Ethio Job Vacancy
45.2K subscribers
23.2K photos
63 videos
157 files
19.1K links
አዳዲስ እና ወቅታዊ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ከተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ለሥራ ፈላጊዎች መረጃ መስጠት ነው።
Post New Job vacancies to Who are looking jobs.
Group discussion https://t.me/+uGe3tVg5jF4yZjk0
Download Telegram
ጀርመን #ባለሞያ ሰራተኞችን ልትቀበል ነው።

የጀርመን ምክር ቤት በተለያዩ ሙያ የሰለጠኑ ከአዉሮፓ ህብረት (EU) ሃገራት ዉጭ የሆኑ ሰራተኞች ወደ ጀርመን እንዲገቡ የሚፈቅደዉን አዲስ ደንብ ማፅደቁ ተነግሯል።

አዲሱ ደንብ ባለሙያዎች፣ የጀርመንኛና የእንግሊዝኛ ቋንቋ እስከቻሉ ድረስ ያለ ብዙ ዉጣ ዉረድ ወደ ጀርመን እንዲገቡና ጀርመን ዉስጥ እንዲሰሩ የሚፈቅድ ነው ተብሏል።

ይህ ደንብ በጀርመን ለሚገኙ በርካታ ስደተኞች እድል የሚሰጥ ሴሆን በካናዳ ደንብና አሰራር መሠረት የተቀረፀ እንደሆነ ተነግሯል።

ደንቡ በተለይ እንደ መስተንግዶ፣ ጤና፣ ግንባታና ቴክኖሎጂን በመሳሰሉ መስኮች ጀርመን ያለባትን የባለሙያ እጥረት ለማቃለል ይረዳል ተብሏል።

መረጃው የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

ታድያ ይሔን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ይሔን ምስኪን ስራ ፈላጊ በሰበብ አስባቡ በደካማ ጎኑ በመግባት ማጭበርበር እንደ መደበኛ ሥራ የያዙ አጭበርባሪዎች ወደ ስራ ገብተዋል። ወገኔ ሆይ ይሔ ደንብ ፀደቀ ተባለ እንጂ ገና በመመሪያ ተደግፎ ከየትኞች አገራት በምን ሕጋዊ መንገድ ምን አይነት ሠራተኞችን፣ በምን የትምህርት ዝግጅት መቀበል እንዳለባቸው ባልተገለጸበት እና እጅግ በርካታ ሥደተኞች በጀርመን ሀገር ስለሚገኙ እነርሱን ወደስራ ያሰማሩ ወይንስ ከሌሎች አገራት እንቀበል የሚሉ በርካታ ጉዳዮች ባልጠሩበት ሁኔታ እንደዚህ አይነት ማስታወቂያ ስትመለከቱ ሕጋዊነቱን ማጣራት ከሚመለከተው ፍቃድ ሰጪ አካል ማረጋገጥ ተገቢ ነው ለማለት እንወዳለን።
ስለዚህ መሰል የማጭበርበሪያ ማስታወቂያ ስትመለከቱ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፣ በዚህም ዙሪያ የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ ሥራ ፈላጊዎችን ከአጭበርባሪዎች መታደግ ተገቢ ነው ለማለት እንወዳለን።
ጓደኞቻችሁም እንዳይጭበረበሩ መረጃው #Share ይደረግ።