ET Securities
694 subscribers
608 photos
7 videos
30 files
310 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የዉጪ ምንዛሪ ግኝትን ከፍ ማድረጉን አስታዉቋል

👉 በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሐዋላ የዉጪ ምንዛሪ ቢሮ ለሚከፍቱ ከሳምንታት በኃላ ፍቃድ መስጠት እንደሚጀመር ባንኩ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የዉጪ ምንዛሪ ግኝት ከፍ ማድረጉን አስታዉቋል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ ደቦ የተሰኘ የውጭ ምንዛሪ ግኝትን የሚያሻሽል ፕሮግራም ባንኩ ይፋ አድርጓል ።

የብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ እንደተናገሩት በህጋዊ መንገድ የሃዋላ የውጭ ምንዛሬ ቢሮ ለሚከፍቱ ግለሰቦች ( ተቋማት) ከሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት በኋላ ፈቃድ መስጠት ይጀምራል ብለዋል።

መንግስት በቅርቡ ተግባራዊ ያደረገዉ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ያበረታታ እና ዜጎችን ወደ ሕጋዊ መንገድ ያመጣ እንደሆነም ተነግሯል ።

በ2023 ከሬሚታንስ ከ653 ሚሊዮን ዶላር በላይ መገኘት መቻሉን የገለፀዉ ብሔራዊ ባንክ ይሄንን ግኝት ከፍ ለማድረግ የሚያስችል አዲስ የውጭ ምንዛሪ አሥተዳደር መመሪያ መዘጋጀቱን አስታዉቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሃዋላ የውጭ ምንዛሬ ሊያሳድግና የተሻሻለውን የማክሮ ኢኮኖሚ ተግባራዊነት ሊያረጋግጥ እንደሚችል የገለፀዉን የስድስት ወር ንቅናቄ ዛሬ በይፋ አስጀምሯል።

Source: capitalethiopia
@Etstocks
👍1
ሰነደ መዋዕለ ንዋይን ለሕዝብ ለማቅረብ የሚያስችል መመርያ ተዘጋጀ

ለአዳዲስ ሥራ ፈጣሪዎች የካፒታል ገበያ ቁጥጥር ማጣሪያ ማዕቀፍ መዘጋጀቱ ተገልጿል
ለካፒታል ገበያ ወደ ሥራ መግባት ትክክለኛና አስፈላጊ ነው የተባለ የሰነደ መዋዕለ ንዋይን ለሕዝብ ለማቅረብ የሚያስችል መመርያ ዝግጅት መጠናቀቁን፣ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን አስታወቀ።

የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን አዳዲስ የሥራ ፈጣሪዎች በሥራ ላይ ያሉትን የቁጥጥር ደንቦችና መመርያዎችን መከተል ሳይጠበቅባቸው፣ አገልግሎቶቻቸውን ለካፒታል ገበያ ማቅረብ የሚያስችል የቁጥጥር ማጣሪያ ማዕቀፍ ሐሙስ ነሐሴ 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ አድርጓል።

የካፒታል ገበያን ወደ ሥራ ለማስገባት ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ በርካታ የሕግ ማዕቀፎች ሲዘጋጁ መቆየታቸውን የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሪት ሀና ተኸልኩ ለሪፖርተር ገልጸዋል።

የካፒታል ገበያን ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ለማስገባትና የኩባንያዎችን መዋዕለ ንዋይ ለሕዝብ ማቅረብ እንዲቻል፣ ባለሥልጣኑ ሲያዘጋጀው የቆየው መመርያ መጠናቀቁን የገለጹት ወ/ሪት ሀና፣ ተግባራዊ ለማድረግም በፍትሕ ሚኒስቴር ማስመዝገብ ብቻ ነው የቀረው ብለዋል፡፡ ‹‹በዚህ መሀል ሰነደ መዋዕለ ንዋይን ለሕዝብ የሚያቀርቡ ድርጅቶች ሰነዶቻቸውን እንዲያዘጋጁ ለማድረግ እየሠራን ነው፤›› ሲሉም ጠቁመዋል።

የውጭ ባለሀብቶች ወደ አገር ውስጥ በመግባት የካፒታል ገበያው ውስጥ አክሲዮን መግዛት እንዲችሉ በቅርቡ የተደረገው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እንደሚፈቅድ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ፣ ነገር ግን የሰነድ መዋዕለ ንዋይን ለሕዝብ ለማቅረብ የሚያስችለው መመርያ ፀድቆ ወደ ሥራ ያልገባ በመሆኑ፣ የውጭ ባለሀብቶች ገብተው አክሲዮን እንዳልገዙ አስታውቀዋል። መመርያው ፀድቆ የካቲፓል ገበያው ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገባ፣ የውጭ ባለህብቶች ወደ አገር ውስጥ ገብተው ሼር የመግዛትም ሆነ የመሸጥ መብት እንዳላቸው ገልጸዋል።

