Ethio Job Vacancy
46.1K subscribers
23.2K photos
63 videos
157 files
19.5K links
አዳዲስ እና ወቅታዊ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ከተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ለሥራ ፈላጊዎች መረጃ መስጠት ነው።
Post New Job vacancies to Who are looking jobs.
Group discussion https://t.me/+uGe3tVg5jF4yZjk0
Download Telegram
ነሐሴ 15/2011 ዓ.ም (21 August 2019) G.C
Advert on Addis Zemen
Aksum University
በ0አመት
For (BSC,BA,MA,MSC,PHD)
#Ethiopia: ባሳለፍነው ሳምንት ፌስቡኮች አንድ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ እንደላኩ ተነግሮ ነበር ያው ስራቸውን ጀምረዋል ለማለት ነው:: ብዛት ያላቸው ስድብና ብሔርን ከብሔር የሚያጋጩ በውሸት ስም የሚጠቀሙና በትክክለኛው ስማቸውም የውሸት ዜናዎችና ስድብን ነውረኝነትን የሚጠቀሙ ከውጪም ከሀገር ውስጥም ያሉ ነውረኞች ፌስቡክ እየተዘጋ ነው:: በተለይ በውሸት ስም የሚጠቀሙ ነውረኞች ፌስቡካቸውን ለማስከፋት ቢሞክርም ፌስቡክ መታወቂያ ስለሚጠይቅ ተመልሶ የመከፈቱ ነገር የሞተ የተቀበረ ጉዳይ ነው::

ሌላው ምክሬ ስማችሁን አሳጥራችሁ ፌስቡክ የምትጠቀሙ ሰዎች ወይም ለምሳሌ Natnael የሚለውን ስሜን Nati ብዬ የምጠቀም ከሆነ ፌስቡካችሁ በሆነ አጋጣሚ ቢዘጋ ለማስከፈት ብትፈልጉ የፌስብክ ቡድን የናተን ማንነት ማወቅ ስለሚፈልግ ወይም መታወቂያችሁን ስለሚጠይቃችሁ ስማችሁ ከላይ የኔን ምሳሌ በማድረግ የጠቀስኩት አይነት ተጠቃሚዮች ስምችሁን በትክክለኛው መታወቂያችሁ ላይ ባለው ስም አስተካክሉ::
Via Natnael Mekonnen
ነሐሴ 15/2011 ዓ.ም (21 August 2019) G.C
Advert on Addis Zemen
Federal Superior Court
የሥራ ውል ማቋረጥና ማራዘም /የመንግስት ሠራተኛ/
==============================
የፌደራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 የህግ ድንጋጌዎች /የተወሰኑ ማብራሪያ ብቻ ተደርጎ/
አንቀጽ 83፡- በራስ ፈቃድ የሥራ ውል ስለማቋረጥ
1. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ በማንኛውም ጊዜ የአንድ ወር ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ሥራውን በፈቃዱ ሊለቅ ይችላል፤ ሆኖም መስሪያ ቤቱ ሠራተኛውን በቀላሉ ሊተካው የሚችል ከሆነ የአንድ ወሩን ጊዜ ሳይጠብቅ ስንብቱን ሊፈቅድለት ይችላል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተመለከተውን የአንድ ወር የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ አገልግሎቱን ያቋረጠ የመንግሥት ሠራተኛ ግዴታውን ባለመወጣቱ ለሚደርሰው ጉዳት እንደተገቢነቱ በፍትሐ ብሔር እና በወንጀል ሕግ መሠረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡
3. የመንግሥት ሠራተኛው ለሥራው እጅግ አስፈላጊና በቀላሉ ለመተካት የማይቻል ሆኖ ሲገኝ ወደ ፊት ከሚቀጠርበት መስሪያ ቤት ጋር በመስማማት የመልቀቂያውን ጥያቄ ሠራተኛው ካመለከተበት ቀን ጀምሮ ከሦስት ወር ለማይበልጥ ጊዜ ሊራዘም ይችላል፡፡
