#ዜና
የተለያዩ የሃገር ውስጥ እና የውጪ ሚድያዎች በዚህ ሳምንት ያስነበቡን ታላቅ ዜና!
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2012 –
የኢትዮጵያ ሴኩሪቲስ ልውውጥ (ESX) መመስረት በመጨረሻ በ2020 ከወጣው የመጀመሪያ ማጠናቀቂያ ማስታወቂያ በኋላ እየተከሰተ ያለ ይመስላል።
የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና ኤፍኤስዲ አፍሪካ ESXን ለመመስረት የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።
"በሀገራችን ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው የሆነው የሴኩሪቲስ ልውውጡ መመስረት በእንደዚህ አይነት የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ለኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ እና ለአጠቃላይ ኢኮኖሚው አዲስ ምዕራፍ ይፈጥራል። ዛሬ በገንዘብ ሚኒስቴር፣ በEIH እና በኤፍኤስዲ አፍሪካ መካከል የተደረገው የትብብር ስምምነት ራዕያችንን እውን ለማድረግ የመጀመሪያው ተጨባጭ እርምጃ ነው ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ ከፊርማው ሥነ ሥርዓት በኋላ ተናግረዋል።
በተፈረመው ስምምነት ኤፍኤስዲ አፍሪካ ተግባራዊ ልውውጥ እንዲኖር ሁሉንም ጉዳዮችን ከሞላ ጎደል ይደግፋል።
በደርግ ጊዜ ሲንቀሳቀስ ከነበረው የአዲስ አበባ አክሲዮን ዲሊንግ ቡድን ውጪ፣ ኢትዮጵያ እስካሁን የካፒታል ገበያን መፍጠር አልቻለችም።
fb.me/Etstocks

Forwarded from ET Securities
የአክሲዮን ዋጋ ምንድን ነው?
የአክሲዮን ዋጋ የሚለው ስያሜ የሚያመለክተው የአክሲዮን ድርሻ በገበያ ላይ የሚነግደውን የአሁኑን ዋጋ ነው።
የአክሲዮን ዋጋ
እያንዳንዱ የሕዝብ ንግድ ኩባንያ ድርሻው ሲወጣ ዋጋ ይሰጠዋል ፤ ይህም የኩባንያውን ዋጋ በሚገባ የሚያንጸባርቅ ነው ። በአጠቃላይ በኢኮኖሚው ውስጥ የሚከሰቱ ለውጦችን፣ በኢንዱስትሪዎች ውስጥ የሚከሰቱ ለውጦችን፣ የፖለቲካ ክስተቶችን፣ ጦርነትን እና የአካባቢ ለውጥን ጨምሮ የአክሲዮን ዋጋ ከተለያየ ምክንያቶች ጋር ሲነፃፀር ዝቅ ይላል።
የአንድ ኩባንያ የአክሲዮን ዋጋ መቀየር
ማንኛውም የአክሲዮን ዋጋ ለውጥ ከሚያደርጉ ሌሎች ነገሮች በተጨማሪ በአንድ ኩባንያ ውስጥ የአክሲዮን ዋጋው ወደ ሁለቱም አቅጣጫ እንዲቀየር የሚያደርጉ ጉዳዮች ሊኖሩ ይችላሉ።
1. የአቅርቦትና የፍላጎት ሕግ
አንድ ኩባንያ ሌሎች ብዙ ምርታ ወይም ከፍተኛ ፍላጎት ወይም አስፈላጊ የሆነ ጥሩ ምርት የሚያመርት ከሆነ ተፈላጊነቱ ከፍተኛ በመሆኑ የአክስዮን ዋጋ ይጨምራል። ጥሩው አቅርቦት ከተፈላጊነቱ ጋር በሚመጣጠንበት ጊዜ የአክሲዮን ዋጋ ከፍተኛ ይሆናል። አቅርቦቱ ከተፈላጊው በላይ ከሆነ የኩባንያው ድርሻ ዋጋ ሊቀንስ ይችላል።
በተጨማሪም ኩባንያው ጥሩውን ምርት ውጤታማና ልዩ በሆነ መንገድ በማምረት ላይ የተመካ ነው ። በአሮጌ መስፈርት ላይ ልዩነት ከፈጠሩ፣ የድርሻቸው ዋጋ ከፍ ያለ ቢሆንም እንኳ ተመሳሳይ ሆኖ ሊቆይ ወይም ሊጨምር ይችላል።
በመጨረሻም, በእርግጥ ስለ አቅርቦት እና ፍላጎት ሕግ ነው.
2. አስተዳደር ወይም የምርት ለውጥ
በአስተዳደር ወይም በምርት ላይ የሚከሰቱ ለውጦችም የአንድ ኩባንያ ድርሻ ዋጋ ከፍ እንዲል ወይም እንዲቀንስ ሊያደርጉ ይችላሉ። ኩባንያው ውጤታማና ውጤታማ በሆነ መንገድ በሚተዳደርበትና ሸቀጦችን በሚመረትበት መንገድ ላይ የተመካ ነው ። የአስተዳደር ቡድን፣ የአጻጻፍ ስልት ወይም ሸቀጦች እንዴት እንደሚመረቱ መለወጥ ውጤታማነትን እና አጠቃላይ ውጤታማነትን ሊጨምር ይችላል - ትርፍ መጨመር እና የሽያጭ ዋጋ እንዲጨምር ያደርጋል። ይሁን እንጂ አሉታዊ ለውጦች ፍጹም ተቃራኒ ውጤት ሊያስከትሉ ይችላሉ።
3. የኩባንያውን ስም መጥቀስ
በአክሲዮን ዋጋ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችል ሌላው የማስታወሻ ነጥብ ደግሞ ኩባንያው ስም በዜና፣ በማህበራዊ ሚዲያ ወይም በቃል መጠቀሱ ነው። በተለይ ከሁለት ክንውኖች መካከል አንዱን ማለትም ቅሬታን ወይም ስኬትን በተመለከተ ነው ።
ቅሌቶች – እውነተኛ ወይም እውነት ያልሆኑ – ከአሉታዊ ነገር ጋር በመዛመድ ብቻ የአንድ ኩባንያ ድርሻ ዋጋ እንዲቀንስ ሊያደርጉ ይችላሉ. በተጨማሪም, በገበያ ወይም በየኢንዱስትሪው ውስጥ አንድ ግኝት ጋር መገናኘት, ወይም ተጠያቂ መሆን አብዛኛውን ጊዜ የአክሲዮን ዋጋ እንዲጨምር ያደርጋል.
