Ethio Job Vacancy
46.2K subscribers
23.2K photos
63 videos
157 files
19.6K links
አዳዲስ እና ወቅታዊ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ከተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ለሥራ ፈላጊዎች መረጃ መስጠት ነው።
Post New Job vacancies to Who are looking jobs.
Group discussion https://t.me/+uGe3tVg5jF4yZjk0
Download Telegram
ሚያዝያ 26/2011 (04 May 2019) ...
Advert on Addis Zemen Magazine
Ministry of Health
ለሥራ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ለመጓዝ የሚፈልጉ ዜጎች ሊያውቋቸው የሚገቡ መሠረታዊ ጉዳዮች
**********************************
መንግስት በሀገር ውስጥ የተለያዩ የስራ እድሎችን በማስፋፋት ስራ ፈላጊ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ መስራት ለሚችሉ ዜጎች ሁሉ በሀገር ውስጥ ላሉ የስራ እድሎች ቅድሚያ በመስጠት ሰርተው የሚለወጡበትን ሁኔታዎች በማመቻቸት ዜጎችን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ሠርቶ ለመኖር በርካታ መልካም አጋጣሚዎች አሉ፡፡ ለዚህም ምሳሌ የሚሆኑ በሀገራቸው ሠርተው የተለወጡ በርካታ ወጣቶችን መጥቀስ ይቻላል፡፡
ከዚህ ባለፈ ወደ ውጭ ሀገራት ለስራ መሄድ የሚያስቡ ዜጎች እራሳቸውን ከአቻ ግፊትና ከህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ሊጠብቁ ይገባል፡፡ ዜጎች ስለሚሄዱበት ሀገር ስላለው እውነታ ያላቸው ግንዛቤና መረጃ ውስንና የተዛባ በመሆኑ ከመሄዳቸው በፊት ስለሚሄዱበት ሀገር ባህል፣ ወግና ልማድ መረዳትና እና የዜጎችን መብት ደህንነትና ክብር ለማስጠበቅ ሲባል በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የወጣውን አዋጅ ቁጥር 923/2008 ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
ለጉዞ ከመነሳታችን በፊት ምን ማወቅ ይጠበቅብናል?
*********************************************
ወደ ውጭ ሀገር ሄደን ለመስራት በምናስብበት ወቅት ጊዜ ሰጥቶ ማሰብ ይገባል፡፡ ለምን እንደምንሄድ፣ ከሄድን በኋላ የሚያጋጥሙንን መልካምና መጥፎ አጋጣሚዎች እንዴት መቋቋምና ማለፍ እንደሚገባን፣ የምንሄድበትን ሀገር ባህል፣ ወግ፣ ልማድና ስርዓት እንዴት ተላምደን መኖር እንደምንችል፣ የሰራንበትን ገንዘብ ወደ ሀገራች እንዴት መላክና መቆጠብ እንደምንችል፣ ኮንትራታችንን ጨርሰን መቼ ወደ ሀገራችን መመለስ እንዳለብን አስቀድመን ማቀድ ያስፈልጋል፡፡
በአዋጅ ቁጥር 923/2008 መሰረት በውጭ አገር ለስራ የሚሰማሩ ዜጎች እድሜያቸው ከ18 አመት በላይ የሆኑ ፣ 8ኛ ክፍል ያጠናቀቁ (ወደ 9ኛ ክፍል የተዛወሩ)፣በሚሄዱበት የስራ መስክ ስልጠና ወስደው የብቃት ማረጋገጫ ያገኙ፣ የቅድመ ጉዞ ስልጠና ወስደው ሰርተፊኬት የያዙ፣ የጤና ኢንሹራንስ የተገባላቸው፣ ሙሉ የጤና ምርምራ ያደረጉና ከወንጀል ነጻ ሊሆኑ ይገባል፡፡
ይህን ያሟሉ ዜጎች በአስቀጣሪ ኤጀንሲ በኩል ወይም በራሳቸው አማካኝነት ሥራውን በማፈላለግ ማለትም በቀጥታ ቅጥር አስፈላጊውን የቅጥር ፎርማሊቲ በማሟላት ቪዛውን አግኝተው መሄድ ይችላሉ፡፡ ብዙ ጊዜ በቀጥታ ቅጥር የሚጓዙ ሠራተኞች መደበኛ ስልጠና የወሰዱና ከቤት ሠራተኝነት ውጭ በልዩ ልዩ ሙያዎች የሰለጠኑ ሲሆን የሚሠሩትም በካምፓኒና በልዩ ልዩ አነስተኛ የቢዝነስ ተቋማት ውስጥ ነው፡፡ ከዚህ በፊት በውጭ ሀገር ሰርተው የተመለሱ ልምድ ይኖራቸዋል ተብሎ ስለሚታሰብ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ ከሆነ ስልጠናውን መውሰድ ግዴታ ባይሆንም የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የት ሀገር ነው መሄድ የሚቻለው?
