#ጥንቃቄ_አዎ_ጥንቃቄ
እሰልሰዋለሁ ጥንቃቄ አድርጉ
በዚህ በ21ኛው የዲጂታል አለም ከውጭም ከአገር ውስጥም እንዲሁም በተቀናጀ መልኩ እጅግ የረቀቀ የማታለል፣ የማጭበርበር ወንጀል ስራዎች እየተሰሩ በርካቶች ሳያውቁ ተታለው ጥረው ግረው የሰሩትን ገንዘብ ተጭበርብረዋል። ይሔን የደረሰባቸው የተጭበረበሩ እልፎች ያውቁታል። ወገን አንዳንዴ ቆም ብለን እናስተውል፤ ለምን ይሔን አድርግ አለኝ፣ ይሔን አዋጭ ቢዝነስ ነው ስራ አለኝ፣ ለምን ይሔን ያህል ዋስትና ለሌለው የቢዝነስ ሃሳብ ኢንቨስት (ብር ክፈል) አለኝ? ተሸላሚ ነህና ብር ክፈል አለኝ? Bla bla bla ወደ አዕምሯችሁ ሊመጡ ልታሰላስሉት የሚገባ በርካታ ጥያቄዎችን ደጋግሞ ማጤን ያስፈልጋል። የሚገርመው ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንተርኔትን በመጠቀም የOnline business መስራት ይቻላል ይሔን ሊንክ Click አድርግና አካውንት ከፍተህ በየቀኑ Click click በማድረግ ገንዘብ መስራት ትችላለህ የሚሉ በርካቶች አሉ። ይሔ እኛ አገር ውስጥ የማይሰራ የፈለገ በነፃ Click ብታደርግ ገንዘብ Invest አድርገህ Click ብታደርግ ያለህን የሞባይል ካርድ አለፍ ሲል Invest ያደረገውን ገንዘብና ጊዜ ከማጥፋት ውጭ ኪሳራ እንጂ ገቢ በፍፁም አታገኙም። እንደሚታወቀው ዛሬ ላይ Mobile Banking, Tele birr, Internet Banking, ሌሎችንም የዲጂታል ፋይናንስ ብዙዎቻችን እንጠቀማለን። ታዲያ እነዚህ አጭበርባሪዎች ስልክ በመደወል ሽልማት ደርሷችኋል፣ አሁን በስልክህ የተላከ ኮድ አለ እሱን ላክልኝ ወይንም ንገረኝ/ሪኝ፣ በዚህ መሰረት ስልክህ ላይ በመጻፍ ሽልማት (Bonus) ይገባልሃል፣ ሌላም የማታለያ ዘዴዎችን በመጠቀም እያታለሉ በርካቶችን ዘርፈዋል። ወገን ኧረ እንንቃ። ማንም የማታውቀው ግለሰብ በዚህ ጊዜ አንተን ሊሸልም፣ ገቢ የሚያስገኝ ቢዝነስ ላይ ሊያሳትፍህ በቀጥታ በስልክ ደውሎ፣ በቴሌግራም ሊንክ (መልዕክት) በመላክ ሊያሰራህና ራስህን እንድትለውጥ አያደርግህም። በርካታ ባንኮች በተለይ ከዚህ ባንክ ነው ሽልማት ደርሷችኋል፣ የተላከ ኮድ አለ እሱን ይላኩልንና መሰል መልዕክት በመላክ እንዳትጭበረበሩ ተጠንቀቁ የሚል በተለያዬ ወቅት ሲያስጠነቅቁ ይታያል። ሽልማት እንኳን ቢሆን በአቅራቢያ ከሚገኝ የባንክ ቅርንጫፍ ሂዶ መጠየቅም ይቻላል። ከተባባሪ አካላት ጋር እጅግ በረቀቀ መልኩ ስለሚሰሩ ከመጠንቀቅ በስተቀር ከስሼ ብሬን አስመልሳለሁ አይሰራም።
ወገን ከመሰል አጭበርባሪዎች እንጠንቀቅ። ቆም ብለን እናስብ፣ እናስተውል፣ ለሌሎችም ግንዛቤ እንፍጠር።
ይሔ ወንጀል በዋናነት ሥራ ፈላጊ ወገኖች ላይ ስለሚበረታ ለጥንቃቄ አካፈልኳችሁ።