Ethio Job Vacancy
46.2K subscribers
23.2K photos
63 videos
157 files
19.5K links
አዳዲስ እና ወቅታዊ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ከተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ለሥራ ፈላጊዎች መረጃ መስጠት ነው።
Post New Job vacancies to Who are looking jobs.
Group discussion https://t.me/+uGe3tVg5jF4yZjk0
Download Telegram
[ ራስን ማሸነፍ ባላንጣን ከማሸነፍ በላይ ጀግና ሲያደርግ ]
.
#በእሥሌማን_አባይ [ Journalist ]

“LOST A MEDAL BUT WON HEARTS”

አትሌቱ የወርቅ ሜዳሊያውን ትቶ ከወርቅ በላይ የሆነ ጀብዱ ፈፀመ። ይህኛው ጀግንነት ተቀናቃኝን ሳይረቱ በሰብአዊ ፍቅር ብቻ የጀግኖች ጀግና የሚሆኑበት ክስተት ነው።

ኬኒያዊው አትሌት ሲሞን ቼፕሮት፣ አለማቀፍ በሆነ የ 10 ሺህ ሜትር አትሌቲክስ ውድድር ላይ በማሸነፊያው ጫፍ ላይ ይገኛል። የአገሩ ልጅና ብርቱ ተቀናቃኙ የሆነው ኬኔት ኪፕኬሞይ ድንገት ሲዝለፈለፍ ተመለከተ። ሲሞን በዚያች ቅፅበት አንደኝነቱን ከልቡ አወጣው። ለሁለተኛ ጊዜ የወርቅ ሜዳሊያ የማሸነፉን ነገርም ተወው። ይልቁንም ጔደኛውን ደግፎ ለማንሳት ወሰነ። ቀስ አድርጎም አነሳው። ከዛም ከጔደኛው ጋር በቀስታ እየተጔዙ ውድድሩን 15ኛ እና 16ኛ ሆነው ጨረሱት።

ሲሞን በሩጫ ከሚገኘው አሸናፊነት የሰው ልጅን በፍቅር ማሸነፍ እንደሚበልጥ በተግባሩ ገለፀ።

የተፎካካሪውን ውድቀት እንደመልካም አጋጣሚ ከመጠቀም ይልቅ ልባዊ ወንድምነቱን በወሳኟ ቅፅበት ማሳየት ታላቅነት ስለመሆኑ ተግብሮ አሳዬ።

ከወርቅ ሜዳሊያው ይልቅ ሰብአዊነት እንደሚልቅ ለመላው አለም አወጀ።

ከአትሌትነት በፊት "ሰው መሆን ይቀድማል" የሚል ትምህርትንም በታሪኩ አሰፈረ።

ትንግርቱን በቀጥታ ቴሌቪዥን የሚከታተሉ ሁሉ ሲሞንን "ጀግና ጀግና" ሲሉ አወደሱ።

በናይጄሪያ የአለም አትሌቲክስ ወኪሎች ሲሞንን "ጀግናችን" ሲሉ አወደሱት። ለመልካም ተግባሩም 1 ሚሊዮን ሺልንግ ሸለሙት።

የውድድሩ አዘጋጆችም ለወንድማዊ መልካም ተግባሩ ሌላ 1 ሚሊዮን ሺልንግ አበረከቱለት።

ከማእረጎች ሁሉ ሰው መሆን በላጭ ነው። የሰው ልጅም ከሁሉም ውድ ነው።

ባላንጣን ከመርታት የራስን ፍላጎት ማሸነፍ እውነተኛው ጀግንነት ነው።
Okpekpe Race Promoter Itemuagbor Hails Amazing Fair Play Hero Cheprot
Mike Itemuagbor, promoter of the IAAF silver label Okpekpe International 10km Road Race has hailed Kenyan athlete, Simon Cheprot for his heroic feat at the 7th edition of the race held last Saturday in Okpekpe, a rusty town in Etsako East local government area of Edo State.
The lanky Cheprot who won the Okpekpe race men’s title in 2016 and was first runner up last year won the hearts of fans both at the venue and those watching live on television across the African continent when he stopped to help a rival, Kenneth Kipkemoi who collapsed towards the end of the race.
Cheprot helped his colleague across the finish line before beckoning on the medical team at the finish for aid.
The Kenyan was rewarded with $10, 000 for his humanitarian effort and Itemuagbor says what Cheprot did is the true definition of sportsmanship.
”Simon (Cheprot) may not have fulfilled his ambition of becoming the first athlete (man or woman) to win two Okpekpe titles since 2013 when we began this race, but he came to Okpekpe this year, ran and left as the hero. He did not win any medals but he won hearts.
https://www.completesports.com/okpekpe-race-promoter-itemuagbor-hails-amazing-fair-play-hero-cheprot/