ET Securities
649 subscribers
572 photos
7 videos
26 files
287 links
At Et securities our aim is in creating condusive space concerning capital markets and financial markets so as to enable learning and awareness creation to the society.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
Financial-Stability-Report_NOV2024.pdf
7.3 MB
ብሄራዊ ባንክ ሁለተኛውን የፋይናንስ መረጋጋት ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ሪፖርቱ ስለ ሃገር ውስጥ ምርት እድገት(GDP) ምን ይላል?

አይ.ኤም.ኤፍ የ2024 የሃገር ውስጥ ምርት እድገት 6.2% እንደሚሆን ከዚህ ቀደም አስታውቆ ነበር። በዚህ ሪፖርት የልማትና እቅድ ሚኒስቴር ቁጥሩን በማሻሻል የ 2024/2025 የGDP እድገት 8.4% እንደሚሆን አስታውቋል።

የዋጋ ንረትን በተመለከተ፡

- የዋጋ ንረት በ 2015 ታህሳስ ወር ከነበረበት 33.8% በሰኔ 2016 ወደ 19.9% እንዲሁም በመስከረም 2017 ደግሞ  ወደ 17.5% መቀነሱን ሪፖርቱ ይገልጻል። በ2019 ሰኔ ወር ደግሞ የውጭ ምንዛሬ ሪፎርሙን ተከትሎ ወደ 12% እንደሚቀንስ ያብራራል።

የባንክ ዘርፍ መረጋጋት
- ባንኮች በሰኔ 2016 ከ96% በላይ የፋይናንስ ንብረቶችን እንደያዙ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ የተወሰነው ውሳኔ እንደ ትልቅ ዕድገት ተገልጿል።
- በ 2024 መጨረሻ ላይ የኢትዮጵያ የሰነደመዋለንዋይ ገበያም ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።

በሪፖርቱ አዲስ የተተገበሩት ፖሊሲዎችም ተዳሰዋል። ምን ምን ፖሊሲዎች ተተገበሩ?

1. ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ፖሊሲ
2. አጠቃላይ የገንዘብ ፖሊሲ(Monetary policy): የወለድ መጠን ላይ የተመሰረተ የገንዘብ ፖሊሲ።

የሚታዩ አደጋዎች፡

- የክሬዲት ስጋት፡ የውስጥ ግጭቶች እና ውጫዊ ተጋላጭነቶች እንደ ስጋቶች ተጠቁመዋል።

- የፈሳሽ ስጋት (Liquidity Risk)፡ መጠነኛ ግን እየጨመረ ያለ፣ ከተቀማጭ ሂሳብ ጋር የተያያዘ ስጋት ነው።

- የገበያ ስጋት፡ በአገር ውስጥ የወለድ ጭማሪ እና የምንዛሪ ዋጋ መቀነስ ምክንያት የገበያ ስጋት መጠነኛ ጭማሪ አሳይቷል።

| YouTube.com/@etstocks📱 | X.com/@etstocks1
📱| Facebook 📱| TikTok📱
ባንኮች በሚሰጡት ዓመታዊ ብድር ላይ የተጣለው ገደብ ሊሻሻል ነው

ባንኮች የሚያቀርቡት ዓመታዊ የብድር መጠን ከ14 በመቶ እንዳይበልጥ ገደብ የሚጥለውና ከአንድ ዓመት በላይ ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ ሊሻሻል መሆኑ ተሰማ፡፡

አቶ ሀብታሙ ወርቅነ
በበርካታ ባንኮች ላይ ጫና እየፈጠረ መሆኑ በተደጋጋሚ ሲነገርለት የቆየው ይህ መመርያ፣ ገደቡን እስከ ማንሳት የሚያስችል ማሻሻያ የሚደረግበት ስለመሆኑ ሪፖርተር ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ሐሙስ ኅዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ኢኮኖሚ ትንተናና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ወርቅነህ፣ መመርያውን ለማሻሻል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንና ማሻሻያውም ገደቡን እስከ ማንሳት ድረስ እንደሚዘልቅ ጠቁመዋል፡፡
የብድር ገደቡ ባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንዲያጋጥማቸው ካደረጉ ምክንያቶች መካከል አንዱ ነው የሚል ተደጋጋሚ ጥያቄዎች መቅረባቸው፣ ብሔራዊ ባንክ መመርያውን ለማሻሻል ገፊ ምክንያት እንደሆነበት ለማወቅ ተችሏል፡፡
በተለይ ዓመታዊ የብድር ምጣኔያቸው አነስተኛ የሆኑ ባንኮች ‹‹በዚህ መመርያ እየተነገደ ነው›› በማለት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አቤት ቢሉም መልስ ሳያገኙ መቅረታቸውን ሲናገሩ ነበር፡፡ አሁን ብሔራዊ ባንክ የብድር ገደቡን የማንሳቱ መረጃ መልካም መሆኑን እየገለጹ ነው፡፡