******************************
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በቤት ሠራተኝነት የሚሄድ ከሆነ ሊጓዝ የሚችለው በኤጀንሲዎች አማካኝነት ብቻ መሆኑን ሊረዳ ይገባል፡፡ የስራ ስምሪት ማድረግ የሚችለውም አገሪቷ የሁለትዮሽ ስምምነት ወደተፈራረመችባቸው ሀገራት ብቻ ነው፡፡ የሁለትዮሽ ስምምነት የተፈፀመባቸው መዳረሻ ሀገራት ለጊዜው ሳውዲ አረቢያ፣ ኳታርና ጆርዳን ሲሆኑ ከሌሎች አገሮች ጋር የሚደረገው ስምምነትም በሂደት ይቀጥላል፡፡
ስምምነት በተፈፀመባቸው ሀገሮች የደመወዝ መጠን ስንመለከት ከኳታር መንግስት 1200 ለቤት ሠራተኛና 1300 ለእንክብካቤ (care giver) የኳታር ሪያል፣ ከጆርዳን መንግስት ለጀማሪ 225 ዶላር፣ ልምድ ላላው 250 ዶላር፣ ከሳውዲ አረቢያ መንግሰት ጋር 1000 የሳውዲ ሪያል እንዲሆን ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
በሠራተኞችና በአሠሪዎች የሚሸፈኑ ወጪዎች
*********************************************
አንድ ሠራተኛ በሥራ ለመሰማራት አስፈላጊውን መስፈርት ካሟላና ብቁ ከሆነ በአዋጁ የተደነገጉ የቅጥርና ምልመላ መንገዶችን በመከተል አስፈላጊውን መፈጸም እና ወጪዎችን መሸፈን ይገባል፡፡
1. አሠሪው ወይንም ኤጀንሲው የሚሸፍናቸው ወጪዎች
በአሠሪው የሚሸፈኑ ወጪዎች ሠራተኛውን ወደ ተቀባይ አገር ለማድረስ፣ በተቀባይ አገር ያለችግር እንዲቆይና እንዲሠራ ለማድረግ፣ እንዲሁም በሥራ ላይ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን የሚወጡ ወጪዎች ናቸው፡፡
እነርሱም የተቀባይ አገር የመግቢያ ቪዛ፣ የደርሶ መልስ መጓጓዣ፣ የሥራ ፍቃድ፣ የመኖሪያ ፍቃድ፣ የሥራ ውል ማጽደቂያ ክፍያዎች፣ የመድህን ዋስትና ሽፋን እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኝ የተቀባይ አገር ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ጽህፈት ቤት የሚከፈል ከቪዛና ከሰነድ ማረጋገጥ ጋር የተያያዘ ማናቸውም ወጪዎች ናቸው፡፡
2. በሠራተኛው የሚሸፈኑ ወጪዎች
አንድ ሠራተኛ ለሥራ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በሚጓዝበት ወቅት የሚያወጣው ወጪ በአብዛኛው በህይወት ዘመኑና በማህበራዊ ህይወቱ ውስጥ የትኛውም ሰው ስለሚጠቀምባቸው የሚያወጣቸው ወጪዎች ናቸው፡፡
እነርሱም ለልደት ሰርተፊኬት፣ ለፓስፖርት፣ ለክትባት፣ ለህክምና ምርመራ፣ ለሙያ ብቃት ማረጋገጫ፣ ከወንጀል ነፃ ማስረጃ ማረጋገጫ ወጪዎች ናቸው፡፡ እነኝህ ክፍያዎች በሙሉ አገልግሎቱን ለሰጡ ሌሎች መሥሪያ ቤቶችና ተቋማት የሚከፈል እንጂ ምልመላውን ለሚያከናውነው ኤጀንሲ የሚከፈል አይደለም፡፡ ኤጀንሲው ምንም አይነት ክፍያ ከሠራተኛው ቢጠይቅ ህገወጥ ያደርገዋል፡፡
ይሁን እንጂ ለሥራ ወደ ውጭ አገር ለመሄድ አስፈላጊ ሁኔታዎች ተጠናቀው ያለበቂ ምክንያት ሠራተኛው ወደ ሥራ ባይሰማራ ከቅጥሩ ጋር በተያያዘ አሠሪው ያወጣውን ወጪ ሠራተኛው እንዲከፍለው ሊጠይቅ ይችላል፡፡ በተመሳሳይ መንገድ በተራ ቁጥር 2 ላይ የተጠቀሱትን ወጪዎች ሠራተኛው አውጥቶ በራሱ ጉድለት ባልሆነ ምክንያት በሥራ ላይ ካልተሰማራ ኤጀንሲው ወይም አሠሪው የሠራተኛውን ወጪ የመተካት ግዴታ ይኖርበታል፡፡
ለውጭ አገር ሥራ ስምሪት የሚሰጡ ስልጠናዎችና ማሰልጠኛ ተቋማቱ
