ET Securities
662 subscribers
584 photos
7 videos
28 files
297 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
Capital Market Glossary

ቡል ማርኬት (Bull Market) ምን እንደሆነ ያውቃሉ?

ይህ ሁኔታ የፋይናንሺያል ገበያው ውስጥ የአብዛኛው ሰነደ መዋለ ነዋይ ዋጋ ሲጨምር ነው። በገበያው ውስጥ ያሉ ብዙ ባለድርሻ አካላት ስለ ገበያው ያላቸው አስተሳሰብ በጣም አዎንታዊና ብሩህ የሚሆንበትም ጊዜ ነው።

የፋይናንሺያል ገበያ በዋጋ በቀላሉ መጨመር እና መቀንስ የሚታወቅ ቢሆንም ይህንን ቡል ገበያ የሚለየው በገበያው ውስጥ ያለው የዋጋ ጭማሮ ለረጅም ጊዜ ያለማቋረጥ የሚቆይና በብዙ መዋለ ሰነደ መዋለ ነዋዮች ላይ የሚከሰት መሆኑ ነው።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ነዋይ ግብይት ነገ አርብ ጥር 2፣ 2017 ዓ.ም ልታስጀምር ነው።

ይህም በሀገሪቱ የፋይናንሺያል ሴክተር ትልቅ ምዕራፍ ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥላሁን ካሳሁን ተናግረዋል።
- The National Bank of Ethiopia (NBE) and the Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) have entered into a Memorandum of Understanding (MoU) to strengthen collaboration in the development of Ethiopia’s capital market infrastructure.

- The MoU aims to establish and oversee securities depository, clearing, and settlement services to support the efficient functioning of the market.

- It outlines a collaborative effort for the issuance and depository of electronic securities, the dematerialization of paper-based securities, and the establishment of secure and efficient securities clearing and settlement systems.

- As part of the agreement, ECMA will regulate and oversee activities related to non-government securities to ensure compliance and market integrity.

- The National Bank of Ethiopia will operate the central securities depository (CSD) in alignment with the terms specified in the Capital Market Proclamation.

- This agreement is expected to provide a robust framework for improving the operations of Ethiopia’s capital market and supporting its overall growth.

Website
በአክሲዮን ገበያ ግብይት ለማድረግ የሚስፈልጉ ቅደም ተከተሎች


አክሲዮን ገበያ ውስጥ ገንዘብ ግብይት ማድርግ  አስደሳች እና ትርፋማ ሊሆን ይችላል።

ነገር ግን፣ አደጋዎችም የያዘ ነው። ስለዚህ፣ በስቶክ ገበያ ትሬድ ከመጀመራችሁ በፊት በደንብ ማጥናት አለባችሁ።

1. ስለ አክሲዮን ገበያ ይወቁ:

* አክሲዮን ምንድነው? የኩባንያ ባለቤትነት ላይ ትንሹ ክፍፋይ ድርሻ ነው።
* አክሲዮን ገበያ ምንድነው? ኩባንያዎች አክሲዮኖቻቸውን የሚሸጡበት እና ባለሀብቶች የሚገዙበት ገበያ ነው።
* የተለያዩ የአክሲዮን ዓይነቶች: የዕድገት አክሲዮኖች፣ የገቢ አክሲዮኖች፣ ወዘተ.
* የአክሲዮን ገበያ አሠራር: እንዴት አክሲዮኖች ዋጋቸውን የሚቀየሩት፣ እንዴት ይገዛሉ እና ይሸጣሉ፣ ወዘተ.

2. የትኛው የአክሲዮን ደላላ እንደሚመርጡ ይወስኑ:

* የደላላ አይነቶች: የመስመር ላይ ደላሎች፣ የባህላዊ ደላሎች፣ ወዘተ.
* የደላሎች ክፍያዎች: የኮሚሽን ክፍያዎች፣ የወርሃዊ ክፍያዎች፣ ወዘተ.
* የደላሎች መሳሪያዎች: የቴክኒካል ትንታኔ መሳሪያዎች፣ የመረጃ መሠረቶች፣ ወዘተ.


3. የኢንቨስትመንት ግቦችዎን ይወስኑ:

* ለምን በአክሲዮን ገበያ ውስጥ እየገቡ ነው? ለጡረታ፣ ለልጆችዎ ትምህርት፣ ወዘተ.
* ምን ያህል ገንዘብ ለማዋል ይፈልጋሉ?
* ምን ያህል አደጋ መውሰድ ይፈልጋሉ?


