ET Securities
697 subscribers
622 photos
7 videos
31 files
322 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
የባንክ ስራ እና የተወካይ ቢሮ አዲስ ፈቃድ እና እድሳት መስፈርቶች መመሪያ SBB/98/2025
👇👇👇👇
የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ሆነ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የባንክ ዘርፍ ለውጭ ተሳትፎ ክፍት የሚያደርግ አዲስ መመሪያን ይፋ አድርጓል። ይህ እርምጃ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ለማድረግ ሲደረግ የቆየው ጥረት የመጨረሻው ምዕራፍ ተደርጎ እንደሚወሰዱ ተገልጿል።

መመሪያ ቁጥር SBB/94/2025 ባለፉት አንድ ዓመት በተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተደረጉ ሰፊ ውይይቶች እና ምክክሮች ግብዓት ተደርጎበት የተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል።

ይህ መመሪያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፀደቀው የባንክ ሥራ አዋጅ መሰረት የወጣ ሲሆን፣ የሚያስፈልገውን የሕግ ማዕቀፍ ማሟላቱ ተገልጿል።

ይህ አዲሱ የፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ባለሀብቶች፣ ባንኮችን እና ሌሎች ስትራቴጂካዊ ባለሀብቶችን ጨምሮ፣ በኢትዮጵያ የባንክ ሥርዓት ውስጥ እንዲሳተፉ ያስችላል ተብሏል።

ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣዉ መግለጫ መመሪያው የውጭ ተዋናዮች የባንክ ዘርፉን እንዲቀላቀሉባቸው በርካታ መንገዶችን ያቀርባል፤ ከእነዚህም መካከል ቅርንጫፍ ባንኮችን፣ የውጭ ባንክ ቅርንጫፎችን ወይም የወኪል ቢሮዎችን ማቋቋም ይገኙበታል።

ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የባንክ ዘርፍ ለውጭ ተሳትፎ ክፍት መሆኑን የገለፀ ሲሆን የውጭ ባንኮች እና ባለሀብቶችም ማመልከቻዎቻቸውን ለብሔራዊ ባንክ ማቅረብ እንደሚችሉ አስታውቋል።
Forwarded from Kelemat Ads Hub
የቴሌግራም ቻናል ባለቤት ከሆኑ ማስታወቂያዎችን በቻናሎቻችሁ ላይ በመልቀቅ በቀላሉ ገንዘብ ያግኙ።

ይህን ማስታወቂያ የሚያዩበትን ቻናል ጨምሮ ከ 65+ በላይ ቻናሎች አብረውን እየሰሩ ነው፡፡

only for Ethiopian Based Telegram Channels.

Payment With Telebirr

Register on kelemat Ads & Start immediately

Interested?
👉 Contact us for registration @temaripath
ብሔራዊ ባንክ የግምጃ ቤት ቦንድ ግዥ መመሪያን ሰረዘ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግምጃ ቤት ቦንድ ግዥን የሚመለከት የቀድሞ መመሪያውን የሚሽር አዲስ መመሪያ አውጥቷል።

አዲሱ መመሪያ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግምጃ ቤት ቦንድ ግዥ (መሻሪያ) መመሪያ ቁጥር MFAD/TRBO/002/2025፣ ከሰኔ 23 ቀን 2017 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል። ይህም ማለት የቀድሞው መመሪያ በዚህ ቀን ሙሉ በሙሉ ተሽሯል።

አዲሱ የግምጃ ቤት ቦንድ ግዥ አፈጻጸም
በቀድሞው መመሪያ አንቀጽ 5 መሰረት ባንኮች የተመደበላቸውን የግምጃ ቤት ቦንድ እንዲገዙ ይጠበቅባቸው ነበር።

የሚቀርበው የግምጃ ቤት ቦንድ መጠን በየወሩ በባንኩ ከሚሰጡት አዳዲስ ብድሮች እና ቅድሚያ ክፍያዎች መጠን ላይ ብቻ የተመካ ሲሆን፣ ይህ አዲስ መመሪያ ከመውጣቱ በፊት በነበረው አሰራር መሰረት ይተገበር እንደነበር ይታወቃል።


ይሁን እንጂ፣ መመሪያው እስከ ሰኔ 2017 ድረስ የግምጃ ቤት ቦንድ ለመግዛት ከባንኮች ጋር የተደረጉ ስምምነቶች ካሉ እና ግዥው ገና ካልተፈጸመ፣ የቀድሞው መመሪያ እንደተጠበቀ ሆኖ ተግባራዊ ይሆናል። የእነዚህ ቦንዶች ግዥ እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ድረስ መጠናቀቅ እንዳለባቸው አፅንኦት ሰጥቷል።


በተጨማሪም፣ ይህ አዲስ መመሪያ ከመውጣቱ በፊት የተሰጡ ወይም በሽግግር ጊዜው ድንጋጌ መሰረት የሚወጡ ሁሉም የግምጃ ቤት ቦንዶች፣ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ፣ በቀድሞው መመሪያ መሰረት የሚተዳደሩ ይሆናል።
ET Securities pinned «https://youtu.be/u9I5Exle-8o?si=go7lE5kZm2TYKqJD»
Forwarded from Kelemat Ads Hub
የማይታመን ቅናሽ ከMeda Store፡፡

እጅግ ውብ የሆኑ የቤት እቃዎች እያስገባን ነው፡፡ ለትንሽ ጊዜ በሚቆየው የዋጋ ቅናሽ ተጠቃሚ ይሁኑ፡፡

አዳዲስ እቃዎች ሲገቡ በቅድሚያ እንዲደርስዎ ቻናላችንን Join ያድርጉ፡፡

https://t.me/Medamart
https://t.me/Medamart
https://t.me/Medamart
The National Bank of Ethiopia (NBE) has announced a full transition to electronic government and NBE securities with the issuance of Directive No. MFAD/001/2025, marking a major step in modernizing the country’s financial markets.

The directive designates the Central Securities Depository (CSD) as the sole official registry ....

Read more 👇 ETsecurities
አዋሽ ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 22 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 22 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቋል።

ባንኩ የ2024/2025 እ.ኤ.አ የሂሳብ አመት የሥራ አፈጻጸምን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫዉም የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው በጀት አመቱ መጠናቀቁን ተከትሎ አዋሽ ባንክ 22 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ከታከስ በፊት ትርፍ ማግኘቱን ገልጸዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚዉ በበጀት ዓመቱ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ መሰብሰብ መቻሉንም ነዉ ያብራሩት።

ባንኩ በበጀት አመቱ የ106 ቢሊየን ብር የተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰቡ የተነሳ ሲሆን ይህም ከአምናዉ ጋር ሲነጻጸር የ42በመቶ እድገት እንዳለዉም ተመላክቷል።

የቅርንጫፎቹ ብዛት ደግሞ 989 መድረሱን ዋና ስራ አስፈጻሚው አመላክተዋል።

በበጀት አመቱ ባንኩ 52 አዳዲስ ቅርንጫፎችን እንዲሁም ከ3ሚሊየን በላይ አዳዲስ ደንበኞችንም አፍርቻለዉ ብሏል።

Etsecurities.com/20250701-2
1
The African Development Bank (AfDB) has approved a $400,000 technical assistance grant to support Ethiopia’s efforts to build a vibrant and inclusive capital market.

The funding, sourced from the Capital Markets Development Trust Fund (CMDTF), will strengthen both the Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) and the Ethiopian Securities Exchange (ESX).

Read more 👇
Etsecurities.com
👍1
ዘመን ባንክ 9 ቢሊዮን ብር ትርፍ አገኘ

ዘመን ባንክ በ2024/25 በጀት ዓመት 9 ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘቱን ያሳወቀ ሲሆን አጠቃላይ ገቢው 14 ቢሊየን ብር ደርሷል። የባንኩ የተከፈለ ካፒታልም ከ9 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ አለው።

ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ደረጀ ዘበነ እንደተናገሩት ጠንካራ አፈጻጸሙ እየተካሄደ ባለው የፋይናንሺያል ማሻሻያ የተደገፈ ሲሆን፥ ወደ ተንሳፋፊ የምንዛሪ ተመን እና የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ መጀመርን ጨምሮ . . .

ተጨማሪ ያንብቡ፡ Etsecurities.com
👍3
𝗔𝘄𝗮𝘀𝗵 𝗜𝗻𝘀𝘂𝗿𝗮𝗻𝗰𝗲 𝗦.𝗖. 𝗥𝗲𝗴𝗶𝘀𝘁𝗲𝗿𝘀 𝗛𝗶𝘀𝘁𝗼𝗿𝗶𝗰 𝗚𝗿𝗼𝘀𝘀 𝗪𝗿𝗶𝘁𝘁𝗲𝗻 𝗣𝗿𝗲𝗺𝗶𝘂𝗺 𝗼𝗳 𝗢𝘃𝗲𝗿 𝗘𝗧𝗕 𝟰.𝟱 𝗕𝗶𝗹𝗹𝗶𝗼𝗻

Awash Insurance reported a Gross Written Premium (GWP) exceeding ETB 4.5 billion for the 2024/25 fiscal year, reflecting a 44% increase compared to the previous year. Growth was supported by underwriting discipline, expanded distribution channels, and customer retention efforts. The Life Assurance segment recorded over ETB 656 million in premiums, a 48% rise year-on-year.
Etsecurities.com
1
የሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ገበያ በሚቀጥለው ሳምንት ይፋዊ ግብይት ሊጀምር እንደሆነ ካፒታል ጋዜጣ አስነብቧል

ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ( ስቶክ ገበያ) በሚቀጥለው ሳምንት ሥራ ሊጀምር መሆኑ ተሰምቷል።

ይህ እርምጃ ለአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ትልቅ ምዕራፍ እንደሆነ ተነግሯል።

ገበያዉ በኖቬምበር 2023 በተደረገ የካፒታል ማሰባሰቢያ ዘመቻ 1.5 ቢሊዮን ብር በማሰባሰብ ከታሰበው ግብ በ631% በልጧል። ይህ ገንዘብ ከ48 የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ተቋማት የተገኘ ነው።

በሕዝብና በግል ሽርክና የሚሰራው አዲሱ የበይነመረብ ንግድ ልዉዉጥ መድረክን መንግሥት 25%፣ የግል ዘርፍ ደግሞ 75% ድርሻ አላቸዉ።

አሁን ላይ ገዳ ባንክ አ.ማ. እና ወጋገን ባንክ አ.ማ. በገበያው ላይ ከተመዘገቡት ኩባንያዎች መካከል ይጠቀሳሉ።

የሰነደ መዋዕለ ንዋይ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ እስከ 50 ኩባንያዎችን፣ በአሥር ዓመታት ውስጥ ደግሞ ከ90 በላይ ንግዶችን ለማካተት አቅዷል።
👏21
Siinqee Bank s.c to have a license of investment bank, third of it's kind in Ethiopia

Siinqee Bank, a prominent player in Ethiopia’s banking sector over the past three years, has announced that it is awaiting regulatory approval to become the country’s third investment bank. If granted, this license will enable Siinqee Bank to expand its role in Ethiopia’s emerging capital market, marking a significant milestone in the nation’s financial sector development.

The bank’s president confirmed that all necessary documentation has been submitted to the Ethiopian Capital Market Authority (ECMA), and the institution is now awaiting a formal response.

Read more
1