************************************************************
ለውጭ አገር ሥራ ስምሪት የሚሰጡ ስልጠናዎች ሶስት ሲሆኑ እነሱም በቤት አያያዝ (HOUSE HOLD SERVICE) በቤት ውስጥ ስራ (DOMESTIC HELP) እና በእንክብካቤ ስራ (CARE GIVING) ናቸው፡፡
የነዚህ ሙያዎች የስልጠና መሳሪያዎች፣ የሙያ ደረጃ፤ ስርዓተ ትምህርት እና የብቃት ማረጋገጫ ምዘና መሳሪያዎች ሲዘጋጁ ለማንኛውም ዜጋ እንዲያገለግል ሲሆን ወንድም ሆነ ሴት በፍላጎቱ ሊሰለጥን ይችላል፡፡ ሠልጣኞች ስልጠናውን በግላቸው ሊሠሩበት፣ በአገር ውስጥ ሊቀጠሩበት እንዲሁም ወደውጭ አገር ሊሰማሩበት እንደሚችሉ ሊገነዘቡና በምልመላ ወቅትም ሊነገራቸው ይገባል፡፡ በተጨማሪም በስልጠናው የተሳተፈ ሁሉ የብቃት ምዘናውን ያልፋል ማለት አይደለም፣ የብቃት ምዘናውን ያለፈ ሁሉ ቀጣሪ ያገኛል ማለትም አይደለም፡፡ በመሆኑም በተጠቀሱት ሙያ እንዲሰለጥኑ የተደረጉ ሁሉ ወደአረብ ሀገር መሄድን እንደመብት ሊያዩት አይገባም፡፡
ይሁን እንጂ ወደአረብ አገር መሄድ የሚፈልጉ ሰልጣኞች ከላይ በተጠቀሱት ሦስት ሙያዎች ከሰለጠኑ በኋላም የብቃት ምዘና ማረጋገጫ ተፈትነው ማለፍና ሰርተፊኬት መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ስልጠናው በየክልላቸውና በአቅራቢያቸው በሚገኙ በተመረጡ ማሰልጠኛ ተቋማት ይሰጣል፡፡ ስልጠናው በየክልላቸውና አቅራቢያቸው የመሰጠቱ ጠቀሜታም የሠራተኞች ምልመላ በየክልላቸው የሚካሄድ በመሆኑ፣ አስፈላጊ መረጃዎችን ለማጣራትና ለማረጋገጥ፣ የዜጎችን ደህንነትና ክብር በቅርብ ለመከታተል እና ከስልጠና፣ ከምልመላ ጋር ተያይዞ ለአላስፈላጊ ወጪና የመብት ጥሰቶች እንዳይጋለጡ ያግዛል፡፡
ስልጠናን በተመለከተም፣ የመንግስት ማሰልጠኛ ተቋማት ትምህርቱን በነፃ የሚሰጡ ሲሆን ማንኛውም ሰልጣኝ በክልሉ በሚገኝ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ወይም በየዞኑና ክፍለ ከተማው ወይም ወረዳዎች በሚገኙ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤቶች በመመዝገብ ለየማሰልጠኛዎቹ በመላክ እንዲሰለጥኑ ይደረጋል፡፡
በተጨማሪም የመንግስት ማሰልጠኛ ተቋማት የተደራሽነትና የአቅም ውስንነት ስላለባቸው በፌደራልና በክልል በሚገኙት የቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ ቢሮዎች ለግል ማሰልጠኛ ተቋማት ፍቃድ በመስጠት በማሰልጠን ስራው እንዲሳተፉ ተደርጓል፡፡ በመሆኑም የግል ማሰልጠኛ ተቋማት የስልጠና ጥራታቸው ላይ ጥንቃቄ በማድረግና አስፈላጊ የስልጠና ቁሳቁሶችን በማሟላት የትምህርቱን ጥራት እንዲጠብቁ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ ፍቃድ ሰጪ አካላትም የጀመሩትን ክትትል፣ ቁጥጥርና ድጋፍ በማጠናከር እገዛ እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡
በየክልሉ የተመረጡ የመንግስት ማሰልጠኛ ተቋማት ዝርዝር
************************************************
በመንግስት የተመረጡ 66 ማሰልጠኛ ተቋማት ሲሆኑ ስልጠናውም በሁሉም ክልል በነፃ ይሰጣል፡፡
የማሰልጠኛ ተቋማት ዝርዝር በየክልሉ፡-
አማራ ክልል
***********
1. ባህርዳር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
2. ወልድያ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
3. ደሴ ወ/ሮ ስህን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
4. ከሚሴ ቴ/ሙያ ኮሌጅ
5. ደ/ብርሃን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