4. የመጀመሪያ ትንታኔ ያድርጉ:

* ኩባንያዎችን ይመርጡ: በኢንዱስትሪ፣ በመጠን፣ በታሪካዊ አፈጻጸም፣ ወዘተ ላይ በመመስረት።
* የኩባንያዎችን ፋይናንሻል መረጃ ይተንትኑ: የትርፍ እና ኪሳራ መግለጫ፣ የገንዘብ ፍሰት መግለጫ፣ የሚዛን ገበታ፣ ወዘተ.
* የገበያውን አጠቃላይ ሁኔታ ይመልከቱ: የኢኮኖሚ ዜናዎች፣ የፖለቲካ ክስተቶች፣ ወዘተ.


5. የኢንቨስትመንት ስትራቴጂ ያዘጋጁ:

* የረዥም ጊዜ ወይም የአጭር ጊዜ ኢንቨስትመንት?
* የትኞቹን አክሲዮንኖች ይገዛሉ እና ይሸጣሉ?
* ምን ያህል ጊዜ በገበያው ውስጥ ይቆያሉ?

6. ትዕዛዞችዎን ያስቀምጡ:

* የገበያ ትዕዛዝ፣ የገደብ ትዕዛዝ፣ ወይም የስቶፕ-ሎስ ትዕዛዝ?
* ትዕዛዝዎን ያረጋግጡ።

7. ኢንቨስትመንቶችዎን ይከታተሉ:

* የአክሲዮኖችዎን ዋጋ በየጊዜው ይመልከቱ።
* የገበያውን ዜናዎች ይከታተሉ።
* አስፈላጊ ከሆነ ስትራቴጂዎን ያስተካክሉ።

ማስታወሻ:

* አክሲዮን ገበያ ውስጥ ኢንቨስትመንት አደጋ የያዘ ነው። ሁሉንም ገንዘብዎን አንድ ጊዜ አያስቀምጡ።
* በአክሲዮን ገበያ ውስጥ ከመጀመራችሁ በፊት በደንብ ያጥኑ እና የባለሙያ ምክር ይጠይቁ።

ማስታወሻ:

ይህ መረጃ ለመረጃ አገልግሎት ብቻ ነው። የኢንቨስትመንት ምክር አይደለም። በአክሲዮን ገበያ ውስጥ ከመጀመራችሁ በፊት የፋይናንስ አማካሪ ያማክሩ።

@Etstocks
የኢትዮጵያ ሰነድ ሙዓለ ገበያ (Ethiopia Security Exchange -ESX ) ግብይት በይፋ ተጀመረ- ደወሉ ተደወለ!!

በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ 50 ያህል ኩባንያዎች በአዲሱ የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ላይ የአክሲዮን ድርሻዎችን ለግብይት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።

https://t.me/Etstocks
እንኳን ደስ አለን!

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ዛሬ በይፋ ሥራ ጀምሯል!

በገበያው የተመዘገበ ኩባንያ (Listed company) ለመሆን ፍላጎት ካለዎት፣ ስለቀረቡት የኢንቨስትመንት ዕድሎች የበለጠ ማወቅ ከፈለጉ ድረ-ገፃችንን www.esxethiopia.com ይጎብኙ።

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር::
Share and Share Trading in AA 1960s.pdf
39.9 MB
Share and Share Trading in Addis Ababa in 1960s

አክሲዮን እና የአክሲዮን ግብይት በአዲስ አበባ በ1960ዎቹ
Wegagen Bank has made history by becoming the first company to list its shares on the Ethiopian Stock Exchange (ESX). The announcement was made during the official launch ceremony of the stock exchange, held at the Science Museum in Addis Ababa in the presence of Prime Minister Abiy Ahmed (PhD) and other high-ranking government officials.

Read more~
https://www.condoaddis.com/250110-2/
የኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን የሽያጭ ጊዜ ተራዘመ!!

ኢትዮ ቴሌኮም ለህዝብ አክሲዮን እየሸጠ ያለበት ግዥ ቀነ-ገደብ በአምስት ሳምንታት ተራዝሟል።

የሼር ሽያጩ የካቲት 07 ቀን 2017 የሚዘጋ ሲሆን ከጥቅምት 2017 ጀምሮ 100 ሚሊየን አክሲዮኖችን እያንዳንዳቸው በ300 ብር እየተሸጠ ይገኛል።

ኢትዮ ቴሌኮም እያከናወነ ያለው የድርሻ ሽያጭ ጥር 2/2017 ስራ በጀመረው የኢትዮጵያ የሰነደ መዋዕለነዋዮች ገበያ አሰራር መሰረት እንደሚደለደል ይጠበቃል።
የናይጀሪያው ፈርስት ባንክ በኢትዮጵያ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው አስታውቋል።