አንቀጽ 84፡- በሕመም ምክንያት አገልግሎት ስለማቋረጥ
1. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 43(2) ወይም (4) በተመለከተው ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ ለመመለስ ካልቻለ በሕመም ምክንያት አገልግሎቱ ይቋረጣል፡፡
2. የዚህ አዋጅ አንቀጽ 59(3) ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ በሥራው ምክንያት ጉዳት የደረሰበት የመንግሥት ሠራተኛ ለዘለቄታው መሥራት አለመቻሉ በሕክምና ማስረጃ ሲረጋገጥ አገልግሎቱ ይቋረጣል፡፡
3. በዚህ አዋጅ አንቀጽ 26 ንዑስ አንቀጽ (3)(ለ) መሠረት በሚፈጸመው ዝውውር ተስማምቶ ለመስራት ፈቃደኛ ያልሆነ የመንግሥት ሠራተኛ አገልግሎቱ ይቋረጣል፡፡
አንቀጽ 85፡- በችሎታ ማነስ ምክንያት ከሥራ ማሰናበት
1. የሙከራው ጊዜውን ያጠናቀቀ የመንግስት ሠራተኛ በሥራ አፈጻጸም ውጤቱ የችሎታ ማነስ ከታየበት ተገቢው የአቅም ማጎልበት ሥልጠናዎች ተሰጥተውት ካልተሻሻለ አገልግሎቱ ይቋረጣል፡፡
2. የመንግሥት ሠራተኛ ያለውን ዕውቀትና ችሎታ እየተጠቀመ በተመደበበት ሥራ ላይ የሥራ አፈጻጸም ውጤቱ በተከታታይ ለሶስት ጊዜ ከሚጠበቀው ውጤት በታች ከሆነ በችሎታ ማነስ አገልግሎቱ ይቋረጣል፡፡
3. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) ድንጋጌ ቢኖርም ለተከታታይ አምስት ዓመታት ከፍተኛ የሥራ አፈጻጸም ምዘና ውጤት ሲያገኝ የነበረ የመንግሥት ሠራተኛ የሥራ አፈጻጸም ምዘና ውጤቱ በተከታታይ ለአራት ጊዜ ከሚጠበቀው ውጤት በታች ካልሆነ በስተቀር ከሥራ አይሰናበትም፡፡
4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) እና (3) መሠረት የመንግሥት ሠራተኛውን ከሥራ ማሰናበት የሚቻለው እንደአስፈላጊነቱ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 31 ላይ የተቀመጠውን የሥራ አፈጻጸም ምዘና ዓላማ በመከተል ይሆናል፡፡
አንቀጽ 86፡- ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከሥራ ማሰናበት
1. የሙከራ ጊዜውን ያጠናቀቀ የመንግሥት ሠራተኛ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በሥራ ገበታው ላይ ካልተገኘ ምክንያቱን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለመሥሪያ ቤቱ ማሳወቅ አለበት፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት ሪፖርት የተደረገለት የመንግሥት መሥሪያ ቤት የበላይ ኃላፊ ወይም ተወካዩ ሠራተኛው ከሥራ ገበታው ላይ የተለየበት ምክንያት ከአቅም በላይ መሆኑን ካረጋገጠ የመንግሥት ሠራተኛው ይዞት የነበረውን የሥራ መደብ ለስድስት ወር ክፍት አድርጎ መጠበቅ አለበት፡፡ ሆኖም የመንግሥት ሠራተኛው በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራው ካልተመለሰ ከሥራ ማሰናበት ይቻላል፡፡
3. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) ድንጋጌ ቢኖርም የመንግስት ሰራተኛው ከስድስት ወር በላይ በሥራ ላይ ያልተገኘው በእስር ምክንያት ከሆነና ከተጠረጠረበት የወንጀል ድርጊት በነፃ ስለመለቀቁ ማስረጃ ካቀረበ የመንግስት መስሪያ ቤቱ ባለው ክፍት የሥራ መደብ ቀደም ሲል ይከፈለው የነበረውን ደመወዝ እያገኘ ወደ ሥራ እንዲመለስ ማድረግ አለበት፡፡
4. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ የሙከራ ጊዜውን ያጠናቀቀ የመንግሥት ሠራተኛ ባልታወቀ ምክንያት ለተከታታይ አሥር ቀናት ከመደበኛ የሥራ ቦታው ላይ ከተለየ በየአስር ቀናት ልዩነት በተከታታይ ለሁለት ጊዜ በማስታወቂያ ተጠርቶ ለመንግስት መሥሪያ ቤቱ ሪፖርት ካላደረገ ከሥራ ይሰናበታል፡፡
5. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (4) መሠረት በማስታወቂያ ጥሪ የተደረገለት የመንግሥት ሠራተኛ ከሥራ ከተለየበት ቀን ጀምሮ አንድ ወር ከመሙላቱ በፊት ወደ ሥራው ለመመለስ ለመንግስት መሥሪያ ቤቱ ሪፖርት ካደረገ የመሥሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ሠራተኛው ከሥራ የቀረበትን ምክንያት በመመርመር የሚወስደው አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተጠበቀ ሆኖ ወደ ሥራው እንዲመለስ ይደረጋል፡፡
6. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (4) ቢኖርም ከስራ የተሰናበተ ሰራተኛ ከሥራ ከቀረበት ቀን ጀምሮ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ከሥራ የቀረበት ምክንያት ከአቅም በላይ ለመሆኑ ለመሥሪያ ቤቱ ሪፖርት ካደረገና በቂ ማስረጃ ካቀረበ በመሥሪያ ቤቱ ውስጥ ተመሳሳይ የሆነ ክፍት የሥራ መደብ ከተገኘ የመሥሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ወይም ተወካዩ ሲፈቅድ ወደ ሥራ ሊመለስ ይችላል፡፡
7. የሙከራ ጊዜውን ያላጠናቀቀ የመንግሥት ሠራተኛ ባልታወቀ ምክንያት ለአንድ ወር ጊዜ በሥራ ገበታው ላይ ካልተገኘ ያለተጨማሪ ሥነ-ሥርዓት አገልግሎቱ ይቋረጣል፡፡
አንቀጽ 87፡- የሠራተኛ ቅነሳ
1. ማንኛውንም የመንግሥት ሠራተኛ፣
ሀ) የሥራ መደቡ ሲሰረዝ፣
ለ) መሥሪያ ቤቱ ሲዘጋ፣
ሐ) ትርፍ የሰው ኃይል ሲኖር፣
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 30(1) መሠረት ለመደልደል ካልተቻለ ወይም የመንግሥት ሠራተኛው ዝቅ ባለ የሥራ ደረጃ ላይ ለመሥራት ፈቃደኛ ካልሆነ ከሥራ ይሰናበታል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1)(ሐ) መሠረት ቅነሳ የሚደረገው የመንግሥት ሠራተኛው በመሥሪያ ቤት ውስጥ በተመሳሳይ የሥራ መደብ ላይ ካሉ ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች ጋር ሲወዳደር በሥራ ውጤቱና ባለው ችሎታ ዝቅተኛ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው፡፡
አንቀጽ 88፡- በዲስፕሊን ምክንያት ከሥራ ማሰናበት
በዚህ አዋጅ አንቀጽ 69 ንዑስ አንቀጽ (1)(ሠ) መሠረት በዲስፕሊን ቅጣት የተወሰነበትና በአስተዳደራዊ ይግባኝ ውሳኔው ያልተሰረዘለት የመንግሥት ሠራተኛ አገልግሎቱ ይቋረጣል፡፡
አንቀጽ 89፡- በዕድሜ ምክንያት አገልግሎት ስለማቋረጥ
1. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 73 መሠረት አገልግሎቱ ካልተራዘመ በስተቀር በሕግ ከተወሰነው የመጦሪያ ዕድሜ ከደረሰበት የመጨረሻ ወር የመጨረሻ ቀን ጀምሮ አገልግሎቱ እንዲቋረጥ ይደረጋል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት በጡረታ ለሚሰናበት የመንግሥት ሠራተኛ ጡረታ ከመውጣቱ ከሶስት ወር በፊት በጽሑፍ እንዲያውቀው ይደረጋል፡፡