የአክሲዮን ዋጋ፣ ገቢና ባለድርሻ አካላት
የአክሲዮን ዋጋ በመጀመሪያ የሚወሰነው አንድ ኩባንያ ለመጀመሪያ ጊዜ ድርሻውን ወደ ገበያ በሚያስገባበት ጊዜ መጀመሪያ ላይ በሕዝብ ፊት በሚያቀርበው መዋጮ (IPO) ነው። የኢንቨስትመንት ድርጅቶች የአክሲዮን ዋጋ ምን መሆን እንዳለበት ለመወሰን የተለያዩ መለኪያዎችን ይጠቀማሉ። ከዚያ በኋላ ከላይ የተጠቀሱት በርካታ ምክንያቶች የድርሻው ዋጋ ከፍ እንዲልና እንዲወድቅ ያደርጋሉ። ይህ ደግሞ በአብዛኛው ከኩባንያው ሊጠበቅ የሚችለው ገቢ ነው።
ነጋዴዎች፣ ኩባንያው የሚያገኘውን ገቢ፣ በገበያ ላይ የሚከሰቱ ለውጦችንና የሚያስገኘውን ትርፍ ጨምሮ ያለውን ዋጋ በየጊዜው ለማወቅ የገንዘብ መለኪያዎችን ይጠቀማሉ። ነጋዴዎች የሽያጭ ዋጋ ከፍ እንዲሉና እንዲቀንሱ ያደርጋል።
ነጋዴዎች በኢንቨስትመንቶቻቸው ላይ ትርፍ ለማግኘት ጥረት ያደርጋሉ። በሁለት ዋና ዋና መንገዶች ይከናወናል።
ዲቪደንድ– የኩባንያው አክሲዮን ትርፍ ከከፈለ ለባለድርሻ አካላት በየድርሻው ቋሚ ክፍያ ይደረጋል
በአነስተኛ ዋጋ ሲገዙ ና ዋጋው ከጨረሰ በኋላ መልሰው መሸጥ፡፡
በአጠቃላይ
አንድ የንግድ ድርጅት ለሚያወጣው ለእያንዳንዱ ድርሻ የአክሲዮን ዋጋ ይሰጣል ። ዋጋው የኩባንያው ዋጋ ነጸብራቅ ነው – ህዝብ ለአንድ ኩባንያ ለመክፈል ፈቃደኛ ነው። በዓለም አቀፉ መልክዓ ምድርና በኩባንያው ውስጥ ባሉት የተለያዩ ምክንያቶች ላይ ተመሥርቶ ሊነሳና ሊወድቅ ይችላል ፡፡

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
በኢትዮጵያ ሊጀመር የታቀደው የአክሲዮን ገበያ በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ ወደ ተግባር ይገባል ተባለ።
ባሳለፍነው ሳምንት እሮብ የአክሲዮን ገበያን በኢትዮጵያ ለማቋቋም ገንዘብ ሚኒስቴር ፤ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና ኤፍ ኤስ ዲ አፍሪካ የትብብር ሰነድ መፈራረማቸው ይታወቃል።
ኤፍ.ኤስ.ዲ አፍሪካ የቴክኒክ ድጋፍ የህግ ምክር እና የገንዘብ ድጋፍ እነደሚያደርግ ተገልጿል
የኤፍ.ኤስ.ዲ አፍሪካ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማርክ ናፒየር ለካፒታል እንዳስታወቁት የአክሲዮን ልውውጡን ለመጀመር ከ18 ወራት እስከ ሁለት ዓመታት እንደሚወስድ በመግለፅ አሁን ለመጀመር በዝግጅት ላይ ነን ሲሉ ሂደቱ ብዙ ስራዎች እንደሚያስፈልጉት ይገልፃሉ ።

ET Securities
Photo
የኢንቨስትመንት ባንኮችና ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የሙዓለ ንዋዮች ሰነድ ገበያ ለመሳተፍ ፍላጎታቸውን እየገለጹ ነው።
ግንቦት 19 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢንቨስትመንት ባንኮችና ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የሙዓለ ንዋዮች ሰነድ ገበያ ለመሳተፍ ፍላጎታቸውን እየገለጹ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገለጸ።
የካፒታል ገበያን በኢትዮጵያ ለመጀመርና ገበያውን ለመምራት የጸደቀውን አዋጅ በማስመልከት ለኢዜአ ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ከፍተኛ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ መለሰ ምናለ፤ የአዋጁ መጽደቅ የገበያው ተዋንያን፣ የቁጥጥር ስርዓቱን፣ በገበያው ላይ ሊፈፀሙ የሚችሉ ወንጀሎችን ለመቆጣጣር የሚያስችል ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ተናግረዋል።
የካፒታል ገበያ አዋጁ መፅደቁን ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ዘርፉን የመምራት ሃላፊነት ስላለበት የፕሮጀክት ቡድን አቋቁሞ ለካፒታል ገበያው እውን መሆን የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (Ethiopians Securities Exchange-ESX) አንዱ መሳሪያ እንደሆነ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ በካፒታል ገበያ አዋጁ 1248/2013 በተቀመጠው ትርጓሜ መሰረት የሙዓለ ንዋይ ሰነድ ገበያ ማለት የሰነዶች ሽያጭ፣ ግዥ፣ ልውውጥ፣ የሽያጭ ዋጋ፣ እንዲሁም ክፍያ በቋሚነት የሚፈፀምበት ቦታ መሆኑን ያብራራል።
ኢትዮጵያ የጀመረችው የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ በሌሎች አገሮች ካለውና በተለምዶ የስቶክ ወይም የአክሲዮን ገበያ ከሚባለው ጋር ተመሳሳይ ስለመሆኑ አማካሪው ያስረዳሉ።
ሆኖም ኢትዮጵያን ጨምሮ የተወሰኑ ሀገራት የስቶክ ገበያን የስያሜ ለውጥ በማድረግ (Securities Exchange) በሚል መጠቀም መጀመራቸውን በማንሳት የስያሜ ለውጡ የተደረገውም ስቶክ ገበያ ከአክሲዮን ግብይት ጋር ብቻ በመያያዙና አሁን ብዙ የሙዓለ ንዋይ ሰነዶች በመምጣታቸው ነው ብለዋል።
ለአብነትም በሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ሊሸጡና ሊገዙ የሚችሉት ከአክሲዮኖች በተጨማሪ፣ የባለ እዳነት ሰነዶች፣ ብድሮች፣ ቦንዶች፣ ወደ ካፒታልነት ሊቀየሩ የሚችሉ ሰነዶች፣ በመንግስት የወጡና ለግብይት የሚውሉ የህዝብ ብድር ሰነዶች፣ ከሙዓለ ንዋይ ጋር የተያያዙ ውሎች፣ የኢንቨስትመንት ፈንድ የድርሻ ሰነድ ይገኙበታል ነው ያሉት።
