ET Securities
708 subscribers
647 photos
8 videos
34 files
342 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

www.Etsecurities.com

YouTube.com/@etstocks

Fb.me/etstocks
Download Telegram
September 17, 2022
ባንኮች ከብሔራዊ ባንክ ለምን ይበደራሉ?

የባንኮች ዋናው የገንዘብ ምንጭ ከቁጠባ የሚሰበስቡት ነው። ከቆጣቢ ሰብስበው (ለቆጣቢ ወለድ እያሰቡ) ለተበዳሪ ያበድራሉ (ከተበዳሪው ወለድ እየተቀበሉ) ገንዘብን ያንቀሳቅሳሉ።

የንግድ ባንኮች ከቆጣቢ የሰበሰቡትን ገንዘብ በሙሉ ሊያበድሩ አይችሉም! ምክንያቱም ቆጣቢ ገንዘቡን ለማውጣት ስለሚፈልግ የተወሰነ ጥሬ ገንዘብ ይዘው መቆየታቸው አይቀርም!

ብሔራዊ ባንክ የቆጣቢዎችን እና የባንክ ባለአክስዮኖች ዋስትና ለመጠበቅ የባንኮች የካፒታል ዋስትና እንዲቀመጥ ያዛል! ከሚያበድሩት ብር መጠን አንፃር የዋስትና ቦንድ ከብሔራዊ ባንክ እንዲገዙ ያስገድዳል (ያበደሩትን መቀበል ባይችሉ ቆጣቢ ብሩን ማጣት የለበትም የሚለው ስጋት ዋና ነው!)

#ለምሳሌ፦ በነባሩ አሰራር ማንኛውም ንግድ ባንክ ከሚያበድረው ገንዘብ ድርሻ 27% ከብሔራዊ ባንክ ቦንድ እንዲገዛ ይገደድ ነበር (1 ሚሊየን ለማበደር የ270 ሺ ብር ቦንድ ከብሔራዊ ባንክ መግዛት አለበት ማለት ነው)።

#ለምሳሌ፦ 1 ቢሊዮን ብር ቁጠባ የሰበሰበ ባንክ 1 ቢሊየኑን በሙሉ ሊያበድር አይችልም (በደንበኛ 2 ሚሊየን ብር ወጪ ቢጠየቅ መመለስ ላይችል ነው!) ስለዚህ የካሽ እጥረት እንዳይፈጠር የመስጋት እና የብሔራዊ ባንክ የአሰራር ሁኔታ ክልከላ ይሆንበታል!

አሰራሩ ይህ ሆኖ ሳለ ባንኮች በቁጠባ የሰበሰቡን በቂ ካሽ ሳያስቀሩ የማበደር እና ያበደሩትን ካሽ በበቂ ያለማስመለስ ችግር የመፈጠር እድል አለ።

#ለምሳሌ፦ በባንኮች ብድር ሲጠየቅ ያለማግኘት እና ጥሬ ብር ለማውጣት አለመቻል (Liquidity Criss) የሚስተዋለው ከላይ ከተጠቀሰው ምክንያት ጋር ይያያዛል።

ንግድ ባንኮች በምሳሌ የተቀመጠው ችግር በገጠማቸው ቁጥር ከብሔራዊ ባንክ ብድር ይጠይቃሉ።

የብሔራዊ ባንክ ገንዘቡን ከየት ያመጣል?

የሃገሪቱ የገቢ ገንዘብ፤ የባንኮች የካፒታል ተቀማጭ፤ በቦንድ እና በግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ የተሰበሰበ (በተለይ ከመንግስት የልማት ድርጅቶች እና የጡረታ ዋስትና ተቀማጭች)፤ አዲስ የሚታተም ገንዘብ፤ ወዘተ መከማቻው ብሔራዊ ባንክ ነው።

የንግድ ባንኮች የብር እጥረት ሲገጥማቸው እና ተጨማሪ ገንዘብ በፈለጉ ጊዜ ከብሔራዊ ባንክ በብድር ይወስዳሉ (በአዲሱ ፖሊሲ በ15% ወለድ ይበደራሉ) ጊዜውን ጠብቀው ከነወለዱ እዳቸውን ይከፍላሉ።
July 15, 2024