Ethio Job Vacancy
46.2K subscribers
23.2K photos
63 videos
157 files
19.5K links
አዳዲስ እና ወቅታዊ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ከተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ለሥራ ፈላጊዎች መረጃ መስጠት ነው።
Post New Job vacancies to Who are looking jobs.
Group discussion https://t.me/+uGe3tVg5jF4yZjk0
Download Telegram
#ATTENTION

በጎንደር ከተማ ሚኒ ባስ ፣ ባጃጅ ፣ ጋሪና ምግብ ነክ ያልሆኑ የንግድ ተቋማት አገልግሎት እንዳይሰጡ ከመጋቢት 26/2012 ዓ/ም ጅምሮ የተከለከለ መሆኑን የከተማዋ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ኮማንድ ፖስት አስታውቋል።

ስራውን እንዲቀጥሉ የተፈቀደላቸው የንግድ ድርጅቶች ደግሞ ወፍጮ ቤቶች፣ ፈርማሲዎች ፣ክሊኒኮች ዳቦ ቤቶች የእህል መጋዝኖች ፣ምግብ ቤቶችና ሆቴሎች መሆናቸውን ተነግሯል።

እንዲሰሩ ፈቃድ የተሰጣቸው ምግብ ቤቶችና ሆቴሎች 50 በመቶ የመቀመጫ ወንበር በመቀነስ እንዲሰሩ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

ምንጭ፦ የጎንደር ከተማ አስተዳደር
@AddisEthiopiaMe
#ATTENTION

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 365 ሰዎች 56ቱ የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክም ሆነ ከበሽታው ተጠቂ ግለሰብ ጋር ንክኪ #ያልነበራቸው መሆናቸውን አሳውቀዋል።

ከእነዚህ ውስም 48 በመቶ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች በመሆናቸው ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው አሳስበዋል- #FBC
For more join here…
@AddisEthiopiaMe
#ATTENTION

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ክፉኛ የሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ነው።

ባለፉት 24 ሰዓት 8,246 ሰዎች ህይወታቸውን በበሽታው አጥተዋል።

አሜሪካ ከ2 ሺህ በላይ፣ ሜክሲኬ 7 መቶ፣ ሩሲያ ከ4 መቶ በላይ ፣ UK ከ4 መቶ በላይ ዜጎቻቸውን በአንድ ቀን ካጡት ውስጥ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው።

በሌላ በኩል ከ551 ሺህ በላይ ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መዘጋናጋት እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው።

የሚደረገው ምርመራ አነስተኛ መሆን ፣ በተገቢው መንገድ በየኣካባቢው ህይወታቸው የሚያልፈውን ሰዎች ትክክለኛ ምክንያት ማወቅ አለመቻል ወረርሽኙ አሁን እየተነገረ ካለው በላይ ጉዳት እያደረሰ ሊሆን እንደሚችል የቲክቫህ አባላት የጤና ባለሞያዎች ተናግረዋል።

የጤና ባለሞያዎቹ ያለው ቸልተኝነት እና መዘናጋት አሳሳቢ በሆኑ ገልፀዋል። ማስክ የማድረግ ባህልም እጅግ ወርዷል ብለዋል።

ተስፋ ሰጪ የኮቪድ ክትባት መገኘቱ ሁሉንም ችግር መፍታት ይችላል ብሎ ማመን ትክክል አይደለም ያሉት የጤና ባለሞያዎቹ ፤ በመንግስትም ሆነ አጠቃላይ ማህበረሰቡ ያለውን አሳሳቢ ሁኔታ ተረድቶ እራሱን እና ወገኑን እንዲታደግ ጥሪ አቅርበዋል።

TIKVAH-ETH