| በስምንተኛው ዙር የዉጪ ምንዛሪ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር አማካይ ዋጋ 136 ብር ደረሰ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባካሄደው 8ኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት መሰረት፣ የአንድ የአሜሪካ ዶላር የምንዛሪ ዋጋ 136.6286 ብር መሆኑን አስታወቀ።
50 ሚሊዮን ዶላር በቀረበበበት ጨረታ ላይ 11 ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ድልድል አግኝተዋል።
ይህ አሁን ይፋ የተደረገው የምንዛሪ ተመን፣ ከሁለት ሳምንት በፊት በተካሄደው 7ኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ከተመዘገበው 134.95 ብር የአሜሪካ ዶላር አማካይ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር፣ የብር የመግዛት አቅም በ1.6786 ብር መቀነሱን ያሳያል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ጨረታዎችን የሚያካሂደው በሀገሪቱ ያለውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለማቃለል እና የባንኮችን የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ለማሟላት መሆኑ መግለፁ ይታወቃል። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@et_securities/video/7517667465489353990

Ethiopia will begin trading under the African Continental Free Trade Area (AfCFTA) on July 1, six years after ratifying the agreement. The announcement was made by Trade and Regional Integration Minister Kassahun Gofe during a session of Parliament this week.
- - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - -
ስምምነቱን ካፀደቀች ከስድስት ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) የንግድ ልውውጥ በመጪው ሐምሌ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ትጀምራለች።
የንግድና ክልል ኢኮኖሚ ውህደት ሚኒስትሩ አቶ ካሳሁን ጎፌ ይህን የገለፁት በዚህ ሳምንት በተደረገው የፓርላማው ስብሰባ ላይ ነው።
Read more
Etsecurities.com

❤1
የቴሌግራም መስራች ሀብቱን ለ100 ልጆቹ ለማውረስ ማቀዱን ገለጸ።
የቴሌግራም መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ፓቨል ዱሮቭ ያለውን ሃብት ለ106 ልጆቹ በእኩል እንደሚያከፋፍል አስታውቋል።
ቢሊየነሩ ዱሮቭ ከተለያዩ ሶስት ሴቶች 6 ልጆችን የወለደ ሲሆን በዘር ፈሳሽ ልገሳ ደግሞ በ12 የተለያዩ ሃገራት የተወለዱ 100 ልጆች እንዳሉት ይፋ አድርጓል።
ዱሮቭ ከቴሌግራም ጋር በተያያዘ ብዙ ጊዜ ጥያቄ የሚነሳበት እንደሆነ ሲታወስ በቅርቡ በዚሁ ምክንያት በፈረንሳይ መታሰሩም ይታወሳል።
እንደ ፎርብስ ከሆነ ዱሮቭ አጠቃላይ ሃብቱ 17.1 ቢሊየን ዶላር ሲሆን ይህንን ሃብቱን ለልጆቹ በእኩል እንደሚያከፋፍል ለፈረንሳዩ የፖለቲካ መጽሔት ለ ፖይንት ተናግሯል።
ልጆቹ እንደ ማንኛውም ሰው እንዲያድጉ እፈልጋለሁ ያለው ዱሮቭ ልጆቹ የተሰጣችውን ሃብት የሚወስዱት በፈረንጆቹ ከሰኔ 19,2055 በኋላ ወይም የዛሬ 30 አመት መሆኑንም ገልጿል።
የ40 ዓመቱ ወጣት አሁን ኑዛዜውን ማሰፈር ያስፈለገበት ምክንያት ከስራው ጋር በተያያዘ ያለውን አደጋ በመገንዘብ እንደሆነ ያስረዳል። "ነጻነትን መደገፍ ኃያላን መንግሥታትን ጨምሮ በርካታ ጠላቶችን ያተርፍልሃል" ይላል።
ቴሌግራም አሁን ላይ ከአንድ ቢሊዮን በላይ ወርሃዊ ንቁ ተጠቃሚዎች አሉት።
Source: tikvahethmagazine
@Etstocks

Forwarded from Kelemat Ads Hub
ቤትዎን እና የስራ ቦታዎን ከሼይን እና አሊኤክስፕረስ በሚገኙ ውብ እቃዎች ማራኪ እና ውብ ያድርጉ።
Decorate your home and working places with classy items from Shein and AliExpress.
ቻናላችንን በመቀላቀል ያሉንን እቃዎች ይመልከቱ | Join our channel
👇
https://t.me/Medamart