6. ጎንደር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
7. እንጂባራ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
8. ቡሬ ቴ/ሙያ ኮሌጅ
9. ደብረታቦር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
10. ደብረ ማርቆስ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
11. ሠቆጣ ቴ/ሙያ ኮሌጅ
ደቡብ ክልል
***********
1. አዋሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
2. አርባ ምንጭ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
3. ሶዶ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
4. ዱራሜ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
5. ሆሳዕና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
6. ወራቤ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
7. ወልቂጤ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
8. ቡታጅራ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
9. ሀላባ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
10. ይርጋለም ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
11. ዲላ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ትግራይ ክልል
***********
1. መቀሌ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
2. ዶ/ር ተወልደ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ
3. አክሱም ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
4. ዶ/ር አርዕያ ካሳ ኮሌጅ
5. ውቅሮ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
6. (ማይጨው)ጥላሁን ይግዛው ፖሊቴክኒክ
7. አላማጣ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
************************
1. እንጦጦ ቴ/ሙ/ት/ስልጠና ኮሌጅ
2. ጄነራል ዊንጌት ቴ/ሙ/ት/ስልጠና ኮሌጅ
3. ንፋስ ስልክ ቴ/ሙ/ት/ስልጠና ኮሌጅ
4. ምስራቅ አጠቃላይ ቴ/ሙ/ት/ስልጠና ኮሌጅ
5. የካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
6. ልደታ ማኒፋክቸሪንግ ኮሌጅ
7. አዲስ ከተማ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
8. ቂርቆስ ማኒፋክቸሪንግ ኮሌጅ
9. አቃቂ ቴ/ሙ/ት/ስልጠና ኮሌጅ
ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር
***********************
1. መለስ ዜናዊ ቴ/ሙ/ትስ/ኮሌጅ
ኦሮሚያ ክልል
*************
1. ሀሮማያ ቴክኒክና ሙያ
2. አሰላ ቴክኒክና ሙያ
3. ሻሸመኔ ቴክኒክና ሙያ
4. መርቲ ፖሊ ቴክኒክ
5. ቢሾፍቱ ቴክኒክና ሙያ
6. ጂማ ቴክኒክና ሙያ
7. መቱ ቴክኒክና ሙያ
8. መቱ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