በካፒታል ገበያ አዋጁ መሰረት ቼክ፣ የተስፋ ሰነድ፣ የሃዋላ ወረቀት፣ የንግድ ወረቀቶችን፣ ሌተር ኦፍ ክሬዲት፣ ጥሬ ገንዘብ ማስተላለፍና በባንኮች መካከል የሚተላለፉ ሰነዶች፣ የመድን ፖሊሲዎች፣ ለተጠቃሚዎች ከጡረታ ክፍያዎች የሚመነጩ መብቶች በሙዓለ ንዋይ ሰነድነት አይካተቱም።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ፣ የገንዘበ ሚኒስቴርና ኤፍኤስዲ አፍሪካ (Financial Sector Deepening Africa) የሰነደ ሙዓለንዋዮች ገበያን ለማቋቋም ባለፈው ሳምንት የተመሰረተውን ፕሮጀክት ስራ ለማስጀመር መስመማታቸውን አቶ መለሰ አስታውሰዋል።
ኢትዮጵያ በካፒታል ገበያ አዋጁ መሰረት የሙዓለ ንዋዮች ሰነድ ገበያን ለመጀመር በእንቅስቃሴ ላይ መሆኗን የሰሙ የውጭ ኩባንያዎች በገበያው ለመሳተፍ እያማተሩ መሆኑንም ገልጸዋል።
ገበያው ለውጭ ኢንቨስተሮችም ክፍት መሆኑን የጠቀሱት አማካሪው፤ በዚህም አዋጁ በፀደቀበት ሰሞን በዓለም ታዋቂ የሆኑ ሶስት የሰነድ ገበያ ኩባንያዎች ፍላጎታቸውን በማሳየታቸው የቴክኒክ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል።
ኩባንያዎቹ የቴክኖሎጂ አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም በባለድርሻነት ለገበያው የሚጠቅሙ የቴክኖሎጂ ኢንቨስትመንት ላይ ለመሰማራት አማራጭ ማቅረባቸውን ገልጸው፤ የቴክኖሎጂ አቅርቦቱን ይዘው በገበያው ባለድርሻነት ለሚሳተፉት በራችን ክፍት ነው ብለዋል።
በቅርቡ የሙዓለ ንዋዮች ሰነድ ገበያን ለመጀመር ፕሮጀክት መቋቋሙን ተከትሎ የውጭ ኢንቨስተር የሆነው ኤፍ ኤስዲ አፍሪካ ባለድርሻ ለመሆን በኢንቨስትመንት መሳተፍ መጀመሩን ገልጸዋል።

ኩባንያዎች ከአክሲዮን ሽያጭ የሚያገኙት ገቢ ከግብር ነፃ ተደርጓል
ከተቋቋሙ በኋላ ካፒታላቸውን ለማሳደግ አዲስ አክሲዮኖችን የሚሸጡ ኩባንያዎች፣ በአክሲዮን ሽያጭ የሚያገኙት ገቢ ላይ የተጣለባቸው የገቢ ግብር ተነሳ፡፡ ከአክሲዮን ሽያጭ ላይ የተነሳው ግብር ድርጅቶች ከዚህ ገቢ ላይ የሚከፍሉትን 30 በመቶ ግብር የሚያስቀር ነው፡፡
ይህ ውሳኔ የተላለፈው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. 10ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሄደው የሚኒስቴሮች ምክር ቤት የአክሲዮን ሽያጭን ከገቢ ግብር ነፃ የሚያደርግ ረቂቅ ደንብ በማፅደቁ ነው፡፡
ምክር ቤቱ ያሳለፋቸውን ውሳኔ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፣ በካፒታል እጥረት ምክንያት የሥራ እንቅስቃሴያቸው የተዳከሙ ድርጅቶች ተጨማሪ ካፒታል ለማሰባሰብ ከሚሸጡት አዲስ አክሲዮን የሚገኝ ገቢን ከግብር ነፃ ማድረግ የሚኖረውን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ከግምት ውስጥ በማስገባት ደንቡን እንዳፀደቀ አስታውቋል፡፡
በገንዘብ ሚኒስቴር የሕግ ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ መነሻ፣ ገንዘብ ሚኒስቴር ይህንን ደንብ ያዘጋጀው በተለይ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ ኩባያዎች የካፒታል እጥረት ተግዳሮት ሆኖባቸው ስለሚታይ መሆኑን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
ይህ ታክስ ኢንቨስትሮችን ወደ አገር ወስጥ ለመሳብ አመቺ እንዳልሆነ የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ ‹‹ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ታክስ ታደርጋለች የሚል ሐሳብ ፈጥሯል፡፡ እንዲህ ዓይነት ታክስ ኢንቨስትመንትን አያሳድግም፡፡ ያቀጭጫል፡፡ የሚል አቤቱታ ቅሬታ ይቀርባል፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ኩባንያዎች ሥራቸውን ለማስፋት በሚል ለተጨማሪ ካፒታል ከሚሸጡት አክሲዮን ላይ አንድ ሦስተኛ ገደማውን ለመንግሥት ስለሚከፍሉ፣ በሚፈልጉት መጠን ካፒታላቸውን ለመሸጥ እንደሚቸገሩ አክለዋል፡፡
ኩባንያዎች የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንና የተለያዩ የመንግሥት አካላት ይህ የግብር ገቢ እንዲነሳ በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲያቀርቡ እንደነበረም አስታውሰዋል፡፡
በ2008 ዓ.ም. የወጣው የገቢ ግብር አዋጅ በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ኩባንያ አክሲዮን በመሸጥ ወይም በመለወጥ የሚገኝ ገቢ እንደ ገቢ ምንጭ ተቆጥሮ ግብር እንደሚጣልበት ደንግጓል፡፡ ከእንደዚህ ዓይነቱ ሽያጭ የሚገኘው ገቢም በ‹‹ምድብ ለ ግብር›› ውስጥ ተካቶ ሰላሳ በመቶ ተጥሎበታል፡፡
ኩባንያዎች ካፒታላቸውን ለማሳደግ አዲስ አክስዮን የሚሸጡት ኩባንያው ሲመሠረት፣ የአንድ አክስዮን ዋጋ ተብሎ የተቀመጠው የገንዘብ መጠን ላይ ወቅታዊ የገበያ ዋጋን በመጨመር ነው፡፡ አክሲዮን ሸጠው ከሚያገኙት ገቢ ላይ የሚከፍሉት 30 በመቶ ግብር የሚታሰበውም በመመሥረቻ ጽሑፋቸው ላይ ያስቀመጡት የአንድ አክሲዮን ዋጋ አሁን ከሸጡበት ዋጋ ላይ ተቀናሽ ከተደረገ በኋላ ነው፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር በገቢ ግብር አዋጁ ላይ የተቀመጠው ይህ ግብር እንዲነሳ የሚያደርግ ደንብ ለሚኒስቴሮች ምክር ቤት ያቀረበው ኢኮኖሚያዊ አስተዳደራዊ ወይም ማኅበራዊ ምክንያቶች መኖራቸው ሲታመን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ በማውጣት አንድን ገቢ ከግብር ነፃ ሊያደርግ እንደሚችል በተደነገገው መሠረት መሆኑ ተገልጿል፡፡
