ET Securities
691 subscribers
616 photos
7 videos
31 files
315 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
Dashen Bank Super App Dashen Bank has launched a banking super app, providing an all-in-one banking solution that is a first for Ethiopia’s banking sector. Developed in partnership with . . .

Read more condoaddis.com/250114-1
January 15
የኢትዮጵያ ሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ሥራ አስፈጻሚ ጥላሁን ካሳሁን፣ ገበያው በርካታ ኩባንያዎችን ለመሳብ የሚያገበያያቸውን ምርቶችና አገልግሎቶች ዓይነት ለማብዛት ማቀዱን እንደነገሩት ጠቅሶ የአሜሪካው ሴማፎር ድረገጽ ዘግቧል።

ኩባንያው፣ ወደፊት ለመጀመር ካሰባቸው አማራጮች መካከል እስላሚክ ቦንድ አንዱ እንደኾነ ዋና ሥራ አስፈጻሚው መግለጣቸውንም ዘገባው አመልክቷል።

ትላልቅ የአክሲዮን ማኅበራትንና በግል ይዞታ ሥር የሚገኙን ጨምሮ የግል ኩባንያዎች ገበያውን ይቀላቀላሉ ብለው እንደሚጠብቁ የጠቆሙት ጥላሁን፣ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ በትንሹ 90 ኩባንያዎች በገበያው አማካኝነት የአክሲዮን ገበያውን እንዲቀላቀሉ ዓላማ ተይዞ እየተሠራ እንደሚገኝም ተናግረዋል ተብሏል።

በአገሪቱ ከሚገኙ 30 ንግድ ባንኮች መካከል እስካኹን በገበያው የአክሲዮን ድርሻዎቹን ለማገበያየት የተመዘገበው ወጋገን ባንክ ብቻ ነው።

(ዋዜማ
)
January 21
ለውጭ ገበያ ከቀረበ ቡና 908 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የቡናና ሻይ ባለስልጣን ገለጸ ፡፡

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሻፊ ኡመር ባለፈው ስድስት ወር ከ204 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለውጭ ገበያ በማቅረብ 908 ሚሊዮን ዶላር  ገቢ መገኘቱን አስታውቀዋል ።

አፈጻጸሙም ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት የ8 ሺህ 251 ነጥብ 17 ቶን ወይም 73 በመቶ ብልጫ እንዳለው ነው የተናገሩት ፡፡
ባለስልጣኑ በ2017 በጀት አመት 400 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ በመላክ 2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ማቀዱ ይታወሳል ፡፡

ስማርት መረጃ
January 21
January 24
January 24
ባንኮች የሚጠይቁት የማስያዣ ብር ከወትሮው ከፍ ማለት በእቅዱ መሰረት የውጭ ምንዛሬ ማቅረብ እንዳልተቻለ ተገለፀ፡፡
የኢኮኖሚ ማሻሻያው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ክምችት እንዲኖር ያስቻለ ቢሆንም የውጭ ምንዛሬ መግዛት የሚፈልጉ አካላት በቂ የመግዣ ብር ያለመኖር በሚፈልጉት መጠን  የውጭ ምንዛሬ እንዳያገኙ እንቅፋት መሆኑ ሲገለፅ ቆይቷል፡፡
የኢንደስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል የስድስት ወር አፈፃፀም ሪፖርታቸውን በፓርላማ ሲያቀርቡ እንደገለጹት በበጀት አመቱ ግማሽ አመት 468.4 ሚሊየን ዶላር ለአምራች ኢንደስትሪው ለማቅረብ ታቅዶ 369 ሚሊየን ዶላር መቅረብ ተችሏል፡፡ ይህም የእቅዱን 79 በመቶ ነው፡፡
እንደ አቶ መላኩ ገለጻ የውጭ ምንዛሬ አቅርቦቱ ከእቅዱ አንፃር ዝቅ ያለው ባንኮች የሚጠይቁት የማስያዣ ብር መጠን ከወትሮው ከፍ ማለቱ ነው ብለዋል፡፡
ሆኖም በ6 ወሩ የቀረበው 369 ሚሊየን ዶላር አምና በተመሳሳይ ወቅት ከነበረው 274 ሚሊየን ዶላር የ 35 በመቶ እድገት ነበረው፡፡
January 24
January 27
January 28
በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፉ ተቀማጭ ገንዘብ ሁለት ነጥብ 74 ትሪሊዮን ብር ደረሰ
የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፉ ተቀማጭ ገንዘብ ሁለት ነጥብ 74 ትሪሊዮን ብር ደርሷል።
በቅርቡ የውጭ ባንኮች ሀገር ቤት ገብተው እንዲሠሩ የጸደቀው አዋጅ በዋናነት የውጭ ባለሀብቶች በባንክ መስክ ተሰማርተው ለኢኮኖሚው አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ነው ያሉት አቶ ማሞ፤ የዘርፉን ተወዳዳሪነት በማሻሻል ባንኮች በኢኮኖሚው ውስጥ የሚጫወቱትን ሚና ከፍ ለማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል።
የባንክ ዘርፉ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ማድረግ ማለት የኢትዮጵያ ባንኮች ችግር ላይ ይወድቃሉ ማለት አይደለም። የሀገር ውስጥ ባንኮች አዳዲስ አሠራርና አገልግሎት ተምረው ለኢኮኖሚ የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ ይጨምራል።  