‹‹በካፒታል ገበያ ሰዎች ከተሻሻጡ በኋላ አክሲዮኑን ከአንድ ሰው ገንዘቡን ደግሞ ከሌላ ሰው የሚያቀያይር ሥርዓት (Central Securities Depository) ያስፈልጋል፤›› ያሉ ዋና ዳይሬክተሯ፣ ይህንንም በብሔራዊ ባንክ ግዥ መካሄዱንና የሙከራ ሒደት ላይ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የልማት ድርጅት አዳዲስ የፋይናንስ ሙከራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሪት ዳግማዊት ሽፈራው በበኩላቸው፣ ባንኮች የሚሰጧቸው እንደ ብድር፣ ገንዘብ ማስቀመጥና ኢንሹራንስ ያሉ አገልግሎቶች ለሚሰጡ ባንኮች፣ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣቸው ሕጎችና መመርያዎች የሚተዳደሩ መሆናቸውን፣ በካፒታል ገበያ ውስጥ ያለ አገልግሎት ከሆነ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በሚያወጣቸው ሕጎች እንደሚተዳደሩ ገልጸዋል።

ሆኖም ኢንቨስትመንት ባንክ ሆነው በተለየ መንገድ የሚሠሩ ከሆነና አሁን ባለው የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አሰጣጥ የማይቻል ከሆነ ደግሞ፣ ባለሥልጣኑ ይፋ ባደረገው የካፒታል ገበያ ቁጥጥር ማጣሪያ ማዕቀፍ እንደሚታይ አስታውቀዋል።

በቁጥጥር ማጣሪያ ማዕቀፉ የሚቀርበው ጥያቄ ተቀባይነት ካገኘ በኋላ አገልግሎቱ የፈጠራ ይዘቱ እንደሚመረመር፣ እንዲሁም ለምን ዓይነት ገበያና ተጠቃሚዎች ይቀርባል የሚለው እንደሚጣራ ወ/ሪት ሀና ገልጸዋል። ይህን ሒደት ያለፈ አገልግሎትም ተግባራዊ ሲደረግ የሚፈጠረውን ሁኔታ ለመገንዘብ የሙከራ ጊዜ እንደሚዘጋጅ አመላክተዋል።

ፈጠራን ማበረታታት አንዱ የማዕቀፉ ዓላማ መሆኑና አዳዲስ የፋይናንስ የፈጠራ አገልግሎቶችና ምርቶች ሲመጡ፣ ባለሥልጣኑ እንዴት መቆጣጠር እንደሚችል የሚማርበትና የቁጥጥር አቋም የሚገነባበት እንደሆነም ገልጸዋል።

ሪፖርተር
@etstocks
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዮሀንስ አያሌው (ዶክተር) ስራቸውን ለቀዋል። በተጠባባቂነት/በጊዚያዊነት የባንኩ ምክትል ፕሬዝዳንት ጌታቸው ዋቄ  ሀለፊነቱን ተረክበዋል።

Source: theethiopianeconomistview
@Etstocks
2
Source:- Banks Ethiopia
@etstocks
ህብረት ኢንሹራንስ አዲስ ያሰራውን መለያም ይፋ አደረገ

ፕሬዝዳንቷ የ2024 የአፍሪካ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ምርጥ ዋና ስራ አስፈፃሚነትን አሸናፊ ሆነዋል።

ከቀዳሚዎቹ የመድን ሰጪ ተቋማት መካከል የሆነው ህብረት ኢንሹራንስ ኩባንያው ላለፉት 30 አመታት ሲገለገልበት የነበረውን መለያ (ብራንድ) ዘመኑን በዋጀ እና አለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መለያ መቀየሩን አስታውቋል፡፡

Read More

Source: capitalethiopia
@Etstocks
የአማራ ባንክን በተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈፃሚነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ጫንያሌዉ ደምሴ መልቀቂያ ደብዳቤ አስገቡ::

ላለፉት 9 ወራት የአማራ ባንክ በተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ጫንያሌዉ ደምሴ ሰኞ ዕለት የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን የካፒታል ምንጮች ተናግረዋል ።

አቶ ጫንያሌዉ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ያስገቡበት በተጠባባቂነት የነበሩበትን የስራ አስፈፃሚው ቦታ አዲስ አመራር እንደሚመጣ ከተነገረ በኃላ መሆኑን ምንጮቻችን ገልፀውልናል።

በባንኩ የቦርድ አመራር ዐርብ ኅዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም. የአማራ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዋና አቶ ኄኖክ ከበደ ታደሰና የኮርፖሬት አገልግሎት ዋና መኰንኑን አቶ ክንዴ አበበን፣ በአፈጻጸም ድክመት ከሓላፊነታቸው እንዳነሳ የሚታወስ ነው። ከሓላፊነታቸው በተነሡት አቶ ሄኖክ አበበ ቦታ፣ የባንኪንግ አገልግሎቶች ከፍተኛ መኰንን አቶ ጫንያለው ደምሴ ከኅዳር 29 ቀን ጀምሮ በጊዜዊነት የዋና ሥራ አስፈጻሚነቱን ደርበው እንዲይዙ እንደመደባቸው ይታወቃል ።
መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ባንኩ በ2016 በጀት ዓመት አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘቡ 25 ነጥብ 1 ቢሊየን መድረሱን እና በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 377 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን አስታውቋል ።

ባንኩ በቅርብ በሰጠዉ መግለጫ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች 311 ቅንጫፎችን መክፈቱንና 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ደንበኞችን ማፍራት መቻሉን ገልጿል።

Source Capital
@Etstocks
DBE boasts a capital base of 39.7 billion Br, second only to the Commercial Bank of Ethiopia (CBE). The turnaround began when the Council of Ministers approved a crucial capital injection of 28.5 billion Br, followed by the National Bank of Ethiopia’s (NBE) directive, which required commercial banks to purchase DBE bonds worth one percent of their annual loans. These bond sales generated 39.04 billion Br over the past three years, significantly bolstering DBE’s financial position.

Read More

Source: addisfortune
@Etstockd
የኢትዮጵያ ልማት ባንክን በፕሬዝደንትነት ሲመሩ የነበሩት ዮሐንስ አያሌዉ (ዶ/ር) የአማራ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነዉ ተሾሙ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ላለፉት 4 ዓመታት ሲመሩ የቆዩት ዮሐንስ ( ዶ/ር) በአደሱ ዓመት ከመስከረም 02 ፤2017 ዓ.ም. ጀምሮ የአማራ ባንክን በስራ አስፈፃሚነት ቦታ እንደተሾሙ ተገልጿል።

ዮሐንስ (ደ/ር) በይፋ ስራዉን ከጀመረ 2 ዓመት ተኩል ያስቆጠረዉ አማራ ባንክን በተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈፃሚነት ሲመሩ የቆዩትን አቶ ጫንያሌዉ ደምሴን የሚተኩ አንደሆነ ለመረዳት ተችሏል።

የግዙፉ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት የነበሩት ዮሐንስ (ዶ/ር) ከቀናት በፊት  በፍቃዳቸው ስራቸውን መልቀቃቸው ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ የአማራ ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው ብሩን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ  መሾሙን በዛሬዉ ዕለት አስታዉቋል።

በአመራር የኃላፊነት ቦታዎች ላይ በማገልገል ልምድ ያላቸዉ ዮሐንስ አማራ ባንክ በፕሬዝዳንትን የሚመሩ ሁለተኛው ሰዉ ያደርጋቸዋል ።

Source: capitalethiopia
@Etstocks
እንኳን አደረሳችሁ
ውድ የ @etstocks ቤተሰቦች
Source~ Banks ethiopia
@etstocks
👍1
Exchange-rate-reform_2016.pdf
449.4 KB
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማኅበር  በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሬ ፖሊሲውን በተመለከተ ያጠናው ባለ 19 ገፅ የዳሰሳ ጥናት ማንበብ ለምትፈልጉ!

Source: theethiopianeconomistview
@Etstocks
ዘመን ባንክ የተከፈለ ካፒታሉ ወደ 7.5 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታዉቋል

የባንክ ኢንደስትሪዉን ከተቀላቀለ 16 ዓመታትን ያስቆጠረው ዘመን ባንክ የተፈረመ ካፒታሉ ወደ 15 ቢሊዮን ብር መድረሱንና የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ ወደ 7.5 ቢሊዮን ብር መጠጋቱን አስታዉቋል።

ባንኩ በተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት ህጋዊ መጠባበቂያዉ ወደ 1.7 ቢሊዮን ብር ማሳደግ መቻሉን ያስታወቀዉ ከ 200 በላይ በባንኩ ረዥም ጊዜ አብረውት ሲሰሩ የነበሩ ደንበኞችን እና አጋሮቹን እዉቅና በሰጠበት መድረክ ላይ ነዉ ።