በተጨማሪ መረጃ ብሔራዊ ባንክ በቀጣይ ሳምንታት በዚህ መመርያ ላይ ውሳኔውን ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ‹‹መመርያው ለባንኮች የገንዘብ እጥረት ምክንያት ጭምር ሆኗል›› የሚል ትችት የሚቀርብበት ቢሆንም፣ ዳይሬክተሩ አቶ ሀብታሙ ግን በዚህ እንደማይስማሙ ገልጸዋል፡፡

አቶ ሀብታሙ በሰጡት ተጨማሪ አስተያየት ብሔራዊ ባንክ የጣለው 14 በመቶ የብድር ገደብ ለባንኮች የገንዘብ እጥረትም ሆነ የብድር አቅርቦት እክል ምክንያት አይደለም ብለዋል፡፡ በተለይ የ14 በመቶ የብድር ደገብን በቅርቡ ከተካሄደው የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም፣ በተለይም የውጭ ምንዛሪ ግብይት ማሻሻያ ጋር ማገናኘት ተገቢ እንዳልሆነም ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡ 
የ14 በመቶ የብድር ገደብ መመርያ ሥራ ላይ የዋለው ከሪፎርሙ በፊት መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሀብታሙ፣ ከባንኮች አካባቢ ብዙ ጊዜ ሲነሳ የሚሰማውም መመርያው ገዳቢ አለመሆኑን ነው ብለዋል፡፡ ባንኮች በዓመቱ መጨረሻ ላይ ከነበራቸው የብድር ክምችት ተነስተው በ14 በመቶ ማሳደግ እንደሚችሉ፣ ነገር ግን ከዚያ በላይ እንዳየልፉ ገደብ ተቀመጠ እንጂ የብድር ክልከላ አልተደረገም ብለዋል፡፡  
ችግሩ ያለው ከመመርያው ሳይሆን ከባንኮች የሊኪውዲቲ ማኔጅመንት (ከራሳቸው ጥሬ ገንዘብ አስተዳደር) ጋር የተያያዘ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በየሁለት ሳምንቱ የሚደረገው የዳሰሳ ጥናት የሚያሳየው፣ ኢኮኖሚው የጥሬ ገንዘብ ችግር እንደሌለበት መሆኑን አጽንኦት የሰጡት ዳይሬክተሩ፣ አለ የሚባለውን ችግር ከባንኮች የጥሬ ንዘብ አስተዳደርና ከብድር አሰጣጣቸው ጋር አያይዘውታል፡፡
የባንኮች የብድር አፈቃቀድ ሒደቶችና ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ማስባት እንዳለባቸውም አመልክተዋል፡፡ ይህም ቢሆን ግን የብድር ገደቡ በብሔራዊ ባንክ ላይ ብዙ ጫና እያመጣ ስለሆነ እየታየ መሆኑን፣ በጉዳዩ ላይ ለውጥ ይደረጋል ተብሎ እየተጠበቀ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡ አንዳንድ የባንክ የሥራ ኃላፊዎች ግን፣ ከ14 በመቶው የብድር ገደብ በበለጠ ባንኮች የተቸገሩት የዓመታዊ ብድራቸውን 20 በመቶ በንድ እንዲገዙ በሚያስገድደው የብሔራዊ ባንክ መመርያ እንደሆነ በመጥቀስ ይህ መመርያ ቢነሳ የተሻለ ትርጉም እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡ ይህ ቢሆን በባንኮች አካባቢ የሚታየውን የጥሬ ገንዘብ እጥረት ለማስታገስ ትልቅ ጠቀሜታ እንደሚኖረውም አክለዋል፡፡