ሰበር፡ የገዳ ባንክ በኢትዮጵያ ሰነደመዋለንዋይ ገበያ (ESX) ላይ ተዘረዘረ!
ገዳ ባንክ በኢትዮጵያ ሰነደመዋለንዋይ ገበያ (ESX) ላይ በይፋ የተዘረዘረ ሁለተኛው ባንክ ሆኗል። ባንኩ 1.23 ሚሊዮን የ አክሲዮኖችን በገበያው ላይ በማቅረብ፣ ለኢትዮጵያ አዲስ ለሆነው የካፒታል ገበያ ባንኮች ያላቸውን እምነት አሳይቷል።
ይህ ዝርዝር አዲስ ገንዘብ ለማሰባሰብ ያለመ ሳይሆን፣ ነባር ባለአክሲዮኖች የአክሲዮናቸውን ፈሳሽነት (liquidity) እንዲያገኙ እና የገበያውን ታይነት ከፍ እንዲል ለማድረግ ነው።
የ ESX ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጥላሁን ካሳሁን “ይህ የገበያው ውጤታማነት ማሳያ ነው፤ እምነት እየገነባን ነው” ብለዋል።
ገዳ ባንክ በ2021 ተመስርቶ በ2022 ሥራ የጀመረ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ2023/24 የ115 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ አግኝቷል። አጠቃላይ ንብረቱም ከ6.1 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል።
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ቡልቶ ይህንን ዝርዝር “ለባንኩ ብቻ ሳይሆን ለመላው የፋይናንስ ሥርዓት ትልቅ ምዕራፍ ነው” ሲሉ ገልፀውታል።
የቦርድ ሰብሳቢው አቶ ሀሰን ሁሴን በበኩላቸው “እያደግን ብቻ ሳይሆን ይበልጥ ግልፅና ተጠያቂ እየሆንን ነው” ብለዋል።

ኢትዮጵያ በመጪው መጋቢት ወር የአለም ንግድ ድርጅት አባል ልትሆን ትችላለች ተባለ
ኢትዮጵያ በመጪው ዓመት መጋቢት ወር ላይ የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) አባል ልትሆን እንደምትችል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ። በርካታ የድርድር ጉዳዮች በስምምነት መጠናቀቃቸውን ተከትሎ፣ በካሜሩን በሚካሄደው የድርጅቱ ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ አባልነቷ እንደሚረጋገጥ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው በ2003 ዓ.ም. እንደነበር ይታወቃል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮም የድርጅቱን ጥብቅ መስፈርቶች ለማሟላት የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎች እንደተሻሻሉ መንግሥት አስታውቋል።
በ2020 ዓ.ም. ከአራተኛ ዙር ድርድር በኋላ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ሌሎች ምክንያቶች ድርድሩ ተስተጓጉሎ ቢቆይም፣ አሁን በብዙ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ መደረሱን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድሙ ፍላቴ ተናግረዋል።
አቶ ወንድሙ በመጪው መጋቢት ወር በካሜሮን በሚካሄደው የድርጅቱ 14ኛው የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ አባል እንደምትሆን ተስፋ አድርገዋል።
የዓለም ንግድ ድርጅት ኢትዮጵያ የአባልነት ጥያቄዋ ተቀባይነት እንዲያገኝ የቴሌኮም እና የባንክ አገልግሎት ዘርፎቿን ለውጭ ባለሀብቶች እንድትከፍት በተደጋጋሚ ሲጠይቅ መቆየቱ ይታወቃል። አሁን የእነዚህ ዘርፎች ለውጭ ባለሀብቶች መከፈት መጀመራቸው የኢትዮጵያ የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት እንዲያገኝ እንደሚያግዝ ተገምቷል።
ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ከሆንች፣ ምርቶቿን በአባል አገራት ያለ ቀረጥ የመሸጥ መብት ታገኛለች። በተለይም እንደ ቡና ያሉ ምርቶቿን ያለ ክልከላ አቅሟ በፈቀደ መጠን የገበያ ፍላጎት ባለበት ሁሉ እንድትሸጥ ዕድል እንደሚሰጣት ተገልጿል።

