Ethio Job Vacancy
46.1K subscribers
23.2K photos
63 videos
157 files
19.5K links
አዳዲስ እና ወቅታዊ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ከተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ለሥራ ፈላጊዎች መረጃ መስጠት ነው።
Post New Job vacancies to Who are looking jobs.
Group discussion https://t.me/+uGe3tVg5jF4yZjk0
Download Telegram
መጭዋ ኢትዮጵያ እንደ ደቡብ አፍሪካ በጠራራት ጸሃይ የሚዘረፍባትና ማጅራት የሚመታባት እንዳትሆን እሰጋለሁ....እየሆነች አይደል እንዴ የምትሉም አትጠፉ

#በቱሉ_ዲምቱ ፍተሻ ጣብያ 33 ኩንታል የካናቢስ ዕፅ ተይዟል...33 ኩንታል አስቡት ኪሎ ግራም አላልኩም።

ከጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ ጭነት ሥር ተደርጎ ወደ አዲስ አበባ ሊገባ ሲል ነው የተያዘው።

#ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ 8ሺ የሚደርሱ ስዎች በቦሌና አካባቢው ብቻ በምሽት ጭፈራ ቤቶች ሲደንሱና አሸሼ ገዳሜ እያሉ ሲጨልጡ ከዚህም አልፎ ሺሻና ሌሎች አደንዛዥ እጾችን ሲጠቀሙ በድንገተኛ አፈና ተይዘዋል ተብሏል/ጠዋት ተመዝግበው ቢለቀቁም።

#ከ1_ወር በፊት ሚያዚያ 5 ቀንም መጠኑ #790_ኪሎ_ግራም የሆነ የካናቢስ ዕፅ ያቤሎ ላይ በቁጥጥር ሥር መዋሉንና አዘዋዋሪው መሠወሩን

#650_ኪሎ_ግራም የካናቢስ ዕፅ ሞያሌ ላይ በቁጥጥር ሥር ውሎ እንደነበርም አብመድ በዘገባው አስታውሷል።

ካናቢስ የማዕከላዊ ሥርዓተ ነርቭ ተግባርን የሚውክና የሰዎችን ስሜት የሚለውጥ አደገኛ ዕፅ ነው፤ ይህን የለመደ ሰው ሲያጣ መዝረፍና መግደሉ መች ይቀራል።