እንደ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያና ህንድ ያሉ አገሮች ካፒታልን ለማሳደግ ከሚደረግ የአክሲዮን ሽያጭ ላይ ግብር እንደሚሰበስቡ የገለጹት የሕግ ዳይሬክተሩ አቶ ሀብታሙ፣ ‹‹ያለው ልምድ የሚያሳየው ኢንቨስትመንት ስለሆነ ከታክስ ውጪ እንደሚሆን ነው፤›› በማለት ደንቡ የተዘጋጀበትን መነሻ ሐሳብ አስረድተዋል፡፡
ከኩባንያዎቹ በአክሲዮን ሽያጭ ገቢ ግብር ከመሰብሰብ ይልቅ ካፒታላቸውን አሳድገው በሚሠሩት ሥራ የሚገኘው የሥራ ዕድል ፈጠራና የውጭ ምንዛሪ ይበልጥ ጥቅም እንደሚያስገኝም አክለዋል፡፡
ገንዘብ ሚኒስቴር ግብሩን ለማንሳት ኢንቨስትመንት ማበረታታትን በምክንያትነት ቢያስቀምጥም በአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ይጀመራል ተብሎ የሚታሰበው የካፒታል ገበያም ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች ይስማማሉ፡፡

የዴቢት፣ ክሬዲት እና ቅድመ ክፍያ ካርዶች ልዩነት
አሁን ላይ በአገራችን ካርዶችን ለግዢ፣ ለወጪ እንዲሁም በተወሰነ መልኩ ለኦንላይን ክፍያ መጠቀም ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ መምጣቱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የካርዶቹም ዓይነት እየጨመረ እንዲሁም የብሔራዊ ባንክ ፈቃድን ተከትሎ ካርዶቹን የመስጠትም ሥራ ከባንኮች በተጨማሪ በሌሎች አካላት ወይም ድርጅቶች ጭምር እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ሆኖም ብዙ ሰዎች በክሬዲት ፣ ዴቢት እና ቅድመ ክፍያ ካርዶች መካከል ያለው መመሳሰልና ልዩነት በግልፅ አይታያቸውም፡፡፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ግልፅ ነው፡፡ እነዚህ ካርዶች ብዙ የሚያመሳስላችው ነገሮች (አገልግሎቱ የሚያበቃበት ቀን፣ የካርድ መለያ ቁጥሩ PAN፣ ሥም፣ የካርድ ሰጪውና የቪዛ ወይም ማስተር ካርድ መለያዎች አንዲሁም አሁን ላይ በተወሰኑት ላይ የኮንታክትለስ ምልክት) በካርዶቹ ላይ በተመሳሳይ መልኩ በመኖራቸው ምክንያት ሲሆን፣ ካርዶቹ ግን መሠረታዊ ልዩነት ያላቸው ናቸው፡፡
የካርዶቹን ተፈጥሮአዊ ልዩነት እንደሚከተለው በዝርዝር እንመለከት፡-
ቅድመ ክፍያ ካርድ
የቅድመ ክፍያ ካርድ የባንክ ሒሳብ መኖር ሳያስፈልግ ወይም ከባንክ ሒሳብ ጋር ሳይገናኝ በዲጂታል ክፍያ ዋሌት (Digital Payment Wallet) አማካኝነት በካርድ ገንዘብ እንዲንቀሳቀስ የሚያስችል ነው፡፡
እነዚህ ካርዶች አብዛኛውን ጊዜ በቪዛ ወይም ማስተር ካርድ የሚደገፉ በመሆናቸው ከአገር ውስጥ በተጨማሪ ዓለም አቀፍ ወይም በውጭ አገርም ሊሠሩ የሚችሉ ናቸው፡፡
የቅድመ ክፍያ ካርዶች አንድ ልዩ የሚያደርጋቸው በገንዘብ ወይም በክፍያ መጠን ላይ ገደብ ያላቸው መሆኑ ሲሆን፣ በካርዶቹ ላይ ያለው ገንዘብ ካለቀ በኋላ እንደገና እስኪጫንባቸው ድረስ መጠቀም አይቻልም፡፡
ለተለያዩ ዓላማ የሚውሉ የቅድመ ክፍያ ካርድ አይነቶች ያሉ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡
1-የቅድመ ክፍያ የሥጦታ ካርዶች
እነዚህ ካርዶች በሥጦታ መልክ ከተለያዩ አካላት ሊገኙ የሚችሉ ሲሆን፣ ካርዶቹ የያዙት የገንዘብ መጠን ካለቀ በኋላ ካርዶቹን መልሶ መጠቀም አይቻልም፡፡
2-የችርቻሮ ቅድመ ክፍያ ካርዶች/Retail Prepaid Cards
እነዚህ ካርዶች ከሥጦታ ካርዶች የተለዩ ሲሆኑ፣ ነዳጅ አቅራቢዎች፣ አየር መንገድ ወይም ሱፐር ማርኬቶች ከባንክ ጋር ወይም ከካርድ ሰጪ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ተጠቃሚዎች ክፍያ ወይም ግብይት በሚፈፅሙበት ወቅት የሽልማት ነጥቦችን ፣ የአየር ማይሎችን (Miles)፣ ቅናሾችን፣ ለመስጠት የሚያገለግሉ ናቸው፡፡
3-የቅድመ ክፍያ የጉዞ ካርዶች
የቅድመ ክፍያ የጉዞ ካርዶች ወደ ውጭ ጉዞ ለሚያደርጉ ግለሰቦች፣ ትኬትና ቪዛ እንዲሁም የደንበኝነት ሁኔታ ታይቶ በባንኮች የሚሰጡ ሲሆኑ፣ የገንዘቡ መጠን በውጭ ምንዛሬ ተጭኖ በሄዱበት አገር ሆስፒታሎች፣ ሱቆች እንዲሁም ለኦንላይን ክፍያዎች ሊያገለግሉ ይችላሉ፡፡
በካርዶቹ ላይ የተጫነው ገንዘብ ሲያልቅና ተጨማሪ ገንዘብ ከተፈለገ እንደገና መሙላት ይጠይቃል፡፡ እንዲሁም አንዳንድ ካርዶች ፓን ቁጥርን በመጠቀም የተወሰነ ገንዘብ ሊተላለፍባቸው ይችላል፡፡ ለምሳሌ፡ የአቢሲንያ ባንክ የጉዞ ቅድመ ክፍያ ካርዶች ከተጫነባቸው የመጀመሪያ የገንዘብ መጠን በላይ አስከ 3000 የአሜሪካን ዶላር ድረስ ከሌላ አካል ሊቀበሉ ወይም ሊተላለፍባቸው ይችላል፡፡
4-ለጠቅላላ አገልግሎት የሚያገለግሉ የክፍያና ግዢ ካርዶች
እነዚህ ካርዶች ለማንኛውም ዓይነት የዕለት ተዕለት ግዢና ክፍያዎች የሚያገለግሉ ሲሆን፣ የተጫነባቸው ገንዘብ ሲያልቅ እንደገና እየተሞሉ(Reloadable) ጥቅም ላይ የሚዉሉ ናቸው፡፡ የቅድመ ክፍያ ካርዶች ፣ ወጪዎች ከቁጥጥር ውጪ እንዳይሆኑ ከሌሎች የተለየ ጠቄሜታ አላቸው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት በካርዶቹ ላይ የተቀመጠው ገንዘብ መጠን አንድ ጊዜ ወጪ ከተደረገና ካለቀ፣ አለቀ ማለት ነው፡፡ ጥናቶችም እንደሚሳዩት ብዙ ሰዎች ከጥሬ ገንዘብ ይልቅ በካርዶች ከመጠን በላይ ማውጣት ይቀላቸዋልና፡፡
ዴቢት ካርድ
