይሆናል።

- ከከፍተኛው የአክሲዮን መጠን በላይ መግዛት አይቻልም።

- ግብይቱ የሚካሄደው በኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው።

https://t.me/etstocks
➡️- ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን   33 ሼር ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 9,900 ብር ይሆናል።

➡️ ከፍተኛው መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 3,333 ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 999,900 ብር ይሆናል።

➡️መግዛት የሚቻለው ከዛሬ ጥቅምት 6 እስከ ታህሳስ 25 ድረስ ይሆናል።

የሼር አባላቱ የሚታወቁት ➡️ ጥር 23/2017

➡️ሽያጩ በቴሌብር ብቻ የሚደረግ ይሆናል።
💠ፕሮስፔክተስ ለባለሀብቶች ስለማቀርብ የሰነደ መዋለ ነዋይ መረጃ የሚሰጥ የጽሁፍ ሰነድ ነው።

ዓላማ
ፕሮስፔክተስ እንደ አክሲዮኖች፣ ቦንዶች ወይም የጋራ ፈንድ ላሉ ዋስትናዎች ለሚሰጡ ኩባንያዎች ዋና የሽያጭ መሣሪያ ነው።

ለባለሀብቶች የገንዘብ ነክ አደጋዎችን እና ዋስትናዎችን የሚገልጽ ይፋ ማድረጊያ ሰነድ ነው።
አንድ ሰው ከኢትዮ ቴሌኮም የገዛውን አክሲዮን ድርሻ ማዘዋወር፤ አትርፎ መሸጥ ፤ እንደ ማሲያዣ መጠቀም ቢፈልግ ይችላል ወይ ?

አትዮ ቴሌኮም አሁን የሚጀመረው የአክሲዮን ሺያጭ የመጀመሪያው ምዕራፍ እንደሆነ አስታውቋል።

በዚህ ምዕራፍ ዜጎች የአክሲዮን ድርሻ ብቻ መግዛት የሚችሉ ይሆናል።

ዜጎች ድርሻቸውን ማዘዋወር ፤ አትርፎ መሸጥ ፤ እንደ ማሲያዣ መጠቀም የሚችሉት ኢትዮ ቴሌኮም ሁለተኛ ምዕራፍ ብሎ ባስቀመጠው ሲሆን ይህም ገና በሂደት ላይ እንዳለ ተጠቅሷል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ቴሌኮም በ " listing " ሂደት ላይ እንደሚገኝ እና ይህም በአጭር ጊዜ እንደሚጠናቀቅ የጠቀሱ ሲሆን ይፋዊ ቀን ግን አልተቆረጠለትም።

የሁለተኛው ዙር አክሲዮን ሽያጭ ሲጀመር ደግሞ ዜጎች ድርሻ ማዘዋወር ፣ አትርፎ መሸጥ ፤ እንደ ማሲያዣ መጠቀም ያስችላቸዋል።

እንዴት ነው አክሲዮን የሚገዛው ?

በቴሌብር ላይ ነው መግዛት የሚቻለው። ቴሌብር ላይ ሲገቡ አክሲዎን ለመግዛት የሚል አማራጭ ይገናኛል (ልክ ላውንች ሲደረግ) በዛ አማካኝነት ነው መግዛት የሚቻለው። በዛ ዝርዝር መረጃ ይገኛል፤ የደብንበኝነት ውልን ስለሚኖር አንብቦ መቀጠል ይችላል ከተስማሙ።

(እስካሁን ድረስ ቴሌብር ላይ ይህ የአክሲዎችን ሽያጭ አማራጭ አልመጣም ልክ ሲመጣ እናሳውቃችኃለን)

ፎርሙን በ48 ሰዓት ውስጥ ማስተካከል  ይቻላል ፤ በተመሳሳይ ክፍያም በ48 ሰዓት ውስጥ መከፈል አለበት። ከ48 ሰዓት በኃላ ፎርሙን ማስተካከል አይቻልም።

ፎርሙን መጀመሪያ በመደበኛ መታወቂያ፣ መንጃ ፍቃድ ፣ ፓስፖርት መሙላት የሚቻል ሲሆን መጨረሻ ላይ የሼር ባለቤት ለመሆን የናሽናል አይዲ (ፋይዳ) ያስፈልጋል።

ሼር ገዢ ተመዝጋቢዎች ቁጥር ለሽያጭ ከቀረበው ሼር በላይ ከመጣ ከዛ ውስጥ እነማን የሼሩ ባለቤት ይሆናሉ የሚለውን ለመለየት የሚያስችል አሰራር ተቀምጧል። (በቀጣይ በዚህ ላይ መረጃ እናቀርባለን)

➡️ ሼር መግዛት ማመልከይ የሚችለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ እና እዚሁ ሀገር ውስጥ በአካል ያለ ነው።