9. ነቀምት ቴክኒክና ሙያ
10. ነቀምት ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
11. ባቱ ተራራ ቴክኒክና ሙያ
12. ዶና ባርበር ቴክኒክና ሙያ
13. ፍቼ ቴክኒክና ሙያ
14. መርቲ ፖሊ ቴክኒክ
15. አዳማ ፖሊ ቴክኒክ
16. አብቦ ፖሊ ቴክኒክ
17. ሰበታ ፖሊ ቴክኒክ
18. ወሊሶ ፖሊ ቴክኒክ
19. አጋሮ ፖሊ ቴክኒከ
20. አደላ ፖሊ ቴክኒክ
21. ቡሌ ሆራ ፖሊ ቴክኒክ
22. ጨርጭር ፖሊ ቴክኒክ
23. ደደር ፖሊ ቴክኒክ
24. አርሲ ነገሌ ፖሊ ቴክኒክ
25. ሀሰሳ ፖሊ ቴክኒክ
26. ጊምቢ ፖሊ ቴክኒክ
27. ወንጂ ፖሊ ቴክኒክ
#epa
የግእዝ ቁጥሮች በአኀዝና በፊደል
=====================
0. - አልቦ
1. ፩ አሐዱ
2. ፪ ክልኤቱ
3. ፫ ሠለስቱ
4. ፬ አርባዕቱ
5. ፭ ሐምስቱ
6. ፮ ስድስቱ
7. ፯ ስብዓቱ
8. ፰ ስመንቱ
9. ፱ ተሰዓቱ
10. ፲ አሠርቱ
11. ፲፩ አሠርቱ ወአሐዱ
12. ፲፪ አሠርቱ ወክልኤቱ
13. ፲፫ አሠርቱ ወሠለስቱ
14. ፲፬ አሠርቱ ወአርባዕቱ
15. ፲፭ አሠርቱ ወሐምስቱ
16. ፲፮ አሠርቱ ወስድስቱ
17. ፲፯ አሠርቱ ወሰብዓቱ
18. ፲፰ አሠርቱ ወስመንቱ
19. ፲፱ አሠርቱ ወተሰዓቱ
20. ፳ እስራ
21. ፳፩ እስራ ወአሐዱ
22. ፳፪ እስራ ወክልኤቱ
23. ፳፫ እስራ ወሠለስቱ
24. ፳፬ እስራ ወአርባዕቱ
25. ፳፭ እስራ ወሐምስቱ
26. ፳፮ እስራ ወስድስቱ
27. ፳፯ እስራ ወሰብዓቱ
28. ፳፰ እስራ ወሰመንቱ
29. ፳፱ እስራ ወተሰዓቱ
30. ፴ ሠላሳ
31. ፴፩ ሠላሳ ወአሐዱ
32. ፴፪ ሠላሳ ወክልኤቱ
33. ፴፫ ሠላሳ ወሠለስቱ
34. ፴፬ ሠላሳ ወአርባዕቱ
35. ፴፭ ሠላሳ ወሐምስቱ
36. ፴፮ ሠላሳ ወስድስቱ
37. ፴፯ ሠላሳ ወሰብዓቱ
38. ፴፰ ሠላሳ ወሰመንቱ
39. ፴፱ ሠላሳ ወተሰዓቱ
40. ፵ አርብዓ
50. ፶ ሃምሳ
60. ፷ ስድሳ
70. ፸ ሰብዓ
80. ፹ ሰማንያ
90. ፺ ተሰዓ
100. ፻ ምዕት
101. ፻፩ ምዕት ወአሐዱ
102. ፻፪ ምዕት ወክልኤቱ
103. ፻፫ ምዕት ወሠለስቱ
104. ፻፬ ምዕት ወአርባዕቱ
105. ፻፭ መዕት ወሐምስቱ
106. ፻፮ ምዕት ወስድስቱ
107. ፻፯ ምዕት ወሰብዓቱ
108. ፻፰ ምዕት ወስመንቱ
109. ፻፱ ምዕት ወተሰዓቱ
110. ፻፲ ምዕት ወአሠርቱ
111. ፻፲ወ፩ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ
112. ፻፲ወ፪ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ
113. ፻፲ወ፫ ምዕት አሠርቱ ወሠለስቱ
114. ፻፲ወ፬ ምዕት አሠርቱ ወአርባዕቱ
115. ፻፲ወ፭ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ
116. ፻፲ወ፮ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ
117. ፻፲ወ፯ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ
118. ፻፲ወ፰ ምዕት አሠርቱ ወስመንቱ
119. ፻፲ወ፱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ
120. ፻፳ ምዕት ወእስራ
130. ፻፴ ምዕት ወሠላሳ
140. ፻፵ ምዕት ወአርብዓ
150. ፻፶ ምዕት ወሃምሳ
160. ፻፷ ምዕት ወስድሳ
170. ፻፸ ምዕት ወሰብዓ
180. ፻፹ ምዕት ወሰማንያ
190. ፻፺ ምዕት ወተሰዓ
200. ፪፻ ክልኤቱ ምዕት
201. ፪፻ወ፩ ክልኤቱ ምዕት ወአሐዱ
202. ፪፻ወ፪ ክልኤቱ ምዕት ወክልኤቱ
203. ፪፻ወ፫ ክልኤቱ ምዕት ወሠለስቱ
204. ፪፻ወ፬ ክልኤቱ ምዕት ወአርባዕቱ
205. ፪፻ወ፭ ክልኤቱ ምዕት ወሐምስቱ