ዴቢት ካርዶች በአብዛኛው ከተንቀሳቃሽ ሒሳብ ጋር ግንኙ(Link) ሆነው የሚሠሩ ናቸው፡፡ በዚህም በቁጠባ ወይም በተንቀሳቃሽ ሒሳብ ውስጥ የሚኖረውን የገንዘብ መጠን ያህል ወጪ ማድረግ፣ ግብይቶችን ማካሄድ ወይም ክፍያዎችን መፈፀም ያስችላሉ፡፡ በሌላ አገላለፅ በሒሳብ ውስጥ የሚገኘውን ገንዘብ በካርዶቹ አማካኝነት በቀላሉ ለተፈለገው አላማ መጠቀም ማስቻላቸው ነው፡፡
አሁን ላይ በዴቢት ካርድ ከአቅም በላይ ወይም በሒሳብ ከሚገኘው ገንዘብ መጠን በላይ ማውጣት ከአለመቻሉ ባለፈ፣ ተጨማሪ ወጪ ማድረግ ቢፈለግ እንኳን ተጨማሪ የወጪ ወይም የክፍያ ገንዘብ ማግኘት አይቻልም፡፡ በርግጥ፣ አሁን ላይ አገልግሎቱ ጥቅም ላይ አልዋለም እንጂ፣ አንዳንድ የዴቢት ካርዶች ከኦቨር ድራፍት ፋሲሊቲ ጋር ግንኙ ሆነው ሊሠሩ የሚችሉበትም ሁኔታ ይኖራል፣ ይህ ሲሆን ሒሳብ ውስጥ ከሚገኘው ገንዘብ መጠን በላይ ለመጠቀም ይቻላል፡፡
ክሬዲት ካርድ
ክሬዲት ካርድ በአጭሩ ለግብይት፣ ለሌሎች ክፍያዎች ወይም ወጪዎች የሚሆን ገንዘብን በብድር መልክ ማግኘት የሚቻልበት ሲሆን፣ በካርዱ ለመጠቀም የተፈቀደው የብድር መጠን ወይም የብድር ገደብ ድረስ መገልገል ያስችላል፡፡
የብድር መጠኑን ለማሳደግ፣ ጥሩ የብድር አጠቃቀም ወይም ክሬዲት ካርድን በኃላፊነት በመጠቀም የብድር ደረጃን (Credit Score) ማሻሻል ይፈልጋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ክሬዲት ካርድን ኃላፊነት በጎደለው መልኩ መጠቀም ከልክ በላይ ወጪ ማውጣትን ፣ የብድር መከማቸትን ፣ የብድር ክፍያ መዘግየትን ብሎም የብድር መበላሸትን ሊያሰከትል ይችላል፡፡
በመጨረሻም ከካርዶች ጋር በተገናኘ፣ በተለያዩ አገልግሎት በአገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ምድቦች በፕርሚየም፣ ፕላቲንየም፣ ጎልድ ወይም መደበኛ መልኩ የተለያዩ ጥቅሞች ያሏቸው ሲሆን፣ የጥቅሞቹ አይነት፣ መጠንና የአገልግሎት ክፍያቸው እንደ ካርድ ሰጪው ባንክ ወይም ድርጅት የሚወሰንና የሚለያይ ነው፡፡
በአለማየሁ ስሜነህ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ለማድረግ በቀረበ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
@Etstocks
@Etstocks
የባንክ ዘርፍ ለውጭ ባለሃብቶች መከፈት በባንክ ዘርፍ ውስጥ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ ተገለፀ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ለማድረግ በቀረበ ፖሊሲ ላይ ተወያይቶ በሥራ ላይ እንዲውል መወሰኑ ይታወቃል።
ይህን ተከትሎ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ ኢትዮጵያን ለኢንቨስትመንት ተወዳዳሪና ተመራጭ የሚያደርግ መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጣ ውሳኔ መሆኑን ነው የገለጹት።
በተጨማሪም የፋይናንስ ኢንደስትሪውን በማዘመን ኢኮኖሚውን ለማሳደግ የማይተካ ሚናውን ይጫወታል ብለዋል::
የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ውሳኔውን ታሪካዊ ነው ብለውታል፡፡
ባለሙያው አክለውም፥ ከ50 ዓመታት በኋላ የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ያፀደቀው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ትልቅ ለውጥ ይዞ ብቅ እንደሚል ያላቸውን እምነት ነው የጠቀሱት፡፡
ፖሊሲው ወደ ስራ ሲገባ የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ ይጠበቃልም ብለዋል፡፡
የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ማድረግ የዘርፉን አገልግሎቶች በእውቀት እና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ፣ የአገራችን ኢኮኖሚ ከዓለም አቀፍ ገበያ ጋር ያለውን ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር፣ የፋይናንስ ዘርፉን ተወዳዳሪነት፣ ውጤታማነትና ቀልጣፋነት በመጨመር በቂ የፋይናንስ አቅርቦት እንዲኖር የሚያስችል ፖሊሲ ነው የጸደቀው፡፡
ፖሊሲው የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት እንዲሳለጥ፣ የሚፈጠረው የሥራ ዕድል እንዲጎለብት፣ ኢኮኖሚያዊ ውጤታማነትን እና ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪትን በማረጋገጥ ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑም ተመልክቷል።

የውጭ ባንኮች የኢትዮጵያን ገበያ መቀላቀላቸውን አስመልክቶ የተለያዩ የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ሐሳቦች እየተንጸባረቁ ነው። በዝርዝር ለመተቸትም ሆነ ለመደገፍ ፖሊሲዎች የኘፈጻጸም መመሪያዎች እስኪወጡ መጠበቅ ተገቢ ስለሆነ፣ ለዛሬው ጥቅል ሐሳቦችንና ትኩረት የሚሹ ነጥቦች ብቻ በጨረፍታ አቀርባለሁ።
የዓለም አቀፍ ገበያ ድርጅትን (WTO) ለመቀላቀል አንዱ መስፈርት የሆነው ባንክና ቴሌን የመሳሰሉ ተቋማትን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ማድረግ ነው። በዚህ ምክንያትም የውጭ ሀገር ባንኮች የሀገራችንን የባንኪንግ ኢንደስትሪ የመቀላቀላቸው ጉዳይ የጊዜ ጉዳይ እንጂ አይቀሬ እንደነበር የሚታወቅ ነው።