2016 ዓ/ም በወጣ የሂሳብ ሪፖርት የድርጅቱ የካፒታል 100 ቢሊዮን ብር ሲሆን በዓለም አቀፍ የ3ተኛ ወገን የገበያ ተመን መሰረት ድርጅቱ የሚያወጣው ዋጋ 300 ቢሊዮን ብር ነው።

በመጀመሪያ ዙር መደበኛ የአክሲዮን ሽያጭ የቀረበው ደግሞ 100 ሚሊዮን ሼር ነው። የአንድ ሼር ዋጋም 300 ብር ነው። ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን  33 ሼር ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 9,900 ብር ይሆናል። ከፍተኛው መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 3,333 ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 999,900 ብር ይሆናል።
-tikvah
📣- በ2016 በወጣው የሂሳብ ሪፖርት የድርጅቱ ካፒታል 100 ቢሊዮን ብር ነው።

- በዓለም አቀፍ የ3ተኛ ወገን የገበያ ተመን መሰረት ድርጅቱ የሚያወጣው ዋጋ 300 ቢሊዮን ብር ነው።

- በመጀመሪያው ዙር መደበኛ የአክሲዮን ሽያጭ የቀረበው 100 ሚሊዮን ሼር ነው።

- የአንድ ሼር ዋጋ 300 ብር ነው።

- 100 ሚሊዮን ሼር በ300 ብር ሲሸጥ ኢትዮ ቴሌኮም ከሼር ሽያጭ 30 ቢሊዮን ብር ያገኛል።
Ethio Telecom Prospectus.pdf
14.5 MB
🔻Ethiotelecom prospectus document
As Ethio Telecom aims to raise 30 billion birr selling shares to the public, here are key figures from the operator’s recently released prospectus.

Source: shegamedia
@Etstocks
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከ5 ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ምርቶችን አገበያይቷል
***
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድማገኝ ነገራ እንደገለጹት፤ በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት አራት የግብርና ምርቶች ወደ ዘመናዊ የገበያ ስርአት እንዲገቡ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከአምስት ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ምርቶች ማገበያየቱን ገልጸዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከጸደይ ባንክ ጋር የክፍያ አጋርነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።

ስምምነቱም አርሶ አደሮችና ኤክስፖርተሮች በመጋዘን የሚኖራቸዉን ምርቶች በማስያዝ ብድር እንዲያገኙ የሚያስችላቸዉ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የግብርና ምርታና ምርታማነት ለማሳደግ ተጨማሪ የግብርና አይነቶች በብዙ አካባቢ እንዲመረቱ እንዲሁም ወደ ዘመናዊ ግብይት እንዲሸጋገሩ እየሰራ ይገኛል።

በመስከረም ሰይፉ

ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓም
@etstocks
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የንግድ ባንኮች የሚገጥማቸውን የጥሬ ገንዘብ እጥረት ለመፍታት አሻሽሎ ያወጣውን መመሪያ ይፋ አድርጓል።

መመሪያው ያስፈለገው፣ የጥሬ ገንዘብ እጥረት የሚገጥማቸው ንግድ ባንኮች ከብሄራዊ ባንክ ሲበደሩ ግልጽና ተጠያቂነት ያለው አሠራር በማስፈለጉ እንደኾነ ባንኩ ገልጧል። ከባንኩ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት የሚችሉት ባንኮች፣ ጊዜያዊ የሆነ የጥሬ ገንዘብ እጥረት የገጠማቸው፣ በቀጣይነት አስተማማኝ ካፒታል መያዝ የሚችሉ፣ ችግራቸውን ለመፍታት ኹሉንም አማራጮች አሟጠው ስለመጠቀማቸው የሚያስረዱ፣ የመጠባበቂያ እቅዳቸውን ተግባራዊ አድርገው ችግሩን መቅረፍ እንዳልቻሉ ማስረጃ የሚያቀርቡና ተቀባይነት ያለው የእዳ ማስመያዣ ያላቸው እንደኾኑ አስታውቋል።


[ዋዜማ]
Ethiopian Securities Exchange Signs MoU with Nairobi Securities Exchange and iCapital Africa Institute

Ethiopian Securities Exchange (ESX) has signed a Memorandum of Understanding (MoU) with the Nairobi Securities Exchange (NSE) and iCapital Africa Institute, aiming to accelerate the growth and integration of capital markets in Ethiopia and Kenya.

Source: 2merkato
@Etstocks
ሌላው በግምገማ ላይ የሚገኘው መመሪያ ስለ የራስ አስተዳደር ድርጅቶችን (SROs) ፈቃድ መስጠት እና መቆጣጠር ነው።  እንደ ESX እና CSD አቅራቢዎች ፈቃድ ያላቸው አካላት በካፒታል ገበያ ውስጥ አገልግሎት አቅራቢዎችን የመቆጣጠር ኃላፊነት እንደ SROs ይመደባሉ።  እነዚህ ድርጅቶች የገበያውን ታማኝነት በመጠበቅ እና የስርዓት አደጋዎችን በመቀነስ ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ
ምንጭ፡ addisfortune
@etstocks