አቶ ሀብታሙ ግን አሁን ባለው ሁኔታ ኢኮኖሚ ውስጥ የጥሬ ገንዘብ እጥረት አለመኖሩን፣ ብሔራዊ ባንክም በየጊዜው በሚያደርገው ክትትል ያለው መረጃ የሚያሳየው ችግር አለመኖሩን ነው ብለዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በዘንድሮው በጀት ዓመት መጨረሻ ላይ በባንኮች ላይ የተጣለው አስገዳጁ የ20 በመቶ ቦንድ ግዥ እንደሚሳ ብሔራዊ ባንክ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ጋር ያደረገው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ያስረዳል፡፡

ሪፖርተር
@etstocks
መንግስታዊዉ ባንክ የሆነዉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኢንዱስትሪው ያለዉ የገበያ ድርሻ ቀነሰ

ግዙፉ የፋይናንስ ተቋም የሆነዉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በባንክ ኢንዱስትሪው ላይ ያለዉ የገበያ ድርሻ ካለፈዉ ዓመት አኳያ ቅናሽ ማሳየቱ አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ሪፖርት አመላክቷል።

ባንኩ በ 2016 ሂሳብ ዓመት አጠቃላይ ሀብቱ እና የተቀማጭ ገንዘብ ከጠቅላላው የባንክ ዘርፍ ከግማሽ በታች ማለትም 47.9 በመቶ እና 47.1 በመቶ በቅደም ተከተል መሆኑን ተመላክቷል።

ይህም ባንኩ በ 2015 የነበረዉ ድርሻ ከባንክ ኢንዱስትሪው አጠቃላይ ሀብቱ 49.5 በመቶ የነበረ ሲሆን ተቀማጭ ገንዘብ ደግሞ 48.7 በመቶ መሆኑ ይታወቃል።

ብሔራዊ ባንክ በተጠናቀቀዉ ሂሳብ ዓመት የባንክ ኢንዱስትሪ የገበያ ድርሻ በሚመለከት ትልቅ ፣ መካከለኛ እና አነስተኛ በሚል በአፈፃፀማቸዉ ልክ አስቀምጧል።

በዓመቱ የገበያ ድርሻዉ ምንም እንኳን ዝቅተኛ ቢሆንም አሁንም በሀገሪቱ ከሚገኙ ባንኮች ትልቁን ድርሻ የያዘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነዉ።

እንደ ብሔራዊ ባንክ መረጃ አዋሽ ፣ አቢሲኒያ ፣ ዳሽን ፣ ኦሮሚያ እና ህብረት ባንክ መካከለኛ ባንኮች ተብለዉ ከተለዩ አምስቱ ተቋማቶች ሲሆኑ አጠቃላይ ሀብታቸው 28.9 በመቶ እና ተቀማጭ ገንዘባቸው ደግሞ 30.3 በመቶ መሆኑ ተገልጿል።

የተቀሩት 25 አነስተኛ ባንኮች ጥምር ንብረቶች እና ተቀማጭ ገንዘብ 23.3 በመቶ እና 22.7 በመቶ ድርሻ የያዙ ሲሆን ይህም ከአጠቃላይ የባንክ ዘርፍ እያንዳንዳቸው 0.8 በመቶ ጭማሪ ማሳየታቸውን ካፒታል ከሪፖርቱ ተመልክቷል።

Source: capitalethiopia
@ETstocks
28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መጭበርበራቸው ተሰምቷል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዓመታዊ የገንዘብ ደህንነት ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል፡፡

📌የባንኩ ሪፖርት እስከ ሰኔ 2024 ድረስ ያሉ የገንዘብ እንቅስቀሴዎች ዙሪያ ትኩረቱን አድርጓል፡፡

📌ባንኩ በሪፖርቱ ላይ እንደጠቀሰው፤ 28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በአጭበርባሪዎች ገንዘባቸውን አጥተዋል፡፡

📌የማጭበርበር ድርጊቶቹ የተፈጸሙት፤ በሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶች፣ በተሰረቁ የኤትኤም ማሽኖች፣ በሐሰተኛ ቼኮች፣ በሐሰተኛ የስልክ መልዕክት እና ተያያዥ መንገዶች አማካኝነት ነው፡፡

📌በዚህ ዓመት ባንኮች ያጡት ገንዘብ ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ300 ሚሊዮን ብር ጭማሪ እንዳሳየም በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡

📌በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ካሉ 31 ባንኮች ውስጥ 28ቱ ሲጭበረበሩ የቀሪዎቹ ሶስት ባንኮች ማንነት ግን በሪፖርቱ ላይ አልተጠቀሰም ሲል አል-ዐይን ዘግቧል፡፡
ንብ ባንክ በዘንድሮ ዓመት ሊከፋፈል የሚገባው የትርፍ ክፍያ ገንዘብ እንደማይኖር አሳወቀ!!

ንብ ባንክ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት ከግብር በፊት 1.2 ቢሊዮን ብር ማትረፉን እና ከግብር በኋላ ደግሞ 957.97 ሚሊዮን ብር እንዳተረፈ አሳውቋል።

ነገር ግን ለባለአክሲዮኖች ሊከፈል የሚገባው የትርፍ ድርሻ ቀደም ባሉ ዓመታት ለተሠሩ ስህተቶች የሒሳብ ማስተካከያ ሥራዎች እንዲውል ተወስኗል፡፡
 
ንብ ባንክ የT24 ሲስተም ለውጥ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ የፋይናንስ ችግር በተለይም የጥሬ ገንዘብ እጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ይምጣ እንጂ መነሻው ካለፉት አምስት ዓመታት ጀምሮ መሆኑ ተገልጿል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የባንኩ አጠቃላይ ዕዳ 56.7 ቢሊዮን ብር መሆኑ ታውቋል፡፡    

በሒሳብ ዓመቱ የባንኩ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን 45.1 ቢሊዮን ብር ነው። ይህም ካለፈው ዓመት አንፃር የ14.3 ቢሊዮን ብር ወይም የ24.1 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡

የባንኩ አጠቃላይ ካፒታል 10.4 ቢሊዮን ብር ሲሆን ካለፈው ዓመት የ1.5 ቢሊዮን ብር ወይም የ16.8 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡

የተከፈለ ካፒታሉም በ26.3 በመቶ አድጎ 7.6 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡

የንብ ባንክ አጠቃላይ ሀብት 67.0 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን ባንኩ የሰጠው ብድር ክምችት መጠንም ከአጠቃላይ ሀብቱ 72.3 በመቶ ነው፡፡

ባንኩ በ2016 የሰጠው አጠቃላይ ብድርና የቅድሚያ ክፍያዎች 49.2 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡ ካለፈው ዓመት የ4.6 ቢሊዮን ብር ቅናሽ አሳይቷል፡፡

የባንኩ ዓመታዊ ገቢ 10.8 ቢሊዮን ብር ሲሆን ካለፈው ዓመት የ1.9 ቢሊዮን ብር ዕድገት ማሳየቱን ተገልጿል።

የባንኩ አጠቃላይ ወጪው ደግሞ በ38 በመቶ ጨምሮ 9.6 ቢሊዮን ብር ሆኖ ተመዝግቧል

YouTube
TikTok
ቢትኮይን ለመጀመሪያ ጊዜ 100 ሺህ ዶላር መመንዘር ጀመረ‼️

በዚህም የአንድ ቢትኮይን ዋጋ በ100 ሺህ ዶላር በመመንዘር ላይ ሲሆን ይህም በዲጂታል መገበያያ ገንዘቡ ታሪክ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

የቢትኮይን ዋጋ እንዲህ ሊጨምር የቻለው ተመራጩ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የክሪፕቶ ከረንሲን የሚደግፉ ፖሊሲዎችን እንደሚቀበሉ በማሳወቃቸው መሆኑ ተገልጿል።

ትራምፕ የቀድሞን የአሜሪካ የሴኪውሪቲስ እና ኤክስቼንጅ ኮሚሽነር ፖል አትኪንስ የሃገሪቱ የስቶክ ገበያ የሆነውን ዎል ስትሪት እንዲመሩ ማጨታቸው ከተሰማ ከሰዓታት በኋላ የቢትኮይን ዋጋ እንዲጨምር ምክንያት መሆኑም ተነግሯል፡፡

ሚስተር አትኪንስ አሁን ካሉት የሴኪውሪቲስ እና ኤክስቼንጅ ኮሚሽን ኃላፊ ጋሪ ጌንስለር የበለጠ የክሪፕቶ ከረንሲ ደጋፊ ስለመሆናቸውም ነው የተገለፀው።

ዶናልድ ትራምፕ ምንም እንኳን ከዚህ በፊት ክሪፕቶከረንሲን የተቹ ቢሆንም አሁን ግን አሜሪካን የምድራችን የክሪፕቶከረንሲ መዲና አደርጋታለሁ ሲሉ ቃል መግባታቸውን ተከትሎ የቢትኮይን ዋጋ እየናረ መምጣቱ ተጠቁሟል።