ስለ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እና ባንኮችን በተመለከተ አዳዲስ እና የተብራሩ ዜናዎችን በየቀኑ ይፈልጋሉ?
ይህንን ቻናል Subscriber በማድረግ ራስዎን ያዘምኑ፡፡
👇
https://t.me/girum_x_links
https://t.me/girum_x_links
ይህንን ቻናል Subscriber በማድረግ ራስዎን ያዘምኑ፡፡
👇
https://t.me/girum_x_links
https://t.me/girum_x_links
ሲቢኢ ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ ካፒታሉን ወደ 300 ሚሊዮን ብር ሊያሳድግ ነው
በኢትዮጵያ ፈቃድ አግኝተው በቅርቡ ወደ ሥራ ከገቡ ሁለት የኢንቨስትመንት ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው ሲቢኢ ካፒታል አክሲዮን ኢንቨስትመንት ባንክ፣ የካፒታል መጠኑን ወደ 300 ሚሊዮን ብር እንደሚያሳድግ ተገለጸ፡፡ የኢንቨስትመንት አካውንቶችን መክፈት ሊጀምር ነው፡፡
ሪፖርተር ያነጋገራቸው የሲቢኢ ካፒታል አክሲዮን ኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ፣ ኢንቨስትመንት ባንኩ በገበያ ውስጥ ያለውን አገልግሎት ለማስፋት በቀጣዩ በጀት ዓመት ሁለት መቶ ሚሊዮን ብር ካፒታል በመጨመር አጠቃላይ ካፒታሉን ወደ 300 ሚሊዮን ብር እንደሚያሳድግ ገልጸዋል፡፡
ባንኩ ወደ ሥራ ሲገባ 100 ሚሊዮን ብር ካፒታል በማስመዝገብ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ዘመዴነህ፣ ከዚህ ውስጥም 70 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድርሻ ሲሆን፣ ቀሪው 30 በመቶ ደግሞ ዳሉል ካፒታል በተባለ የግል ኩባንያ የተያዘ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ሲቢኢ ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ...
ተጨማሪ ያንብቡ: https://Etsecurities.com

የኢትዮጵያ ሰነድ ሙዓለ ንዋይዮች ገበያ ደንበኞች የኢንቨስትመንት ሂሳብ እንዲከፍቱ ጥሪ አቀረበ።
የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጥላሁን እስማኤል (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ ገበያው በተፈለገው መንገድ እየሄደ ሲሆን፣ ባንኮች እና ሌሎች ድርጅቶችም በገበያው እየተመዘገቡ ነው።
ይህ ጥሪ የቀረበው የገዳ ባንክ በገበያው ላይ ሦስተኛው ተመዝጋቢ ድርጅት በሆነበት ወቅት ነው። ባንኩ የደንበኛ ሳቢ መግለጫውን በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ካስመዘገበ በኋላ በሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ላይ ቀርቧል።
ሸገር እንደዘገበዉ የገዳ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ቡልቶ፣ ባንኩ በዚህ ገበያ በመመዝገቡ ባለአክሲዮኖች ሰፊ የገንዘብ ተደራሽነት እንዲኖራቸው ያደርጋል ብለዋል። በESX የተመዘገቡት ድርጅቶች ወጋገን ባንክ እና ገዳ ባንክ መሆን ችለዋል።

የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ሆነ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የባንክ ዘርፍ ለውጭ ተሳትፎ ክፍት የሚያደርግ አዲስ መመሪያን ይፋ አድርጓል። ይህ እርምጃ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ለማድረግ ሲደረግ የቆየው ጥረት የመጨረሻው ምዕራፍ ተደርጎ እንደሚወሰዱ ተገልጿል።
መመሪያ ቁጥር SBB/94/2025 ባለፉት አንድ ዓመት በተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተደረጉ ሰፊ ውይይቶች እና ምክክሮች ግብዓት ተደርጎበት የተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል።
ይህ መመሪያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፀደቀው የባንክ ሥራ አዋጅ መሰረት የወጣ ሲሆን፣ የሚያስፈልገውን የሕግ ማዕቀፍ ማሟላቱ ተገልጿል።
ይህ አዲሱ የፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ባለሀብቶች፣ ባንኮችን እና ሌሎች ስትራቴጂካዊ ባለሀብቶችን ጨምሮ፣ በኢትዮጵያ የባንክ ሥርዓት ውስጥ እንዲሳተፉ ያስችላል ተብሏል።
ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣዉ መግለጫ መመሪያው የውጭ ተዋናዮች የባንክ ዘርፉን እንዲቀላቀሉባቸው በርካታ መንገዶችን ያቀርባል፤ ከእነዚህም መካከል ቅርንጫፍ ባንኮችን፣ የውጭ ባንክ ቅርንጫፎችን ወይም የወኪል ቢሮዎችን ማቋቋም ይገኙበታል።
ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የባንክ ዘርፍ ለውጭ ተሳትፎ ክፍት መሆኑን የገለፀ ሲሆን የውጭ ባንኮች እና ባለሀብቶችም ማመልከቻዎቻቸውን ለብሔራዊ ባንክ ማቅረብ እንደሚችሉ አስታውቋል።

የቴሌግራም ቻናል ባለቤት ከሆኑ ማስታወቂያዎችን በቻናሎቻችሁ ላይ በመልቀቅ በቀላሉ ገንዘብ ያግኙ።
ይህን ማስታወቂያ የሚያዩበትን ቻናል ጨምሮ ከ 65+ በላይ ቻናሎች አብረውን እየሰሩ ነው፡፡
only for Ethiopian Based Telegram Channels.
Payment With Telebirr
Register on kelemat Ads & Start immediately
Interested?
👉 Contact us for registration @temaripath

ብሔራዊ ባንክ የግምጃ ቤት ቦንድ ግዥ መመሪያን ሰረዘ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግምጃ ቤት ቦንድ ግዥን የሚመለከት የቀድሞ መመሪያውን የሚሽር አዲስ መመሪያ አውጥቷል።
አዲሱ መመሪያ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግምጃ ቤት ቦንድ ግዥ (መሻሪያ) መመሪያ ቁጥር MFAD/TRBO/002/2025፣ ከሰኔ 23 ቀን 2017 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል። ይህም ማለት የቀድሞው መመሪያ በዚህ ቀን ሙሉ በሙሉ ተሽሯል።
አዲሱ የግምጃ ቤት ቦንድ ግዥ አፈጻጸም
በቀድሞው መመሪያ አንቀጽ 5 መሰረት ባንኮች የተመደበላቸውን የግምጃ ቤት ቦንድ እንዲገዙ ይጠበቅባቸው ነበር።
የሚቀርበው የግምጃ ቤት ቦንድ መጠን በየወሩ በባንኩ ከሚሰጡት አዳዲስ ብድሮች እና ቅድሚያ ክፍያዎች መጠን ላይ ብቻ የተመካ ሲሆን፣ ይህ አዲስ መመሪያ ከመውጣቱ በፊት በነበረው አሰራር መሰረት ይተገበር እንደነበር ይታወቃል።
ይሁን እንጂ፣ መመሪያው እስከ ሰኔ 2017 ድረስ የግምጃ ቤት ቦንድ ለመግዛት ከባንኮች ጋር የተደረጉ ስምምነቶች ካሉ እና ግዥው ገና ካልተፈጸመ፣ የቀድሞው መመሪያ እንደተጠበቀ ሆኖ ተግባራዊ ይሆናል። የእነዚህ ቦንዶች ግዥ እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ድረስ መጠናቀቅ እንዳለባቸው አፅንኦት ሰጥቷል።
በተጨማሪም፣ ይህ አዲስ መመሪያ ከመውጣቱ በፊት የተሰጡ ወይም በሽግግር ጊዜው ድንጋጌ መሰረት የሚወጡ ሁሉም የግምጃ ቤት ቦንዶች፣ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ፣ በቀድሞው መመሪያ መሰረት የሚተዳደሩ ይሆናል።

የማይታመን ቅናሽ ከMeda Store፡፡
እጅግ ውብ የሆኑ የቤት እቃዎች እያስገባን ነው፡፡ ለትንሽ ጊዜ በሚቆየው የዋጋ ቅናሽ ተጠቃሚ ይሁኑ፡፡
አዳዲስ እቃዎች ሲገቡ በቅድሚያ እንዲደርስዎ ቻናላችንን Join ያድርጉ፡፡