አንቀጽ 90፡- በሞት ምክንያት አገልግሎት ስለማቋረጥ
1. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ከሞተበት ቀን ጀምሮ አገልግሎቱ ይቋረጣል፡፡
2. አገልግሎቱ በሞት ምክንያት የተቋረጠ የመንግሥት ሠራተኛ የሞተበት ወር ሙሉ ደመወዙ እንዲሁም በዚህ አዋጅ አንቀጽ 41(1) መሠረት ላልተወሰደ የዓመት ዕረፍት ፈቃድ የሚፈጸም ክፍያ ለትዳር ጓደኛው፣ የትዳር ጓደኛ ከሌለው ለሕጋዊ ወራሾች ይከፈላል፡፡
3. አግባብ ባለው የጡረታ ህግ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ በሞት ምክንያት አገልግሎቱ ሲቋረጥ ለሚሠራበት መሥሪያ ቤት በጽሑፍ ላሳወቃቸው የትዳር ጓደኛው ወይም በስሩ ይተዳደሩ ለነበሩ ቤተሰቦች የሦስት ወር ደመወዝ በአንድ ጊዜ ይከፈላል፤ ሆኖም የትዳር ጓደኛውን ወይም በሥሩ የሚተዳደሩ ቤተሰቦቹን ሳያስመዘግብ የሞተ እንደሆነ ሥልጣን ካለው አካል ወይም ፍርድ ቤት በሚሰጥ ማስረጃ መሠረት ክፍያው ይፈጸማል፡፡
4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) መሠረት የሚሰጠው ክፍያ ከግብርና ከጡረታ መዋጮ ነጻ ይሆናል፤ እንዲሁም በዕዳ ሊከበር ወይም በማቻቻያነት ሊያዝ አይችልም፡፡
አንቀጽ 91፡- የአገልግሎት ምስክር ወረቀት አሠጣጥ/Certificate of Service/ ክሊራንስ/
1. ለማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ የሚሰጥ የሥራ ልምድ የምስክር ወረቀት ሠራተኛው ሲያከናውን የነበረውን የሥራ ዓይነት፣ የአገልግሎት ዘመኑና ሲከፈለው የነበረውን ደመወዝ የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡
2. የሥልጠና ውል ግዴታ ወይም በመንግሥት መሥሪያ ቤቱ የሚፈለግበት ማናቸውም ዕዳ ያለበት የመንግስት ሠራተኛ በማንኛውም ምክንያት አገልግሎቱን ሲያቋርጥ የውል ግዴታውን ስለመፈጸሙ ወይም ከዕዳ ነጻ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ከማግኘቱ በፊት የሥራ ልምድ የምስክር ወረቀት አይሰጠውም፡፡
3. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) በሥራ ላይ እያለ የሥራ ልምድ የምስክር ወረቀት ለሚጠይቅ የመንግስት ሠራተኛ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡
አንቀጽ 92፡-አገልግሎት ሲቋረጥ የሚፈጸም ክፍያ
1. የሙከራ ጊዜውን ያጠናቀቀ የመንግሥት ሠራተኛ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 87 መሠረት በቅነሳ ምክንያት ከሥራ ከተሰናበተና የሥራ ውሉ በተቋረጠበት ዕለት የጡረታ አበል የማይከፈለው ከሆነ፣
1.1. ለመጀመሪያ አንድ ዓመት የሦስት ወር ደመወዝ፣
1.2. በተጨማሪ ለአገለገለበት ለእያንዳንዱ ዓመት የወር ደመወዙ አንድ ሦስተኛ እየታከለ፣ ይከፈለዋል፤ ሆኖም የሚሰጠው ክፍያ ከሠራተኛው የአሥራ ሁለት ወር ደመወዙ መብለጥ የለበትም፡፡
2. የሙከራ ጊዜውን ለጨረሰና ከአንድ ዓመት በታች ላገለገለ የመንግስት ሠራተኛ የሚፈጸመው ክፍያ ከአገልግሎቱ ጋር ተመጣጣኝ ይሆናል፡፡
አንቀጽ 93፡- አገልግሎትን ማራዘም
1. የመንግሥት ሠራተኛ የመጦሪያ ዕድሜው ከደረሰ በኋላ በአንድ ጊዜ እስከ አምስት ዓመት በጠቅላላው ከአሥር ዓመት ለማይበልጥ ጊዜ አገልግሎቱን ማራዘም ይቻላል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት የአንድን የመንግሥት ሠራተኛ አገልግሎት ማራዘም የሚቻለው፣