206. ፪፻ወ፮ ክልኤቱ ምዕት ወስድስቱ
207. ፪፻ወ፯ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓቱ
208. ፪፻ወ፰ ክለኤቱ ምዕት ወስመንቱ
209. ፪፻ወ፱ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓቱ
210. ፪፻ወ፲ ክልኤቱ ምዕት ወአሠርቱ
211. ፪፻፲ወ፩ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ
212. ፪፻፲ወ፪ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ
213. ፪፻፲ወ፫ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሠልስቱ
214. ፪፻፲ወ፬ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአርባቱ
215. ፪፻፲ወ፭ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ
216. ፪፻፲ወ፮ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ
217. ፪፻፲ወ፯ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ
218. ፪፻፲ወ፰ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰመንቱ
219. ፪፻፲ወ፱ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ
220. ፪፻፳ ክልኤቱ ምዕት ወእስራ
230. ፪፻፴ ክልኤቱ ምሪዕት ወሠላሳ
240. ፪፻፵ ክልኤቱ ምዕት ወአርብዓ
250. ፪፻፶ ክልኤቱ ምዕት ወሃምሳ
260. ፪፻፷ ክልኤቱ ምዕት ወስድሳ
270. ፪፻፸ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓ
280. ፪፻፹ ክልኤቱ ምዕት ወሰማንያ
290. ፪፻፺ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓ
300. ፫፻ ሠለስቱ ምዕት
400. ፬፻ አርባዕቱ ምዕት
500. ፭፻ ሐምስቱ ምዕት
600. ፮፻ ስድስቱ ምዕት
700. ፯፻ ስብዓቱ ምዕት
800. ፰፻ ስመንቱ ምዕት
900. ፱፻ ተሰዓቱ ምዕት
1000. ፲፻ አሠርቱ ምዕት
2000. ፳፻ እስራ ምዕት
3000. ፴፻ ሠላሳ ምዕት
4000. ፵፻ አርብዓ ምዕት
5000. ፶፻ ሃምሳ ምዕት
6000. ፷፻ ሳድስ ምዕት
7000. ፸፻ ሰብዓ ምዕት
8000. ፹፻ ሰማንያ ምዕት
9000. ፺፻ ተሰዓ ምዕት
10,000. ፻፻ እልፍ
20,000. ፪፻፻ ክልኤቱ እልፍ
30,000. ፫፻፻ ሠለስቱ እልፍ
40,000. ፬፻፻ አርባዕቱ እልፍ
50,000. ፭፻፻ ሐምስቱ እልፍ
60,000. ፮፻፻ ስድስቱ እልፍ
70,000. ፯፻፻ ሰብዓቱ እልፍ
80,000. ፰፻፻ ስመንቱ እልፍ
90,000. ፱፻፻ ተሰዓቱ እልፍ
100,000. ፲፻፻ አሠርቱ እልፍ
200,000. ፳፻፻ እስራ እልፍ
300,000. ፴፻፻ ሠላሳ እልፍ
400,000. ፵፻፻ አርብዓ እልፍ
500,000. ፶፻፻ ሃምሳ እልፍ
600,000. ፷፻፻ ስድሳ እልፍ
700,000. ፸፻፻ ሰብዓ እልፍ
800,000. ፹፻፻ ሰማንያ እልፍ
900,000 ፺፻፻ ተሰዓ እልፍ
1,000,000 ፻፻፻ አእላፋት
10,000,000 ፲፻፻፻ ትእልፊት
100,000,000. ፻፻፻፻ ትልፊታት
1,000,000,000. ፲፻፻፻፻ ምእልፊት
ሚያዝያ 26/2011 ዓ.ም
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ማስታወቂያ
በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣ
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታዎቂያ