ET Securities
693 subscribers
614 photos
7 videos
30 files
314 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
#NBE #FOREX
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮ ለመከፈት የሚፈልጉ የሥራ ፈቃድ መስጠት መጀመሩን አስታዉቋል

በገበያ ላይ ተመሥርተው የውጭ ምንዛሪ በጥሬ ገንዘብ መሸጥና መግዛት የሚፈልጉ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች እንዲቋቋሙ በተፈቀደው መሠረት ብሔራዊ ባንክ ይህኑ ፍቃድ መስጠት ጀምሬያለሁ ብሏል።

የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች መቋቋም የውጭ ምንዛሪ ገበያን መሠረት ለማስፋትና ለማጠናከር እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ በጥሬ ገንዘብ ለመሸጥም ሆነ ለመግዛት የሚሹ ደንበኞችን ፍላጎት ለማሳካት እንደሚረዳ ይታመናል ብሏል ባንኩ ባወጣዉ መግለጫ ።

የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች እንዲከፈቱ የሥራ ፈቃድ መስጠት መጀመሩን የገለፀው ባንኩ ይህ እርምጃ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስትመንት ለመክፈትና ዘርፉን በቀጣይ ዓመታት ተወዳዳሪ ለማድረግ የተጀመርነው አዲስ ምዕራፍ መሆኑ ገልጿል።

Condoaddis.com/240809-3
#Afdp #DashenBank
የአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድን ዳይሬክተሮች ቦርድ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ የመጀመሪያ የሆነውን ለዓለም አቀፍ ንግድ ልውውጥ ዋስትና የሚውል 40 ሚሊዮን ዶላር ለዳሸን ባንክ አፅድቋል።

የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ ባንካችን የአፍሪካ ልማት ባንክ ያስቀምጣቸውን ጥብቅ ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላቱ ይህ 40 ሚሊዮን ዶላር የንግድ ፋይናንስ ልውውጥ ዋስትና ማዕቀፍ በመፈቀዱ በጣም ደስተኞች ነን። ይህም ባንካችን በክፍለ አህጉሩና ከዚያም ባለፈ የንግድ አገልግሎታችንን ለማሳደግ በጣም  አስፈላጊ ድጋፍ ነው ብለዋል።

ይህን  ድጋፍ ለማግኘት ያሟላቸው ቅድመ ሁኔታዎች እና በሂደቱ የተገኙ የልምድ ልውውጦች ዳሸን ባንክ ከአፍሪካ ተመራጭ እና ቀዳሚ ባንኮች ተርታ ለመሰለፍ ያለውን ራዕይ ዕውን ለማድረግ እንደ ግብአት እንደሚጠቅም አመልክተዋል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ቢሮ ዳይሬክተር ጀነራል ኔና ኑዋቡፎ በበኩላቸው የአፍሪካን ንግድ መደገፍ ባንካችን ተቀዳሚ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው። ይህም የአህጉሩን የኢኮኖሚ ዕድገት ለመጨመርና ድንበር ዘለል ንግድ ለማሳደግ ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል።

ባንኩ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ያገኘው ይህ የድጋፍ ማዕቀፍ ባንኩ በዓለም አቀፍ ንግድ ልውውጥ ያለውን ተቀባይነት እና ተመራጭነት ይበልጥ እንደሚያሳድገው ተመልክቷል።

የፋይናንስ አቅርቦቱ ዳሸን ባንክ አነስተኛና መካከለኛ ተቋማት እንዲሁም ሌሎች አገር በቀል ድርጅቶች ምርት ለመላክና ለማስመጣት የሚፈልጉትን አቅርቦትና ዋስትና እንዲያገኙ ዕድል እንደሚፈጥር ተገልጿል።

የገንዘብ አቅርቦቱ ለኢትዮጵያ በጣም አስፈላጊ የሆኑ እንደ ማዳበሪያ፣መድሃኒት፣የሶላር ሃይል ማመንጫ፣የግብርና ማሽነሪዎችና ሌሎች ምርቶችን ለማስገባት ያግዛል።

Condoaddis.com/240809-4
#Forex #NBE
የውጭ ምንዛሬ (Forex) ቢሮ ፍቃድ ለማውጣት መስፈርቶች!

ነፃ የውጭ ምንዛሪ ቢሮ (In dependent Forex Bureau) የውጭ ምንዛሪ ጥሬ ገንዘብ ኖቶችን #በመግዛትና #በመሸጥ ላይ ብቻ የሚሰማራ እንጂ በሌላ የባንክ ሥራ ላይ መሰማራት የለበትም።

1. በማንኛውም ህጋዊ መንገድ የተቋቋመ፣ በኢትዮጵያዊ ዜጋ፣ ነዋሪ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ እና/ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጋ የሆነ የተቋቋመ የንግድ ድርጅት፤

2. ዝቅተኛውን የብር 15 ሚሊዮን ካፒታል አሟልቷል እናም 30 ሚሊዮን ብር የደህንነት ማስያዣ በተዘጋ አካውንት (ወለድ ሊያስገኝ ይችላል) በማንኛውም ባንክ ማቅረብ የሚችል፤

3. የደህንነት ማስያዣ ተቀማጭ ገንዘብ ፊት ዋጋ በገለልተኛ Forex ቢሮ ለሁለት ዓመታት ከቀጠለ አገልግሎት ይለቀቃል፤

4. የውጭ ምንዛሬ (Forex) ቢሮን ንግድ ለመፈፀም በሁሉም ረገድ ተስማሚ የሆነ እና ብሔራዊ ባንክ እንደ ባንክ ላሉ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ያስቀመጠውን የደህንነት እና የደህንነት መስፈርቶችን የሚያሟላ፤

5. የውጭ ምንዛሬ (Forex) ቢሮ አድራሻን የሚያመለክት የስም ሰሌዳ፤

6. የውሸት ማስታወሻዎችን ለመለየት አስፈላጊ መሳሪያ መያዝ፤

7. የውጭ ምንዛሬ (Forex) ቢሮ ሰራተኞችን ስም ዝርዝር እና ስያሜ መስጠት፤

8. የውጭ ምንዛሬ (Forex) ቢሮ ሰራተኞች የማጭበርበር ፣የማታለል እና የሙስና መዝገብ የሌላቸው ታማኝ ፣ታማኝነት እና ብቃት ያላቸው ሰዎች መሆናቸውን ማረጋገጥ፤

9. በማንኛውም የውጭ ምንዛሬ (Forex) ቢሮ ሳይት የሚገኘውን ከፍተኛውን የገንዘብ መጠን ለመሸፈን በቂ ኢንሹራንስ መግዛቱን ያረጋገጡ።

Condoaddis.com/240810-1
AliExpress, a major online retail service owned by Alibaba Group, is set to enter the Ethiopian market, according to Abiyot Bayu (PhD), a Senior Advisor to the Minister of Innovation and Technology. In an interview with Shega, Dr. Abiyot confirmed that an agreement has been reached, and an official announcement will be made soon.

This development follows a virtual meeting on August 7, 2024, between Ethiopian officials and an Alibaba team led by Chandee Zhuang, Senior Advisor at Alibaba Global Initiatives. The entry of AliExpress into Ethiopia aligns with the country’s recent reforms aimed at attracting foreign direct investment, which could have a significant impact on the nation’s economic landscape.

Condoaddis.com/240809-2-2
NBE to suspend mandatory bond purchases for banks, aiming to boost liquidity

The National Bank of Ethiopia (NBE) has announced that it will suspend the two mandatory bond instruments that banks were required to buy, even though it anticipated that Treasury bonds (T-bonds) alone would bring in 50 billion birr during the current fiscal year.

Regarding the introduction of the economic reform program on July 29th, the administration has pledged to implement several changes throughout the economy, including the banking sector.

Following a deal negotiated with international partners, such as the International Monetary Fund (IMF), the central bank has committed to suspending T-bonds by the end of this year and Development Bank of Ethiopia (DBE) bonds by the end of 2025, respectively.


Read more
Ethiopia’s Securities Exchange Signs Agreement for Trading Platform

Ethiopia’s securities exchange is set to receive a major technological upgrade, having signed two landmark agreements for an Electronic Trading Platform (ETP) and a Broker Back Office and Order Management System (BBOMS).

Read More

@etstocks
በብሔራዊ ባንክ ተመን የአንድ ግራም ወርቅ ዋጋ ስንት ደረሰ?
ብሄራዊ ባንክ እለታዊ የወርቅ መግዣ ዋጋ ይፋ በማድረግ ላይ ይገኛልብሔራዊ ባንክ ወርቅ የሚገዛው በዓለም አቀፍ እለታዊ ዋጋ መሆኑን አስታውቋል

ብሔራዊ ባንክ ከምንዛሬ ስርአት ለውጥ በኋላ ወርቅ የሚገዛው በአለምአቀፍ እለታዊ ዋጋ መሆኑን መግለጹን ተከትሎ እለታዊ የወርቅ መግዣ ዋጋ በድረ ገጹ ይፋ እያደረገ ይገኛል።

በእየለቱ በምን ያህል የውጭ ምንዛሬ ወርቅ እንደሚገዛ በጽረ-ገጹ ይፋ እንደሚያደርግ የገለጸው ባንኩ፣የዛሬ የወርቅ መግዣ ዋጋን ይፋ አድርጓል።

ብሔራዊ ባንክ 1 ግራም ወርቅ በስንት ብር እየገዛ ነው?
በዚህም መሰረት ባለ 24 ካራት 1 ግራም ወርቅ 79.2074 የአሜሪካ ዶላር ወይም በእለቱ የብሄራዊ ባክ የምንዛሬ ዋጋ 8 ሺህ 834.4113 ብር እየገዛ መሆኑን አስታውቋል።

ባለ 23 ካራት 1 ግራም ወርቅ 75.9071የአሜሪካ ዶላር ወይም በእለቱ የብሄራዊ ባክ የምንዛሬ ዋጋ 8 ሺህ 466.3108 ብር እየገዛ መሆኑን የባንኩ መረጃ ያመለክታል።

ባለ 22 ካራት 1 ግራም ወርቅ 72.6068 የአሜሪካ ዶላር ወይም በእለቱ የብሄራዊ ባክ የምንዛሬ ዋጋ 1 ሺህ 098.2104 ብር እየገዛ መሆኑን ባንኩ አስታውቋል።

ባለ 21 ካራት 1 ግራም ወርቅ 69.3065 የአሜሪካ ዶላር ወይም በእለቱ የብሄራዊ ባክ የምንዛሬ ዋጋ 7 ሺህ 730.1099 ብር እየገዛ ይገኛል።

ባለ 20 ካራት 1 ግራም ወርቅ 66.0062 የአሜሪካ ዶላር ወይም በእለቱ የብሄራዊ ባንክ የምንዛሬ ዋጋ 7 ሺህ 362.0094 ብር እየገዛ መሆኑን ነው ባኩ በድረ ገጹ ያወጣው መረጃ ያሚያመለክተው።
Official and Parallel Exchange Rates—Recognizing Reality.pdf
2 MB
IMF በ2021 ስለ መደበኛ እና የጥቁር ገበያ ምንዛሬን ስለማቀራረብ (Recognizing Reality፡ Unification of Official and Parallel Exchange Rates) ሪፎርም የሰሩ ሀገራትን ሁኔታ የተነተነበት የጥናት ሰነድ ነው! ምንዛሬን በገበያ የመወሰን ጉዳይ ላይ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ለምትፈልጉ ሰዎች! https://www.condoaddis.com/category/etstocks
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የ2025 በጀት ዓመት የሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል።

በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 4.6 ሚሊዮን የሚሆኑ ንቁ ደንበኞች በተከታታይ ባሉ 90 ቀናት ውስጥ የሳፋሪኮምን ኔትወርክን መጠቀማቸውን ያመለክታል።

በተከታታይ ባሉ 30 ቀናት የሳፋሪኮምን ኔትዎርክ የተጠቀሙ ንቁ ደንበኞቹ ቁጥር ደግሞ 3.4 ሚሊዮን እንደሆነ ገልጿል።

(ይህ ማለት ሳይጠቀሙ 90 ቀን ወይም 30 ቀን ያለፋቸው ደንበኞች ንቁ ተጠቃሚ በሚለው ውስጥ አይካተቱም።)

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል አገልግሎቱን ከጀመረ በኋላ ባሉት ጊዜያት ከፍተኛ የደንበኞች ቁጥር ማግኘቱን አስታውቋል።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት በተከታታይ ባሉ 30 ቀናት የተጠቀሙ ደንበኞቹ ቁጥር በዚህ ደግሞ 2.4 ሚሊዮን ደንበኞች ናቸው።

በሪፖርቱ እንደተጠቀሰው አንድ የሳፋሪኮም ደንበኛ በወር ውስጥ በአማካይ 6.5 GB ኢንተርኔት ይጠቀማል።

ተቋሙ በቅርቡ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ክፍያ በኤም ፔሳ መክፈል የሚያስችል ሥርዓት ከዘረጋ በኋላ 3ሺ 500 ደንበኞች ማስተናገዱን ገልጿል። በዚህም 13 ሺ ክፍያዎች የተስተናገዱ ሲሆን 8.1 ሚሊየን ብር ክፍያ ተፈጽሟል።

በተጠቀሰው ጊዜ 2 ቢሊዮን የኬንያን ሽልንግ (1.6 ቢሊየን ብር ) በላይ ገቢ መገኘቱን የገለጸው ተቋሙ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው ከኢንተርኔት አገልግሎት ያገኘው እንደሆነ አስታውቋል። ይህም ከገቢው 78 በመቶ የሚሆነውን የሚሸፍን ነው።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአማካኝ ኢንተርኔት የሚጠቀሙ ደንበኞቹ 244.7 የኬንያ ሽልንግ (196.6 ብር) በወር የሚያወጡ ሲሆን ከአጠቃላይ አገልግሎቱ 155.3 የኬንያ ሽልንግ (124.8 ብር) በወር ያወጣሉ።

Source: tikvahethmagazine
@Etstocks
የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ   ዓለም አቀፍ የካፒታል ገበያ የቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን አቅራቢ ከሆነው ከኢንፎቴክ ፕራይቬት ሊሚትድ ጋር ሁለት የቴክኖሎጂ ስምምነቶችን መፈራረሙን ገልጿል ።

የሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያው ከአለም አቀፉ የቴክኖሎጂ አቅራቢ ጋር አድርጌያለሁ ያላቸዉ ስምምነቶች  የኤሌክትሮኒክ መገበያያ መድረክ እና የደላላ የኃላ ቢሮ እና የትዕዛዝ አስተዳደር ስርዓት ናቸዉ።

እነዚህ ስርዓቶች ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ እና ግልጽ የካፒታል ገበያ በኢትዮጵያ እንዲመሰረት፣ ንግዱን በማሳለጥ አጠቃላይ የገበያ መሠረተ ልማትን ለማሳደግ ወሳኝ ናቸው ተብሏል።

በመጪው ጥቅምት ወር ስራ ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቀው ገበያዉ ትላንት ያደረገዉ ባደረገው ስምምነት መሰረት አዲሱ ሥርዓት ኢንቨስተሮችን ተቀብሎ የመመዝገብ፣ ትዕዛዞችን የመቀበል፣ ሪፖርት የማድረግ፣ ግብይትን ማቀነባበር እና የመሳሰሉትን ዋና ዋና ተግባራትን እንደሚያስተናግድ ይጠበቃል ።

Read more
Currency Exchange Rates and the Need for Forward Exchange Rate Market Financial Instruments: A Call for New Competencies in Local Banks

It is essential to distinguish between an individual currency and an exchange rate. While one can possess a specific currency, an exchange rate indicates the value of one currency in relation to another (for instance, the exchange rate between the Birr and the USD).

Read More

Source: capitalethiopia
@Etstocks
አሊባባ

እ.ኤ.አ በ1999 በጃክ ማ የተመሰረተው አሊባባ ኩባንያ፡ የኢ-ኮሜርስ፣ የክፍያ ስርዓት፣ የገበያ መረጃና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ያካተተ ሁለገብ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ነው።

አሊባባ በቻይና ውስጥ የኢ-ኮሜርስ ለውጥ ያመጣ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃም ቢሆን በተለይም አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች (SME's) ወደ ገበያ እንዲደርሱ እና ስራቸውን እንዲያስፋፉ ረድቷል። ከዚህ በተጨማሪም የአሊባባ ሎጂስቲክስ በዓለም ደረጃ የሎጂስቲክስ ኢንዱስትሪውን እንደቀየረ ይታመናል። በአሊባባ የቴክኖሎጂ ካምፓኒ ከሚሰጡ አገልግሎቶች መካከል የሚከተሉት በዋናነት ይጠቀሳሉ :-

🥢 Alibaba.com - A B2B platform connecting global buyers and suppliers.
🥢 Taobao - A C2C platform similar to eBay, popular for a wide range of products.
🥢 Tmall - A B2C platform featuring branded products and stores.
🥢 Alipay - A mobile and online payment platform. 🥢 Alibaba Cloud - A cloud computing service provider.

አሊባባ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በርካታ የኤክስፖርት እድሎችን የሚፈጥር ሲሆን በተለይ . . . .

Read more
የአሜሪካ ዶላር ለመግዛት ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነው።