ET Securities
665 subscribers
589 photos
7 videos
28 files
299 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
የድርጅታቸውን የተወሰነ ድርሻ በአክሲዮን ለመሸጥ የሚያስቡ ድርጅቶች የሚከተሉት 3 አማራጮች አሏቸው!

አንደኛ
ድርጅቶች ለመሸጥ የወሰኗቸውን አክሲዮናቸውን #ለህዝብ መሸጥ ከፍተኛ ካፒታል ለማሰባሰብ ጥሩ ዘዴ ቢሆንም ሂደቱ ውድ እና አድካሚ ነው! ምክንያቱም ድርጅቶቹ አክሲዮኖችን ለማሻሻጥ ፍቃድ ለተሰጣቸው ድርጅቶች ሃላፊነት ስለሚሰጡ የሚጠየቁት የአገልግሎት ክፍያ ውድ ሊሆን ይችላል እንዲሁም የሚፈልጉት ያህል አክሲዮን ተሸጦ እስከሚያልቅ ረጅም ጊዜ ለመፈጅ ይችላል።

ሁለተኛ
ድርጅቶች ለመሸጥ የወሰኗቸውን የተወሰኑ አክሲዮኖቻቸውን ለትልልቅ #የቢዝነስ_ተቋማት አውጥቶ መሸጥ! ከፍተኛ ካፒታል ለማሰባሰብ ጥሩ ዘዴ ሆኖ ሂደቱ እርካሽ እና ቀላል ነው! ምክንያቱም ተቋማት ትልልቅ ድርሻ የመግዛት አቅም ስለሚኖራቸው በጥቂት ተቋማት እና በአጭር ጊዜ አክሲዮኖቻቸውን ሸጠው ሊጨርሱ ይችላሉ።

ሶስተኛ
ድርጅቶች ለመሸጥ የወሰኗቸውን አክሲዮኖቻቸውን #ለውስጥ_ሰራተኞች መሸጥ! ሰራተኞች ከቁጠባቸው አልያም ከደሞዛቸው ላይ ከፍተኛ ካፒታል ሊኖራቸው ስለማይችል ትልቅ ካፒታል ከአክሲዮን ሽያጭ ለማሰባሰብ አስቸጋሪ ሲሆን (የሰራተኛ ተነሳሽነት ለመጨመር ጥሩ ዘዴ ነው!) የአክሲዮን ድርሻዎችን ለውስጥ ሰራተኞች የመሸጥ ሂደቱ ግን ቀላል ነው!

Source: The Ethiopian Economist View
@etstocks