ኢትዮጵያ በሯን ለውጭ ባንኮች ክፍት ማድረጓን ተከትሎ የተለያዩ የውጭ ባንኮች እንደሚገቡ በመግለጽ ላይ ናቸው። አሁን ደግሞ የናይጀሪያው ፈርስት ባንክ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአንጎላ እና ኮትዲቯር የመስራት ፍላጎት እንዳለው የባንኩ ምክትል ሀላፊ ለአፍሪካን ሪፖርት ተናግረዋል። የኬንያው ኬቢሲ፣ የደቡብ አፍሪካው ስታንዳርድ ባንክ እና ሌሎችም በኢትዮጵያ ፍላጎት ካሳዩ ባንኮች መካከል ዋነኞቹ ናቸው።
Out of the 32 commercial banks operating in Ethiopia according to their declared annual report only half fulfilled the additional capital required from them as per 2021 directive of the National Bank of Ethiopia.

The coming of the new Ethiopian Securities Exchange (ESX) will be a great opportunity for these banks to raise the required additional capital from the opened market of capital and should take note of the pioneer Wegagen Bank.
Dashen Bank Super App Dashen Bank has launched a banking super app, providing an all-in-one banking solution that is a first for Ethiopia’s banking sector. Developed in partnership with . . .

Read more condoaddis.com/250114-1
የኢትዮጵያ ሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ሥራ አስፈጻሚ ጥላሁን ካሳሁን፣ ገበያው በርካታ ኩባንያዎችን ለመሳብ የሚያገበያያቸውን ምርቶችና አገልግሎቶች ዓይነት ለማብዛት ማቀዱን እንደነገሩት ጠቅሶ የአሜሪካው ሴማፎር ድረገጽ ዘግቧል።

ኩባንያው፣ ወደፊት ለመጀመር ካሰባቸው አማራጮች መካከል እስላሚክ ቦንድ አንዱ እንደኾነ ዋና ሥራ አስፈጻሚው መግለጣቸውንም ዘገባው አመልክቷል።

ትላልቅ የአክሲዮን ማኅበራትንና በግል ይዞታ ሥር የሚገኙን ጨምሮ የግል ኩባንያዎች ገበያውን ይቀላቀላሉ ብለው እንደሚጠብቁ የጠቆሙት ጥላሁን፣ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ በትንሹ 90 ኩባንያዎች በገበያው አማካኝነት የአክሲዮን ገበያውን እንዲቀላቀሉ ዓላማ ተይዞ እየተሠራ እንደሚገኝም ተናግረዋል ተብሏል።

በአገሪቱ ከሚገኙ 30 ንግድ ባንኮች መካከል እስካኹን በገበያው የአክሲዮን ድርሻዎቹን ለማገበያየት የተመዘገበው ወጋገን ባንክ ብቻ ነው።

(ዋዜማ
)
ለውጭ ገበያ ከቀረበ ቡና 908 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የቡናና ሻይ ባለስልጣን ገለጸ ፡፡

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሻፊ ኡመር ባለፈው ስድስት ወር ከ204 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለውጭ ገበያ በማቅረብ 908 ሚሊዮን ዶላር  ገቢ መገኘቱን አስታውቀዋል ።

አፈጻጸሙም ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት የ8 ሺህ 251 ነጥብ 17 ቶን ወይም 73 በመቶ ብልጫ እንዳለው ነው የተናገሩት ፡፡
ባለስልጣኑ በ2017 በጀት አመት 400 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ በመላክ 2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ማቀዱ ይታወሳል ፡፡

ስማርት መረጃ
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ በኑሮ ውድነት አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠች
ቢዝነስ ኢንሳይደር በ2025 መጀመሪያ በአፍሪካ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ያስመዘገቡ ሀገራትን ዝርዝር ባወጣበት መረጃው ኢትዮጵያን ቀዳሚ አድርጓታል፡፡
በባለፈው አመት አራተኛ ደረጃ ላይ የነበረችው ኢትዮጵያ በዚህ አመት ወደ አንደኛ ደረጃ ከፍ ስትል  ሞዛምቢክ ፣ ሴኔጋል እና አይቮሪኮስት በዚህኛው አመት መጠነኛ ማሻሻያዎችን አስመዝግበዋል፡፡
በ2025 መጀመሪያ በኑሮ ውድነት ቦትስዋና ፣ ሞዛምቢክ እና አይቪሪኮስት ኢትዮጵን በመከተል ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ መያዛቸውን  አል-ዐይን ቢዝነስ ኢንሳይደርን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል ፡፡