አሁን ሊያወያየን የሚችለው ጉዳይ ባንኮቹ ገበያውን እንዲቀላቀሉ የተፈቀደበት ወቅት ተገቢ ነበር ወይ? የመንግስት፣ የብሔራዊ ባንክና ሀገር በቀል ባንኮች አቅምና ቅደም ዝግጅታቸውስ ምን ይመስላል? የገበያችንን ስርዓት ( Market Structure) ምን ያህል ሕጋዊነትን የተከተለና ለወንጀልና ወንጀለኞች ያልተጋለጠ ነው። የግብር አከፋፈል፣ የመረጃ አሰባሰብና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂያችን ምን ያህል ጥብቅና ለውንብድናና ለጠለፋ ( Hacking ) ያልተጋለጡ ናቸው የሚሉትና መሰል ጉዳዮች ይሆናሉ
የውጭ ሀገር ባንኮች ወደ ሀገራችን የሚመጡት ገበያ፣ ነባርና አዲስ ደንበኛና ትርፍ ፍለጋ ስለሆነ ስለ ሀገር እድገት በተለይ የሚጨነቁና የማይጠበቡ ልማታዊ እሳቤም የሌላቸው እንደሆነ የሚታወቅ ነው። የሚቀላቀሉት ገበያ ያለበት ሀገርም ሀገራቸው ስላልሆነ ትርፍ እስካገኙ ድረስ በማንኛውም መንገድ ከማትረፍ ወደኃላ የማይሉና የሕግ አስገዳጅነት እንጂ የሞራል ጥያቄ እምብዛም የማይገዳቸው ሊሆኑ እንደሚችሉ ታሳቢ መሆን አለበት። በተቃራኒው ደግሞ ሀገር በቀል ባንኮች ከትርፍ ባሻገር የሀገራቸው፣ የመንግስትና የልማታቸው አጋር ስለሆኑ ከሕግ ባሻገር በርካታ የውዴታ ግዴታና የሞራል ፈተና ስላለባቸው ውድድሩ የተለየ ጫና ሊያሳድርባቸው ይችላል።
የውጭ ሀገር ባንኮች በርካታ የውጭ ምንዛሬ ያመጣሉ የሚለውም እሳቤ የተጋነና በአብዛኛው የተሳሳተ መረጃ ነው። የውጭ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ በገፍ ይዘው መጥተው በብር የመለወጥ ፍላጎት አይኖራቸውም። በአብዛኛውም ያለችውን ገበያና የውጭ ምንዛሪ መቀራመት ላይ እንደማያተኩሩ ይገመታል።
ትርፋቸውንም በውጭ ምንዛሪ ከሀገር የማውጣት እድላቸው ጠባብ ስለሆነና ዋና መስርያ ቤታቸውን እንዲገነቡ ለሚሰበስቡት ብር ተመጣጣኝና ኃላፊነትና ግዴታ (Risk) እንዲወስዱ ካልተገደዱ በስተቀር የባንክ ስራ ቅርንጫፍ ተከራይቶ ቁሳቁስ በማሟላትና ገንዘብ በመሰብሰብ በትንሽ ኢንቨስትመንት የሚሰራ ዘርፍ ስለሆነ ኢንቨስትመንታቸውም ውስን በማድረግ ያለ በቂ ኃላፊነት፣ ስጋትና መተማመኛ ሊነግዱ ይችላሉ።
ሌላው ሀገር በቀል ባንኮች ከተደራሽነትና ሕዝብን ከማገልገል አኳያ ትርፍ ኖረም አልኖረ እንደ አቅማቸው ሁሉም ቦታ ቅርንጫፍ ይከፍታሉ። የውጭ ባንኮች ግን ሀብትና ኢኮኖሚያዊ አቅም በስፋት የሚታይባቸው አካባቢዎች ላይ ብቻ አትኩረው ሊሰሩ ስለሚችሉ አቅም ባለበት ቦታ ላይ ብቻ የሚኖረው ውድድሩ በሚፈጥረው ሽሚያ በሚፈጠረው አቅም መዳከም ምክንያት ቀሪው አካባቢና ማህበረሰብ የባንክ አገልግሎት ላያገኝ ይችላል።
ሌላው ሀገራችን ውስጥ የሚገኙ ከፍተኛ አስቀማጭና ተበዳሪዎች በጥቂት መቶዎች የሚቆጠሩ ሰለሆኑ እነዚህን ደንበኞችና ገበያ (Niche Market) ላይ ብቻ በማተኮር ወይም ከፍተኛ እጥረት ያለበት የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትን በማባበያነት በመጠቀም፣ የኢንዱስትሪውን አቅም ከ70 በመቶ በላይ በቀላሉ ለመቆጣጠር ይችላሉ።ይህ ደግሞ የተዛባና ወደ አንድ ጎን ያጋደለ (Economic imbalance) ፣ ኢ-ፍትሐዊ ወይም ሚዛናዊ ያልሆነ ውድድር (Unfair Competition ) ሊፈጥሩ ይችላሉ።
በዚህ መንገድ ከሞላ ጎደል ገበያውን መሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ስለሚችሉም የፈለጉትን የአገልግሎት ዋጋ በመጣል፣ ወለድ በመተማንና ለፈቀዱለትና ለሚመስላቸው ዘርፍ ብቻ በማበደር ኢኮኖሚውን ወደ ፈለጉበት በመጠምዘዝ ልማታዊ እድሎችን እስከማደናቀፍ ሊደርሱ ይችላሉ። የውጭ ምንዛሪ ሲፈቅዱ የሀገራቸው ምርት ብቻ እንዲገባ በማድረግም ሀገሪቱን የሸቀጥ ማራገፊያ ( Damping ground) ሊያደርገት ይችላሉ። እንደዚህ ዓይነት አካሄዶች በማደግ ላይ ባሉ በርካታ ሀገራት ላይ ያጋጠመ ፈተናና ችግር ነው። በአንዳድ ሀገራትም አንዴ ባንኮቹ ጡንቻ ካፈረጠሙ በኃላ ለተለያዮ ኃይሎች የፖለቲካ መሳርያ በመሆን የመንግስትን እጅ እስከ መጠምዘዝ የደረሱበት ሁኔታም ታይቷል።
የውጭ ባንኮች ወድ ሀገር ውስጥ መግባታቸው በጠንካራ ጎንነት ሊወሳ የሚችለው የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ዘመናዊ የባንክ ሙያና እውቀት ስርጸት፣ አዳዲስ የማኔጅመንትና የአመራር ጥበብ ሽግግር የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ። ከዚህም በላይ ለነባርና ብቃት ላላቸው የባንክ ሰራተኞችን ጨምሮ ለአዳዲስ ስራተኞችም የስሬ እድል ይፈጥራል። የውጭ ባንኮቹ ሀገር ውስጥ መኖራቸው በወጭና በገቢ ንግድ ላይ የነበረውን የተንዛዛ አሰራርና ተደራራቢ የክፍያ ስርዓት ሊቀንስ ይችላል። ኢንደስትሪው በስርዓትና በሕግ ከተመራም የዘመነና ጤናማ ውድድርን ሊያስከትል ይችላል። በአጠቃላይ ዘመናዊ አሰራር በማስተዋወቅ አዲስ ሃብት በማሸጋገርና በማበልጸግ የተቀማጭም ሆነ የውጭ ምንዛሪ ይበልጥ እንዲሳለጥና Economics of Scale ከፍ እንዲል ሊያግዝ ይችላል።
ሙሼ ሰሙ

የባንኩን ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ማድረግ ባንኮች ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ዕድል ይፈጥራል- አቤ ሳኖ