በተለይም ባለፈው ወር ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ካሸነፉ በኋላ የቢትኮይን ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ ሲያሳይ መቆየቱ ነው የተገለፀው።

አንዳንድ ትልልቅ ኩባንያዎችና ተቋማት ቢትኮይንን እንደ ገንዘብ መቀበል መጀመራቸውም ለተፈላጊነቱ ማደግ ሌላ ምክንያት ነው ተብሏል።

የዲጂታል መገበያያ ገንዘቡ 100 ሺህ ዶላር መግባቱን ተከትሎ በዓለም ዙሪያ ያሉ የቢትኮይን ተጠቃሚዎች እና ደንበኞች ደስታቸውን እየገለፁ መሆኑን የዘገበው ቢቢሲ ነው።

Source: BBC
የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ለውጭ ውድድር ሊከፈት መሆኑ ተሰማ

ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የባንክ ዘርፉን ለውጭ ውድድር ለመክፈት በዝግጅት ላይ ትገኛለች። ይህን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት አዲስ ህግ በፓርላማ እየተገመገመ እና በሚቀጥለው ወር ይፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

ይህ ውሳኔ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ገጽታ ላይ ከፍተኛ ለውጥን የሚያመለክት ሲሆን ይህም ውድድርን ለማሳደግ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እና የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ያለመ ነዉ ተብሏል ።

ርምጃው በኢትዮጵያ መንግስት እና በብሄራዊ ባንክ የተጀመሩት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች አካል ሲሆን እነዚህ ማሻሻያዎች የተነደፉት የፋይናንስ ሴክተሩን ለማዘመን እና ለሀገር ውስጥ እና ለአለም አቀፍ ንግዶች የበለጠ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ጭምር ነዉ።

የውጭ ባንኮችን ወደ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ምኅዳር ማስገባቱ ፉክክር እንደሚያመጣ የሚጠበቅ ሲሆን ይህም ለተጠቃሚዎች የተሻሻሉ አገልግሎቶችን እና ምርቶችን ሊያመጣ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።

ህጉ የውጭ አካላት በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ እንዳይሳተፉ በታሪክ የሚገድቡ እንቅፋቶችን ለመበተን ያለመ ነው። የውጭ ባንኮች ከአገር ውስጥ ተቋማት ጋር አብረው እንዲሠሩ በመፍቀድ፣ መንግሥት የፋይናንስ አካታችነትንና ፈጠራን ሊያጎለብት የሚችል ዓለም አቀፍ እውቀትና ካፒታል ለመጠቀም ያለመ መሆኑ ታዉቋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ በቅርቡ በተካሄደዉ እና የአውሮፓ ምክር ቤት በኢትዮጵያ ባዘጋጀው ዝግጅት እንደተናገሩት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ ማሻሻያው ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል ።

ከዚህ በተጨማሪ የግሉ ሴክተር በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ያለው ፍላጎትና ተሳትፎ በተለይም የውጪ ንግዶች ለእድገት ፍፁም ወሳኝ ናቸዉ ሲሉም አክለዋል ።
እስላሚክ ካፒታል ገበያ!!

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የእስላሚክ ካፒታል ገበያን ኢትዮጵያ ውስጥ ለማስተዋወቅ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ማድረጉ ዋዜማ ሚዲያ ጠቁሟል።

ይህ ፕሮጀክት የአምስት ወራት ቆይታ ያለው መሆኑ እና ለእስላሚክ ካፒታል ገበያ የሕግ ማዕቀፍ ለማበጀት ጠቃሚ እንደሆነ ተገልጿል።

ባለሥልጣኑ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የልማት ፕሮግራምና ሌሎች አሕጉራዊ ተቋማት ጋር በመተባበር ነው የሚሰራው ተብሏል።

የዓለማቀፉ እስላሚክ ፋይናንስ የምክር አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ እስላሚክ የካፒታል ገበያ ለማቋቋም ብሄራዊ ባንክንና የኢትዮጵያ ሙዓለ ንዋይ ገበያን ጨምሮ በርካታ ባለድርሻዎች የተሳተፉባቸውን ግምገማዎችና አውደ ጥናቶችን ማካሄዱን ተገልጿል።

በፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ላይ ይሄው አማካሪ ኩባንያ የእስላሚክ ካፒታል ገበያ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ ያቀርባል ተብሏል።
Oromia Insurance Company achieves remarkable growth in 2023/24 solidifying its market position in Ethiopia’s insurance industry

Oromia Insurance (OIC) has announced impressive financial results for the fiscal year ending June 30, 2024, reinforcing its position as one of Ethiopia’s premier private insurers. Despite the challenges posed by a volatile economic landscape, OIC has made substantial strides in expanding its services, delivering exceptional results, and achieving key milestones throughout the fiscal year ending June 30, 2024, across multiple key indicators.