የባንኩ ዋና አስፈፃሚዉ አቶ ደረጀ ዘነበ እንደተናገሩት የፋይናንስ ዘርፉ እና አገልግሎቶቹ ነፃ እየሆኑ ባለበት በአሁኑ ጊዜ ከደንበኞቹ እና አጋሮቹ ጋር መስራት በመቻላችን እድለኞች ያደርገናል ብለዋል።

ከዘመን ባንክ እዉቅና የተሰጣቸው በንግድና ኢንቨስትመንት ፣ አበባ እርሻ ልማት ፣ በቴክኖሎጂ ፣ በአየር ትራንስፖርት ፣ በሆቴል እና በቱሪዝም ላይ የተሰማሩ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ደንበኞች መሆናቸዉ ተነግሯል ።

Source: capitalethiopia
@Etstocks
የዶላር ምንዛሬ ዋጋ ከፍ ያለ ጭማሪ አሳይቷል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ7 ቀናት ጭማሪ ያልታየበት ወጥ የምንዛሬ ዋጋ ነበር።

ባንኩ ዛሬ ሲያገበያይበት የነበረው የምንዛሬ ዋጋ ከፍ ያለ ጭማሪ የታየበት ነበር።

አንዱ የአሜሪካ ዶላር መግዣው ወደ 112 ብር ከ3957 ሳንቲም ደርሷል።

የመጫው ዋጋም 124 ብር ከ7592 ሳንቲም ገብቷል።

በፓውንድ ላይም ጭማሪ ተመዝግቧል።

አንዱ ፓውንድ መግዣው 141 ብር ከ6314 ሳንቲም ተቆርጦለት ውሏል። መሸጫው 157 ብር ከ9487 ሳንቲም ነበር።

ዩሮ መግዣው 125 ብር ከ0177 ሳንቲም መሸጫው 138 ብር ከ7697 ሳንቲም ሆኖ ውሏል።

የUAE ድርሃም መግዣው 30 ብር ከ6030 ሳንቲም መሸጫው 33 ብር ከ9693 ሳንቲም ገብቷል።

@Etstocks
👍2
ዘመን ባንክ ከየት ወዴት?
***

👉🏼 ካፒታሉ 15 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን 7.5 ቢሊዮን የተከፈለ ካፒታል ደርሷል።
👉🏼 የደንበኞች ብዛት በ2016 ዓ.ም. መጨረሻ 222,645 ደርሷል።
👉🏼የገቢ መጠን በ2016 የሒሳብ ዓመት 7.7 ቢሊዮን ብር ደርሷል።
👉🏼የብድር መጠን በተጠናቀቀው 2016 የሒሳብ ዓመት መጨረሻ ላይ 35.6 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡
****
በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ለየት ባለ መንገድ አገልግሎት ለመስጠት ወደ ሥራ የገባው ዘመን ባንክ ዛሬ 16 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡

ባንኩ በወቅቱ የነበረውን የባንኮች አሠራር በመፈተሽ የተሻለ ውጤት ያስገኝልኛል ብሎ ያመነውን የአንድ ቅርንጫፍ አገልግሎት ለመስጠት በመወሰን ነበር ወደ ሥራ የገባው፡፡

ወሳኝ የተባሉ የባንክ አገልግሎቶችን በአንድ ቅርንጫፍ በመስጠት ሌሎችን በዲጂታል የባንክ አገልግሎት መስጠት እንደሚችል በማመን የጀመረው ሥራ በወቅቱ እንዴት ይሆናል የሚል ጥያቄ አስነስቶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ባንኩ . . .

Read more
ኢትዮ ቴሌኮም በ2017 በጀት ዓመት የቴሌብር ደንበኞችን ቁጥር በ15.7% በመጨመር 55 ሚሊዮን ለማድረስ ማቀዱን በዛሬው ዕለት ይፋ ባደረገው የሦስት ዓመት ስትራቴጂ እና የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የቢዝነስ ዕቅድ መግለጫ ላይ ጠቅሷል።

ኩባንያው፥ የቴሌብር ወኪሎችን ቁጥር በ28% በማሳደግም 275 ሺህ ለማድረስ እንዲሁም በቴሌብር ግብይት የሚፈጽሙ ነጋዴዎችን (Merchant) ቁጥር በ102% በማሳደግ 367 ሺህ ለማድረስ በእቅዱ እንደተቀመጠም ጠቅሷል።

በተጨማሪም፥ የኤሌክትሮኒክ ንግድ ክፍያዎችን፣ አለም አቀፍ የኦንላይን ክፍያዎችን፣ ተጨማሪ አጋሮችን በማሳተፍ የሃዋላ አገልግሎቶችን ለማሳደግ እንደሚሰራም ነው የገለጸው።

Source: tikvahethmagazine
@Etstocks