2.1. የሠራተኛው ትምህርት፣ ልዩ ዕውቀትና ችሎታ ለመሥሪያ ቤቱ ሥራ ጠቃሚ ሆኖ ሲገኝ፣
2.2. በደረጃ ዕድገት፣ በዝውውር ወይም በቅጥር ተተኪ ሠራተኛ ለማግኘት አለመቻሉ ሲረጋገጥ፣
2.3. ሠራተኛው ለሥራው ብቁ መሆኑ በሕክምና ማስረጃ ሲረጋገጥ፣
2.4. ሠራተኛው አገልግሎቱን ለመቀጠል ሲስማማ፣ እና
2.5. የአገልግሎቱ መራዘም ጥያቄው የመጦሪያ ዕድሜው ከመድረሱ ከሦስት ወር በፊት ለሚኒስቴሩ ቀርቦ ሲፈቀድ፣ ነው፡፡
ኤ.ቢ.ኤች. (ABH) በሚል መጠሪያ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የተሰማራ በኤጀንሲው እውቅና የተሰጠው ተቋም የለም
1. ማንኛውም ተቋም በግል ከፍተኛ ትምህርት ለማቋቋምና አስተምሮ የት/ማስረጃ መስጠት የሚችለው በከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የእውቅና ፈቃድ ሲሰጠው እንደሆነ በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ 650/2001 አንቀጽ 74 ላይ አስገዳጅ የህግ ድንጋጌ ተቀምጧል፡፡ ነገር ግን ኤ.ቢ.ኤች. (ABH) በከፍተኛ ትምህርት ተቋምነት በኤጀንሲው ተገምግሞ የእውቅና ፈቃድ ያልተሰጠውና በኤጀንሲው የማይታወቅ በመሆኑ በየትኛውም የከፍተኛ ትምህርት ፕሮግራም ላይ ማስተማር የማይችልና በዘርፉ ላይ ለመሰማራትም ይሁን ከኤጀንሲው ጋር ህጋዊ ግንኙነት ለማድረግ የማይመለከተው መሆኑ ይታወቃል፡፡
2. በተጨማሪም አንድ ከፍተኛ ትምህርት እንዲሰጥ የተቋቋመ የመንግስት ተቋም በተለየ ሁኔታ ካልተቋቋመ በስተቀር የተቋሙ ቁልፍ ተግባር በተቋቋመበት አካባቢ በመደበኛ ፕሮግራሞች ትምህርትና ስልጠና መስጠት ምርምር ማካሄድና የማህበረሰብ አገልግሎት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በሌላ በኩል ተቋሙ ብቃት ያለው መሆኑ ሲረጋገጥ ማንኛውም ተቋም የርቀት ወይም በመረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂ የሚታገዝ ትምህርት ሊሰጥ እንደሚችል በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 19 ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡
3. ነገር ግን ጂማ ዩኒቨርሲቲ ኤ.ቢ.ኤች. (ABH) ከሚባል በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ካልተሰማራ የንግድ ተቋም ጋር የሚሰጠው ትምህርት በከፍተኛ ትምህርት መስክ ተገቢ በሆነ የጥራት ማረጋገጥ ስርዓት ብቃት ያለው መሆኑ ያልተረጋገጠና፤ ዩኒቨርሲቲው ካምፓሴ ነው ቢል እንኳ የመንግስት ዩኒቨርሲቲ የካምፓስ አከፋፈት ስርዓትን ያልተከተለና በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንደ ካምፓስ እውቅና ያልተሰጠው በመሆኑ በትብብር የሚሰጠው ትምህርት እንዲቋረጥ ቀደም ሲል በትምህርት ሚኒስቴር በድጋሚ በቅርቡ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡
በሚኒስቴር መ/ቤቱ ውሳኔ መሰረት ዩኒቨርሲቲው ተግባራዊ ባለማድረጉ ኤጀንሲው ህጋዊ የማስተካከያ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፤ ስለሆነም ህብረተሰቡ ጉዳዩን በመረዳት የትብብር ትምህርቱ የተቋረጠ መሆኑን አውቆ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኤጀንሲው ያሳስባል፡፡
Via HERQA