የባንኩን ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት የማድረግ ውሳኔ የኢትዮጵያ ባንኮች በትብብር ብቁ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ዕድል ይፈጥል ሲሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ተናገሩ፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ13ኛ መደበኛ ስብሰባው የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ለማድረግ የቀረበው ረቂቅ ፖሊሲ በሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ውሳኔውን አስመልክቶ ለኢዜአ እንደገለጹት÷ የባንኩ ዘርፍ ለዓለም ገበያ ዝግ ሆኖ መቆየቱ የሀገር ውስጥ ባንኮችን ዕድገት አቀጭጯል፡፡
የባንክ አገልግሎቱን ቀስ በቀስ ለዓለም አቀፍ ውድድር ክፍት በማድረግ የሀገር ውስጥ ባንኮች የውድድር አቅማቸውን እያጎለበቱ እንዲሄዱ መሥራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ውድድሩ ዓለም አቀፍ ልምዶችን ለመቅሰም ዕድል እንደሚፈጥርም ጠቁመዋል፡፡
የባንኩ ዘርፍ ለዓለም ገበያ ክፍት መደረጉ የሚበረታታ ቢሆንም በጥንቃቄ መመራት እንዳለበትም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡
በውድድሩ የሀገር ውስጥ ባንኮች እንዳይጎዱ በተወሰነ የአክሲዮን ድርሻ የውጭ ባንኮች እንዲገቡ በማድረግ በሂደት የአክሲዮን መጠናቸውን እያሳደጉ የሚሄዱበትን አሠራር መዘርጋት እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል።
FBC

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ለማድረግ በቀረበ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
@Etstocks
@Etstocks
በአሁን ሰዓት የባንክ ስራ ፕሮሞሽናል እንስቃሴ አያደረጉ ያሉ የዉጪ ባንኮች
በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ የ9 የውጪ ባንኮች ተወካዮች እንስቃሴ እያደረጉ ነው። በስም ደረጃ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ, ስታንዳርድ ባንክ, ደቸ ባንክ,ኮሜርዝ ባንክ, ኬሲቢ ባንክ, ባንክ ኦፍ አፍሪካ, ዚራት ባንክ, ኢምፖርት አክስፖርት ባንክ ኦፍ ኢንዲያ እና ኢኪውቲ ባንክ ናቸው፡፡
Fb:- www.facebook.com/Etstocks

የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ስለሚፈቅደው የፖሊሲ ውሳኔ የዘርፉ ባለሙያዎች ምን አሉ?
#ሪፖርተር በዳዊት ታዬ
September 7, 2022
"የአገር ውስጥ ባንኮች ጠንካራ ካፒታል ከፈጠሩና ራሳቸውን ከጊዜው ጋር ሊያራምድ ወደሚችል ውሳኔ ከደረሱ ምንም ተፅዕኖ እንደማይገጥማቸው፣ ሰፊ ገበያ ያለበት አገር በመሆኑ እንደማይቸገሩ ገልጸዋል።........"
+++++++++++++++++++
ኢትዮጵያ ከ20 ዓመታት በላይ በተለያየ መንገድ አስተያየት ሲሰጥበት የቆየውና ከዛሬ ነገ ዕውን ይሆናል እየተባለ ሲጠበቅ የነበረው የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ እንዲገቡ የሚፈቅደው የፖሊሲ ውሳኔ በመንግሥት ተወስኗል፡፡ ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም. በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ያረፈበት የውጭ የፋይናንስ ተቋማት እንዲገቡ መፈቀድ ታሪካዊ የሚባል እንደሆነም እየገለጸ ነው፡፡
ይህ ውሳኔ የውጭ ባንኮች ከግማሽ ምዕተ ዓመት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ዳግም እንዲገቡና የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት እንደሚሆን መንግስት በይፋ የገለጸበት የፖሊሲ ሰነድ ነው፡፡
የውጭ የፋይናንስ ተቋማት ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ የፖሊሲ ውሳኔ መተላለፉ ታሪካዊ የሚባል መሆኑን ከገለጹት የኢኮኖሚ ባለሙያዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ አሰግድ ገብረመድን የፖሊሲ ውሳኔው ከታሪካዊነቱ ባሻገር ወቅቱን የጠበቀ ስለመሆኑም ያመለክታሉ፡፡
የውጭ የፋይናንስ ተቋማት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡበት መንገድ ምንም ይሁን ምን በኢትዮጵያ በፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ አዲስና ጠቃሚ የሚባል አሠራር የሚፈጥር መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው የሚገልጹት አቶ አሰግድ በፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ በርካታ ሥር ነቀል ለውጦች የሚፈጥር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
አቶ አሰግድ የሚኒስሮች ምክር ቤት የፋይናንስ ዘርፉ ክፍት እንዲሆን መወሰኑ ለአገሪቱ ቀጣይ ዕድገት አስፈላጊ ነው ብለዋል። ውሳኔው ወቅቱን የጠበቀ ስለመሆኑና የኢንዱስትሪውን አሠራር አደረጃጀትና አጠቃላይ ይዘት የሚለውጥ እንደሚሆን የገለጹት የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር ምክትል ፕሬዚዳንትና የዳሸን ፕሬዚዳንት አቶ አስፋው ዓለሙ በበኩላቸው የኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት ራሳቸውን እንደ አዲስ የሚያደራጁበትና ውድድሩን ለመወጣት ምን ማድረግ እንዳለባቸው የሚተልሙበት ወሳኝ ሰዓት ላይ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡
በእርግጥም ይህ ውሳኔ ዝርዝር መረጃዎችን ያላመላከተ ቢሆንም ታሪካዊ ሊባል እንደሚችል የጠቀሱት አቶ አስፋው ለአገራዊ ኢኮኖሚው ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል፡፡ ዋናው ጉዳይ ግን እነዚህ የውጭ ባንኮች እንዴት ይገባሉ የሚለው ነገር በቶሎ መገለጽና መታወቅ ያለበት መሆኑን ነው፡፡ ይህ የመንግሥት ውሳኔ ዝርዝር መሰጃው ባይገለጽም እስከዛሬ ድረስ በቃል ሲነገር የነበረውን የፋይናንስ ዘርፉን ለውጭ ባንኮች ክፍት የማድረግ ፍላጎት መንግስት ለመጀመሪያ ጊዜ በፖሊሲ ደረጃ በይፋ ያሳወቀበትና ሁሉም ተዋንያኖች እንዲያውቁት መልዕክት የተላለፈበት ነው ብለዋል፡፡ ይህ የፖሊሲ ውሳኔ
የውጪ ባንኮች መግባት እርግጥ መሆኑንና እያንዳንዱ የአገር ውስጥ ባንክ የራሱን ዝግጅት ከወዲሁ በትኩረት እንዲሠራ ያደርጋል ብለዋል፡፡
የውጭ ባንኮች መግባት ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ትልቅ ኢኮኖሚ ይዛ እንድትወጣና ተፅዕኖ ፈጣሪነቷን ለማጉላት መንገድ የሚቀድ ነው ያሉት አቶ አሰግድ ፣ የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡበት መልክ የተገለጸ ባይሆንም የእነዚህ ተቋማት መግባት በእጅጉ ጠቃሚ እንደሆነ የምናሉ፡፡
የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ችግር ለመፍታት፣ በአነስተኛ ወለድ ብድር ለማግኘትና ከ50 እና 60 ዓመታት በላይ በተለምዶ ሲሠራበት የነበረው የባንክና የኢንሹራንስ አገልግሎት ዓለም አቀፍ ስታንዳርድን ይዞ እንዲሠራ ጭምር ይህ ውሳኔ ትልቅ ዕገዛ እንደሚያደርግም ገልጸዋል፡፡
ይህ ብቻ ሳይሆን የአገሪቱ የፋይናንስ ተቋማት በኢትዮጵያ ብቻ የታጠረውን አገልግሎታቸውን ድንበር ተሻግረው እንዲሠሩ ጭምር የሚያግዝ እንደሆነ አቶ አስፋውና አቶ አሰግድ የገለጹ ሲሆን ወደ ተግባር ለመግባት ግን አሁንም ተጨማሪ ሥራዎች የሚጠበቁ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡እነዚህ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡት መልክ ምን ይሁን ምን በሊያመጣ የሚችለው ተፅዕኖ እንደሌለ አቶ አሰግድ ይገልጻሉ። አቶ አስፋው ግን የውጭ ባንኮች አገባብ ደረጃ በደረጃ ቢሆን ይመረጣል የሚል ምልከታ አላቸው፡፡
ሙሉ በሙሉ ቢገቡም ብዙዎች እንደሚሉት ከአገር ውስጥ ባንኮች ጋር በመጣመር እንዲገቡ ቢፈቅድም ጠቀሜታው ለአገር ነው የሚል አስተያየታቸውን ያጎሉት አቶ አሰግድ የአገር ውስጥ ባንኮች ተወዳዳሪ ለመሆን ግን ከወዲሁ ሊዘጋጁባቸው ይገባል ሲሉ መክረዋል። ለአብነት ካነሱዋቸው መካከል በየትኛውም መንገድ የውጭ ባንኮች ቢገቡ ይዘውት የሚመጡት ካፒታል ከፍተኛ መጠን ያለው ስለሚሆን ይህንን የሚመጥን ካፒታል የአገር ውስጥ ባንኮች ማደራጀት ይኖርባቸዋል፡፡ ስለዚህ አሁን ያሉት ባንኮች በያዙት ካፒታል ተወዳዳሪ ሊሆኑ ስለማይችሉ ትልልቅ የሚባሉት ባንኮች ሁለት ሦስት ሆነው፣ እንዲሁም አነስተኛ ካፒታል ያላቸው ደግሞ አምስት ስድስት ሆነው መዋሃድ ሊጠይቃቸው እንደሚችል ያምናሉ፡፡ ይህንን ማድረግ ግድ የሚል መሆኑንም የሚገልጹት አቶ አሰግድ የአገር ውስጥ ባንኮች ወህደት በመፍጠር ጠንካራ የኢትዮጵያ ባንክ በመመሥረት ከውጪዎቹ ጋር መወዳደር ወይም ተጣምረው በመሥራት ከኢትዮጵያ ውጪ በመውጣት ተወዳዳሪ ባንክ መፍጠር የሚያስችላቸው ዕድል ለመፍጠር ጭምር የሚረዳቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አቶ አስፋው ግን የውጭ ባንኮች በአንድ ጊዜ ሙሉ በሙሉ እንዲገቡ የሚፈቀድ ከሆነ ተፅዕኖ ሊያመጣ እንደሚችል በመጥቀስ ፣ የውጭ ባንኮች ከአገር ውስጥ ባንኮች ጋር ተጣምረው እንዲሠሩ በማድረግ ውሳኔውን ማስጀመር ተገቢ እንደሆነ ያመለክታሉ፡፡
ነገር ግን ከመደበኛው ባንክ አገልግሎት ሌላ በአንድ ዘርፍ ላይ ያተኮሩ (ስፔሻላይዝድ በሆኑ) ለምሳሌ እንደ እርሻ፣ ኢንቨስትመንትና በመሳሰሉ ዘርፎች ባንኮችን እንዲያቋቁሙ ቢፈቀድ የበለጠ ጠቀሜታ እንዳለውም አቶ አስፋው ይናገራሉ፡፡
በሰሞናዊው የመንግሥት ውሳኔ በቀጥታ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፋይናንስ ተቋማት የውሳኔው ዝርዝር መረጃ ያልደረሳቸው ሲሆን ውሳኔው ግን በተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የለተያዩ አስተያየቶች እየተሰጡበት ይገኛል፡፡
መንግሥት ገንዘብ ስለቸገረው የወሰነው ውሳኔ ነው የሚሉ ያሉትን ጨምሮ ፣ ውሳኔው ተገቢ ቢሆንም ፈጠነ የሚሉ ትችቶችም እየቀረቡበት ነው፡፡ አቶ አሰግድ እንዲህ ያለውን አስተያየት አይቀበሉም፡፡ እንደውም የዘገየ ውሳኔ ነው ብለው ያምናሉ፡፡ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ አሁን ያለውን ችግር ለመፍታት ከተፈለገ ከዚህ ዕርምጃ ሌላ ሊወሰድ የሚችል የተሻለ ውሳኔ ያለመኖሩን ያሰምሩበታል፡፡ ስለአገር መበልፀግና ዕድገት ከታሰበ ከዚህ ውሳኔ በተፃራሪ መቆም ተገቢ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡
በዚህ ውሳኔ ዙሪያ የተለያዩ አመለካከት እንዳለ የጠቆሙት አቶ አስፋው ደግሞ ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቅሱት አዲስ የሆነ አሠራር የሚፈጠር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሚፈጠር ብዥታ በመኖሩ ነው ይላሉ፡፡ ሁሌም ወደ አዲስ አሠራር በሚገባበት ጊዜ እንዲህ ያለ ግርታ ይፈጠራል፡፡
www.facebook.com/Etstocks