ተጨማሪ👉 Condoaddis.com/250130-1
January 30
የባንኮች ብድር ጉዳይ‼️
ባንኮች ላይ ተጥሎ የነበረው የብድር ጣሪያ መስከረም ላይ ይነሳል‼️
ካለፈው ነሀሴ 2015 ዓ.ም. አንስቶ ተጥሎ የነበረው ባንኮች መስጠት የሚችሉት አዲስ ብድር ገደብ ሙሉ ለሙሉ ሊነሳ መሆኑን ተሰምቷል።

የአለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅትን (IMF) መረጃ እንደሚጠቁመው ባንኮች የሚችሉት የብድር መጠን ላይ ተጥሎ የቆየው ጣሪያ በቀጣይ መስከረም ይነሳል።

በነሀሴ 2015ዓም ወደ ስራ የገባው የብድር ጣሪያ ባንኮች አመታዊ የብድር እድገታቸው ከቀደመው የብድር ክምችት  መጠን በ14 በመቶ ብቻ እንዲያድግ የሚያደርግ ነው።

ባለፈው ወር መጨረሻ እድገቱ ወደ 18 በመቶ እንዲሆን በብሄራዊ ባንክ ተወስኖ ነበር። ሆኖም ውሳኔው በባንኮች በአወንታዊ የታየ አልነበረም።

ተጨማሪ 👇
ET Securities
February 2
February 3
February 4
February 5
African Top Stock Markets & Their Potential
February 6
February 6
February 7
#Quiz

What term describes investing in foreign assets such as stocks and bonds without obtaining significant influence?
Anonymous Quiz
28%
Direct investment
10%
Venture capital
56%
Portfolio investment
5%
Leverage buyout
February 7
February 7
February 10
Wegagen_Bank_S_C_Prospectus_05675dcb1d.pdf
1.3 MB
February 11
February 12
February 12
February 13
February 13
February 13
February 13
Six-Month Monetary and External Sector Developments.pdf
2.2 MB
የኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ ያለፈውን 6 ወር ኢኮኖሚያዊ አፈጻጸም ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

- የዋጋ ግሽበት ባለፈው አመት ከነበረበት 29.4 በመቶ በ13.9 በመቶ በመቀነስ ወደ 15.5 በመቶ ዝቅ ብሏል ሲል ብሄራዊ ባንክ ገልጿል።

- የወርቅ የወጪ ንግድ በ735% አድጓል። ይህም ከ161 ሚሊየን ዶላር ወደ 1.36 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱን ተነግሯል።

- የቡና የወጪ ንግድ በ60% ያደገ ሲሆን፣ ያለፈው አመት ከነበረው ተመሳሳይ ጊዜ ከ 574 ሚሊዮን ዶላር ወደ 918 ሚሊዮን ዶላር አድጓል።

- አጠቃላይ የወጪ ንግድ በ6 ወራት ውስጥ ከ1.6 ቢሊዮን ዶላር በ104.3% በማደግ ወደ 3.3 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ብሏል።

- ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በ4% የቀነሱ ሲሆን ከ8.99 ቢሊዮን ዶላር ወደ 8.63 ቢሊዮን ዶላር ወርዷል።

- በባንኮች የሚደረጉ የግለሰቦች ዝውውር በ23.3% የጨመረ ሲሆን ይህም ከ1.48 ቢሊዮን ዶላር ወደ 1.83 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።

- የኢንተርባንክ የገንዘብ ገበያ ግብይት በከፍተኛ ደረጃ እየሰፋ በመሄዱ በመጀመሪያው ሳምንት ከነበረው ከ1.6 ቢሊዮን ብር በአስራ ሁለተኛው ሳምንት ወደ 183.3 ቢሊዮን ብር አድጓል።

መረጃው ከብሄራዊ ባንክ ግማሽ አመት ሪፖርት የተወሰደ ነው።



ምንጭ~ብሔራዊ ባንክ
https://www.condoaddis.com/wp-content/uploads/2025/02/Six-Month-Monetary-and-External-Sector-Developments.pdf
February 13
February 14
የንብ ባንክ አዲስ የክፍያ ሥርአት አስጀመረ

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ያስጀመራቸው የክፍያ ሥርአት ሁለት ዓይነት ሲሆኑ እነሱም ንብ አምበር ፔይ እና ንብ ፔይስትሪም የተሰኙ የዲጅታል አገልግሎት መተግበሪያዎች ናቸው፡፡

የመተግበሪያዎቹ ሥራ ማስጀመር በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሔኖክ ከበደ ባደረጉት ንግግር፣ “ወደ ሥራ ከሚገቡት ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው ንብ አምበር ፔይ በንግድ ሥራ ላይ ለተሰማሩ የባንካችን ደንበኞች ለሚሰጡት አገልግሎት ከደንበኞቻቸው የሚከፈሉ ክፍያዎችን በቀላሉ በአስተማማኝ መንገድ በመተግበር፤ ክፍያን ከመቀበያነት በተጨማሪ ደንበኞች የንግድ እንቅስቃሴያቸውን በቀላሉ በእጅ ስልካቸው የሚከታተሉበትን መንገድ ተግባራዊ አድርጓል” ብለዋል።

ሁለተኛው ወደ ሥራ የሚገባው የክፍያ ስርዓት ንብ ፔይስትሪም የተሰኘው የአገልግሎት መተግበሪያ ሲሆን፤ በበይነ መረብ የሚደረጉ ግብይቶችን ለማቀላጠፍ ታስቦ የተተገበረ ሲሆን ይህን መተግበሪያ በመጠቀም የንግዱ ማኅበረሰብ ለሚሰጧቸው አገልግሎቶች ክፍያቸውን በኦንላይን መቀበል የሚያስችላቸው መሆኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አስረድተዋል፡፡

ማንበብ ይቀጥሉ 👇
Condoaddis.com/250214-1
February 14
February 14
የፋይዳ አገልግሎቶችን አጠቃሎ የያዘ የሞባይል መተግበሪያ ተለቀቀ



በዲጂታል ስትራቴጂ 2025 መሰረት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አስቻይ ከሆኑት የዲጂታል መሰረተልማቶች ቁልፍ እና ዋነኛው ሲሆን እንደሚታወቀው ፋይዳ ለኢትዮጵያ ሃገር አቀፍ ምዝገባን ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶበት የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንሰፎርሜሽን ግብን ለማሳካት አንደ ዋነኛ አስቻይ ሆኖ እየተገበረ ይገኛል።

እስካሁን ድረስ 12 ሚሊዮን ሰዎችን ባለቤት በማድረግ ከተቋማት ጋር ሲስተሞችን በማስተሳሰር የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ እያደረገ ይገኛል።

ነዋሪዎች የሚያገኟቸውን የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎቶች በአንድ የሚያገኙበትን የፋይዳ ሞባይል መተግበሪያ በተቋሙ የውስጥ ሀይል ተገንብቶ በአንድሮይድ (Android) እና በኣይኦኤስ (iOS) ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ለህዝብ ይፋ ሆኗል።

ይህን የሞባይል መተግበሪያ በመጠቀም ነዋሪዎች፡

• በተለያየ ምክንያት የጠፋባቸውን ወይም ያልደረሳቸውን የፋይዳ ቁጥር ወዲያው መልሰው ማስላክ ይችላሉ

• የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያቸውን በዲጂታል መልኩ ለማግኘት እንዲሁም አውርዶ ለመያዝ

• በምዝገባ ወቅት በባለሞያ ምክንያት የተሳሳተ የስነህዝብ (Demographic) መረጃን ጣቢያ ድረስ መምጣት ሳይጠበቅባቸው በስልካቸው ለማረም እንዲሁም የአድራሻ እና የኢሜይል ለውጥ ሲኖር ካሉበት ሆነው ለማደስ

• የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን በካርድ መልክ አሳትሞ ለመያዝ የካርድ ህትመት ለማዘዝ እንዲሁም

• የተለያዩ አስተያየት እና ቅሬታ ለመስጠት እና የደንበኞች አገልግሎትን ለማግኘት የሚያስችል ለአጠቃቀም ቀላል እና ምቹ መተገበሪያ ነው።


ይህ የሞባይል መተግበሪያ መበልጽጉ የፋይዳ አገልግሎቶችን በማዘመን፡ የደንበኞችችን ቅሬታዎች ወዲያው ለመፍታት እና በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ነዋሪዎችን ተደራሽነትን በማሻሻል ረገድ ትልቅ ምዕራፍ አለው ሲል ተቋሙ ገልጿል።

መተግበሪያውን ከአፕ ስቶር እንዲሁም ከፕሌይ ስቶር ላይ በማውረድ መጠቀም ይቻላል።

LinkedIn| YouTube | X | Facebook | TikTok
February 14
February 15