Website (https://www.condoaddis.com/category/etstocks )
| Facebook (https://www.fb.me/etstocks)
| X (https://www.X.com/@etstocks1)
| TikTok (https://www.tiktok.com/@etstocks
| Linkedin (https://www.linkedin.com/company/etstocks)
|Youtube (https://www.YouTube.com/@etstocks)
ግዙፉ የአሜሪካው የቢትኮይን ኩባንያ "ቢ አይ ቲ" ኢትዮጵያ ውስጥ ከቢትኮይን መረጃ ማቀነባበሪያ ማዕከል ከፍተኛ የአክሲዮን ድርሻ በመግዛት ኢንቨስትመንቱን ሊያስፋፋ እንደኾነ አስታውቋል። ኩባንያው እስከ ሚያዝያ ድረስ በክሪፕቶ መረጃ ማቀነባበሪያ ማዕከላት ተጨማሪ ድርሻዎችን በመግዛት 51 ሜጋዋት ኃይል የሚጠቀም ማዕከል ባለቤት እንደሚኾንም ገልጧል። ኩባንያው፣ ይህንኑ ሂደት ሲያጠናቅቅ በጠቅላላው 45 ሚሊዮን 278 ሺሕ የአክሲዮን ድርሻዎችን ለመሸጥ እንዳሰበ አመልክቷል።
ምንም እንኳን በየሰኮንዱ ዋጋው ቢቀያየርም አንድ Bitcoin በቅርቡ 100,000 ዶላር መሸጡ ይታወሳል።
አማራ ባንክ ከታክስ በፊት ከ550 ሚሊየን ብር በላይ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።

በ2013 ከ180 ሺህ በላይ ባለ አክሲዮኖች የተመሰረተው አማራ ባንክ ባለፉት አመታት ኪሳራዎች ገጥመውት እንደነበር ይታወሳል።

እየተጠናቀቀ ባለው የፈረንጆቹ 2024 ሰኔ ወር ድረስ ከገባበት ኪሳራ በመውጣት ከ550 ሚሊየን ብር በላይ ጠቅላላ ትርፍ ማስመዝገቡን የባንኩ 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተነግሯል።

ባንኩ ከ801 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞችን አግኝቻለሁ ያለ ሲሆን በዚህም አጠቃላይ የደንበኞቹን ቁጥር ከአንድ ሚሊየን ስምንት መቶ ሺህ በላይ ለማድረስ መቻሉ ነው የገለፀው።

የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ ጋሻው ደበበ ባለፈው አመት በባንክ ኢንደስትሪው አወንታዊና አሉታዊ ሁኔታዎችን የፈጠሩ አለም አቀፋዊና አገራዊ ክስተቶች ማጋጠማቸውን አስታውሰው የተፈጠሩት ጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል በኢኮኖሚው ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩን ጠቁመዋል።

በሀገሪቱም በአንዳንድ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች ተደማምረው አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደራቸውን ተናግረዋል።

አማራ ባንክ በ3ኛው የባለ አክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ 43 አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመጨመር የቅርንጫፎቹን ብዛት 310 ማድረሱ የተገለፀ ሲሆን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎትን የሚሰጡ ቅርንጫፎቹም ብዛት 15 ደርሰዋል።
ስኬት ባንክ ክፍተኛ የፋይናንሻል ዕድገት በማሳየት 1.54 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ አስመዝግቧል። ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ50 በመቶ ብልጫ አለው። ይህ አፈጻጸም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከሚጠይቀው ዝቅተኛ የካፒታል መስፈርት ብልጫ ያለው የተከፈለ ካፒታል የ25 በመቶ እድገት አሳይቷል፣ አሁን 5.46 ቢሊዮን ብር ደርሷል።

ቁልፍ ውጤቶች
📈 በአጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ 36 በመቶ እድገት፣ 4.9 ቢሊዮን ብር ደርሷል
📈 የብድር ፖርትፎሊዮን አሁን በ9 ቢሊዮን ብር ሰፍቷል
📈 8% የተሰበሰበ ዕዳ ጨምሯል፣ በአጠቃላይ 4.2 ቢሊዮን ብር
📈 አጠቃላይ ገቢው 41% ከፍ ያለ ሲሆን 2.37 ቢሊዮን ብር ሲሆን 75% በወለድ ገቢ

በጠቅላላ ወጪው የ28 በመቶ እድገት ቢኖረውም፣ 828.5 ሚሊዮን ብር ቢደርስም፣ ስኬት ባንክ ጤናማ የትርፍ አስመዝግቧል።
የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ጥር ወር 2017 ዓ.ም ስራ እንደሚጀምር ተገለፀ!!

የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጥላሁን ኢስማኤል (ዶ/ር) ባለፈው አንድ ዓመት ኩባንያውን እውን ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ገልፀዋል።

ገበያው የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ሽያጭ፣ ግዥ እና ልውውጥ በቋሚነት የሚደረግበት ሲሆን ለመንግሥትና የግሉ ዘርፍ የገንዘብ ምንጭ በመሆን ለምጣኔ ኃብት እድገት ጠቃሚ መሆኑን ገልፀዋል።

መንግስት እና የግሉ ዘርፍ ለሚያከናውኗቸው ኢንቨስትመንቶች ካፒታል ለማሰባሰብ አቅም እንደሚጨምር ይጠበቃል።

በሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ አክስዮን የሚሸጡ ኩባንያዎች በየጊዜው የሂሳብ ሁኔታቸው እየተገመገመ ይፋ የሚሆንበት አሰራር መዘርጋቱ ተጠቁሟል።

ይህ ጅምር የኢትዮጵያን አዲስ የካፒታል ገበያ ለማራመድ የተቀናጀ ሲሆን ከኢንተር ባንክ ስራዎች ባሻገር ለንግዶች እና ባለሀብቶች አዳዲስ እድሎችን የሚከፍት ቀልጣፋ የገበያ ቦታ ነው።
Vacancy Announcement for Fresh Graduates
-------------------------------------
Abay Bank S.C. invites interested and qualified applicants for Customer Service Officer (CSO)-II position.

For detail information, please visit our website with the link attached below.
https://www.abaybanksc.com/vacancy-announcement-8/

Follow our social media pages for new vacancy announcements.
ፌስቡክ (http://www.facebook.com/abaybanksharecompany)
ቴሌግራም (https://t.me/abaybanksharecompany)
ትዊተር (https://twitter.com/AbayBank)
ሊንክድኢን (https://www.linkedin.com/company/abaybank)
ዩትዩብ (https://www.youtube.com/@abaybank4665)
ቲክቶክ (https://www.tiktok.com/@abaybank)

Good Luck!p
አንበሳ ኢንሹራንስ በኢንዱስትሪዉ ከፍተኛዉን የአርቦን ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አስታውቋል

በኢንዱስትሪ ደረጃ በበጀት ዓመቱ በጠቅላላ መድን ዘርፉ ብር 28.3 ቢሊዮን አረቦን የተሰበሰበ ሲሆን፤ የአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ ደግሞ ብር 1.178 ቢሊዮን የእረቦን ገቢ በማስመዝገብ የገበያ ድርሻውን 4.38 በመቶ ማድረስ መቻሉን ገልጿል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከጠቅላላ መድን ዘርፍ ብር 1.15 ቢሊዮን እና ከህይወትና ጤና መድን ዘርፍ 23.1 ሚሊዩን በድምሩ ብር 1.173 ቢሊዮን የአረቦን ገቢ በማስመዝገብና ግብርና ህጋዊ መጠባበቂያ ተቀንሶ የተገኘው የተጣራ ትርፍ 185.3 ሚሊዮን ብር መሆኑን በሪፖርቱ ጠቁሟል።

ይህ የተባለው ኩባንያው ባካሄደው 17ኛ የባለ-አክሲዮኖች መደበኛ ጉባኤ ላይ ነዉ ። በዚህም በተጠናቀቀዉ ሂሳብ ዓመት አንበሳ ኢንሹራንስ አጠቃላይ ሃብት ብር 2.78 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን፤ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃጸር የብር 705.9 ሚሊዮን ወይም 33.9 በመቶ እድገት ማስመዝገብ ችሏል ብሏል።