ET Securities
698 subscribers
623 photos
7 videos
31 files
323 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ያጋጠሙትን ቀውሶች በመፍታት ከታክስ በፊት ከ1.7 ቢሊዮን ብር በላይ አተረፈ

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በተለያዩ ጊዜያት ያጋጠሙትን ተግዳሮቶች እየፈታና እያስተካከለ ወደ ውጤታማነት እየተሸጋገረ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡ ባንኩን ወደፊት ያራምድልኛል ያለውን የአምስት ዓመታት ፍኖተ ካርታና ስትራቴጂክ ዕቅድም ይፋ አደረጓል፡፡
ከባንኩ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የባንኩን እንቅስቃሴ ተጭነው የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት በተደረጉ ጥረቶች በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት ክፍያዎችንና ዕዳዎችን የማቃለል ስትራቴጂ ቀይሶ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል።
የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሔኖክ ከበደ፣ የባንኩ የአምስት ዓመታት ፍኖተ ካርታና ‹‹ንብ ተራ›› የተሰኘውን አዲስ የኦላይን መተግበሪያ ይፋ በተደረገበት ፕሮግራም ላይ እንደገለጹት፣ ባንኩ ያጋጠሙትን ተግዳሮቶች እየፈታ ውጤታማ አፈጻጸሞችን እያሳየ ነው ብለዋል፡፡ ለዚህም አብነት የሚሆኑ በርካታ ሥራዎች መሥራታቸውን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ በሁሉም መመዘኛዎች ባንኩ ይበልጥ ውጤታማ እን...

ማንበብ ይቀጥሉ
Etsecurities.com
1
ገዳ ባንክ በ2024/25 የበጀት አመት ጠቅላላ ሀብቱ 10.1 ቢሊዮን ብር መድረሱን ገለጸ፡፡

ባንኩ በተጠናቀቀው የ2024/25 የበጀት አመት በቁልፍ የአፈጻጸም መለክያዎች የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገብ ማጠናቀቁን አስመልክቶ የባንኩ ዋና ስራ አስፋጻሚ አቶ ወልዴ ቡልቶ ለሚዲያ በሰጡት መግለጫ በበጀት ዓመቱ በአለም አቀፍ እና አገር አቀፍ ደረጃ የጋጠሙትን ተግዳሮቶችን በጽናት በማለፍ በቁልፍ የአፈጻጸም መለክያዎች የላቀ አፈጻጸም ማስመዝገቡን አብስሯል፡፡

በበጀት ዓመቱ የባንኩ ጠቅላላ ሀብት 10.1 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 80 በመቶ ዕድገት ያሳየ ስሆን፤ በተጠናቀቀዉ የሂሳብ ዓመት የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ ብር ከ7.7 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ይህም ከአምናዉ ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 91 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡ በተመሣሣይ የባንካችን ጠቅላላ ገቢ ብር 1.6 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን፤ ከአምናዉ ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም 106 በመቶ እድገት በማሳየት በዓመቱ ከዕርጅና እና የብድር መጠባበቂያ በፊት ብር 575 ሚሊዮን ትርፍ ማስመዝገብ ችሏል፡፡

ባንኩ በጀት ዓመቱ የዲጅታል ግብይት ተጠቃሚ የሆነ ማህበረሰብን ለመፍጠር ለደንበኞቹ ዘመናዊ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ካለው ቁርጠኝነት ዓለም አቀፍ የባንኪንግ ኢንዱስትሪ የደረሰበትን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ደረጃ ያሟላና ሁሉንም የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶችን አንድ ላይ ያካተተ ኦምኒ ቻናል አገልግሎት ‘ገዳ ዲጂታል’ በሚል ስያሜ አስጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ገበያ በይፋ ስራ መጀመራቸውን ተከትሎ ባንካችን በባለአክሲዮኖች የተያዙ አክሲዮኖችን በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በማስመዝገብ ብሎም ለግብይት ወይም ለውውጥ በኢትዮጰያ የሠነደ-መዋዕለ ነዋዮች ገበያ ላይ አመቻችተዋል፡፡

ማንበብ ይቀጥሉ
Etsecurities.com
የዓለም ባንክ የሀገራትን የገቢ ደረጃ ሲያወጣ የኢትዮጵያን ደረጃ ሳያወጣ ቀርቷል!